Quantcast
Channel: ዓለማየሁ ጉጀ
Viewing all 88 articles
Browse latest View live

ጉዞ ወደ ሱዳን

$
0
0

ዓባይ በረሃ መግቢያ፡፡ ፈረሶች ከተለያዩ አካባቢዎች ይሰበሰቡና በጎንደር መተማ በኩል ለሱዳን ገበያ ይቀርባሉ፡፡ ይህ ጉዞዋቸው በእግር ሲሆን፣ ዓባይ በረሃን ማቋረጥም የጉዞው አካል ነው፡፡ (ፎቶ በታምራት ጌታቸው)

* * *

ማምንድነው

ባልተስተዋልኩበት የልቤን አውጥቼ

እንዳልሰማሁ ሆኜ ሁሉንም ሰምቼ

ያጋጣሚ ሆኖ ‹‹ያርባ ቀን ዕድሌ››

ሚኮነውን ልሆን ባለመታደሌ

ንቀትና በደል እንዳላየሁ አይቼ

መች ነገሩ ጠፍቶኝ

መች ሳላውቅ ቀርቼ፡፡

ሰምሮልሃል ቢሉኝ

ያልሆነውን ቀና

ሳልደርስ መመለሴ

ከድል ፈር ጎዳና

መሆን የሚገባው መች ሆኖ ያውቅና

ቅጥፈት ቀንቷት ስትገን

እውነት ግን ታፍና፡፡

  • ዮሴፍ ሰቦቃ

* * *

ባለአምስት ኮከብ ሆቴል ጥልቅ የውኃ ገንዳ ውስጥ እየተገነባ ነው

በሻንጋይ አንድ ግዛት ውስጥ ሺማኦ በተባለ የግንባታ ተቋራጭ ጥልቅ የውኃ ገንዳ ውስጥ ባለአምስት ኮከብ ሆቴል እየተገነባ መሆኑን የሚረር ዘገባ አመለከተ፡፡

የሆቴሉ 383 የእንግዳ ማረፊያ ክፍሎችም በሆቴሉ የውኃ ውስጥ ፎቆች ላይ የሚገኙ መሆናቸው ተገልጿል፡፡ ምንም እንኳ በግንባታ ላይ ያለው ሆቴል እስከሚቀጥለው ዓመት ለአገልግሎት ክፍት የማይሆን ቢሆንም የውስጥ ዲዛይኑን በሚመለከት ዓለም አቀፍ ጨረታ መውጣቱ በዘገባው ተገልጿል፡፡

ሆቴሉ የሚገኝበት ቦታ በተፈጥሮ ውበት የተቸረው በመሆኑ የሆቴሉ ዲዛይንም ይህን ውበት ይበልጥ የሚያንፀባርቅ እንዲሆን ይፈለጋል፡፡ ሆቴሉ እየተገነባበት ያለው ገንዳም 90 ሜትር ጥልቀት ያለው ነው፡፡

ሆቴሉ የመናፈሻ ቦታዎች፣ የእንግዳ ማረፊያዎች፣ እስከ 1000 ሰው የሚያስተናግዱ የስብሰባ አዳራሾችና የስፖርት ማዘውተሪያ እንደሚኖረው ተጠቁሟል፡፡ ይህ ሆቴል ምናልባትም እስከዛሬ ከተሠሩት ሆቴሎች እጅግ አረንጓዴው እንደሆነ እየተነገረ ነው፡፡

* * *

በዘረመል ምህንድስና የተፈጠሩ አሳማዎች የውስጥ አካል ለሰው ሊሆን ይችላል ተባለ

በዘረመል ምህንድስና የተፈጠሩ አሳማዎች የውስጥ አካል በቀዶ ሕክምና ጭላዳ ዝንጀሮ ላይ ተደርጐ ዝንጀሮው ለሁለት ዓመት ጤናማ ሆኖ በመቆየቱ የእነዚህ አሳሞች አካል ለሰው ሊሆን እንደሚችል ተስፋ መኖሩን ሳይንቲስቶች ገልጸዋል፡፡

የሚረር ዘገባ እንደሚያሳየው ይህ ሳይንሳዊ እርምጃ እንደ ኩላሊት ያለ የውስጥ አካል ለማግኘት ያለውን ፈተና ያቀልላል፡፡ ሳይንቲስቶቹ እዚህ ደረጃ ላይ የደረሱት ችግር የነበረበትን የጭላዳ ዝንጀሮ ልብ በአሳማ ልብ በመተካት ጭላዳ ዝንጀሮውም ለሁለት ዓመት በጤና መኖር መቻሉ በመረጋገጡ ነው፡፡ እስከዚህ ጊዜ ድረስ ግን ተመሳሳይ ቀዶ ሕክምና የተደረገላቸው እንስሳት የኖሩት ከስድስት ወር ለማይበልጥ ጊዜ ነበር፡፡

እነዚህ ከአሳማ የሚወሰዱ የውስጥ አካሎች በትክክልም የሰው አካልን ተክተው ውጤታማ እንዲሆኑ አሳሞቹ በዘረመል ምህንድስና ሲፈጠሩ አምስት የሰው ዘረመል እንዲኖራቸው ተደርጓል፡፡ በዚህ መልኩ ለሰዎች የሚደረገው የቀዶ ሕክምና በሚቀጥሉት ጥቂት ዓመታት ውስጥ እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡ ተመራማሪዎቹ አሳማዎቹ ላይ የሚደረገው ጥናት እንደሚቀጥል በተለይም ደግሞ በዕድሜ ገና የሆኑ አሳሞች የውስጥ አካል ለሰዎች በደንብ የሚሆን መጠን እንዳለው እያስረዱ ነው፡፡

* * *

መሬት መንቀጥቀጥ የማይበግረው አልጋ

ተፈጥሮአዊ አደጋዎችን በተለይም መሬት መንቀጥቀጥን መቋቋም የሚችል አልጋ በመሥራት ዋንግ ዌንዚ የተባሉ ቻይናዊ የባለቤትነት ማረጋገጫ ማግኘታቸውን ቻይና ዴይሊ ዘግቧል፡፡ የፈጠራ ባለቤትነት ማረጋገጫው የተሰጠው እ.ኤ.አ. 2010 ላይ ነበር፡፡

አልጋው የሬሳ ሳጥን የመሰለ ቢሆንም የታሸገ ውኃ፣ የታሸጉ ምግቦች፣ ድምፅ ማጉያ፣ ባትሪዎችና የእሳት ማጥፊያ ያለው ነው፡፡ ይህ የሆነው ደግሞ በአደጋ ወቅት የነፍስ አድን ሠራተኞች እስኪደርሱ ሰዎች ነፍሳቸውን ለማቆየት፤ ያሉበትን አካባቢም ማወቅ እንዲችሉ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በደቡብ ካሊፎርኒያ የመሬት መንቀጥቀጥ ማዕከል ኤክስፐርት የሆኑት ማርክ ቤንቲን ለሲኤንኤን ‹‹የሚያስፈልጉ ነገሮች ሁሉ ባሉበት የብረት ሳጥን ውስጥ መሆን መጥፎ ነገር አይደለም፡፡ ግን በጣም ወጪ የሚጠይቅ ነው፤›› ብለዋል፡፡

የፈጠራው ባለቤት የሆኑት ጡረተኛው የ66 ዓመቱ ሚስተር ዌንዚ በዕድሜያቸው ተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጦችን በማየታቸው በመጨረሻ በመሬት መንቀጥቀጥ ምክንያት የሚደርስን ሞት ለመቀነስ በማሰብ እዚህ ፈጠራ ላይ መድረሳቸውን አስረድተዋል፡፡

Standard (Image)

‹‹ሃይላንድ›› እግሩ ውስጥ የገባው ሳላ

$
0
0

ይህ በፎቶው ላይ የሚታየው ሳላ፣ ከሦስት ወራት በፊት ድርቁ በፓርኮችና በዱር እንስሳቱ ላይ ያደረሰውን ጉዳት ለመዘገብ ሪፖርተር በአዋሽ ብሔራዊ ፓርክ በተገኘንበት ወቅት የተነሳ ነው፡፡ ሳላው በድርቁ ከመጎዳቱ ባለፈ መግቢያው በር አካባቢ ባግባቡ መሄድ ያቃተው በአካባቢው በተጣለውና በተቆረጠው ሃይላንድ ውስጥ እግሩ በመግባቱ ነበር፡፡

ፎቶ በታምራት ጌታቸው

******

. . . በሬው! . . .

እዩት ያንን በሬ በቀንዱ ተማምኖ
ያሸብረን ይዟል ላሞች ላይ ጀግኖ
ላሞች እንደሆኑ መጠቃት ልምዳቸው
ወተት እንዲያጠጡ ኮርማ ነው ግዳቸው።

በሬ እየሸለለ፣ በሬ እየፎከረ 
በሬው እያጓራ፣ ስንቱ ደጅ አደረ፤
ይወጋል ይረግጣል፣ ሲሻው ያንሳፍፋል
በሬ ሆይ አይምሬው፣ ትውልድ ያጣድፋል።

ተው በሬ … ተው ኮርማ 
እባክህ ተመከር፣ ያገር ምክር ስማ 
ተጥለህ እንዳናይህ፣ ከቄራው አውድማ።

የሚሮጥ፣ የሚሸሽ፣ የሚበረግገው፣ 
ቀንድህን በመፍራት፣ የሚያደገድገው፣
ገና ብቅ ስትል መንገድ የሚጠርገው ᎐᎐᎐ 

ይሄ ሁሉ ፈሪ፣ ይህ ሁሉ ቦቅቧቃ
ከዘመን ፍራቻው፣ ሲባንን ሲነቃ
ሆ! ያለብህ እንደሁ ታጥቆ በቆንጨራ
ያዝ ያለህ እንደሆን ከቦ በገጀራ 
ማምለጫም አይኖርህ ለአንገትህ ካራ። 

“በሬ ሆይይ 
በሬ ሆይይ 
ሳሩን አየህና ገደሉን ሳታይ 
መግባትህ ነው ወይይይይ”

ብለን እንዳናለቅስ ቆዳህን ሲገፉ
ዛሬን አታስጀግር ተው ሰዎች ይለፉ
በሰላም፣ በጤና፣ በፍቅር ይረፉ 
ላንተም አይበጅህም፣ ያጠፋሃል ግፉ።

(አብዲ ሰዒድ፣ 2005 ዓ.ም.)

******

ከአስከሬን ላይ ቀለበት የሰረቀችው ሴት እየተፈለገች ነው

በቴክሳስ በአንድ የመቃብር ሥፍራ ክፍት ከሆነ የአስከሬን ሳጥን ውስጥ ከ88 ዓመት ሟች ላይ ቀለበት አውልቃ ስትወስድ በደኅንነት ካሜራ የተቀረፀችው ሴት እየተፈለገች መሆኑን የሮይተርስ ዘገባ አመለከተ፡፡

ፖሊስ እንዳስታወቀው፣ ከሟቿ አዛውንት ሬሳ ሳጥን ፊት ለፊት ለደቂቃ የቆመችው ሴት ወዲያው የሟችን ጣት በመጠምዘዝ ቀለበት ስታወልቅ ቪዲዮው ያሳያል፡፡

ሰራቂዋ ወዲያው ቀለበቱን ይዛ በመኪና መሰወሯም በዘገባው ተመልክቷል፡፡ በደኅንነት ካሜራ የተቀረፀውን ቪዲዮ እንድትመለከት የተደረገችው የሟች ልጅ ሰራቂዋን እንደማታውቃት ገልጻለች፡፡

*********

በደቡብ ኮሪያ አዛውንቶች በምርጫ ድምፃቸውን እንዲሰጡ መደለያ ቫያግራ ተሰጣቸው

ስንፈተ ወሲብ ያለባቸው ደቡብ ኮሪያውያን አዛውንቶችን ድምፅ ለማግኘት አዛውንቶቹ ቫያግራ እንዲሰጣቸው በመደረጉ፣ ጉዳዩ እንዲጣራ በፍርድ ቤት መወሰኑን የአዣንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘገባ ያመለክታል፡፡

ደቡብ ኮሪያውያን ከጥቂት ቀናት በፊት ምርጫ ማካሄዳቸው ይታወቃል፡፡ ነገር ግን ምርጫው የሰሜን ኮሪያ የኒውክሌር ማስፈራሪያና የኢኮኖሚ ፈተና ጥላት ያጠላበት ነበር፡፡

የስንፈተ ወሲብ መድኃኒት በመስጠት ድምፅ የመግዛት ወንጀል ተፈጸመበት የተባለው ሱዎን፣ ከአገሪቱ መዲና ሴዑል 30 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኝ ነው፡፡ የሱዎን ዓቃቤ ሕግ ቃል አቀባይ ‹‹ወንጀሉ መፈጸሙን አላረጋገጥንም፡፡ እውነት ሆኖ ከተገኘ ግን የምርጫ ሕግን የሚፃረር ነው፤›› ማለታቸውን የአዣንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘገባ ያመለክታል፡፡ በአገሪቱ የምርጫ ሕግ መሠረት ባልተገባ መልኩ የሕዝብ ድምፅ መግዛት በአምስት ዓመት እስራትና 8,750 የአሜሪካ ዶላር ያስቀጣል፡፡

በአገሪቱ የስንፈተ ወሲብ መድኃኒት በሐኪም ትዕዛዝ ብቻ የሚሸጥ በመሆኑ፣ እነዚህን መድኃኒቶች በመጠቀም የአዛውንቶችን ድምፅ ለመግዛት የሞከሩት የምርጫ ተወዳዳሪ መድኃኒቶቹን እንዴት በብዛት አገኟቸው? የሚለውም አጠያያቂ ሆኗል፡፡

በሕጉ መሠረት በተለያየ መንገድ የዜጎችን ድምፅ ለመግዛት የሞከረ ተመራጭ ብቻ ሳይሆን በተጠቀሰው መንገድ ድምፁን የሸጠ ዜጋም ከቅጣት አያመልጥም፡፡

*******

የትራምፕ ልጆች ለአባታቸው ድምፅ አይሰጡም

በአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ተወዳዳሪ ለመሆን የሪፐብሊካኑን ፓርቲ ለመወከል እየተንቀሳቀሱ ያሉት ዶናልድ ትራምፕ ሴት ልጃቸው ኢቫንካ ትራምፕና ወንድ ልጃቸው ኤሪክ ትራምፕ ለአባታቸው ድምፅ መስጠት እንደማይችሉ ተረጋገጠ፡፡

ልጆቻቸው ድምፃቸውን ሊሰጧቸው ያልቻሉት የመራጮች ምዝገባ ስላመለጣቸው እንደሆነ ትራምፕ ልጆቻቸውም ለመገናኛ ብዙኃን ገልጸዋል፡፡ አባትና ልጆቹ የምዝገባ ሥርዓቱንም ኮንነዋል፡፡ ‹‹ፖለቲከኛ ቤተሰብ አይደለንም፡፡ በፖለቲካ ውስጥም ለረዥም ጊዜ አልቆየንም፤›› ያለችው ኢቫንካ የምዝገባ ሕጉ ከዓመት በፊት እንዲመዘገቡ የሚጠይቅ መሆኑን፤ ስለዚህም ያንን ምዝገባ የሚያድሱበት ዳግም ምዝገባ እንዳመለጣቸው ገልጻለች፡፡

ወንድሟ ኤሪክም ‹‹ይህ በፖለቲካ የመጀመርያ ጊዜያችን ነው፡፡ አጠቃላይ ሥርዓቱ እንዴት እንደሚሠራ አናውቅም ነበር፤›› ብሏል፡፡

******

ሱናሚና የምሥራቅ አፍሪካ አገሮች

‹‹ሱናሚ›› የጃፓን ቃል ሲሆን፣ ትርጓሜውም ከቁጥጥር በላይ የሆነ የውኃ ሞገድ ወይም መሬት ተዛንፎ አለበለዚያም ተንቀጥቅጦ በአንድ ጊዜ ሲተረተር የሚለቀው ሞገድ ነው፡፡ ይህም ሞገድ ሲነሳ ወይም መሬት ሲደረመስ ውኃውም አብሮ ይዘልና ወደታች ይወርዳል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ከጣሪያ በላይ የሚደርስ ቁመት የመዝለል ኃይል አለው፡፡ በዚህ መልኩ ወደ ላይ የዘለለው ውኃ ወደታች ወይም ወደ መሬት ሲወርድ ያገኘውን ሁሉ ጠራርጎ ይወስዳል፡፡

ዶ/ር አታላይ አየለ፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂኦፊዚክስ ስፔስ ሳይንስና አስትሮኖሚ ኢንስቲትዩት ኃላፊና የመሬት መንቀጥቀጥ ሳይንስ ባለሙያ እንደገለጹት፣ የምሥራቅ አፍሪካ በተለይም ከኬንያ ከሞምባሳ እስከ ደቡብ አፍሪካ ያሉት አገሮች ለሱናሚ አደጋ የተጋለጡ ናቸው፡፡

ቀይ ባሕርና ጂቡቲ ሱናሚ እምብዛም አያሠጋቸውም፡፡ ነገር ግን ጂቡቲ ባሕር ዳርቻ ያለች አገር በመሆኗ መጠነኛ የሆነ የሱናሚ ሞገድ ሊፈጠርባት ይችላል፡፡

የምሥራቅ አፍሪካ አገሮች ለሱናሚ ሊጋለጡ የቻሉት ከህንድ ውቅያኖስ ወደ ኢንዶኔዢያ አካባቢ ከባሕር ጠለል ሥር የሚነሳው የመሬት መንቀጥቀው በሬክተር ስኬል ሰባትና ስምንት ማግኒቲዩድ በመሆኑ ነው፡፡ ይህም ማለት ሱናሚ የመነሳቱ አጋጣሚ ከፍ ያለ ነው ማለት ነው፡፡

ቀይ ባሕርና ጂቡቲ ሱናሚ የሚያሠጋቸው ከተፈጥሮአዊ አቀማመጣቸው የተነሳ ሸለቆ ውስጥ በመገኘታቸው ነው፡፡ በ2004 ዓ.ም. በኬንያዋ ሞምባሳና ሶማሊያ ጠረፍ ሱናሚ ተከስቶ ለበርካታ የሕይወትና ንብረት መጥፋት ምክንያት መሆኑ አይዘነጋም፡፡

 

Standard (Image)

ከጥቂት ቀናት በፊት በሰሜናዊ ጃፓን ከሚገኝ የእንስሳት ማቆያ ያመለጠው የ24 ዓመቱ ቺምፓንዚ

$
0
0

ከጥቂት ቀናት በፊት በሰሜናዊ ጃፓን ከሚገኝ የእንስሳት ማቆያ ያመለጠው የ24 ዓመቱ ቺምፓንዚ ቻቻ ሴንዳይ በተሰኘችው ከተማ የተለያዩ አካባቢዎች እየዘዋወረ ከኤሌክትሪክ ፖል ወደ ኤሌክትሪክ ፖል እንዲሁም ከሕንፃ ሕንፃ ሲዘል ታይቶ እንደበር ሮይተርስ ዘግቧል፡፡ ወደነበረበት ከፍታ በመውጣት ከፖሉ ጫፍ የነበረውን ቻቻ ለአፍታ ለማደንዘዝ የሞከሩት የእንስሳት ሐኪምን ቺምፓንዚው አስደንግጧቸዋል፡፡ በመጨረሻ ቺምፓንዚው ማደንዘዣ ተወግቶ ሊያዝ ችሏል፡፡

******************

እናትና እድሜ
.
ዝናቡ ይዘንባል..... . . . . . . . . . . .
በር ላይ ቆሜያለሁ፤
የደጁ ወጨፎ ያንዘፈዝፈኛል፣
ብልጭታ - መብርቁ፣ ከሰማዩ ጋራ፣ ከመንደሩ ጋራ፣ ይሰነጥቀኛል፡፡
.
አወይ እናት ማጣት!
አይ ልጅ መሆን መጥፎ፤
ዛሬም ባምሳ አመቱ፣ በደመነ ቁጥር፣ በዘነበ ቁጥር፣ ደጃፍ ተደግፎ፤
ምን መብረቅ ቢወርድ፣ ምን ቆፈን ቢይዘው፤
‹‹ደጃፍ ላይ አትቁም፣ መብረቅ ትጠራለህ፣
ወጨፎ ይመታሀል፣ ለሊት ታስላለህ፡፡››
ካላለችው እናቱ፤
አይገባም ከቤቱ፡፡
.
ይኸው ክረምት መጣ፣ ዝናቡ ዘነበ፣
መብረቁ ይወርዳል፣
አድባር ይታረሳል፤
በር ላይ ቆሜያለሁ፤
ሞቴ ላይ ቆሜያለሁ፤
ከቆፈኑ በላይ፣
ከመብረቁ በላይ፣ . . .ሳጣሽ ያስፈራኛል፤
እማ ‹‹ግባ›› በዪኝ፣ ቃልሽ ያድነኛል፡፡

  • በድሉ ዋቅጅራ ( ሚያዝያ፣ 2008)
     

****************

የዶላር ላይ ምስል በጥቁሯ የነፃነት ታጋይ ሀሪየት ቱብማን ሊተካ ነው

የአሜሪካ የባንክ ገዢዎች እንዳስታወቁት በ20 ዶላር ላይ ያለው የፕሬዚዳንት አንድሪው ጃክሰን ምስል የጥቁር መብት ትግል ተምሳሌት በሆኑት ሀሪየት ቱብማን እንዲተካ ተወስኗል፡፡

የዘ ኢንዲፔንደንት ዘገባ እንደሚያመላክተው፣ ይህ ለውጥ በቀላሉ የተሳካ ሳይሆን ለጥቁር መብት ታጋዮች ዕውቅና ይሰጥ በሚሉ ጠንካራ ሕዝባዊ ቅስቀሳዎች ነው፡፡ በአምስት ዶላር ላይም ተመሳሳይ ለውጥ በማድረግ ለጥቁር ነፃነት ታጋዮች ዕውቅና እንደሚሰጥም ተገልጿል፡፡

በአሥር ዶላር የፊት ገጽ ላይ ያለው የአሌክሳንደር ሀሚልተን ምስል ግን ባለበት የሚቀጥል ሲሆን ከወራት በፊት ይህ የአሌክሳንደር ሀሚልተን ምስልም እንደሚቀየርና በሴት እንደሚተካ ተገልጾ ነበር፡፡ በአሜሪካ ዘመናዊ የፋይናንስ ሲስተም የዘረጉት ሀሚልተን ምስል ይነሳል የሚለው ነገር ግን አድናቂዎቻቸውን አስቆጣ፡፡ ተንታኞችም ሀሚልተን ከአሥር ዶላር ላይ የሚነሱ ከሆነ ቀደምት አሜካዊያንን ከመሬታቸው ያፈናቀሉት አንድሪው ጃክሰን ከሀያ ዶላር ላይ ተነስተው የሀሚልተን ምስል መተካት መሆን አለበት የሚል አስተያየት ሠንዝረው ነበር፡፡

ዘገባው እንደሚያመለክተው ምናልባትም ይህ ለውጥ የአንዲት ሕፃን በአሜሪካ የዶላር ቅጠሎች ላይ የሴት ምስል አለመኖሩን በሚመለከት ለባራክ ኦባማ የጻፈችውን ደብዳቤ ተከትሎ የመጣ ነው፡፡ በሌላ በኩል 20 ዶላር ላይ ያሉት ጃክሰን በሴት ይተኩ የሚለው የማኅበራዊ ድረ ገጽ ዘመቻም ተፅዕኖ አሳድሯል፡፡

******************

የሥራ ማስታወቂያ፣ የንግሥት ኤልሳቤትን ትዊተር ገጽ ማስተዳደር

የእንግሊዝ ጋዜጦች እንደዘገቡት ባለቀው ሳምንት የ90ኛ ዓመት የልደት በዓላቸውን ያከበሩት የእንግሊዟ ንግሥት ኤልሳቤት ሁለተኛን የትዊተር ገጽ የሚያስተዳድር ሰው ፍለጋ የሥራ ማስታወቂያ ወጥቷል፡፡ እንደ ሮማው ጳጳስ ፍራንሲስና ሚሼል ኦባማን ያሉ በማኅበራዊ ድረ ገጾች ላይ የጎሉ ታላላቅ ሰዎችን ለመወዳደር የሚያስችላቸው በሚመስል መልኩ የትዊተር ገጻቸውን ለሚያስተዳድረው ሰው ንግሥቷ በዓመት እስከ 50 ሺሕ ፓውንድ እንደሚከፍሉ አስታውቀዋል፡፡

የንግሥቲቱን የትዊተር ገጽ የሚያስተዳድረው ኤክስፐርት የንጉሣዊያኑን የፌስቡክና የትዊተር ገጾችን ከማስተዳደር በተጨማሪ በማኅበራዊ ድረ ገጾች ላይ የንግሥቲቱ ተከታዮችን የሚያበዛ አዲስ መንገድም እንዲፈጥር ይጠበቅበታል፡፡

የሥራ ማስታወቂያው የወጣው በንጉሣውያኑ ድረ ገጽ ላይ ሲሆን ዓላማው የንግሥቲቱን የማኅበራዊ ድረ ገጽ ጉልህነትን መጨመር ነው፡፡

ንግሥቲቱ መጀመሪያ ትዊት ያደረጉት እ.ኤ.አ. በ2014 ነበር፡፡ በአሁኑ ወቅት 2.16 ሚሊዮን ተከታዮች ሲኖሯቸው የራሳቸው ድረ ገጽና ዩቲውብ ቻናልም አላቸው፡፡

Standard (Image)

ባህላዊ የፋሲካ ማዕድ

$
0
0

በዓለም የሚገኙ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ለ55 እና ለ48 ቀናት የሚዘልቀውን የፋሲካ (ትንሣኤ) ጾም የሚፈቱት የተለያዩ ባህላዊ ምግቦችን በማዘጋጀት ነው፡፡ የጾሙ ወቅት ከእንስሳት ተዋጽኦና ከመጠጥ የሚቆጠቡበት ሲሆን፣ ሲፈታ ደግሞ አንደየአገሩ ባህል የተለያዩ ማዕዶችን ያዘጋጃሉ፡፡ ዳቦ ወይም ኬክ ከማዕዱ መቅረት ከሌለባቸው ምግቦች አንዱ ነው፡፡

ሩሲያ

የፒራሚድ ቅርፅ ያለው ኬክ በትንሳኤ በዓል ዕለት ማቅረብ የተለመደ ነው፡፡ ኬኩ ሃይማኖታዊ የሆኑ ምልክቶች የሚቀረፁበት ነው፡፡ በተለይ የክርስቶስ መነሳትን የሚያመላክቱ ቅርጾች በኬኩ ላይ ይደረጋሉ፡፡

ጣሊያን

በጣሊያን ለትንሣኤ በዓል የሚጋገረው ኬክ የርግብ ቅርፅ ያለው ነው፡፡

ግሪክ

ግሪኮች በትንሣኤ ማዕዳቸው ላይ ከሚያቀርቧቸው ምግቦች አንዱ ኬክ ነው፡፡ ኬኩ በተቀቀለና ቀይ የምግብ ፓውደር በተቀባ እንቁላል ይጌጣል፡፡ ተምሳሌቱም የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ነው፡፡

ምሥራቅ አውሮፓ

በምሥራቅ አውሮፓ በትንሣኤ በዓል ጣፋጭ ዳቦ አዘጋጅቶ የመብላት ባህል አለ፡፡ ዳቦው በመስቀል ቅርፅ የሚጋገር ነው፡፡ በተለይ በስሎቫኪያና በክሮሺያ የተለመደ ሲሆን፣ በጣሊያን በአንዳንድ ስፍራዎችም ይዘወተራል፡፡

ስፔን

ስፔናውያን ከሰሞነ ሕማማት ጀምረው የፋሲካ ኬክ በባህላዊ መንገድ ያዘጋጃሉ፡፡ ይህ ኬክ የዶናት ዓይነት ቅርፅ ያለው ሲሆን፣ መሐሉ ላይ የተቀቀለ እንቁላል ሳይላጥ ይደረግበታል፡፡

እንግሊዝ

በእንግሊዝ ፋሲካን በዓል የሚያስመስለው፣ በቅመማ ቅመም የጣፈጡና በላያቸው ላይ የመስቀል ቅርፅ የተሠራባቸው ትናንሽ ዳቦዎች ገበታው ላይ ሲቀርቡ ነው ተብሎ ይታመናል፡፡ በእያንዳንዱ ዳቦ ውስጥ 11 ወይም 12 ዘቢብ የሚደረግ ሲሆን፣ ምሳሌውም ሐዋርያትን ለማስታወስ ነው፡፡

ሜክሲኮ

በሜክሲኮ በቺዝ ቀረፋና በቅሩንፉድ የጣፈጠ ዳቦ ለትንሣኤ ማቅረብ የተለመደ ነው፡፡ ቀረፋው ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበትን የእንጨት መስቀል የሚያመላክት ሲሆን፣ ቅሩንፉዱ ደግሞ የተወጋበት ሚስማር ተምሳሌት ነው፡፡ ዳቦው ደግሞ የኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ ነው፡፡

አብዛኞቹ የኦርቶዶክስ ክርስትና ተከታይ አገሮች ‹‹ኩሊች›› የተባለ ኬክ ያዘጋጃሉ፡፡ ከስንዴ ዱቄትና ከተለያዩ ቅመማ ቅመሞች፣ እንቁላል፣ ዘቢብ፣ ኦቾሎኒ የሚዘጋጀው ይህ ኬክ ቀጠን ብሎ ረዘም ያለ ነው፡፡ በትንሣኤ ዋዜማ ቅዳሜ ሌሊት የፀሎት ሥነ ሥርዓት ካለቀ በኋላ፣ በቄሶች ተባርኮ የሚቆረስም ነው፡፡ ይህ ኬክ በተለይ በቡልጋሪያ፣ ጆርጂያና ሩሲያ የተለመደ ነው፡፡ ምዕመኑም ዳቦው እንዲባረክለት በሌሊቱ ቅዳሴ ሥነ ሥርዓት ላይ ዳቦውን ይዞ ይገኛል፡፡

ብራዚል

በብራዚል ለትንሣኤ በዓል የሚቀርበው ምግብ ከተለነቀጠ ኦቾሎኒ፣ ከስኳርና ከካሳቫ ዱቄት የሚጋገር ዳቦ ነው፡፡

ዴንማርክ

ዴንማርክ ለትንሣኤ ማዕድ ማወራረጃ በተለየ ሁኔታ በሚጠመቀው ቢራ ትታወቃለች፡፡ በዴንማርክ ለፋሲካ በዓል የሚዘጋጀው ቢራ በሌሎች ጊዜያት ከሚዘጋጀው ጠንከር ያለ ነው፡፡

(ዘ ቴሌግራፍ)

********

ሆድ እና ህሊና

በመብል የወፈረን የቀፈቱን ክብደት

በኪሎ ሊፈርጅ

መንገድ ካለ ሚዛን … በተራ በተራ

ይወጣል … ይለካል ይወርዳል አልፎ ሒያጅ፡፡

ነገር ተገልብጦ

ሰው ሚዛን ላይ ወጦ

ማሰብ እና መሥራት …የዕውቀቱን ዳርቻ የሚለካ ነገር

በቴክኖሎጂ ውስጥ አንድ ቀን ቢፈጠር

ሚዛን ሲያይ የሚሮጥ

እሳቤው የከሳ ሺ ሰው እናይ ነበር፡፡

  • አንዳርጋቸው አበጀ ‹‹የማማት ፆመኛ›› (2005)

***********

 

ከሥራፈትነት የገላገለን አዳም ነው

አዳም ባመጣው ኃጢአት ነው የሰው ልጆች የምንሰቃየው የሚሉ ወገኖች ይኖሩ ይሆናል፡፡ አዳም የተከለከለው ዕፀ በለስ  በመብላቱ ወደ ምድር ተሰደድን ይሉ ይሆናል፡፡ ለኔ ግን አዳም ዕፀ በለስ መብላቱ ለበጐ ነው፡፡ አዳም ዕፀ በለስ  ባይበላና እስከአሁን በገነት የምንኖር ብንሆን ምን ዓይነት ሕይወት ነበር የምንኖረው? በጣም አሰልቺ ሕይወት ነበር የሚሆነው፡፡ የሰው ልጅ ምንም ነገር ሳይሠራ መኖር ምን ያህል አሰልቺ እንደሆነ ከሕይወት ልምዳችን የምናውቀው ጉዳይ ነው፡፡ ከሥራ ፈትነት የገላገለን ግን አዳም ነው፡፡ ምንም ዓይነት ሥራ በሌለበት ዓለም ምንም ዓይነት ጣፋጭ ሕይወት ሊኖር አይችልም፡፡ እርስ በእርሳችን እንኳን ምንም ነገር ማውራት ሐሳብ ለሐሳብ መጋራት አንችልም፡፡ ሥራ ከሌለ ምንም ዓይነት ሐሳብ አይኖርም፡፡ የሐሳብ ልዩነት ከሌለ ደግሞ የሐሳብ መጋራት የለም ማለት ነው፡፡

  • አብርሃም ሐዱሽ ‹‹ነገር በምሳሌ …›› (2005)

******

አሳ ጐርጓሪ

ውሻው ደንዲ ከተማ (ስኮትላንድ) የሚገኝ ሥጋ ቤት ዘሎ ገብቶ ሊቆረጥ ከተደረደረው ሥጋ በቅርቡ ያገኘውን መንትፎ ይሄዳል፡፡ ውሻው የጠበቃው ጐረቤቱ መሆኑን ያወቀው ባለ ሥጋ ቤት ስልክ ደውሎ “ውሻህ ከልኳንዳዬ ለጥብስ የሚሆን ምርጥ ሥጋ ቢሰርቅ ለደረሰብኝ ኪሳራ ተጠያቂ ትሆናለህ ወይ?” ሲል ይጠይቀዋል፡፡

“በሚገባ እንጂ፤ ለመሆኑ የሥጋው ዋጋ ስንት ነው?”

“ሰባት ፓውንድ ነው” አለ ባለሥጋ ቤቱ ተደስቶ፡፡

ከጥቂት ቀናት በኋላ ለባለ ሥጋ ቤቱ በፖስታ ቤት በኩል የሰባት ፓውንድ ቼክ ደረሰው፡፡ ከቼኩ ጋርም “ለምክር አገልግሎት የተጠየቀ ሒሳብ 150 ፓውንድ” የሚል ኢንቮይስ ተያይዞ ነበር፡፡

*************

ፀጉራሙ ባለመንጃ ፈቃድ

      ወጣቱ የመንጃ ፈቃድ ስላወጣ መኪናቸውን መጠቀም ይችል እንደሆነ ካህን አባቱን ጠየቃቸው፡፡ “አባቱም የትምህርት ውጤትህን ካሻሻልህ፣ መጽሐፍ ቅዱስህን ካጠናህ ፀጉርህን ከተስተካከልክ በጉዳዩ ላይ ልንገጋገር እንችላለን” አሉት፡፡

      ልጅየው ከወር በኋላ ነገሮችን አስተካክሎ መኪናቸውን መጠቀም ይችል እንደሆነ በድጋሚ ጠያቃቸው፡፡

      ውጤትህ ተሻሽሏል መጽሐፍ ቅዱስህንም በትጋት አጥንተሃል፡፡ ሆኖም ፀጉርህን አልተቆረጥክም አሉት፡፡

“አባዬ፣ ሰለዚህ ጉዳይ ብዙ ሳስብ ነበረ፡፡ የሳምሶን ፀጉር ረጅም አልነበረምን? ሙሴና ኖህ እንዲሁም ኢየሱስ ረጅም ፀጉር አይደል የነበራቸው?”

“እዚህ ላይ እውነት አለህ፣ ልጄ አሉ አባቱ “ነገር ግን እነዚህ የጠቀስካቸው ሁሉ የሚጓዙት በእግራቸው ነበር፡፡”
*****

 

‹‹ሚቺቃፓ›› የካፊቾ ባህላዊ ምግብ

 

ሚቺቃፓ የከብት ሥጋን እንደ ጉራጌ ክትፎ ሳይደቅ በጎረድ ጎረድ መልክ በመክተፍ የሚዘጋጅ የካፊቾ ብሔረሰብ ባህላዊ ምግብ ነው፡፡ ሚቺቃፓን ለማዘጋጀት በትኩሱ ከታረደ የከብት ሥጋ ከታናሽ ታላቅና ሽንጥ ላይ ጮማ ያልበዛበት ሥጋ ይመረጣል፡፡ ከዚያም ሥጋው በደንብ በተሞረደ ቢለዋ ዝርግ መክተፊያ ላይ ጎረድ ጎረድ (ቃፓ) ተደርጎ ይከተፋል፡፡ የተከተፈው ሥጋ በትልቅ የሸክላ ጣቢያ (ጣቦ) ላይ ይደረጋል፡፡ ነጭ ሽንኩርትና ጨው አንድ ላይ ተደቁሶ ሥጋው ላይ ይጨመራል፡፡ ከዚያም ቅቤ ኮራኖ (ትንሽ ማሰሮ) ውስጥ ተደርጎ ምድጃ ዳር በማስቀመጥ እሳት በደንብ መቶት መቅለጥ ሲጀምር ጎርድ  ጎረዱ ሥጋ ላይ ይጨመርና ይማሰላል፡፡ ሥጋው ግን እሳት አይነካውም፡፡ ጥሬውን ከነጭ ሽንኩርት፣ ጨውና ቅቤ ጋር ተዋህዶ የሚበላው፡፡ ማባያው ከምርጥ ቆጮ የተጋገረ ሳሳ ያለ ቂጣ ነው፡፡ ይህ ምግብ በዋናነት የሚዘጋጀው ለመስቀልና ሌሎች ዓመታዊ ክብረ በዓላት ሲሆን፣ አቅም ያለው ሰው በእንግዶች ሲጎበኝ አዘጋጅቶ በማቅረብ ዘመዶቹንም ሆነ ጓደኞቹን ሊያስተናግድበት ይችላል፡፡ አዳኞች የድኩላ ሥጋ በከብት ሥጋ ምትክ በመጠቀም እላይ በተጠቀሰው መልክ ሚቺቃፓ የሚያዘጋጁበት ሁኔታ አለ፡፡ ከከብትም ሆነ ከድኩላ ሥጋ የሚዘጋጀው ሚቺቃፓ ከተበላ በኋላ በደንብ የበሰለ የጤፍ ወይም ደጋ ከሆነ የገብስ ዶጮ (ቦርዴ ጠላ) ይጠጣበታል፡፡

Standard (Image)

ሀገር ማለት የኔ ልጅ

$
0
0

ሀገር ማለት ልጄ፣ ሀገር ማለት፤

እንዳይመስልሽ የተወለድሽበት ቦታ፣

የተወለድሽበት አፈር፣

እትብትሽ የተቀበረበት ቀድመሽ የተነፈስሽው አየር፤

ብቻ እንዳይመስልሽ፡፡

ሀገር ረቂቅ ነው ቃሉ፡፡

ሀገር ውስብስብ ነው ውሉ፡፡

ሀገር ማለት ልጄ

ሀገር ማለት ምስል ነው፣ በህሊና የምታኖሪው…

…በእውቀትሽና በሕይወትሽ

በውነትሽና በስሜትሽ

የምትቀበይው ምስል ነው፣

በህሊናሽ የምታኖሪው፤

ስወጅ ሰንደቅ ታደርጊው

ቢያስጠላሽ የማትቀይሪው፡፡

ሀገር ማለት የኔ ልጅ

ሀገር ማለት ቋንቋ ባንደበት አይናገሩት

በጆሮ አያዳምጡት

አማርኛ፣ ኦሮምኛ፣ አፋርኛ፣ ቅማንትኛ፡፡

ጉራግኛ ወይ ትግርኛ ብለው የማይፈርጁት፡፡

  • ከበድሉ ዋቅጅራ ‹‹ሀገር ማለት ልጄ›› (2004 ዓ.ም.) የተቀነጨቡ ስንኞች

*****

‹‹አገር መውደድ…››

‹‹አገርን መውደድ ራስን መውደድ ነው፡፡ ሰው የሰውነቱ ክብር የሚታወቀውና የሚታፈረው አንገቱን ቀና አድርጎ በኩራት ለመናገርና ቃሉ ክብደት ለማግኘት የሚችለው ሐዘኑንና ልቅሶውን፣ ደስታውንና ዘፈኑ የሚያምርበት፡፡ ሰው ስለ መብቱ ቢሟገት የሚሰምርለት በአገሩ ነው…››

መስፍን ወልደማርያም ‹‹ኢትዮጵያዊነት፣ ልማት በኅብረት›› (1966 ዓ.ም.)

* * *

የአፍሪካውያን መካነ መቃብር በድሬዳዋ

ድሬዳዋ ውስጥ በተለምዶ ነምበር ዋን በሚባለው አካባቢ የሚገኘው የአፍሪካውያን መካነ መቃብር 70 አፍሪካውያን ወታደሮች ያረፉበት ነው፡፡ ከእነኚህ መካከል 60ዎቹ የፋሺስት ወራሪ ሠራዊትን ከኢትዮጵያ ምድር ጠራርጎ ለማስወጣት ከቃል ኪዳኗ አጋር የእንግሊዝ ጦር ጋር በምሥራቅ አፍሪካ በኩል የገቡት የቅኝ ግዛቶች (ኬንያ፣ ታንዛኒያና ኡጋንዳ…) ወታደሮች መሆናቸውን መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ በቀብር ሥፍራው ከተቀበሩት አፍሪካውያን መካከል የአምስቱ አፍሪካውያን ዜግነትና ማነነት ግን አይታወቅም፡፡

ከ70ዎቹ አፍሪካውያን በተጨማሪ በጦርነቱ ወቅት የተገደሉ ሦስት የብሪታንያ አየር ኃይል አባል የነበሩ እንግሊዛውያን ቀብራቸው በሀገሬው የቀብር ሥፍራ ቢቀበርም ቆይቶ አስከሬናቸውን ለይቶ ማውጣት ባለመቻሉ በአፍሪካውያን መካነ መቃብር ውስጥ መታሰቢያ ተተክሎላቸዋል፡፡

ይህንን ታሪካዊ ሥፍራ የእንግሊዟ ንግሥት ኤልዛቤትና የኬንያው መሪ ጆሞ ኬንያታ የጎበኙት ሲሆን ለሀገራችን መስዋዕት ለሆኑ ለእነኚህ አፍሪካውያን ወንድሞቻችን እንደ ሀገር ተገቢውን ክብር እየሰጠን መሆን ያለመሆኑ በሚገባ ሊጣራ ይገባል፡፡

- አዲስ ቸኮል፣ ከድሬዳዋ

* * *

አመፀኛ ዋሻ

ሰሜን ሸዋ፣ መንዝ ውስጥ ቀያ ገብርኤል በተባለ ቦታ የሚገኘው አመፀኛ ዋሻ እጅግ የገዘፈ ታሪክ ያለው ነው፡፡ ከወራሪው የፋሽስት ሠራዊት ጥቃት ለመሸሽ በዋሻው ውስጥ የተጠለሉ 5,500 ያህል ሰዎችን አረመኔዎቹ የፋሺስት ሠራዊት ወራሪዎች በመርዝ ጋዝ አፍነው ፈጅተዋቸዋል፡፡ በየካቲት ወር 2008 ዓ.ም. የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች የተወሰኑ የምክር ቤት አባላትና ሌሎች እንግዶች ከአካባቢው ነዋሪ ጋር በመሆን ለመጀመሪያ ጊዜ በዋሻው ውስጥ በመግባት ያንን አሰቃቂ የጠላት ግፍ ተመልክተዋል፡፡  

  • ‹‹እኔ ለአገሬ (፲፱፻፴፫ - ፳፻፰)››

* * *

ባፈነገጠ አለባበሳቸው ከስብሰባ የተባረሩት ሚኒስትር

በቅርብ የተሾሙት የደቡብ ሱዳኑ የመስኖና ውኃ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ማቢዮር ጋራንድ ደማቢዮር ሙሉ ጥቁር ለብሰው ቦው ታይ (ቢራቢሮ ከረባት) አድርገው ወደ አንድ ስብሰባ ያመራሉ፡፡ ስብሰባውን ይመሩ የነበሩት የደቡብ ሱዳኑ ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ሚኒስትሩን እንዳዩዋቸው በብስጭት ከስብሰባ አባረዋቸዋል፡፡ ፕሬዚዳንቱ ሚኒስትሩን ያባረሯቸው ለስብሰባ ከሚለበስ አለባበስ ያፈነገጠ አለባበስ በመከተላቸው ነው፡፡ ፕሬዚዳንቱ በሚኒስትሩ ያልተገባ አለባበስ መበሳጨታቸውን የዘገበው ዴይሊ ሞኒተር፣ ሚኒስትሩ ቤታቸው ሄደው ቢራቢሮ ከረባታቸውን በረዥም ከረባት ለውጠው ጥቁር ኮፍያ አድርገው ቢመጡም በድጋሚ ወደ ስብሰባው እንዳይገቡ መከልከላቸውን አሳውቋል፡፡ የተለያዩ ግለሰቦች በጉዳዩ ላይ አስተያየት እየሰጡ ነው፡፡ አንዳንዶች የሚኒስትሩ አለባበስ እንደ ትልቅ ነገር ተወስዶ ከስብሰባ መታገዳቸው አግባብ እንዳልሆነ ገልጸዋል፡፡ አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች ሀገሪቱ ያለችበት ቀውስ ቅድሚያ ሊሰጠው እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡  

 

Standard (Image)

ዝንቅ

$
0
0

ይሄ እንደቀይ ምንጣፍ ጎዳናው ላይ የተበተነው ቀይ ፅጌረዳ እንዳይመስላችሁ፡፡ ከደቂቃ በፊት የኮካ ኮላ ሳጥን የጫነ ባለ ተሳቢ ተሽከርካሪ ኮልፌ አበራ ሆቴል አካባቢ ተገልብጦ የመንገዱን አጥር ከመሰባበር አልፎ ጠርሙሶቹን በታትኖና ከጥቅም ውጪ አድርጓቸው

ነው፡፡ በነገራችን ላይ እዚሁ ቦታ ከ15 ቀናት በፊት ባለ ተሳቢ ተሽከርካሪ ተገልብጦ ነበር፡፡ ጋዜጠኛ ጌጡ ተመስገን በፌስቡክ ገጹ ላይ

በግንቦት 1 ቀን 2008 ዓ.ም. ካሰፈረው

*******

 

ፊደል ሲሸሽ

ሆሄ ብዙ ቃላት …

ለማጠር አስበው

አደባባይ ወጡ …

ፊደል አንጠባጥበው፡፡

‘ፍ’ን ተወና ፍቅር …

ታየ ሰው ብሎት ‘ቅር’፤

 ‘ጋ’ ን ትቶ ለጋሱ  …

ሆኖ ቀረ ‘ለሱ’፤

‘ብ’ ን ወርውሮ ንብረት …

ሸሸ ጥሎ ‘ንረት’፤

 ዝ‘ ን ክዶ ዝነጣ …

ባዶ ቀርቶ ‘ነጣ’፤

‘ው’ ን ጥሎ መውደዴ …

ሆነብኝ ‘መደዴ’፡፡

  • ዶ/ር ኤልያስ ሳሙኤል ‹‹ከርከሬሻ›› (2008)

********

በበረዶ ገና ጨዋታ ላይ የወደቁት ፑቲን ዋንጫ አነሱ

የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድርሚር ፑቲን ለስፖርታዊ እንቅስቃሴ ባላቸው ፍቅር ይታወቃሉ፡፡ ፈረስ ግልቢያ፣ ዋናና አይስ ሆኪ ወይም የበረዶ ገና ጨዋታ ከሚያዘወትሯቸው ስፖርቶች ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ በአንድ ወቅት ፕሬዚዳንቱ የሳይቤሪያን በረዷማ ውኃ በዋና ማቋረጣቸው የብዙዎችን ቀልብ ስቦ ነበር፡፡ በዚህ ሳምንት ደግሞ ከፍተኛ ባለሥልጣኖችና ነጋዴዎችን የያዘ የአይስ ሆኪ ቡድን ይዘው ወደ ውድድር አምርተዋል፡፡ በበረዶው ላይ ወዲያ ወዲህ በመንሸራተት ለተጋጣሚ ቡድኑ ችሎታቸውን እያሳዩ በነበረበት ወቅት ግን ያልጠበቁት ነገር ገጠማቸው፡፡ ሮይተርስ እንደዘገበው፣ ፕሬዚዳንቱ ሲጫወቱ በረዶው አንሸራቷቸው ወድቀዋል፡፡ በሩሲያ፣ ሶቺ በተካሄደው አይስ ሆኪ ላይ ቀይ በሰማያዊ ማልያ ለብሰው ቡድናቸውን ይመሩ የነበሩት ፑቲን፣ ባልተጠበቀ ሁኔታ ቢወድቁም፣ ጨዋታውን ከማጠናቀቅ አላገዳቸውም፡፡ ጨዋታውንም በድል ፈጽመዋል፡፡ የቀድሞው የሶቭየት ኅብረት አይስ ሆኪ ተጨዋች አሌክሳንደር ያኩሼፍም ዋንጫ አበርክቶላቸዋል፡፡

*******

 

በታይላንድ በተራቀቀ የኩረጃ ቴክኖሎጂ የታጀበው ፈተና ተሰረዘ

በታይላንድ ሦስት ተማሪዎች የሕክምና ትምህርት መግቢያ ፈተና ላይ የተራቀቀ ቴክኖሎጂ ተጠቅመው መኮራረጃቸውን ተከትሎ ፈተናው ሙሉ ለሙሉ ተሰረዘ፡፡

ቢቢሲ እንደዘገበው፣ ተማሪዎቹ የተጠቀሙት በእጅ ሰዓታቸው ላይ የተገጠመና በስለላ ወቅት አካባቢን መቃኘት የሚችል የተራቀቀ መሣሪያ ነው፡፡

ሰዓታቸው ላይ የተገጠመው ቴክኖሎጂ ‹‹ሚሽን ኢምፖሲብል›› በተሰኘውና እ.ኤ.አ. በ1996 በተለቀቀው የስለላ ፊልም ላይ ይታይ የነበረ ዓይነት ቴክኖሎጂ ነው፡፡

የታይላንዱ ቻናል ሦስት እንደሚለው፣ የተማሪዎቹ ማንነት ለጊዜው ባይገለጽም፣ በጥቁር መዝገብ ውስጥ ሰፍረዋል፡፡

ሦስቱ ተማሪዎች ገመድ አልባ ካሜራ ከእጅ ሰዓታቸው ላይ በመግጠም፣ የፈተናውን ጥያቄና መልስ ፎቶ በማንሳትና ቁጥራቸው በግልጽ ላልታወቁ ተማሪዎች በማስተላለፍ ነው ኩረጃውን በተራቀቀ ዘዴ የመሩት፡፡

የራንግሲት ዩኒቨርሲቲ አስተዳዳሪ እንደሚሉት፣ በሚያዝያ 29 እና 30 ቀን 2008 ዓ.ም. ተሰጥቶ የነበረው የሕክምና ትምህርት መግቢያ ፈተና ተሰርዞ ግንቦት 2008 ዓ.ም. ማብቂያ ላይ እንዲሆን ተወስኗል፡፡

********

ጥቁሩ አሜሪካዊ ማርቲን በነጭ ፖሊስ የተገደለበት መሣሪያ ለጨረታ ቀረበ

የፍሎሪዳ ነዋሪ የሆነው የ17 ዓመቱ ትራይቮን ማርቲን እ.ኤ.አ. በ2012 ጆርጅ ዚመርማን በተባለው ፖሊስ የተገደለበት ሽጉጥ ለጨረታ ቀረበ፡፡

ቢቢሲ እንደዘገበው፣ መሣሪያውን ለጨረታ ያቀረበው፣ ማርቲንን ራስን በመከላከል ምክንያት ተኩሶ የገደለው ዚመርማን የተባለው ፖሊስ ነው፡፡

ዚመርማን መሣሪያውን ለጨረታ ያቀረበበት ምክንያትም፣ በ2016 ማብቂያ አሜሪካ ለምታካሂደው ምርጫ ዕጩ የሆኑት ሒላሪ ክሊንተን ያቀረቡትን ‹‹መሣሪያዎች ላይ ገደብ የመጣል ዕቅድ›› ለማክሸፍ ነው፡፡

ክሊንተን፣ በአሜሪካ የጦር መሣሪያ ያለገደብ ለግለሰቦች መሸጡን፣ ንፁኃንም በግለሰቦች የጦር መሣሪያ እየተገደሉ መሆናቸውን በመቃወም፣ በፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ቢያሸንፉ፣ የጦር መሣሪያ ሽያጭ ላይ ገደብ እንደሚጥሉ አሳውቀው ነበር፡፡

ወጣቱና ጥቁሩ ማርቲን በነጩ ፖሊስ ዚመርማን በመሣሪያ መገደሉ በፍሎሪዳ ብጥብጥ አስነስቶ እንደነበር ይታወቃል፡፡ ጉዳዩም የዘር ሆኖ ነበር፡፡ ዚመርማን መሣሪያ ያልታጠቀውን ማርቲን ተኩሶ ቢገድልም፣ ‹‹ራሱን ለመከላከል ነው›› በሚል በነፃ መለቀቁም ይታወሳል፡፡

Standard (Image)

ዝንቅ

$
0
0

አጥሩ የት አለ?

እጅግ የተከበሩ የዓለም ሎሬት፣ ሜትር አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ ባረፉ በአራት ዓመታቸው፣ በመካነ መቃብራቸው ላይ የቆመው ሐውልት፣ ሚያዝያ 2 ቀን 2008 ዓ.ም. መመረቁ ይታወሳል፡፡ በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል አፀድ ውስጥ የሚገኘው ሐውልታቸው በተመረቀበት ጊዜ፣ የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ዮናስ ደስታ፣ የሐውልቱ አጥር ለምረቃው ሲባል አለመደረጉንና ከሰዓት በኋላ ወይም በቀጣዩ ቀን እንደሚተከል ተናግረው ነበር፡፡ ቃላቸው ሳይፈጸም 43 ቀናት ተቆጥረዋል፡፡ በታላቁ የስፖርት ሰው፣ ዶ/ር ወልደመስቀል ኮስትሬ ሥርዓተ ቀብር ላይ የተገኙ ሐዘንተኞች፣ ‹‹የኚህ የአፈወርቅ ተክሌ ሐውልት እንደ ሌሎች አጥር የለውም እንዴ? ወይስ ተነስቶ ነው?›› ሲሉም ተደምጠዋል፡፡ አጥሩም እንደ ሐውልቱ ዘመኑን ይቆጥር ይሆን?

(ፎቶ በመስፍን ሰሎሞን)

 

ኑ ግቡ…

 

ሕይወት አያልቅባት…

እልፍኟ ሰፊ ነው

ማእዷ ብዙ ነው፤

ሁሉን አቅርባለች…

ውስጧን ለጎበኘው፤

እምነትና ስርቆት

እጦትና ድሎት

ምስጋናና ስድብ

ዳንስና ድብድብ፣

ሰላም…አምባጓሮ

የምስራች…ሮሮ

ጥላቻና ፍቅር

እፎይታ…ግርግር፣

ለቅሶና ሙዚቃ

እልልታና ሲቃ

ተንኮል ሐቀኝነት

ድጋፍ.. ምቀኝነት

ጭንቀት… ፈንጠዝያ

ነፃነት.. ዘብጥያ፣

ሁሉን አሰባጥራ

ብፌ አርጋ ደርድራ፣

እልፍኟን ክፍት አድርጋ…

ደጃፏ ቆማለች፤

‹‹ብሉልኝ ጠጡልኝ…

ኑ ግቡ›› ትላለች፤

ጥሪዋን አድምጦ…

ደጇ ሰው ሰፈረ፤

የሚገባው ገባ…

ያልገባው ከሰረ፡፡

- ዶ/ር ኤልያስ ሳሙኤል ማቴዎስ፣ ‹‹ከርከሬሻ›› (2008)

* * *

ኔዘርላንድስ እስረኛ አልባ የሆኑ እስር ቤቶችን የስደተኛ መጠለያ አደረገች

በኔዘርላንድ የወንጀል ድርጊት መቀነስን ተከትሎ እስር ቤቶች ባዶ እየሆኑ ሲሆን፣ የአገሪቱ መንግሥትም ባዶ እስር ቤቶችን ለስደተኞች መጠለያ ማድረግ ጀምሯል፡፡

ናሽናል ጂኦግራፊ በድረገጹ እንዳሰፈረው፣ ኔዘርላንድስ በዓረብ አገሮች ተከስቶ የነበረውንና አሁንም ያልተቋጨውን አብዮት ተከተሎና ከሌሎች አገሮች የሚሰደዱትን ጨምሮ 50 ሺሕ የሚደርሱ ስደተኞችንና የፖለቲካ ጥገኝነት ጠያቂዎችን በ2015 ተቀብላለች፡፡

እንደዘገባው ከሆነ፣ በኔዘርላንድስ ወንጀልን ለመከላከል የተቀመጡ ሕጐችና የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎች ለወንጀል መመናመን ያበረከቱት አስተዋጽኦ እስር ቤቶች ባዶ እንዲሆኑ ረድቷል፡፡ ይህም ስደተኞች ሳይጉላሉ የተሟላ ቁሳቁስ ባሏቸው እስር ቤቶች ውስጥ እንዲኖሩ ዕድል ፈጥሯል፡፡

በእስር ቤቱ እንዲጠለሉ ዕድል የተሰጣቸው ስደተኞች በፈለጉት ሰዓት ከእስር ቤቱ መውጣትና መግባት ይችላሉ፡፡ ተቀጥረው መሥራት የማይፈቀድላቸው ሲሆን፣ ወደፊት በኔዘርላንድስ ለሚኖራቸው ሕይወት ወሳኝ የሆኑትን የደች ቋንቋና ብስክሌት መንዳት ይማራሉ፡፡

አሶሽየትድ ፕሬስ አንዳንድ በእስር ቤቱ የሚገኙ ስደተኞችን አነጋግሮ እንደዘገበው፣ ስደተኞች በመጠለያ ውስጥ ሥጋት ሳይገባቸው እየኖሩ መሆናቸውን ወደውታል፡፡

በእስር ቤቱ ስፖርታዊ ጨዋታዎች የሚደረጉባቸው ሥፍራዎችን ጨምሮ፣ በአውሮፓ ደረጃ መሠረታዊ የሚባሉ ፍላጐቶች ሁሉ ተሟልተው እንደሚገኙ ተዘግቧል፡፡

* * *

የተናገሩትን ውሸት ያለማስታወስ ምስጢር

በሕይወት ዘመን በአንድም ይሁን በሌላ መልኩ ውሸት መናገር ያጋጥማል፡፡ በኢትዮጵያ ‹‹ዋሽቶ ማስታረቅ›› የሚባል ብሂልም አለ፡፡

ከታዳጊነት ዕድሜ ጀምሮ በክፍል ውስጥ ፈተና በመኮራረጅ፣ የቤት ሥራን የራስ አስመስሎ ከሌላ ተማሪዎች መገልበጥ፣ እንዲሁም ለትዳር አጋር ወይም ለጓደኛ ታማኝ አለመሆንም፣ ምንም ዓይነት ምክንያት ይኑራቸው ከውሸት ይመደባሉ፡፡ መንግሥታትም ሕዝባቸውን የሚዋሹበት ሁኔታ አለ፡፡

ውሸት እንዳለ ሆኖ፣ አንድ ሰው ውሸት ከተናገረ በኋላ የሚሰማው ስሜትና ያንን ውሸት ደግሞ የመናገር ወይም የማስታወስ አቅሙ ምን ያህል ነው የሚለው እንደየሰዉ የተለያየ ቢሆንም፣ በአሜሪካ የሚገኙ ሳይንቲስቶች በጥናት ያገኙትን በ‹‹ናሽናል አካዴሚ ኦፍ ሳይንስ ፕሮሲዲንግ›› ላይ አሳትመዋል፡፡

እንደ ግኝቱ ከሆነ፣ ውሸት የሚናገሩ ግለሰቦች አንዴ የተናገሩትን ውሸት በሌላ ጊዜ ራሱን ደግመው መናገር ወይም መፈጸም አይችሉም፡፡ ምንም እንኳን በጥንቃቄ የሚዋሹ ሰዎች ቢኖሩም፣ ጥናቱ ከተካሄደባቸው ሰዎች አብዛኞቹ ቀድመው የተናገሩትን ወይም የፈጸሙትን ውሸት በሌላ ጊዜ አላስታወሱትም፡፡ ይህም አዕምሮ በአብዛኛው መዝግቦ የሚይዘው የሰውን መልካሙን ወይም ውስጡ የሚያውቀውን እውነት መሆኑንና ውሸት አንዴ ከተፈጸመ በኋላ በዋሸው ሰው ዘንድ እየተረሳ እንደሚሄድ ያሳያል፡፡ አዕምሮም ከውሸት ይልቅ እውነትን ይዞ የመቆየት አቅሙም ይበረታል፡፡

* * *

የ100 ዓመቷ አዛውንት የ100 ሜትር ሩጫ ሪከርድ አስመዘገቡ

በደቡብ ካሮሊና ነዋሪ የሆኑት የ100 ዓመቷ አዛውንት የ100 ሜትር ሩጫ በ46.7 ሰከንድ ሮጠው በማጠናቀቅ በእሳቸው ዕድሜ ቀድሞ የተመዘገበውን አንድ ደቂቃ ከ16 ሰከንድ ሰበሩ፡፡

ፎክስ ካሮሊና እንደዘገበው፣ መምህርት የነበሩት ኤላ ኮልበርት ውድድሩን ያደረጉት፣ ‹‹ሚድል ስኩል›› ውስጥ ሲሆን፣ ውጤታቸውም ተረጋግጦ በጊነስ የሚሰፍርበትን ጊዜ እየተጠባበቁ ነው፡፡

ለ36 ዓመታት የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት መምህርት ጡረተኛዋ ኮልበርት፣ ‹‹ያስመዘገብኩት ውጤት ተማሪዎች ከሠሩ ውጤት እንደሚያገኙ እንዲገነዘቡ ያበረታታል፤›› ብለዋል፡፡  

ኮልበርት 100ኛ ዓመታቸውን ያከበሩት ግንቦት 3 ቀን 2008 ዓ.ም. ነበር፡፡

Standard (Image)

366 ሰንደቅ ዓላማዎችን የተነቀሱት ህንዳዊ አዛውንት

$
0
0

የ74 ዓመቱ ህንዳዊ አዛውንት ፓርካሽ ሪሺ የ366 አገሮችን፣ እንዲሁም ዓለም አቀፍ ተቋማትን ሰንደቅ ዓላማዎችና የመሪዎች ምስልን በመነቀስ የዓለም የድንቃ ድንቅ መዝገብ ላይ ስማቸውን ማስፈራቸውን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡ አዛውንቱ ከ20 በላይ ሪከርዶችን መስበራቸውን የሚናገሩ ሲሆን በአጠቃላይ ሰውነታቸው ላይ ያለው ንቅሳት (ታቶ) 500 ይሆናል፡፡ 500 የመጠጥ ስትሮዎችን እንዲሁም 50 የሚበሩ ሻማዎችን በአፋቸው ለመያዝ ያስችላቸው ዘንድ ጥርሳቸውን በሙሉ አስወልቀዋል፡፡ ምንም እንኳ በሰውነታቸው ላይ ያኖሩት ንቅሳት ከ500 በላይ ቢሆንም፣ ከባዱ ነገር ግን በርካታ ስትሮዎችን ከአፋቸው ማኖር እንደሆነ ራሳቸውን ጊነስ ሪሺ እያሉ የሚጠሩት አዛውንት ይናገራሉ፡፡ ‹‹496 ስትሮዎችን በአንድ ጊዜ በአፌ ይዣለሁ፡፡ ይህን ለማድረግ ደግሞ ሁሉንም ጥርሶቼን ማስወገድ ነበረብኝ፤›› በማለት ለሮይተርስ ተናግረዋል፡፡ ከሰንደቅ ዓላማዎች በተጨማሪ አዛውንቱ፣ የህንዱን ጠቅላይ ሚኒስትርና የባራክ ኦባማን፣ የንግሥት ኤልሳቤጥንና የማህተመ ጋንዲን ምስሎች ተነቅሰዋል፡፡ አሁንም የሌሎች የዓለም መሪዎችን ምስል እንደሚጨምሩ አሳውቀዋል፡፡  

 

አንድ ቀን

አንድ ቀን አድጌ አንድ ቀን ተምሬ

አንድ ቀን ሠርቼ አንድ ቀን ከብሬ፤

አንድ ቀን ወድጄ አንድ ቀን አግብቼ

አንድ ቀን ወልጄ አንድ ቀን አርጅቼ፤

አንድ ቀን! አንድ ቀን! አንድ ቀን አርፋለሁ

እያልኩ አንድ ቀኔን ስናፍቃት አለሁ፡፡

ነገር ግን ውሏ’ድሮ ዘግይቶ ሲገባኝ

ቀኔን መሸኘቴን አንድ ቀን እያልኩኝ፤

አልገባኝም እንጂ ሁሌም የምመኘው

ለካስ አንድ ቀኔ ሕይወቴ ዛሬ ነው፡፡

መላኩ ደምለው፣ ‹‹ብልጭታ›› (2008)

* * *

የቆላ አገር በጊዜ መከራ መሥሪያ ሥራ

በአገራችን ኢትዮጵያ በ1928 ዓ.ም. በጥንታዊ ጠላቷ በተወረረች ጊዜ የግርማዊ ንጉሥ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴን አርአያ በመከተልና ለሕዝባቸውም በየጊዜው በዲስኩር የገለጹትን መልካም ምክርና ትዕዛዝ መሠረት በማድረግ የአርበኞች ማኅበር በየስፍራው ተመሠረተ፡፡

ኢትዮጵያ ከሦስት ሺሕ ዘመን በፊት የነበረች ሥርወ መንግሥት ስለሆነች ከጥንት ጀምራ እስከ ዛሬም በጀግኖቿና በንጉሠ ነገሥቷ እየተመካች፤ በኮረብታዋና በበረሃዋ እየኮራች ትኖራለች፡፡ የሚመጣበትን ማናቸውንም ጠላት ባላት መሣሪያ በጀግኖች ደፋርነት እየመከተች የምትኖር ነች እንጂ ያልሠለጠነች ወይም አሠልጣኝ የሚያሻት አለመሆኗን ለማስረዳት ጀግኖቿም በሰፊው ሰዓት ያደረጉት ተጋድሎ የሚያስረዳ ሆኗል፡፡ በእነሱም ምንም እንኳ መከራ ቢበዛባቸው በተፈጥሮዋቸው የአደጋ ችሎታ ያላቸው ብርድ ትኩሳት ረሃብ፣ ውኃ ጥም፣ በሽታ፣ ጦር፣ የማይፈሩ ስለሆኑ ጠላትን በድፍረት ይቃወሙት ጀመር፡፡

አርበኞች ወደ ጦር ሜዳ የተሰማሩት ከጥንት ተያይዞ ዘር በዘር እየተቀዳ በሚተላለፍና ከአባቶቻቸው ባገኙት ጀግንነት ነው እንጂ በስብከት ወይም በጭቆና መሰቀቅ የሸሹ አልነበሩም፡፡ ጠላት የሚወጋቸውም በጃቸው ባለ መሣሪያ ዓይነት ሳይሆን በአውሮፕላን አደጋ በቦምብ በመርዝ በብርቱ ጭከና ነበረ፡፡

ኢጣልያኖች ባላገሩን ወንዱን፣ ሴቱን እየገደሉ ሕፃኑን እየሰለቡ፣ ቤቱን፣ ሰብሉን እያቃጠሉ፣ ከብቱን እያረዱ የአርበኝነት ሥራ ከሀገር ላይ እንዲጠፋ ለማድረግ ምንም እንኳ ቢያስብ ከሞት የተረፈው ባላገር ከብት ካለበት አገር ከብት እየገዛ፤ መግዣም ያጣ በያረሁ በዶማ እየቆፈረ ራሱ ረሃቡን ታግሶ በጦር ውስጥ የሚውሉት ቢበሉት ይሻላል በማለት ስንቅ እያቀበለ የታመመውን በቤቱ እየደበቀ ያስታምም ጀመረ የሞተውንም አርበኛ ምንም እንኳ ኢጣሊያ በቤተ ክርስቲያን እንዳይቀበር ቢያውጅ ቀሳውስትም ቢገዝቱ አዋጁን አፍርሶ በክርስቲያን ሕግ እየቀበረ ከጥንት ጀምሮ ከአባቶቹ በክብር ለተቀበላት ነፃነቱ ይጋደልላት ጀመረ፡፡

 አባቶቻችን በግራኝ ዘመን ዕረፍት ያገኙት ከ15 ዓመት በኋላ አይደለምን? ይህ ሁሉ ቤተክርስቲያን የተሠራና ይህ ሁሉ ሰው የበዛስ ከዚያ ወዲህ አይደለምን? ከአባቶቻችን እንደሰማነው መቼውንም ቢሆን የቆላ አገር በመከራ ጊዜ ሥራ መሥሪያ ነው፡፡

  • ከ1 ኢትዮጵያዊ ተጻፈ “የአርበኞች ትግል ከፋሺስት ጋር” (በ1936 ዓ.ም.)

* * *

ራሱን ለማጥፋት ለየት ያለ ሙከራ ያደረገው ሰው

 በቺሊ ዋና ከተማ የሚገኝ አንድ የእንስሳት ዙ ቅዳሜ ዕለት ሁለት አንበሶችን ለመግደል ተገደደ፡፡ አንበሶቹን ለመግደል ምክንያት የሆነው ነገር ከወትሮው ለየት የሚል ይመስላል፡፡ ራሱን ማጥፋት  የፈለገ አንድ ወጣት ከአንበሶቹ ክፍል በመግባቱ የሰውየውን ሕይወት ለማዳን አንበሶቹን መግደል ግድ እንደነበር የአገሪቱ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል፡፡ የአፍሪካ አንበሶች ካሉበት የሽቦ አጥር ዘሎ የገባውን ሰው ወዲያው ሁለቱ አንበሶች ያጠቁት ጀመር፡፡ መጀመሪያ በተወርዋሪ ማደንዘዣ አንበሶቹን ለማቆም ቢሞክርም አንበሶቹ በዚህ ሊቆሙ አልቻሉም፡፡ ስለዚህም መግደል ብቸኛው አማራጭ ሆነ፡፡ አንበሶቹ    በመጠለያው ለ20 ዓመታት ያህል የኖሩ ሲሆን ዕድሜው በ20ዎቹ ውስጥ የሚገኘውና ራሱን በተጠቀሰው መልክ ለመግደል የሞከረው ወጣት በከባድ ጉዳት ወደ ሆስፒታል ተወስዷል፡፡

* * *

 

ቀይ ወፎች በቀላሉ ጥንዳቸውን ያገኛሉ

በአሜሪካ በሴንት ሉዊዝ ዩኒቨርሲቲ የተሠራ ጥናት እንደሚያሳየው ቀይ ቀለም ያላቸው ወንድ ወፎች በቀላሉ ተጓዳኝ (አጋር) ያገኛሉ፡፡ አጋር የማግኘት ዕድላቸውም ሌላ ቀለም ካላቸው ወፎች ጋር ሲነፃፀር ሰፊ ነው፡፡ ጥናቱ እንደሚያመለክተው ቀይነት በብዙ የወፍ ዝርያ ጥንዶች እንደ ጥራት የሚታይ ነገር ነው፡፡ በሌላ በኩል የተወሰኑ ወፎች እንደ ካናሪስና ዜብራ ፊንችስ ያሉ ቢጫ ቀለም የሚሰጣቸውን እንደ ጥሬ፣ ፍራፍሬና ነፍሳት ይመገባሉ፡፡ በተጨማሪም ቀይ ቀለምን በመለየትና ቀይ ቀለም በመያዝ ረገድም የተለየ ነገር ያላቸው የወፍ ዝርያዎች እንዳሉ በጥናቱ ተጠቅሷል፡፡

* * *

 

 

Standard (Image)

የሦስተኛው ፓትርያርክ አዲስ ሐውልት

$
0
0

ኢትዮጵያ የራሷን ፓትርያርክ መሾም ከጀመረች ወደ ስድስት አሠርታት ይጠጋል፡፡ በ57 ዓመት ውስጥ የአሁኑን ቅዱስ ፓትርያርክ ጨምሮ ስድስት ቅዱሳን አበው ቤተ ክርስቲያኒቱን መርተዋል፡፡ ከእነዚህ መካከል ከ27 ዓመት በፊት በዛሬው ዕለት ግንቦት 28 ቀን 1980 ዓ.ም. ያረፉት ሦስተኛው ፓትርያርክ (1968-1980) ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ይገኙበታል፡፡ በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ምዕራብ አቅጣጫ በሚገኘው መካነ መቃብራቸው ላይ የቆመው ሐውልታቸው፣ በዘመን ብዛት የማርጀቱና በመጐሳቀሉ እንደ አዲስ ተሠርቶ ባለፈው ሳምንት በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ተመርቋል፡፡ አዲሱን ሐውልት በግል ገንዘባቸው በ1.5 ሚሊዮን ብር ወጪ ያሠሩት በጎ አድራጊው አቶ ቁምላቸው ገብረ ሥላሴ መሆናቸው በምረቃው ዕለት ተነግሯል፡፡ በቀድሞ መጠርያቸው አባ መልአኩ ወልደ ሚካኤል ይባሉ የነበሩት አቡነ ተክለ ሃይማኖት፣ የተወለዱት በቤገምድርና ስሜን ጠቅላይ ግዛት፣ ማኅደረ ማርያም ገዳም አካባቢ፣ ጋዠን በሚባል ቦታ መስከረም 10 ቀን 1910 ዓ.ም. መሆኑን ገጸ ታሪካቸው ያመለክታል፡፡ (በሔኖክ ያሬድ) 
 

 

ምሳሌያዊአነጋገሮችከደራሲዎቻችንብዕር

ለአንቺ ብርቅሽ፣ የዘንጋዳ ሙቅሽ። - አሌክስ አብርሃም
ለወገን ጽናት፤ ለጠላት ቅናት። - አቤ ቶኪቻው
ለዶሮ አጥንት፣ መጥረቢያ አያስፈልገውም። - በጋሻው ሐዲስ
ልብ ያሰበውን፣ ኩላሊት ያመላለሰውን ያውቃል። - ንቡረዕድ ኤርምያስ ከበደ
ልጅ በጡት፤ እህል በጥቅምት። - ካህሳይ ገብረ እግዚአብሔር
ሙት አይሰማም፣ አይለማም። - አዳም ረታ
ሲመች በእጅ፣ ሳይመች በመጅ። - ሔኖክ የሺጥላ
ቢጨብጧት ትሞታለች፣ ቢለቋት ትበራለች። - አጥናፍ ሰገድ ይልማ
አለንጋ ባይገርፉበት ያስፈራሩበት። - ኤፍሬም እሸቴ
አይቴ ቁርጠቴ፣ ደፋ በይ ከፊቴ። - ዶ/ር እንዳላማው አበራ
አዳም በበደለ መድኃኒዓለም ካሰ። - ፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም
ከአሥር ዲግሪ፣ አንድ ግሮሠሪ። - ዶ/ር ፈቃደ አዘዘ
ከደሃ ቤት ጥቅስ፤ ከሀብታም ቤት ጥብስ። - በዕውቀቱ ሥዩም
የሮጠ አመለጠ፤ የቆመ ቀለጠ። - ዓለማየሁ ገላጋይ
የተቀማጭ፣ አፉ ምላጭ። - አቡነ መልከ ጻዴቅ
ጋን በጠጠር ይደገፋል። - ኃይለ መለኰት መዋዕል

- ዳንኤል ኤ. አበራ በድረ ገጹ እንደቀመረው

*******

‹‹እርኩምን ሊበሉ ጅግራ ነው አሉ››

ራስን መደለል በእንስሳትም መካከል በጥቂቶች ላይ የተደረገ ሆኖ፤ በምሳሌ ዓይነት እንደ ተረት የሚነገር ቃል እናገኛለን፡፡ ተረቱም እንደሚከተለው ነው፡፡

ከዕለታት አንድ ቀን አንዲት የተራበች ጦጣ ባንድ የወይን ስፍራ አጠገብ ስታልፍ ቁመቷ ከማይደርስበትና ዘልላም ልታወርደው ከማይቻላት አስቸጋሪ ከሆነ ካንድ ከፍተኛ ስፍራ ላይ በስሎ መልኩ ብቻ እንኳን የሚያስጐመጅ አንድ የወይን ዘለላ ተንዠርጐ ተመለከተች፡፡ ለማውረድም ሞክራ ሳይሆንላት ስለቀረ ልቧ እያወቀ፣ ራሷን በማታለል  ወይኑ እኮ እንደሆን በእውነቱ ገና አልበሰለም፤ ለጊዜው የደረሰ መሰለ እንጂ ጥሬ ነው፡፡ ስለዚህ ላንድ ጥሬ ለሆነ ላልበሰለ ወይን ይህን ያህል ምን ያደክመኛል? የሱን ዓይነት ከሌላስ ስፍራ አጥቼ ነውን? በማለት ራሷን ደልላ ይኸንኑ ቃል በመደጋገም ራሷን እየነቀነቀች ነገሩን አኳስሳ ትታው ሄደች ይባላል፡፡

እንደዚሁም አንዲት ሰጐን አንድ አዳኝ ጠመንጃውን ደግኖ ሊተኩስባት ሲያነፃፅርባት እያየች፤ ሮጣ  ሕይወቷን ለማዳን ከመሞከር ይልቅ፤ እዚያው ሁና ተደፍታ ዓይኖቹዋ እንዳያዩ ወደታች አቀርቅራ፤ የት አለና ነው አዳኝ? ቢኖር ለምን አላየውም? ይኸው ምንም ነገር አላይም እያለች በሐሳቧ ራሷን ደልላ ከዚያው አንገቷን ደፍታ ተቀመጠች ይባላል፡፡    

የቀድሞ አባቶቻችን፤ ሰው ያልኾነውን ነው በማለት ራሱን የሚደልል ከንቱ መኾኑን ተመልክተው ‹‹እርኩምን ሊበሉ፤ ጅግራ ነው አሉ›› ብለው ይተርኩት የነበረ ቃልም ይገኛል፡፡

ስለዚህ ሰው ራሱን በራሱ እንደ ሕፃን  ልጅ በመደለል በሐሳቡ የተመኘውን ነገር ሁሉ ሲፈጽም መታየቱ የቆየ እንጂ፤ አዲስ አይደለም፡፡

  • ዶ/ር የማነ ገብረማርያም ‹‹የፍልስፍና ትምህርት›› (1955)

******

ቻይና ለሴቶች የተለየ የመኪና ማቆሚያ ስፍራ አዘጋጀች

በቻይና ሴት አሽከርካሪዎች መኪናቸውን ለማቆም፣ ካቆሙበት ሥፍራ ለማውጣት የሚገጥማቸውን ችግር ለማቃለል ሲሉ፣ ለነርሱ ብቻ የሚያገለግለውን  ማቆሚያ ከሌሎቹ ስፍራዎች 50 በመቶ ያህል ሰፍቶ እንዲሠራ መደረጉን ዩፒአይ ዘገበ፡፡

ከመደበኛ የመኪና ማቆሚያ ሥፍራ በተለየ መልኩ በሐንግዙ ታንግሉ አውራ ጎዳና አካባቢ ፓርኪንጉ የተሠራው ሴቶች መኪና ለማቆምና መልሶ ለመውጣት መቸገራቸውን ከግምት በማስገባት ነው፡፡

መኪና ለብቻ የሚያቆሙበት ስፍራ መዘጋጀቱ ግን፣ ለጾታ ትንኮሳ ያጋልጣቸዋል የሚሉ ትችቶች በማኅበራዊ ድረ ገጾች እየተሰነዘሩ ነው፡፡

እ.ኤ.አ. በ2009 በደቡብ ኮሪያ ሲዖል ተመሳሳይ የሴቶች መኪና ማቆሚያ የተሠራ ቢሆንም፣ ሴቶች ላይ የሚደርስ ጾታዊ ጥቃትን ለመከላከል ተብሎ በንግድ ማዕከላት በሮች አካባቢ መሠራቱ ከቻይናው ለየት ያደርገዋል፡፡

******

ቻይና ሰዉ በቀን ከ200 ግራም በላይ ሥጋና እንቁላል እንዳይመገብ አቀደች

ቻይናውያን እያጋጠማቸው ያለውን ከመጠን ያለፈ ውፍረት ለመከላከል፣ የሥጋና የከብት ተዋፅኦ ምግባቸውን እንዲቀንሱ የቻይና መንግሥት ጠየቀ፡፡ የጤና ባለሙያዎችም አንድ ሰው በቀን ከ200 ግራም በላይ ሥጋና እንቁላል እንዳይበላ ዕቅድ አውጥተዋል፡፡

ኢንዲፐንደት ዩኬ እንደዘገበው፣ ቻይናውያን በቀን የሥጋና እንቁላል አመጋገብ መጠናቸው ከ200 ግራም እንዳይበልጥ የጤና ባለሙያዎቹ ዕቅድ ያወጡት፣ አንድ ቻይናዊ በቀን በአማካይ የሚመገበውን 272 ግራም ሥጋና 235 ግራም የከብትና የዶሮ ተዋጽኦ ለማስጣል ነው፡፡ የጤና ባለሙያዎች ዕቅድ ግን አሜሪካ ወደ ቻይና የምትልከውን የሥጋ መጠን ያሽቆለቁለዋል ተብሏል፡፡

 

 

Standard (Image)

ዝንቅ

$
0
0

የኢትዮጵያ አቪየሽን አካዳሚ 347 የአቪየሽን ባለሙያዎችን ሰኔ 2 ቀን 2008 ዓ.ም. በዲፕሎማ አስመርቋል፡፡ ከእነዚህ ውስጥ 25ቱ አብራሪዎች፣ 35 ቴክኒሻን፣ 43 የበረራ አስተናጋጆች እንዲሁም 244 በንግድና አገልግሎት በመስጠት ሥልጠና የወሰዱ ናቸው፡፡ ከተመራቂዎቹ ውስጥ የሩዋንዳ ዜግነት ያላቸውም ይገኙበታል፡፡

ፍለጋ

ከዛሬ ወደ - ትላንት ጉዞዬ

ለማንነቴ ወደ - ስሬ

ከቅርንጫፌ ከእንጭፍሩ

ከወደ ሰማይ - ሥሩ

በትዝታ ወደ አፈሩ

      ወደ ምድሩ

ከመሬቱም ወደ ንጥሩ

  • ምግቡ

ወደ አስተዳደጉ

  • መሠረቱ

ወደ ተራክቦ ዘሩ

  • ጽንሱ

ከዚያማ - እንዲያ . . .!

እንዲያ! እያለ ነው

ፍሬው ጣዕሙን - የሚለየው

መጎምዘዙ ወይ ጥፍጥናው

መተለቁ ወይ ማነሱ!

ወይ መርገፉ ወይ ማፍራቱ

ወይም ሞቱ ወይ ሕይወቱ፡፡

  • አዳነ ድልነሳሁ፣ ጨለማን ሰበራ፣ (1997)

********

ኬንያ በጦጣ ምክንያት አንድ ቀን ሙሉ በጨለማ ተዋጠች

ባለፈው ማክሰኞ ኬንያ ሙሉ በሙሉ በጨለማ ተውጣ እንደነበር ለዚህ ምክንያት የሆነው ድግሞ ጦጣ መሆኑን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡ በኬንያ ፓወር ዲስትሪቢውተርና ኬንጀን በሚተዳደረው ጊታሩ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ዝንጆሮ ትራንስፎርመር በማቃጠሉ 180 ሜጋ ዋት ኃይል ጠፍቷል፡፡ በዚህ ደግሞ መላ አገሪቱ ለአንድ ቀን በጨለማ ልትዋጥ ግድ ሆኗል፡፡ ‹‹ጦጣ በጊታሩ የኃይል ማመንጫ ጣቢያ ጣሪያ ላይ ወጣ ከዚያም ትራንስፎርመር ላይ ወደቀና ትራንስፎርመሩን አቃጠለ፡፡ ይህ በጣቢያው ያሉ ማሽኖች ላይ ጫና እንዲፈጠርና እንዲቃጠሉ ተፅዕኖ አሳድሯል፡፡ በዚህ ደግሞ 180 ሜጋ ዋት ኃይል አጥተናል፤›› በማለት ኬንጀን አስታውቋል፡፡ ኩባንያው በቀጣይ የሚያስተዳድራቸው የኃይል ማመንጫ ጣቢያዎች ከእንደዚህ ያለው በዱር እንስሳት ሊደርስ ከሚችል አጋጣሚ ይጠበቁ ዘንድ ደኅንነታቸውን እንደሚያረጋግጥ አስታውቋል፡፡

*******

ለየት ያለ የሥራ ቅጥር ቃለመጠይቅ

ቻርልስ ሽዋብ የተባለ አንድ የአሜሪካ ኩባንያ የሥራ ማስታወቂያ አውጥቶ ለመረጣቸው ሰዎች ቃለ መጠየቅ ያረገው በአንድ ሬስቶራንት ቁርስ ላይ እንደሆነ ዘኢንዲፔንደንት ዘግቧል፡፡ የኩባንያው ሥራ አስኪያጅ ዋልት ቢቲንገር ለቃለመጠይቅ የተጠሩት ባለሙያዎች የመረጡትን ዓይነት ቁርስ እንዲያዙ ካደረገ በኋላ በጎን ለአስተናጋጁ ምርጫቸውን አምጥቶ እንዲያመጣ በመንገር ምን ሊሉ እንደሚችሉ ለመመልከት መሞከሩንም ዘገባው ያብራራል፡፡ ‹‹ምርጫቸው ተቀያይሮ ሲመጣ ምን እንደሚሉ ማወቅ ስለፈለኩ ነው እንደዚያ ያደረኩት፡፡ ይበሳጫሉ፣ ግራ ይጋባሉ ወይስ እንዲሁ ነገሩን ለመረዳት ይሞክራሉ?›› በማለት በአጠቃላይ ምን ዓይነት ሰዎች እንደሆኑና ችግሮች ሲያጋጥሙ በምን ዓይነት መንገድ ማለፍ የሚመርጡ ሰዎች ናቸው? የሚለው ለማየት እንደሚያስችለው ተናግሯል፡፡ ሥራ አስኪያጁ እንዳለው የተጠቀመው መንገድ አዕምሯቸውን ሳይሆን ልባቸውን ለመመልከት የሚያስችለው ነው፡፡ ተቀጣሪዎቹ በሕይወታቸው ትልቅ ስለሚሉት ስኬትም ይጠየቃሉ፡፡ ለዚህ የሚሰጡት መልስ የዓለም ምልክታቸው ሰፊ ነው ወይስ በራሳቸው ዙሪያ የተወሰነ ነው የሚለውን ለማወቅ እንደሚያስችልም ሥራ አስኪያጁ ይገልጻል፡፡

******

በመቶ ሺዎች በሚቆጠሩ የሌሊት ወፎች የተወረረች ከተማ

በአውስትራሊያ በደቡብ ዌልስ የምትገኘው ቤታሚንስ ቤይ በመቶሺዎች የሚቆጠሩ የሌሊት ወፎች ተወራ እንደነበር ስካይ ኒውስ ዘግቧል፡፡

ከተማዋ ባለፈው ሳምንት በባለግራጫማ ጭንቅላቶቹ የሌሊት ወፎች ስትወረር፣ ነዋሪች ከቤት ለመውጣት፣ በርና መስኮት ለመክፈት ተቸግረው ነበር፡፡ የወፎቹ ድምፅ ነዋሪዎችን ሲረብሽ እንደዋለም ዘገባው ያሳያል፡፡

ወፎቹን ለመቆጣጠር የተቋቋመው ግብረ ኃይል እንዳስታወቀው እንደዚህ ብዛት ያላቸው የሌሊት ወፎች ከዚህ ቀደም ታይቶ አይታወቅም፡፡ በመሆኑም አብዛኞቹ የከተማዋ ነዋሪዎች የቤት ውስጥ እስረኛ ሆነው ለመዋል ተገደው ነበር፡፡

ወፎቹን ከከተማው እንዲዋጡ ለማድረግ ጭስና ድምፅ ከመልቀቅ በተጨማሪ የከተማዋ የጓሮ አትክልቶችና ዛፎች ተጨፍጭፈዋል፡፡

 

Standard (Image)

ለውይይትና ለውሳኔ የቀረበ አጀንዳ ሳይኖር ውሳኔ አይኖርም በሌለ ውሳኔም የሚጣስ ውሳኔ የለም

$
0
0

በዐምደሚካኤል ተክሌ

የነገው ሰው ትምህርት አክሲዮን ማኅበር አስመልክቶ ሰኔ 1 ቀን 2008 ዓ.ም. ሪፖርተር ጋዜጣ ያወጣውን ዘገባ ተመልክተናል፡፡ እንዳለመታደል ሆኖ በአክሲዮን ማኅበራችን ላይ የሚወጡ የተለያዩ የሚዲያ ዘገባዎችና የጥቂት አባሎች ጉሸማ የአክሲዮን ማኅበራችንን ምን ደረጃ ላይ እንደሚጥለው ዛሬም ያልተረዱ ጥቂት ባለአክሲዮኖች በሚሰጡት መረጃ መነሻ የሚወጡ ዘገባዎች ላይ ከልማዳዊና ተራ አመለካከት ለመውጣት ሲባል ጊዜን መስዋዕት በማድረግ መልስ መስጠት አስፈላጊ ሆኗል፡፡

  1. ቦርዱ የጣሰው የጠቅላላ ጉባዔ ውሳኔ ስላለመኖሩ

ቦርዱ እንደጣሰው ተደርጎ የቀረበው የኅዳር 25 ቀን 2008 ዓ.ም. ጉባዔ ምልአተ ጉባዔ ባለመሙላቱ ለሦስተኛ ጊዜ የተጠራ ድንገተኛ ጠቅላላ ጉባዔ ነበር፡፡ በአክሲዮን ማኅበሩ ችግሮች ዙሪያ በ2004 ዓ.ም. በጠቅላላ ጉባዔው ተሰይሞ የነበረው አምስት አባላት ያሉት አጥኚ ኮሚቴ ባቀረበውና በውስጥ ችግሮቻችን ምክንያት እየተንከባለለ ያለውሳኔ አድሯል ይባል በነበረው ሪፖርት ላይ ኮሚቴው በመጨረሻ አማራጭነት ባቀረባቸው ‹‹ኩባንያው ይከራይ ወይም ይሸጥ›› በሚሉ ሁለት የውሳኔ ሐሳቦች ላይ ውሳኔ ለማሰጠት ነበር፡፡ በኢትዮጵያ ንግድ ሕግ መሠረት የተጠራው ድንገተኛ ጉባዔ በእነኚህ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ የሚያሳልፈው ውሳኔ ‹‹ውሳኔ የሚሆነው›› በጉባዔው ከተገኘው ድምፅ በሁለት ሦስተኛው ከሁለት አንዱ የውሳኔ ሐሳብ ሲደገፍ ነው፡፡ ነገር ግን በዕለቱ ከተገኘው ድምፅ ውሳኔ የቀረቡት ‹‹ይሸጥ ወይም ይከራይ›› የሚለው አማራጭ የውሳኔ ሐሳብ አንዳቸውም በሁለት ሦስተኛ ድምፅ ባለመደገፋቸው ጉባዔው በዚህ የአጥኚ ኮሚቴ የውሳኔ ሐሳብ ላይ የሰጠው ውሳኔ የለም፡፡ ከእነኚህ አጀንዳዎች ውጪ የትምህርት ሥራው መቀጠል አለበት ወይስ የለበትም የሚለው ጭብጥ በአጀንዳነት አልቀረበም፡፡ ውይይትም አልተደረገም፡፡ ድምፅም አልተሰጠበትም፡፡ ጠቅላላ ጉባዔው በዚህ ላይም አልወሰነም፡፡

‹‹አክሲዮን ማኅበሩ ባለበት፣ በተቋቋመበትና በተሻሻለው ዓላማ መሠረት ሥራውን እንዲቀጥል ወስነናል፤››በሚለው የቃለ ጉባዔው አገላለፅ ላይ የቦርዱ ሊቀመንበር የተወሰነ ውሳኔ አለመኖሩን ተናግሯል የተባለው፣ በአጀንዳ ለጠቅላላ ጉባዔ ቀርቦ የሕጉን መስፈርት አሟልቶ የተላለፈ ውሳኔ እንደሌለ ለማመልከትና የትምህርት ሥራው እንዲቀጥል በግልጽ የተሰጠ ውሳኔ አለመኖሩን ለማመልከት እንጂ በቃለ ጉባዔው ላይ የሰፈረውን ቃል አልተጻፈም ለማለት አለመሆኑን ግልጽ ሊሆን ይገባል፡፡ ስለሆነም ከቃለ ጉባዔው የመጨረሻ አነጋገር መገንዘብ የሚቻለው ለጉባዔው ውሳኔ አጀንዳ ሆነው የቀረቡት ሁለቱ የውሳኔ ሐሳቦች ውድቅ መሆናቸውን በጥቅሉ የሚያሳይ፣ ከፍ ሲልም አክሲዮን ማኅበሩ ሕልውናውን እንደያዘ በተቋቋመበትና በተሻሻለው ዓላማ መሠረት ሥራውን እንዲቀጥል መባሉ ቦርዱ ከደረሰበት ውሳኔ ጋር የሚቃረን አይሆንም፡፡

ኩባንያው የተቋቋመው አንድም ለአባሎቹ ትርፍ ለማስገኘት ሲሆን፣ ጠቅላላ ጉባዔው እንዲሻሻል ያደረገው አንዱና ዋነኛው ተግባር ኩባንያው የማከራየት ሥራን በዓላማው ውስጥ እንዲያካትት የመተዳደሪያ ደንቡ አንቀጽ ማሻሻሉን ነው፡፡ ስለዚህ የተቋቋመበትን ትርፍ የማግኘት ዓላማ ለማሳካት አንደኛው አማራጭ ሥራ የሚሆነው ማከራየት ከሆነ ቦርዱ ከኩባንያውና ከባለአክሲዮኖቹ ጥቅም አንጻር ለአሥራ ስምንት ዓመት ከተዳከመና በጭቅጭቅ የዳከረበትን መንገድ ማጽዳት በምንም መስፈርት ከኅዳር 25 ቀን 2008 ዓ.ም. ጠቅላላ ጉባዔ ውሳኔ ጋር አይገናኝም፡፡ ይገናኛል ከተባለም የቦርዱ ውሳኔ የተሻሻለውን የአክሲዮን ማኅበሩን የማከራየት ዓላማ ወደ አትራፊነት መለወጡ መሠረታዊ ከሆነው የባለአክሲዮኖቹ ጥቅም አንጻር ጠቃሚ ሥራ መሆኑን የቦርዱ ኃላፊነት ብቻ ሳይሆን፣ እንደ አንድ መሥራችና ባለአክሲዮንም የውሳኔውን ትክክለኛነት እንደቦርድና በግል ጭምር የምንደግፈው ለትክክለኛነቱ የምንቆምለት ነው፡፡

  1. በዘገባው ላይ የተነሱ አሳሳችና አደናጋሪ ግን በግልጽ መታረም ያለባቸው እውነታዎች
  1. የነገው ሰው ትምህርት አክሲዮን ማኅበር የተቋቋመው ብር 250.00 (ሁለት መቶ ሃምሳ ብር) ዋጋ ያለውን አንድ አክሲዮን በመሸጥ ሆኖ በጊዜው መሥራች የተባሉት 104 ሰዎች አክሲዮን ሲገዙ የተከፈለው ገንዘብ ብር 2,709,250.00 (ሁለት ሚሊዮን ሰባት መቶ ዘጠኝ ሺሕ ሁለት መቶ ሃምሳ ብር) ብቻ ነበር፡፡ ይህ የአክሲዮን የካፒታል መጠን በብዙ ጥረት፣ ልፋትና እንዲያም ሲል ማግባባት እየታከለበት መሥራቾቹም የተወሰነ አክሲዮን ሲጨምሩ፣ አዳዲስ ግለሰቦችንም ወደአክሲዮን በመጋበዝ ላለፉት 18 ዓመታት አክሲዮን ማኅበሩ እሸጠዋለሁ ካለው 200,000 (ሁለት መቶ ሺሕ) አክሲዮንና ይህንም ሸጬ አገኘዋለሁ ካለው ብር 50,000,000 (ሃምሳ ሚሊዮን ብር) ውስጥ የሸጠው አክሲዮን 33,752 (ሰላሳ ሦስት ሺሕ ሰባት መቶ ሃምሳ ሁለት) 28 በመቶ የተከፈለ ካፒታሉም ብር 8,468,000 (ስምንት ሚሊዮን አራት መቶ ሰላሳ ስምንት ሺሕ) ብቻ ነው፡፡ ለአክሲዮን ማኅበሩ የትምህርት ሥራ ስኬት ማጣት በቂ ካፒታል አለመገኘትና ወሳኝ የሆነ ድምፅና ካፒታል ያለው ባለአክሲዮን አለመኖሩ ነው፡፡ ይህንም አጥኚ ኮሚቴው ያረጋገጠው እውነት ነው፡፡ እውነታው ይህ ሆኖ እያለ በባለአክሲዮኖች መካከል ጥርጣሬን በሚከት ሁኔታ አክሲዮን ማኅበሩ የተከፈለ ብር 34,970,500 ካፒታል እንዳለው ተደርጎ በጋዜጣው መዘገቡ ስህተት በመሆኑ የአክሲዮን ማኅበሩ የተከፈለ ካፒታል ብር 8,438,000 (ስምንት ሚሊዮን አራት መቶ ሰላሳ ስምንት ሺሕ ብር) ብቻ መሆኑን እናረጋግጣለን፡፡
  2. አክሲዮን ማኅበሩ ለትምህርት ሥራ አገልግሎት ይጠቀምባቸው የነበሩ ክፍሎችን ያከራየው ትርፋማ ባለመሆኑ ብቻ ሳይሆን በውስጥና በውጭ በተፈጠሩበትና አጥኚ ኮሚቴው ባረጋገጠው ተጨባጭና ገፊ ምክንያቶች መሠረት ‹‹ጥራት ጥልቀትና ምጥቀት ያለው››የትምህርት ሥራ አገልግሎት የማቅረብ ተልዕኮውን ማሳካት አለመቻሉ በመሠረታዊነት ሊወሰድ የሚገባው ነው፡፡ ለዚህ ማረጋገጫው ዛሬ ለአብነት ያህል የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ቁጥር ወርዶ ወርዶ ሰባት የሶሻል ሳይንስና አሥር የተፈጥሮ ሳይንስ፣ በጠቅላላ 17 ተማሪዎችን በሁለት ክፍል ይዞ መጓዙ ብቻ ሳይሆን፣ ባለአክሲዮኖቹ ራሳቸው ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት ለማምጣት ፈቃደኛ ያለመሆናቸው ነው፡፡ ምናልባት አንዳንዶቹ አመሠራረቱን ተስፋ አድርገው በጅምሩ ጊዜ ልጆቻቸውን ለማስገባት ቢሞክሩም እያወጡ ወደ ሌላ ትምህርት ቤት ለመውሰድ ጊዜ አልፈጀባቸውም፡፡ አንዳንዶቹም ልጆቻቸው ከሌላ ትምህርት ቤት በሥነ ምግባር ጥሰት ሲባረሩባቸው ትምህርት ቤቱን ማገገሚያ ከሚያደርጉት በቀር በትምህርት ሥራው ላይ እምነት አልነበራቸውም፡፡ ‹‹ባለቤቱ ያቀለለውን…›› እንደሚባለው ሆነና ዛሬ ለራሳቸው ልጆች የማይመርጡትን ትምህርት ቤት ‹‹መቀጠል›› ነበረበት ሲሉ ትርፍ የሌለው ግን በሌላው የሰው ልጅ የትምህርት ሕይወት ላይ መፍረድ ምን ትርፍ ለማግኘት እንደሆነ ግራ የሚያጋባ ነው፡፡
  3. ባለድርሻዎች እነማን ናቸው? በመሠረቱ ሕንጻዎቹንና ንብረቶቹ ማከራየት ወይም መሸጥ የሚል ሐሳብ ያቀረበው ጠቅላላ ጉባዔ ሳይሆን፣ የነበረው አጥኚ ኮሚቴ እንጂ ባለድርሻ የሚባል ቡድን የለም፡፡ በጋዜጣው ባለድርሻ የተባሉት ተቃውመዋል ሲባል ይህን የውሳኔ ሐሳብ ያቀረቡት አጥኚ ኮሚቴውን ለማመልከት ከሆነ ስህተት ነው፡፡ በአጥኚ ኮሚቴው ውስጥ ከነበሩ ሁለቱ ባለአክሲዮኖች ዛሬም በቦርዱ ውስጥ የሚያገለግሉ በመሆኑ ‹‹ባለድርሻዎች›› የሚል ቅጽል የሰጣቸው ሰዎች የአጥኚ ኮሚቴውን ውሳኔ እንዳቀረቡ ተደርጎ የቀረበው ዘገባም ትክክል አይደለም፡፡
  4. ሌላው ግልጽ መሆን ያለበት ጉዳይ የአክሲዮን ማኅበራት የሚመሩበት ሥርዓት በሕግ የተበጀ ነው፡፡ በተለያዩ የንግድ ሕጉም ሆነ በመመሥረቻና መተዳደሪያ ደንቡ ላይ የአክሲዮን ማኅበራት ጉባዔ ስብሰባ የሚጠሩበት ውሳኔ የሚወስኑበት ወይም ቅሬታ የሚደመጥበት አካሄድ የድምፅ ልኬትና መሠረት ያደረገ ነው፡፡ በአናሳ ድምፅ የአብዛኛው ባለአክሲዮን መብትና ጥቅም እንዳይጎዳ ለመከላከል ነው፡፡ ለምሳሌ ቦርዱ በወሰደው ዕርምጃ በጋዜጣው ባለድርሻ የተባሉትን ሰዎች ድምፅ አናውቅም እንጂ፣ ምናልባት ቢያንስ በቦርድ ውስጥ ካሉት ያነሰ ድምፅ ያላቸው ቢሆኑ እንኳ በአነስተኛ ድምፅ አብዛኛውን ድምፅ መጫን የሚቻልበት ሥርዓት በሌለበት ሁኔታ ጋዜጣው ዘገባውን ከማውጣቱ በፊት አክሲዮን ማኅበራችን ከ1-1088 አክሲዮን ያላቸው የ570 ሰዎች ስብስብ በመሆኑ ባለድርሻ ተብዬዎቹ በሕግ ዘንድ የሚኖራቸው ድምፅ የአብዛኛውን ወገን መብትና ጥቅም የማይጻረር መሆኑን ግምት ውስጥ ማስገባት እንደነበረበት እናምናለን፡፡
  5. ከዚህ ውጪ የኪራይ ሒደቱ በጨረታ ለምን አልተደረገም የተባለው ቢያንስ የተወሰኑ ባለአክሲዮኖችን ጠርተን ባወያየንበት ወቅት በቅንነት ለማስረዳት ተሞክሯል፡፡ በመሠረቱ የጨረታ ሥርዓት በግዴታነት የተቀመጠበት አሠራር በአክሲዮን ማኅበሩ ቦርድ ሥርዓት ውስጥ የለም፣ ጨረታ ግልፅነት ይኖረዋል ተብሎ የሚገመት ቢሆንም፣ ለአብዛኛው የአሠራር ጥፋትና ጉድለት ጨረታ ሽፋን ነው፡፡ በሌላ በኩል ምናልባትም ያሉትን አነስተኛ ተማሪዎች በትምህርት ላይ ባሉበት ወቅት ጨረታ ወጥቶ ባይሳካ በጊዜው ሊፈጠር የሚችለውን የሥነ ልቦና ጫናና በቦርዱም ላይ ሊወርድ የነበረው ውግዘት ሲታሰብ የጨረታ ጥያቄ በነበረው ሁኔታ የማያስኬድና ተጨባጩን ውጤት መምረጥ የቦርዱ እምነትና ኃላፊነት መሆኑን መረዳት ይቻላል፡፡

ስለዚህ ጨረታ መከላከያ የማይሆንበት አጋጣሚን ማወቅ ቀላል ነው፡፡ በዚህ ሒደት ቦርዱ የተከተለው ግልጽ የሆነ ድርድርን ነው፡፡ ድብቅ ሳይሆን ለቦርዱ ግልጽ በሆነ አካሄድና አሠራር የአካባቢውን ዋጋ ግምት በመውሰድ በአጠቃላይ በሁለት ደረጃ በመደራደር ከተጨማሪ እሴት ታክስ በፊትና በኋላ በድምሩ በአጠቃላይ የብር 45,000,000 (ብር አርባ አምስት ሚሊዮን) ገቢን ግብ አድርጎ በመደራደር ተዋውሏል፡፡

ይህም ለባለአክሲዮኖች የተወሰነ ትርፍ ለመንግሥት ደግሞ በታክስ መልክ የተሻለ ገቢ የሚያስገኝ ፕሮጀክት እንጂ፣ በወር ብር 300,000.00 (ሦስት መቶ ሺሕ ብር) እንደተባለው ተቃሎ የሚታይ አይደለም፡፡ ይህ የኪራይ ፕሮጀክት ደግሞ የአክሲዮን ማኅበሩን መርከብ ከወጀብ የሚታደግ፣ ቦርዱም ሆነ ባለአክሲዮን ስለቀጣዩ የቢዝነስ ዓላማና ስለካፒታል ዕድገት ረጋ ብሎ የሚያስብበትና ወደተሻለ ደረጃና ተግባር የሚሸጋገርበት የተሻለ ወቅትንና መንገድ እንደፈጠረ ቦርዱ ያምናል፡፡ ከዚህ ውጭ ‹‹የሕዝብን ንብረት የሚያባክን›› የሚለው ሥጋት ውኃ የማይቋጥር ምንም ዓይነት ተጨባጭ መሠረት የሌለው ነው፡፡ ሥጋት ያለባቸው ወገኖች ቢኖሩና ማንኛውም በቦርዱና በማኔጅመንቱ በሚወሰደው ዕርምጃ ሥጋታቸውን ለማስወገድ በቅንነት ለሚተባበሩና ለአክሲዮን ማኅበሩ ዕድገት ለሚተጉ በጎ አባሎቻችን የአክሲዮን ማኅበሩ ጽሕፈት ቤት በማንኛውም ጊዜ ተባብሮ ለመሥራት በሩ ክፍት መሆኑን እናረጋግጣለን፡፡

ከአዘጋጁ፡- ጽሑፉ የጸሐፊውን አመለካከት ብቻ የሚያንፀባርቅ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

 

 

Standard (Image)

አወዛጋቢ የሰብዓዊ መብት መግለጫዎችና ለተጠያቂነት ያልተዘጋጀ አካሄድ

$
0
0

በመንግሥቱ መስፍን

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአምስተኛ ዓመት የሥራ ዘመን ‹‹የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን›› የምርመራ ሪፖርት አዳምጧል፡፡ ጉዳዩ ደግሞ በአገሪቱ በተለይ በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች በርከት ያሉ ወረዳዎች ላይ በተከሰተው ሰላማዊ ሠልፍ ሁከትና የመንግሥት ታጣቂዎች ግድያ ላይ ያነጣጥራል፡፡ ኮሚሽኑ በሪፖርቱ በኦሮሚያም ሆነ በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን ላይ በመቶዎች የሚቆጠሩ ዜጎች መሞታቸውንና ከፍተኛ ግምት የሚሰጠው ሀብት መውደሙን አረጋግጧል፡፡

‹‹ይህ ድርጊት የተከሰተው ደግሞ ሕገ መንግሥቱ በፈጠረው ቀውስ ሳይሆን የሕገ መንግሥት ውሳኔዎችን በጊዜው ምላሽ ባለመስጠትና በመልካም አስዳደር ዕጦት ነው፤›› የሚለው ሪፖርት ለዚህም በችግር ውስጥ ዋነኛ አጥፊና ተዋናይ የነበሩ የመንግሥት ባለሥልጣናት፣ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችና አክቲቭስቶች እንዲጠየቁም አሳስቧል፡፡ ይኼ መግለጫ ‹‹መንግሥት ያልተመጣጠነ ዕርምጃ ወስዷል፤›› የሚለውን ትችት ፉርሽ ያደረገ ሲሆን፣ ስለታሠሩና ደብዛቸው ጠፍቷል ስለሚባሉ ዜጎችም ያለው ነገር የለም፡፡ ከሁሉ በላይ በዚያም ተባለ በዚህ ንብረታቸው ወድሞ ለስደትና ለልመና የተጋለጡ ቤተሰቦችን ጉዳይ ትኩረት የሰጠው አይመስልም፡፡

የማይካደው እውነት ግን ሕዝቡ ያነሳውን ሕገ መንግሥታዊ ጥያቄ ወደራሳቸው የፖለቲካ ዓላማ በመቀየር ለከፍተኛ ጥፋት አውለውታል ያላቸውን በውጭ የሚገኙ የትጥቅ ተቃዋሚዎችን ነው፡፡ አንዳንድ ታዛቢዎች ታዲያ መንግሥትስ እንደተቋም ራሱን ችሎ የሚጠየቅበት ጥፋት ምንድነው? ሲሉ በግርምት ጠይቀዋል፡፡

ከዚህኛው መግለጫ ተቃራኒ ሊባል የሚችል የምርመራ ውጤት በተለይ በሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ (ሰመጉ) የቀረበው መጋቢት 5 ቀን 2008 ዓ.ም. ሲሆን፣ ‹‹140ኛ ልዩ መግለጫ›› የሚል ገዥ ርዕስም ተሰጥቶታል፡፡ መግለጫው የወጣበት ጊዜ ገና ግለቱ ባልበረደለት አፍላ ወቅት ላይ በመሆኑ ‹‹በመንግሥት፣ የፀጥታና ታጣቂ ኃይሎች በዜጎች ላይ የሚፈጸም አስቀያሚ ግድያ ሕገወጥ እስር፣ ድብደባ፣ ማስፈራራትና ማዋከብ በአስቸኳይ ይቁም!›› የሚል ማስጠንቀቂያንም ያዘለ ነበር፡፡

ይኼ የሟቾችና የከፍተኛ ቁስለኞችን ዝርዝር፣ ፎቶ ግራፍ ጭምር የያዘ የሰመጉ ሪፖርት እጅግ ዝርዝር የምርመራ አካሄድ የተከተለና ግልጽነትን የተከተለ መሆኑን ብዙዎች ይስማሙበታል፡፡ አምነስቲ ኢንተርናሽናል የተባለው ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋችም ሪፖርቱን በገለልተኝነቱ የተቀበለው ሲሆን፣ ‹‹የመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች ለተቃውሞ በወጡ ዜጎች ላይ በወሰዷቸው ከመጠን ያለፉ የኃይል ዕርምጃዎች የበርካታ ዜጎች ሕይወት ጠፍቷል፡፡ በርካታ ሰዎች በጥይት ተመትተው የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡ በርካቶች ታስረዋል፡፡ ቁጥራቸው በውል የማይታወቅ ሰዎች የደረሱበት አይታወቅም፡፡ ኪሳራ ያስከተለ ከባድ የንብረት ውድመት ደርሷል፤›› ይላል፡፡ ይኼም ከሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 30(1) ጋር እንደሚጋጭም ጠቁሟል፡፡

የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ሰሞኑን ካቀረበው ሪፖርት የማይገኝ፣ ነገር ግን ሰመጉ ያቀረበው ሪፖርት የያዘው አወዛጋቢ ሀቅም አለ፡፡ ይኸውም ‹‹መንግሥት በችግሩ ውስጥ ተጠያቂ ነው፤›› ያለበት መከራከሪያ ነው፡፡ ሰመጉ በሪፖርቱ በገጽ 4 ላይ ‹‹መንግሥት የተቀናጀ የማስተር ፕላኑን በማቅረብ ሒደት ዜጎችን በተለይም በአዲስ አበባ ዙሪያ የሚገኙ የኦሮሚያ ገጠርና ከተማ ነዋሪዎችን ባለማሳተፉ፣ ረቂቅ ሰነዱንም እስከዛሬ ድረስ ለሕዝብ ይፋ ባለማድረጉ የበርካታ ዜጎችን ሕይወት ለቀጠፈውና የአካል የንብረት ጉዳት ለተከሰተው ቀውስ ምክንያት ሆኗል፡፡ ረቂቅ ማስተር ፕላኑ ለባለሙያዎችና ለሌሎችም ባለድርሻ አካላት ቀርቦ ግልጽ ውይይት፣ ክርክርና ትችት ሊደረግበት ሲገባ ለዓመታት በሚስጥር መያዙና ይዘቱም ለዜጎች አለመገለጹ ለጥርጣሬ፣ ለውዥንብርና ደም ላፋሰስ ግጭት መንስዔ ሆኗል፤›› ነው የሚለው፡፡

እንደማንኛውም ተቆርቋሪ ዜጋ ‹‹ከሰላማዊ ሠልፍ ወደ ሁከት፣ ብጥብጥና አመፅ የተቀየረን የሕዝብ ቁጣ መንግሥት በምን ሊያረጋጋው ይችል ነበር?›› የሚል ጥያቄ በጭንቅላታችን ይመላለሳል፡፡ በተለይ ሁከቱ ተባብሶ በነበረበት ከኅዳር አጋማሽ እስከ ጥር 2008 ዓ.ም. በተለይ በኦሮሚያ ክልል ብቻ በ18 ዞኖችና በ300 ወረዳዎች የተነሳ የሕዝብ ማዕበል ሴት ወንድ፣ ልጅ አዋቂ፣ እግረኛና ፈረሰኛ አሳትፎ እያለ ማብረጃው ምን ሊሆን ይችል ነበር ማለት ተገቢ ነው፡፡

ይኼ ማለት ግን በጠራራ ፀሐይ ሕፃናትን ጨምሮ (ከ13 ዓመት በታች ሁሉ) አልተገደሉም ማለት አይደለም፡፡ በጥይት ግንባራቸውን መምታት በምንም መንገድ ሕጋዊ ሊሆን አይችልም፡፡ በተለይ ሰመጉ ይፋ ባደረገው መረጃ የመከላከያ ሠራዊት አባላት፣ የፌዴራል ፖሊስና የኦሮሚያ ልዩ ኃይል በግድያው መሳተፋቸው ብቻ ሳይሆን አንዳንዶቹ ሟቾች ወደ መስጊድ ሲሄዱና ትምህርት ቤታቸው ላይ መገደላቸው ‹‹እንዴትና ለምን?›› ያስብላል፡፡

ሌላው በተለይ የሰመጉ ሪፖርትና የተጎጂዎች የስም ዝርዝር አስደንጋጭ አንድምታ በኦሮሚያ ቤት ንብረታቸው የተቃጠለባቸው አብዛኛዎቹ አርሶ አደሮች የሆኑበት 800 አባዎራዎች ጉዳይ ነው፡፡ የእነዚህ ዜጎች ስም ዝርዝር እንደሚያሳየው ጉዳት የደረሰባቸው በአብዛኛው የኦሮሞ ብሔረሰብ አባል ያልሆኑና ‹‹መጤ›› ኢትዮጵያዊያን መሆናቸው ነው፡፡

ከላይ የተጠቀሰውን ውድመት ተከትሎ ኩም ቁሊት ቀበሌ በተባለ ሥፍራ ‹‹መጤዎቹ›› 96 የኦሮሞዎችን ንብረት ማቃጠላቸውም ተጠቅሷል፡፡ ቁጥራቸው ትንሽ የማይባል የኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት /ኦሕዴድ/ አባላትና የሥራ መሪዎች ቤት ንብረትም ወድሟል፡፡ ይኼ ያልተሸፈነ እውነት ታዲያ ኢሕአዴግ ከሚለው ‹‹ሕብረ ብሔራዊ አንድነት ተፈጥሯል›› ጋር እንዴት ይታረቅ ይሆን? ያስብላል፡፡

በሰመጉ ምርመራ ወቅት አስተያየታቸውን የሰጡ የየአካባቢው ነዋሪዎች በዚህ ጉዳይ ላይ ተጠይቀው በሰጡት አስተያየት ‹‹ይኼ ሕዝብን በሕዝብ ላይ የማነሳሳት ድርጊት የሚፈጸመው በዋነኛነት በጥቂት የራሳቸው ያልሆነውን መሬትና ሀብት ለመንጠቅና ያለአግባብ በሚፈለጉ የአካባቢ ሀብታሞች አነሳሽነትና መሪነት እንዲሁም በመሰል ጥቅም ፈላጊ ባለሥልጣኖች አይዞህ ባይነት ነው፤›› ብለዋል ሲል ሪፖርቱ ገጽ 30 ላይ አስፍሮታል፡፡

የዘንድሮው የሰብዓዊ ጥሰት በኦሮሚያ ብቻ አልነበረም፡፡ ሰሞኑን የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረበው ሪፖርት በአማራ ክልል በቅማንት የማንነት ጥያቄ ስም በሰሜን ጎንደር በተለይ መተማ፣ ጭልጋና አርማጮህ የ96 ዜጎች ሕይወት እንዳለፈ ገልጿል፡፡ ከ100 በላይ ቁስለኛና በመቶዎች የሚቆጠሩ መኖሪያ ቤቶችና ሱቆች መቃጠል መገለጹ ሲታሰብ የምን ያህል ዜጎት ሕይወት እንደተመሰቃቀለ መገንዘብ አያዳግትም፡፡ ኮሚሽኑ ክልሉ ሕዝቡን ይቅርታ እንዲጠይቅ የውሳኔ ሐሳብ ሰጥቶ ፓርላማው አፅድቆ ወስኗል፡፡

ሲያልፍ ቀላል ቢመስልም በግጭቱ ለምን የሱዳን ጎንደር የምዕራብ ዋና መንገድ ለአንድ ሳምንት ተዘግቶ ነበር፡፡ የጎንደር ማረሚያ ቤት ቃጠሎና መሰበር እንዲሁም እስካሁንም ያንዣበበ ፍርሃትና መጠራጠር የዚያው መዘዝ አካል ነው፡፡ የኮሚሽኑ ሪፖርት የሚያሳየው ግን የዚያ ግጭት መዘዝ የቅማንት ሕዝብን ሕገ መንግሥታዊ ጥያቄ በፍጥነትና በሕጉ መሠረት ያለመመለስና የውጭ ጽንፈኛ ኃይሎች ያነሱት ሰፊ ቅስቀሳ ነው፡፡

የሰብዓዊ መብት ኮሚሽንም ሆነ ሰመጉ የማጣሪያ ግምገማና ሪፖርት አያቅርቡበት እንጂ በምዕራብ ትግራይ ጠገዴ አካባቢ የሚኖሩ የአማራና የትግራይ ብሔር ዜጎች ‹‹የማንነት›› በሚመስል ጥያቄ ከፍተኛ ውዝግብ ውስጥ ገብተዋል፡፡ ተፈናቅለናል ተሰደናል ከሚባሉት በላይ የደረሱበት ያልተውቁ እየተባለ መረጃ የሚወጣባቸው ዜጎች ጉዳይ የአገሪቱን ፖለቲካ ክፉኛ የሚያጨልሙ ናቸው፡፡

አሁን ሪፖርቱ በማንም ይውጣ በማን ዜጎች በየአካባቢው ተገድለዋል፣ ቆስለዋልና ታስረዋል የሚለው ገለጻ የሚያሻማ አልሆነም፡፡ ስደትና ውጣውረድም ከዚህ ተነጥሎ ሊታይ አይችልም፡፡ ለዚህ ፀረ ሕገ መንግሥታዊ ክስተት እውን መሆን መብታቸውን ተላልፈውና ባልተገባ መንገድ ሁከት ያስነሱ ዜጎች ቢጠየቁም፣ በተለይ አላግባብ ሕይወታቸው ያለፉ ንፁኃን ደምም ፍርድ ሊያገኝ ይገባል፡፡ የሁከቱ መቀስቀስ መንስዔ የሚባሉትም (መንግሥትም ይሁን ተቃዋሚዎች)ም ይቅርታ ጠይቀው አልያም ተጠያቂ ሆነው ከሒደቱ ትምህርት ካልተወሰደ ሪፖርቱም ሆነ ማጣራቱ ፍሬ አልባ ናቸው፡፡

ኢሕአዴግ ወደ ሥልጣን ከመጣ በኋላ አገሪቱ በአንፃራዊ ሰላምና ዴሞክራሲ ሒደት ገብታለች፡፡ በዚህም ውስጥ እየመጣ ያለ ፈጣን ልማትና ለውጥ አለ የሚሉ ወገኖችን ያህል፤ የፌዴራል ሥርዓቱ ከአንድነት ይልቅ መነጣጠልን፣ ግጭትና ሁከትን አምጥቷል የሚሉም አሉ፡፡ መንግሥትም በሕገ መንግሥቱ መሠረት የተደራጁ ወይም ሰላማዊ ሠልፍ ያደረጉ ዜጎችን በጥይት ከማስገደል አልታቀበም የሚሉ ድምፆች ይሰማሉ፡፡

ከ1988 ዓ.ም ጀምሮ በአርባ ምንጭ፣ በሐዋሳና በጎንደር ከተሞች በሃይማኖት ግጭት ስም፤ ከ1984 ዓ.ም. ጀምሮ ለተደጋጋሚ ጊዜ በተለይ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ የኦሮሚያና የአሞቦ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ጥያቄ በግድያ ተመልሷል፡፡ ከሁሉ በላይ ከምርጫ 97 በኋላ ይፋ በሆነ የምርጫ ውጤት በተለያዩ የአገሪቱ ከተሞች በተለይ በአዲስ አበባ በመንግሥት ተጠቂዎች የተገደሉ ከ196 በላይ ዜጎች ሕልፈት ጥቁር ጠባሳ ጥሎ ያለፈ ነው፡፡

ዘንድሮ በተለይ በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች የተከሰተው የሕዝብ ጥያቄና ሁከት ሲታይም በ25 ዓመታት የዚህ መንግሥት ታሪክ ውስጥ ከፍተኛ ጉዳት የተከሰተበት ነው፡፡ ከ280 በላይ ዜጎች ግድያና ያንኑ ያህል ቁስለኛ ያውም በግልጽ ‹‹ታጥቀዋል›› ሊባሉ በማይችሉ ዜጎች ላይ መድረሱ ‹‹የተመጣጠነ ዕርምጃ›› ወሰኑ እምን ድረስ ነው ያስብላል? በዚህ ድርጊት ውስጥስ የገደለ፣ ትዕዛዝ የሰጠ ወይም የሰብዓዊ መብት ጥሰቱን ያቀነባበረ ካልተጠየቀ በምን ሊጠየቅ ይሆን?

የሰብዓዊ መብት ኮሚሽንም ሆነ ሰመጉ ሁለቱም የተስማሙበት ‹‹የሰብዓዊ መብት ጥሰት መፈጸሙን›› ነው፡፡ ይህ ደግሞ ለመንግሥት እንዴት? የት? መቼ? ለምን? እና በምን? የሰብዓዊ መብት ጥሰት ሊፈጸም ቻለ የሚል ጥያቄ እንዲነሳ ዕድል የሚሰጠው ቁልፍ ጉዳይ ነው፡፡ ይህን ማድረግ ካልተቻለ ግን ዓለም አቀፍ የሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶችን ‹‹ያካተተ›› ሕገ መንግሥትን አንቀጾች በመጥቀስ ብቻ ‹‹ዴሞክራቶች›› ነን ለማለት አይቻልም፡፡ ሕዝብ አልተከፋም ይደግፈናል እያሉ መታበይም አጉል ልበድፍንነት ነው፡፡

ሌላው ከሪፖርቶቹ ውዝግብ በመውጣት ትምህርት ሊወሰድበት የሚገባው ተግባር በቀጣይስ ለዘለቄታው ችግሮቹ እንዴት ተፈቱ፤ እየተፈቱስ ነው ማለት ሲቻል ነው፡፡ አሁንም ድረስ በኦሮሚያ አንዳንድ አካባቢዎች ‹‹ወታደራዊ›› አስተዳደር የሚመስል ውጥረት አለ፡፡ በከፋ ሙስናና አገር አጥፊ ምዝበራ የተጠረጠሩ የመንግሥት አካላት ወይ በሥልጣን ላይ ናቸው፣ አልያም ከኃላፊነት ቢነሱም ሲጠየቁ አልታዩም፡፡ (ሰሞኑን ቱባ የሚባሉ አንዳንድ ተጠርጣሪዎች እየተያዙ ቢሆንም)

በአዲስ አበባ ዙሪያም ሆነ በከተማ ዳርቻዎች በሕገወጥ መንገድ የተያዙ መሬቶች ጉዳይ አሁንም በእንጥልጥል ላይ ነው፡፡ ግማሹ በግብረ ኃይል ሲፈርስ፤ ሌላው ከመንግሥት አካላት መረጃ አገኘሁ ‹‹አንነካም››፣ እያለ ሲሻሻጥ ይውላል፡፡ የአዲስ አበባና ፊኒፊኔ ዙሪያ የጋራ ማስተር ፕላን ጉዳይም በምን ሁኔታ እንደተቋጨ ግልጽ መረጃ ሲወጣ አልታየም፡፡

በአማራና በቅማንት ማኅበረሰብ በኩልም ተንጠልጥሎ የቀረ አጀንዳ አለ፡፡ ሌላው ቀርቶ በክልሉ ከፍተኛ አመራሮችና የምክር ቤት አካላት ሳይቀር ውሳኔ ትክክል እንዳልሆነ በሌሎች ግፊት እየተቀነቀነ እንዳለ ‹‹የማንነት ጥያቄ›› ይነገራል፡፡ እንዲሁም በኦሮሚያ፣ በደቡብም ሆነ በትግራይ ክልሎች እምብዛም ፈጣን መልስ የማያገኙ የማንነት ጥያቄዎች የአማራና የቅማንት በአጭር ጊዜ እንዴት ተጣድፎ ተወሰነ? ለሚለው ጥያቄም በቂ መልስ የሚሰጥ ወገን የለም፡፡

በውጭ የሚኖረው ‹‹ጽንፈኛ›› የተባለው ተቃዋሚ ኃይል ሁሉ ዓላማው ሥልጣን ማግኘት መሆኑ ጥርጥር የለውም፡፡ ስለሆነም የተለያዩ ማደናገሪያዎችንም ሆነ የሕዝብን ሥጋቶችን ቢያቀጣጥል እንደመደበኛው ሥራው ነው ሊቆጠር የሚችለው፡፡ ሕዝቡም ይህንን ይዞ ቢነጉድ የሚጠበቅ ነው፡፡

ከዚያ ይልቅ መፍትሔው ያለው በመንግሥት እጅ ነው የሚል ዕምነት አለኝ፡፡ በአንድ በኩል የሕዝብ አመኔታን ባተረፈ መልኩ አሳታፊና ግልጽ በሆነ መንገድ መሥራት አለበት፡፡ መሬት ሲሸጥ፣ ወሰን ሲለይ፣ ማንነት ዕውቅና ሲያገኝ ወዘተ. ሕዝብ ካላወቀ ማን ሊያውቅ ነው? ሌላው ተጠያቂነት የሚባለውን የገዘፈ ጉዳይ ከመሸርሸር ሊወጣ ግድ ይለዋል፡፡ ሌባን፣ ሙሰኛን፣ ጠባብና ዘረኛን፣ ትምክህትኛና ጽንፈኛና፣ አክራሪና ሌላውንም ወንጀለኛ መንግሥት ደፍሮ ለሕግና ለሕዝብ ካልሰጠ ማን ሊቀበለው ይችላል?

በመጨረሻ መንግሥት ሆደ ሰፊ፣ ይቅር ባይና ይቅርታ ጠያቂ መሆን አለበት፡፡ አሁን በተነሳንበት ርዕስ ጉዳይ አንፃር በመንግሥት ትዕዛዝ ሥር ያሉ ተጠያቂዎች ንፁሐንን ገድለዋል፡፡ በማወቅም፤  በድፍረትም ምክንያታቸው ምንም ይሁን ምን እነዚህ በወገኖቻቸው ላይ የተኮሱ ተጠያቂዎች ላደረሱት በደል መንግሥት ሕዝብን ይቅርታ መጠየቅ፣ የተበደለን መካስና አገር ማረጋጋት አለበት፡፡ በተጨባጭ ወንጀል ያልተጠረጠረ እስረኛም ካለ ይቅር ሊባል ግድ ነው፡፡

ከሁሉ በላይ ሕዝቡን ያስቆጣውን ጉዳይ በግልጽ ለይቶ ፊት ለፊት መታገልና ውስጥን መፈተሽ ይገባል፡፡ ችግሩ ሌላ ሆነ ወደ ውጭ ብቻ ጣትን መቀሰር (ለምሳሌ ተቃዋሚ ፓርቲዎችን ማሳደድ) እንደመፍትሔ ከተወሰደ ያለጥርጥር ነገም መፍትሔ አይመጣም፡፡ በራሳችን ዜጎች ሕጋዊ ዕውቅና ባላቸው ተቋማት እየወጡ ያሉ አወዛጋቢ የሰብዓዊ መብት መግለጫዎችም ከፕሮፓጋንዳ ያለፈ ትርጉም አይኖራቸውም፡፡ ስለዚህ ሁሉም ራሱን ለተጠያቂነት ያዘጋጅ፡፡

ከአዘጋጁ፡- ጽሑፉ የጸሐፊውን አመለካካት ብቻ የሚያንፀባርቅ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

 

Standard (Image)

ግልጽነት የጎደለው የዳኞች ምልመላ

$
0
0

በኃይለገብርኤል ሠዐረ

የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ሕገ መንግሥቱና ሌሎች የአገሪቱን ሕጎች መሠረት አድርገው በሰዎች መካከል ባሉ ግንኙነቶች መካከል የሚፈጠሩ አለመግባባቶችን ይፈታሉ፣ መብትን ያስከብራሉ፣ በአጥፊ ላይ ቅጣት ይጥላሉ፡፡ ፍትሕን ፈልገው ወደ ፍርድ ቤት ለሚመጡ ባለጉዳዮች ፍላጎት መሳካት የፍርድ ቤቶቹ ዳኞች፣ ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞችና የበላይ ኃላፊዎች የየራሳቸው ድርሻ አላቸው፡፡

በዚህ ጽሑፍ ሰሞኑን ለፌዴራል ፍርድ ቤቶች (ለመጀመሪያና ከፍተኛ) የተከናወነው የዳኞች የምልመላና የሹመት ክንውን እንዲሁም በቀጣዩ ሳምንት ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ለሹመት በሚቀርቡ ዳኞች አመላመል ሒደት ፍትሐዊነት ምን ይመስላል የሚለውን በመጠኑ ለመዳሰስ እሞክራለሁ፡፡

የፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ጉባዔ በአዋጅ ቁጥር 684/2002 በአዲስ መልክ ሲቋቋም ከተሰጡት ኃላፊነቶች አንዱ ዕጩ ዳኞችን መመልመልና መለየት በመሆኑ፣ ጉባዔው ባለፉት ስድስት ዓመታት ለፌዴራል ፍርድ ቤቶች ዳኞችን መልምሎ በጠቅላይ ሚኒስትሩ አቅራቢነት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲሾሙ አድርጓል፡፡

ለበርካታ ዓመታት በፌዴራል ፍርድ ቤቶች ያለውን የዳኞች የብሔር ተዋጽኦ ለማመጣጠን በሚልና መሰል ምክንያቶች ለበርካታ ዓመታት ዳኞች ይመለመሉ የነበረው ከክልሎች የነበረ ሲሆን፣ ይህም በዳኞች አስተዳደር ጉባዔ አባላትና የጉባዔውን አባላት በሚያውቁ ግለሰቦች ጥቆማ የሚከናወን ግልጽነት የጎደለው ስለነበረ ውጤታማ ሆኖ ባለመገኘቱ ዕጩ ዳኞች ማስታወቂያ ወጥቶ ፈተና ተሰጥቶ ለሕዝብ አስተያየት ቀርበው የመሾም ሒደት ከአዋጅ ቁጥር 684/2002 መውጣት በኋላ ተጀምሯል፡፡

ከፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጥገኝነት እስካሁን ያልወጣው የዳኞች አስተዳደር ጉባዔ ጽሕፈት ቤትም ኃላፊ ለመመደብ በርካታ ወራት ፈጅቶ ኃላፊውም በመልቀቃቸው አሁን የሚገኙት ኃላፊ ተመድበው መደበኛው ሥራ ከሞላ ጎደል እየተሠራ ነው፡፡

በፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ጉባዔ ጽሕፈት ቤትና በጽሕፈት ቤቱ ኃላፊ ላይ ከዳኞች በርካታ ቅሬታዎች የሚቀርቡ ሲሆን፣ ባለፉት አምስት ዓመታት የጉባዔው አባላት ከዳኞች ጋር የተገናኙት አንድ ጊዜ ብቻ ነው፡፡ በዳኞች ጥቅማ ጥቅምና ደመወዝ፣ በሚወሰዱ የዲሲፕሊን ዕርምጃዎች ላይ ግልጽ የሆነ አሠራር እየታየ አይደለም፡፡

የዚህ ጽሑፍ ትኩረት ሰሞኑን ተመልምለው በተሾሙ ዳኞች የፌዴራል የመጀመሪያና ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኞች የምልመላና የመረጣ ሒደት እንዲሁም ሰሞኑን በተዘጋጁ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዕጩ ዳኞች የምልመላ ሒደት ላይ ግልጽ ያልሆኑ ነገሮችን ለመዳሰስ ነው፡፡

ለፌዴራል የመጀመሪያና ከፍተኛ ፍርድ ቤት ስለተሾሙ ዳኞች ምልመላ

የፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ጉባዔ ጽሕፈት ቤት በመጋቢት ወር 2007 ዓ.ም. ለፌዴራል የመጀመሪያና ከፍተኛ ፍርድ ቤቶች ዕጩ ዳኞችን ለመመልመልና ለማሾም ማስታወቂያ በማውጣቱ፣ ከመላው የአገሪቱ ክልሎች መመዘኛውን እናሟላለን የሚሉ በሺሕ የሚቆጠሩ ተመዝጋቢዎች ተመዝግበው የመጀመሪያውን መመዘኛ አሟልተዋል ተብለው የተመረጡ ተፈታኞች በሐምሌ ወር 2007 ዓ.ም. የጽሑፍ ፈተና ተሰጣቸው፡፡

የጽሑፍ ፈተናውን በተመለከተ ከ700 በላይ ተፈታኞች በአንድ አዳራሽ ውስጥ ሆነው በቂ ቅድመ ዝግጅት ሳይደረግ የፈተናው ዓይነት የሕግ መጻሕፍትና ሌሎች ሰነዶች ተይዞ የሚገባበት (ግልጽ ይሁን ዝግ) መሆኑ ሳይታወቅ የተወሰነው ተፈታች መጻሕፍትና ሰነዶች ይዞ ሌላው ሳይኖረው አብዛኛው ተፈታኝ መልስ እየተኮራረጀ፣ በስልክ እዚያው አዳራሽ ውስጥ መልስ እየተነጋገረ እየወጣ እየገባ ፈተና የሚመስል ‹‹ፈተና›› ተሰጠ፡፡

ወትሮም ዘገምተኛ የሆነው የጉባዔው ጽሕፈት ቤት የዚህን የጽሑፍ ፈተና ውጤት ለማሳወቅ አራት ወራት ፈጅቶበት በኅዳር ወር 2008 ዓ.ም. የጽሑፍ ፈተና ውጤትን አሳውቆ በዚሁ ወር ቃለ መጠይቅ በጉባዔው አባላት ተደርጎ በታኅሳስ ወር 2008 ዓ.ም. 39 ዕጩ ዳኞች ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት፣ 121 ዕጩ ዳኞች ለፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተወዳዳሪ ባለሙያዎች መሆናቸው ተገልጾ ሕዝቡ አስተያየቱን ለአሥር ቀናት በአካል፣ በስልክ፣ በድረ ገጽ እንዲገልጽ ጥሪ አደረገ፡፡

ከሰባት ወራት በኋላ ባለፈው ሳምንት የጉባዔው ጽሕፈት ቤት ስማቸው ለሕዝብ አስተያየት ከቀረበው ዕጩዎች መካከል ለተወሰኑት እየደወለ ለመሾም ዝግጁ መሆናቸውን ከጠየቀ በኋላ፣ ባለፈው ሳምንት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፊት ቀርበው ቃለ መሐላ ፈጽመው ተሹመዋል፡፡

ግልጽነት የሚባለውን መርህ ከቃሉ በቀር የማያውቀው የፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ጉባዔ ከጽሑፍ ፈተና ውጪ፣ በቃለ መጠይቅ ተፈታኞች ያገኙት ውጤት፣ ከሕዝብ በተሰበሰበ አስተያየት ቅሬታ የቀረበባቸውም ካሉ ቅሬታውን በትክክል አጣርቶ ምን እንደሆነ ሳያመለክት ሹመቱ ተከናውኗል፡፡

ከተሾሙት ዳኞች መካከል ብቃት የነበራቸው ያሉ ሲሆን፣ ሌሎች ደግሞ በጽሑፍ ፈተና ዝቅተኛ ውጤት አምጥተው ከአንዳንድ ኃላፊዎች ጋር በነበራቸው ቅርበት የተሾሙ መሆኑ ቅሬታ እየተሰማበት ነው፡፡ በተለይ በፍርድ ቤቶቹ በዳኝነትና በረዳት ዳኝነት ይህ ቢስተካከል እያሉ አስተያየት ይሰጡ ከነበሩት መካከል ሳይሾሙ የቀሩ ይገኙበታል፡፡

የዳኝነት መመዘኛ መስፈርት የዳኛው ችሎቱን የመምራት ብቃት፣ ለጉዳዩ አግባብነት ባለው ሕግ ዙሪያ ያለው ዕውቀት፣ የሙግቱን ሒደት በሥነ ሥርዓት ሕጎች የመምራት፣ ለሚይዘው መዝገብ አስፈላጊውን ዝግጅት አድርጎ በችሎት መገኘት፣ በሚሰጠው ፍርድ ማስረጃውን አግባብነት ካለው ሕግ ጋር ማገናዘብ መመዘንና መተንተን፣ ጭብጥ የመለየት ብቃት፣ ከአድልዎ በፀዳ መልኩ ክርክርን የመምራትና   ፍርድና ውሳኔ መስጠት ሊሆን ይገባዋል እንጂ ሌላ መመዘኛ ከሆነ መንግሥትም ሕዝብም ይጎዳሉ፡፡

ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ስለተመለመሉ ዕጩ ዳኞች

ጉባዔው የራሱ ጽሕፈት ቤት ኖሮት ሥራውን ከጀመረበት ከ2003 ዓ.ም. ጀምሮ ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞችን ያሾመው በ2005 እና በ2007 ዓ.ም. መጨረሻ ላይ ነው፡፡ በእነዚህ የመመልመያ ወቅቶች በተሰጠው የጽሑፍና የቃለ መጠይቅ  መመዘኛ ውጤታቸው ከፍ ካለ ዳኞች መካከል ያልተሾሙ በፌዴራል የመጀመሪያና ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሚገኙ ዳኞች ምስክር ናቸው፡፡

ለወትሮው ዳኞችን ለማሾም በርካታ ወራት የሚወስድበት የፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ጉባዔ በግንቦት ወር 2008 ዓ.ም. የመጨረሻ ቀናት ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዕጩ ዳኞችን መልምሎ ለማሾም እንደሚፈልግ ባወጣው ማስታወቂያ፣ ለተመዘገቡት ባለፈው ሳምንት ሐሙስና ዓርብ ከጉባዔው ጽሕፈት ቤት ተደውሎላቸው ቅዳሜ ሰኔ 18 ቀን 2008 ዓ.ም. ለፈተና እንዲቀርቡ ተነግሮ የጽሑፍ ፈተና ጠዋት ቃለ መጠይቅ ከቀትር በኋላ ተደርጎላቸዋል፡፡

በዚህ የጽሑፍ ፈተና ላይ እጅግ የሚገርመው ነገር ለጽሑፍ ፈተና ተፈታኞች ከተቀመጡ በኋላ በ2007 ዓ.ም. ተፈትነው ለነበሩት ‹‹እናንተ ባለፈው ዙር የወሰዳችሁት የጽሑፍና የቃል ፈተና በቂ ስለሆነ ተመለሱ እኛ እንደውልላችኋለን፤›› ተብለው ፈተናውን ሳይወስዱ ቀርተዋል፡፡ እነዚህና ሌሎችን ጨምሮ 41 ዕጩ ዳኞች አስተያየት እንዲሰጥባቸው የስም ዝርዝራቸው በያዝነው ሳምንት መግቢያ ላይ በፍርድ ቤቱ የፌስቡክ ገጽ ላይ ወጥቷል፡፡

የጉባዔውንና የጉባዔውን ጽሕፈት ቤት አሠራር እጅግ አሳዛኝ የሚያደርገው ከአንድ ዓመት በፊት የጽሑፍ ፈተና ወስደው ቃለ መጠይቅ ተደርጎላቸው ከእነርሱ የተሻለ ተመርጠው ተሹመዋል ከተባለ በኋላ፣ ለእነዚሁ ዳኞች ያለፈው ዓመት ፈተና ውጤት ለዚህ ዙር እንደመመዘኛ መወሰዱ ነው፡፡ በተጨማሪም በፍርድ ቤቱ የፌስቡክ ገጽ ላይ ዝርዝራቸው የወጣው ዳኞች በፌዴራል ፍርድ ቤቶችና በክልል ፍርድ ቤቶች የሚያገለግሉ ናቸው፡፡ የእነዚሁ ዳኞች ስም በፌስቡክ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአራት ቀናት ውስጥ (ከሰኔ 21 እስከ 24 ቀን 2008 ዓ.ም.) በዕጩዎች ላይ አስተያየት ስጡ መባሉ አድርገናል ለማለት ካልሆነ በቀር ጊዜውና ተደራሽነቱ ምን ያህል በቂ ነው?

የዚህ ዓመት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሥራ ዘመን ከመጠናቀቁ በፊት በአሥር ቀናት ውስጥ የጽሑፍ ፈተና ሰጥቶ፣ ቃለ መጠይቅ አድርጎ፣ የተፈታኞችን የተለያየ ጊዜ የፈተና ውጤት ወስዶ በጠቅላይ ሚኒስትሩ በኩል ለምክር ቤቱ አቅርቦ ለማሾም እየተደረጉ ያለው ዝርክርክ አሠራር የመንግሥት ያለህ የሚያሰኝ ነው፡፡

ለጉባዔው ጽሕፈት ቤት ቅሬታ ለማቅረብ ቢሞከርም ቅሬታ ተቀባዩም፣ አጣሪውም፣ መልስ ሰጪውም የዳኞች አስተዳደር ጉባዔ ጽሕፈት ቤት በመሆኑ አስቸጋሪ ሆኗል፡፡

ስለሆነም የጉባዔው አባላትም ሆነ የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የበላይ አመራሮች በዚህ ጉዳይ ላይ ግልጽ የሆነ ማብራሪያ ሊሰጡ ቅሬታዎችንም ሊያስተናግዱ የጽሕፈት ቤቱን አሠራርም የመንግሥት የሚመለከተው አካል በቅርብ ሊከታተል ይገባል፡፡

ከአዘጋጁ፡- ጽሑፉ የጸሐፊውን አመለካከት ብቻ የሚያንፀባርቅ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

 

Standard (Image)

ያልተገታው የመሬት ወረራና እያስከፈለ ያለው ዋጋ

$
0
0

በይነበብ ባህሩ

አዲስ አበባ ከተማ በአየር ካርታና በነባሩ የመሬት ይዞታ ክልሉ 54 ሺሕ ካሬ ኪሎ ሜትር ስፋት ያላት፣ በአፍሪካ በፍጥነት እያደጉ ከመጡ ከተማዎች በቀዳሚነት የምትጠቀስ ናት፡፡ መታወቂያ የሌለውና በደባልነት የሚኖረው ሕዝብ ሳይቆጠርም እስከ 3.8 ሚሊዮን ሕዝብ ይኖርባታል፡፡ ከተማዋ ከአገራዊ የፖለቲካና የኢኮኖሚ መዲናነቷ ባሻገር የአኅጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ድርጅቶችና ማኅበራት መገኛ መሆን ጀምራለች፡፡

በዚህና መሰል በጎ ገጽታዎች መካከል አሁንም የኤሌክትሪክ ኃይልና ንፁኅ የመጠጥ ውኃ እጥረት ካለባቸው ከተሞች መካከል ትመደባለች፡፡ ምንም እንኳን የኤሌክትሪክ፣ የቴሌኮምና የመሠረተ ልማት ግንባታ በፍጥነት እየተቀረፉ የመጡ ቢሆንም፣ ከመኖሪያ ቤት እጥረት፣ ከትራንስፖርት አለመሟላት፣ ከኑሮ ውድነትና ከሌሎች ማኅበራዊ ፈተናዎች (ልመና፣ ሴተኛ አዳሪነት፣ ሌብነት …) ጋር በተያያዘ ገና ያልተፈቱ በርካታ ችግሮችም የታጨቁባት ናት፡፡

በዛሬው ሒሳዊ አስተያየቴ ግን ከተማዋን ክፉኛ እየፈተነ ስላለው የመሬት ይዞታ ወረራ ሕገወጥነትና ሙስናን አስመልክቶ አንዳንድ ነጥቦችን እናወጋለን፡፡ እንዳጋጣሚ ሆኖ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርን የመልካም አስተዳደርና የሙስና ችግር እንደ ሪፖርተር ጋዜጣ የሞገተ ባለመኖሩ ደግሞ ምልከታዬ በዚሁ ጋዜጣ ላይ እንዲሰፍር አነሳስቶኛል፡፡ እርግጥ የአዲስ አበባ የመኖሪያ ቤትና የመሥሪያ ቦታ ችግር ከምስቅልቅሉ አካሄድ ይወጣ ይሆን ማለትም እፈልጋለሁ፡፡

የኢትዮጵያ ሕዝብ በተለይ በከተሞች ያለው ዜጋ የመኖሪያ ቤት እንደ ልቡ የሚሠራበት ዕድል እየጠበበ ነው የመጣው፡፡ በተለይ በአዲስ አበባ ከተማ ባለርስትና ፊውዳሉ ወይም ለገዥው መደብ የቀረበው ወገን በስፋት ይይዘው የነበረው ቦታና ቤት ከደርግ ሥርዓት መምጣት ጋር ሲያከትም፣ እንደ ልብ ቤትና ይዞታ መያዝ የሚቻል አልነበረም፡፡ ያም ሆኖ ከ1996 ዓ.ም. በፊት ቤት አልሚ ግለሰቦች እንደነበሩ መካድ አይቻልም፡፡

በከተማ ቦታና ትርፍ ቤት አዋጅ ቁጥር 47/1967 መሠረት ወደ መንግሥት የዞሩት ቤቶች ሲታዩ የግለሰብ ይዞታ ምን ያህል ሰፊ ድርሻ እንደነበረው መገንዘብ አያዳግትም፡፡ ያም ሆኖ ደርግ የሚከተለው የሶሻሊስት ሥርዓት በአንድ በኩል በቤት ልማት ላይ የተሰማሩ ባለሀብቶችን የማያበረታታ፣ በሌላ በኩል የግል ቤት ግንባታ በተለይ ለኪራይ የሚውል ግንባታ ለመሥራት የሚያስችል አልነበረም፡፡ እንዲያም ሆኖ ግን ዜጎች (ምንም እንኳን የሕዝቡ ቁጥር እንዲህ እንደ አሸን ባይፈላም) አንገት ማስገቢያ ጎጆ የሚሠሩበት እራፊ መሬት የሚቸገሩ አልነበረም፡፡

ኢሕአዴግ መራሹ መንግሥት ወደ ሥልጣን ሲመጣ ሥር ነቀል ሕገ መንግሥታዊ ዕርምጃ ከተወሰደባቸው መስኮች አንዱ መሬት ነው፡፡ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 40 መሠረት ‹‹መሬት የማይሸጥ የማይለወጥ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች የጋራ ንብረት›› በመሆኑ ዋነኛው የአገሪቱ መሬት ባለይዞታ ሕዝብና መንግሥት ብቻ ናቸው፡፡ ግለሰብ መሬት ላይ ያረፈ ቤትና ንብረት ይኖረው እንደሆነ እንጂ የመሬት ባለቤትነቱ አብቅቷል፡፡

ይህን በመርህና በሕገ መንግሥት የፀና ድንጋጌ እያፈረሰውና ጥርሱን እያወላለቀው የሚገኘው አደጋ ግን ሕገወጥነት፣ ሙስናና ብልሹ አሠራር ሆኗል፡፡ በተለይ በአዲስ አበባና በዙሪያዋ በሚገኙ የኦሮሚያ ከተሞች አንዳንድ ሕገወጥ ባለሥልጣናት፣ ደላላና ጉዳይ ገዳይ በጥምር በጀመሩት ዘመቻ ‹‹የመሬትና የቤት ባለቤት መሆን የሚሻውን ዜጋ›› ለከፍተኛ ጉዳት እያጋለጡት ይገኛሉ፡፡ መንግሥትም ጀምሬዋለሁ በሚለው ፍትሐዊ ልማት የማረጋገጥ ትግል ውስጥ ሕገወጥ ድርጊት ዋነኛ እንቅፋት ሆኖ ተደንቅሯል፡

ሰሞኑን በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ አንድ ከሃና ማርያም ቤተ ክርስቲያን አለፍ ብሎ በሚገኘው ‹‹ቀርሳ ኮንቶማ›› የሚባል አካባቢ በሰነድ አልባ (ጨረቃ) ቤቶች ላይ የደረሰው ክስተት አንዱ ማሳያ ነው፡፡ እነዚህ 20 ሺሕ የሚደርሱ ቤቶች በአማካይ በቤት አምስት ቤተሰብ ቢኖር ከአንድ መቶ ሺሕ በላይ ዜጎች በሕገወጥ መንገድ ቦታ ይዘውና ቤት ሠርተው መኖር የጀመሩ ነበሩ፡፡ ይህ ከነደብረ ብርሃን፣ ደብረ ማርቆስ፣ ኮምቦልቻና ወልድያ ዓይነት የዞን ከተሞች የሚመጣጠን ሕዝብ እንደሆነ መገንዘብ ይቻላል፡፡

እንግዲህ መራራውን እውነት መፈተሽ የሚያስፈልገው በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ይህን ሁሉ መሬት ከሕገወጥ ደላሎችና አጭበርባሪ የወረዳ አስተዳዳሪዎች ወይም ከአካባቢ ገበሬዎች ሲገዙም መንግሥት የት ነበር? ሲባል ነው፡፡ የከተማዋ አስተዳደርስ ይህን ያህል ጊዜ በስብሰባና በግምገማ ‹‹ልቡ ሲጠፋ›› እንዴት ችግሩን አላየውም? ሌላው ይቅር እነዚህ ወገኖችን እንደ ሕጋዊ በመቁጠር ኤሌክትሪክ፣ ውኃና የውስጥ ለውስጥ መንገድ እንዲገባላቸው ማን አደረገ? የሚሉ ጥያቄዎችን መምዘዝ ሲቻል ነው፡፡

አሁን እየወጡ ያሉ መረጃዎች እንደሚያስረዱት ሕገወጦች በሙስና በተዘፈቀውና በነፍስ ወከፍ ከመሬት ወራሪዎች በአሥር ሺዎች ጉቦ እያስከፈሉ ነበር ይኼ ሁሉ ቤት የተሠራው፡፡ በዚሁ መዘዝም ራሳቸው የፈቀዱትና ጉቦ ሲለቃቅሙ የኖሩት ሕገወጦች ‹‹ና ተነሳ›› ብለው ሲያወያዩት ‹‹ሆ›› ብሎ አንገት ለመቁረጥና ከኢትዮጵያዊ ጨዋነት ወጥቶ ለመግደል እሰከመነሳት ደርሷል፡፡ ነገ ከነገወዲያም ከቂምና በቀል ስለመውጣቱ፣ በሥርዓቱ ላይም ኩርፊያ ስላለመሰነቁ ማረጋገጫ ማስቀመጥ ያዳግታል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአሁኑ ጊዜ 54 ሺሕ ካሬ ኪሎ ሜትር ስፋት አላት ቢባልም፣ ከፊንፊኔ ዙሪያ የኦሮሚያ ከተሞች ጋር በምትጎራበትባቸውና በከተማዋ ዳርቻዎች ከ150 ሺሕ ካሬ ኪሎ ሜትር በላይ የሚሆን መሬት በሕገወጥነት እንደተያዘ ይገመታል፡፡ ይህ የሆነው በውስጥ ለውስጥና በኪስ ቦታዎች ላይ ከተያዙ ሥፍራዎች ውጭ ሲሆን፣ በአብዛኛው ያለ ካርታ ከአርሶ አደር በተገዙ መሬቶች ላይ የሰፈሩ ናቸው፡፡ ታዲያ ይህ ሁሉ የሕዝብና የአገር ሀብትስ እንዴት መፍትሔ ሊያገኝ ነው? ብሎ ሲታሰብ ሌላ ራስ ምታት ይቀሰቅሳል፡፡ ድርጊቱስ (ሕገወጥ ወረራውና የውንብድና መሬት ሽያጩ) በምን ይቆም ይሆን? ብሎ መፈተሽ ግድ ይላል፡፡

የአዲስ አበባ የቤት ረሃብ ሕገወጥነትን አስፋፍቶ ይሆን?

በአዲስ አበባ ከተማ እስከ ቅርብ ጊዜ ባለው መረጃ 150 ሺሕ ቤቶች በቀበሌ አስተዳደር ሥር ናቸው፡፡ ከነዋሪው መካከልም የግል ይዞታ አለው የሚባለው ከ38 በመቶ ያነሰ ነው፡፡ የመንግሥትና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችና ተቋማት የያዙት ቦታም እስከ 18 በመቶ የመሬት ይዞታ እንደሚሸፍን ይገመታል፡፡ ከዚህ ሌላ መንገዶች፣ አረንጓዴ ቦታዎችና ክፍት መሬቶችም የየራሳቸው ድርሻ አላቸው፡፡

በ1999 ዓ.ም. ይፋ የተደረገው የአገሪቱ ስታስቲክስ መረጃ እንደሚያስረዳውም በአዲስ አበባ እስከ 700 ሺሕ የሚደርሱ ቤቶች በግለሰብ ይዞታ ሥር ናቸው፡፡ ይሁንና ባለፉት አሥር ዓመታት ውስጥ በከተማዋ አቅም ኖሮት በቤት አልባነት እየተፈተነ ካለው የተከራይነት እስር ቤት ለመውጣት የሚፈልገው የከተማዋ ነዋሪ ቁጥር ከ1.5 ሚሊዮን በላይ እንደሆነም በሌላ የከተማ የአስተዳደሩ የዳሰሳ ጥናት ተረጋግጧል፡፡ እንግዲህ ይህ ቁጥር ከክልል ወደ አዲስ አበባ መምጣት የሚሻው፣ ከውጭ ወደ አገር ውስጥ የሚገባው፣ ዕድሜና ኢኮኖሚ ‹‹ጎጆ እንዲወጣ›› ከሚያነሳሳው ሕዝብ ጋር ተዳምሮ ሲታይ የት እንደሚደርስ መገመት ይቻላል፡፡

እርግጥ ኢሕአዴግ መራሹ መንግሥት በተለይ ከ1998 ዓ.ም. ወዲህ የቤት ልማት መርሐ ግብርን አማራጭና ወሳኝ መፍትሔ ማድረጉ አንድ ጠቃሚ ዕርምጃ ነው፡፡ እስካሁንም 56 በሚደርሱ የአገሪቱ ከተሞች ከ250 ሺሕ በላይ የጋራ የኮንዶሚኒየም የቁጠባ ቤቶች ተገንብተው ለዜጎች ተላልፈዋል፡፡ ከዚህ ውስጥም ከ143 ሺሕ በላይ የሚሆኑት በአዲስ አበባ ከተማ ተገንብተው መተላለፋቸው ቢያንስ አብጦ ሊፈነዳ የደረሰውን የመኖሪያ ቤቶች ችግር ማስተንፈስ ችሏል፡፡ አሁን በሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ተጨማሪ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ቤቶች በመገንባት ላይ ናቸው፡፡

በግል ሪል ስቴት ልማትና የተሻለ አቅም ባላቸው የቤት ሠሪ ማኅበራት የተሠሩ፣ እንዲሁም በሕጋዊ የመሬት ጨረታ በሊዝ ተወዳድረው ዘመናዊ የመኖሪያ ቤት የገነቡ ከሩብ ሚሊዮን የማያንሱ የከተማዋ ቤቶችም አዲስ የዕድገት ምዕራፍ ከፍተዋል፡፡ በጀሞ፣ ላፍቶ፣ አያት፣ ሲኤምሲና መሰል አካባቢዎች አዳዲስ መለስተኛ ከተሞች የፈጠሩ ግንባታዎች ለአባባሉ አብነቶች ናቸው፡፡

እንዲህም ሆኖ የአዲስ አበባን የመኖሪያ ቤት ረሃብ ማስታገሻውን አላገኘም፡፡ ለጋራ ኮንዶሚኒየም ባለዕድለኝነት ተመዝግበው ዕጣ የሚጠብቁ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ዜጎች ገና ቤቶች ልማትን እየተማፀኑ ነው፡፡ ሕገወጥ የመሬት ወረራው ላይ እየተዋከበ ውስን የሆነውን የደሃ አገር የግለሰቦች ሀብት እያስበላ ያለውም ‹‹የጨነቀው እርጉዝ ያገባል›› እንዲሉ ሆኗል፡፡

እንግዲህ ጥያቄው የከተማዋንና የአገሪቱን ነዋሪዎች የቤት ችግር ለመፍታት የታዩና ያልዩታ መፍትሔዎችን ሁሉን አሟጦ መጠቀም አያስፈልግም ወይ? ሲባል ነው፡፡ ለምሳሌ በጋራ ኮንዶሚኒየም ግንባታ ረገድ ዕጣ ከሚወጣባቸው ቤቶች በተጨማሪ፣ ‹‹ለመልሶ ማልማት ምትክ ቤት፤›› እየተባለ በሺዎች ከሚቆጠሩ የቀበሌ ቤቶች ለመሀል ከተማ ተነሽዎች በዱቤ ይሸጣል፡፡ መንግሥት ግን የመሀል ከተማ ቦታዎችን እያፀዳ በውድ ዋጋ ለቢዝነስና ለሌላ ዘርፍ እየሸጠ ነው፡፡ ግን ይህን ከኮንዶሚኒየም ባነሰ ምትክ አነስተኛ የቁጠባ ቤቶችን በተለይ አሁን በሕገወጥ መንገድ በተወረሩ አካባቢዎች መሥራት አይቻልምን?

ሌላው የመንግሥት ቤቶች ኤጀንሲ ጉዳይ ነው፡፡ ይህ የከተማ ቦታና ትርፍ ቤት አዋጅ 47/1968ን ተከትሎ በተለያየ ስምና ቅርጽ የቀጠለ ተቋም የመንግሥት ቤቶችን እያከራየ ያለ ነው፡፡ በቅርቡ ለፓርላማ ሪፖርቱን ሲያቀርብ እንደሰማነው ግን የያዛቸውን ዘመናዊ ቪላዎችና አፓርትመንቶች በቅናሽ ዋጋ በማከራየቱ የሚያስገባው ገቢ በዓመት ለኪራይ የሚወጣውን እንኳን ለመሸፈን አላስቻለውም፡፡ በዚያ ላይ የገነነ የሙስናና የአድልኦ ድርጊት የሚፈጸምበት ነው፡፡ ‹‹በመቶዎች ብር የተከራዩ አንዳንድ ሰዎች የራሳቸውን ቤት ሠርተው በአሥር ሺዎች ለሦስተኛ ወገን አከራይተው የሚኖሩበት፣ አንዳንድ የመንግሥት ባለሥልጣናት የራሳቸውን ቤት አከራይተው የሚኖሩበት፣ ለሥርዓቱ አገልጋዮችና የቅርብ ሰዎች ካልሆነ ዜጋው የማይጠቀምባቸው ቤቶችን የሚያስተዳድር የኢፍትሐዊነት ተምሳሌት፤›› የሚለውን ጥብቅ ትችት መቅረፍ ያልቻለ ተቋም ነው፡፡ እዚህ ላይ ለምን ‘ሪፎርም’ ማሰብ አልተለቻለም?

ተጨማሪው መፍትሔ መንግሥት ‹‹እኔ ብቻ ቤት ልሥራ›› ከማለት መውጣት አለበት የሚለው ነው፡፡ እርግጥ ለግል የቤት አልሚዎች (ሪል ስቴቶች) በመፈቀዱ በሕዝብ መሬት የተንደላቀቁ የቅንጦት ቤቶች ተገንብተው ለከፍተኛ ገቢ ያለው ዜጋ እየተሸጡ ነው፡፡ ይህ ግን ደሃውንና መካከለኛ ገቢ ላይ ያለውን አይታደግም፡፡ ስለዚህ በመንግሥት ድጎማ፣ በሕዝብ መሬት ላይ ተመጣጣኝ ዋጋ ያላቸውን ቤቶች የሚሠሩ የአገር ውስጥም ሆነ የውጭ ተቋራጮች መግባትና ማልማት አለባቸው፡፡ ይህ ካልሆነ እጥረቱን በማይሆን መፍትሔ ለመፍታት እጅግ አዳጋችና ፈታኝ መሆኑ ሊጤን ይገባዋል፡፡

ገጠሬው እያጥለቀለቃት ያለው አዲስ አበባ ምን ይበጃት?

ኢትዮጵያ ከአገር ውስጥ ወደ ውጭ የሚደረገው ስደት ብቻ አይደለም የሚያስጨንቃት፡፡ ከገጠር ወደ ከተማ (በተለይ ወደ አዲስ አበባ) እየተባባሰ የመጣው ፍልሰት ነው፡፡ ስለዚህ አባባል ጥሩ ማሳያው ከሊስትሮና ከሎተሪ ሻጭ አንስቶ እስከ ትልልቁ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ከከተማዋ ‹‹ልጆች›› (አራዶች) ይልቅ የገጠሩ እያጥለቀለቋት መሆኑ ብቻ አይደለም፡፡ ይልቁንም በሌሎች አካባቢዎች ያፈራውን ሀብት ይዞ፣ ቤት ንብረቱን እየሸጠ ጭምር ወደ አዲስ አበባ በየጊዜው እየተመመ ያለው ዜጋ እየበረከተ ነው፡፡

ይህን ፍልሰት አስመልክቶ ጠንከር ያለ ጥናት ስለመደረጉ መረጃ ባይኖርም፣ መነሻውን አስመልክቶ ግን ግምታዊ መላምት ማስቀመጥ ይቻል ይሆናል፡፡ አንደኛውና ዋናው የተሻለ ሥራ ለማግኘትና የተሻለ ሕይወት ለመኖር (በተለይ ትምህርት ለማግኘት) ሊሆን ይችላል፡፡ በሌላ በኩል በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአንዳንድ ክልሎች እየታየ ያለው የሰላም ዕጦትና ‹‹የመኖር ዋስትና ማጣት›› (ኦሮሚያና ጋምቤላን በመሰሉ ክልሎች) እንዲሁም በደቡብ ክልል ጥቂት ዞኖች ከነባሩ ውጪ ያለውን ዜጋ ለመግፋት የሚደረገው ሙከራ አቅም ያለው ‹‹መንግሥት ወዳለበት ልጠጋ›› እንዲል እያደረገው ይመስላል፡፡

የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ባለሙያዎች ማኅበር ከወራት በፊት ባቀረበው የገጠር-ከተማ ፍልሰት መለስተኛ ጥናት ‹‹በገጠር የመሬት መጣበብ ችግር በቁራሽ የእርሻ መሬት ላይ የሚሰፍረው ሰው ብዛትና የነፍስ ወከፍ መሬት ድርሻ በየጊዜው ማነስ በገጠር ሥራ አጥነት ያስፋፋል፣ ብዙ የሥራ ኃይልና ጉልበት ይወዝፋልና ወደ ከተማ የሚደረገውን ፍልሰት ያባብሳል፤›› ሲል ደምድሟል፡፡ አሁን በአገሪቱ ያለው ያለ ሥራ የተቀመጠው ጉልበት (Sulplus Labour) ከ600 በመቶ በላይ እንደሚደርስ በማስመልከት ነው፡፡ ብዙዎቹ በሕገወጥ መንገድ የተያዙ መሬቶችና ሕገወጥ ግንባታዎች እየተፈጸሙ ያሉት ከክልል በመጣው ኃይል መሆኑ ሲታይ የድምዳሜውን ትክክለኛነት ያረጋግጣል፡፡

እንግዲህ ለዚህም መፍትሔ ማበጀት ለነገ የሚባል ሥራ አይሆንም፡፡ አንደኛው በገጠር ከግብርና ወደ ሌላ መስክ ትራንስፎሜሸንን ማፋጠን ግድ ይላል፡፡ የሥራ ዕድል ፈጠራውም ያለማቅማማት ሊገባበት ይገባል፡፡ ከሁሉ በላይ የፌዴራሊዝምን ‹‹ለብሔር ባርኔጣና ለጠባብነት ልክፍት ማቀንቀኛ›› እያደረጉ ያሉ መንግሥት ውስጥ ያሉ ሰዎች፣ ፖለቲከኞችም የሚባሉ ጥገኞች በይፋ ቁጣና ተግሳጽ ሊደርስባቸው ይገባል፡፡ መወገዝም አለባቸው፡፡ የዜጎችን ተንቀሳቅሶ የመሥራትና በየትም የመኖር ሕገ መንግሥታዊ መብቶች እየገፉ አገር ለመገንባት ማሰብ ከንቱ ጨዋታ ነው፡፡

ማጠቃለያ

አዲስ አበባ የሁላችንም ከተማ ነች፡፡ ሕገወጥነትንም የምታገለው ሁላችንም መሆን አለብን፡፡ በተለይ ግን በሥልጣን ላይ ያለው መንግሥት የአንበሳውን ድርሻ ወስዶ መታገልና ማስተካከል አለበት፡፡ በመሬት ወረራ ላይ የታየው መዘናጋትና ‹‹የመሬት ባንክ አለን›› እየተባለ ሥውር ሕገወጥነትን ማበረታታት በፍፁም መታረም  አለበት፡፡ ይህ የደሃ ዜጎችን ሀብት ለጥቂት ዘራፊዎች እየማገደ ያለ ድርጊት ዛሬ የሕይወት ዋጋም ማስከፈል ጀምሯል፡፡ ነገ በጊዜ ካልታረመም ዕዳው ከዚህ የባሰ ነው፡፡ ስለዚህ ሕዝቡን ያሳተፈና በሆደ ሰፊነት የተያዘ የትግል ሥልት በመከተል ሳያቅማሙ ውጤት ማምጣት ያስፈልጋል፡፡ ያለጥርጥር ትግሉም ከውስጥ መጀመር አለበት፡፡

ሕዝቡም ቢሆን ከሙሰኛውና ከኪራይ ሰብሳቢው እግረ ሙቅ መላቀቅ አለበት፡፡ መንግሥት መሬት የሕዝብና የመንግሥት ነው ብሎ በቁጠባ ሲሸጥ እያየ በሕገወጥ መንገድ በአቋራጭ መግባትን ምን አመጣው?  እየተጠረጠረ ገብቶ በመከራ ያገኘውን ሀብትስ ስለምን ይበትናል?  ከዚህ ይልቅ ሕጋዊውን መስመር ተከትሎ፣ መንግሥት ላይም ተፅዕኖ እያሳደረ የቤት ባለቤት መሆን ለምን አይመርጥም መባል ይኖርበታል፡፡

ከአዘጋጁ፡- ጽሑፉ የጸሐፊውን አመለካካት ብቻ የሚያንፀባርቅ ሲሆን፣ ጸሐፊውን በኢሜይል አድራሻቸው   yinebeb@gmail.comማግኘት ይቻላል፡፡ 

 

Standard (Image)

ሰሚ ያጣ ጩኸት

$
0
0

በአንተነህ አዲስ ‹‹መልካም አስተዳደር፣ ግልጽነት፣ ተጠያቂነት፣ ለሕዝብ ጥያቄ ምላሽ መስጠት…›› የሚባሉት ቃላት ዘመን ያዘመናቸው የሪፖርት ማድመቂያዎች፣ ከእኔ በላይ ላሳርን የሚያዘምሩ የንግግር ማሳመሪያዎች፣ ሥልጣንን የሚያደላድሉ ሕዝበ አልባ ቃላት ከሆኑ ሰነባብተዋል፡፡ በየመሥሪያ ቤቱ ኮሪደርና በየኃላፊው ቢሮ ባማረ ፍሬም ተንጠልጥለው የሚታዩት አሥራ ሁለቱ የሥነ ምግባር መርሆዎች የድንጋይ ዘመን ተረቶች ይመስሉ ዘንድ ከተግባር ከተፋቱ፣ ከህሊና ከራቁ ከራርመዋል፡፡ እንደ አማረ ፍሬያቸው ተግባራቸው ሰምሮ፣ እንደ ጎላ ጽሑፋቸው ውሏቸው ኑሯችንን ታድጎ መልካም አስተዳደር ያሰፍኑልናል ብለን የተመኘናቸው የሥነ ምግባር መርሆዎች የሚታዩ እንጂ የማይበሉ ፍሬዎች ሆነዋል፡፡ መርሆዎቹን እያዩ ከመደሰት ይልቅ መከፋትን፣ ከመሳቅ ይልቅ ማልቀስን፣ ከመኩራት ይልቅ ማፈርን ዕጣ ክፍላችን አድርገናል፡፡ ዱሮ ዱሮ መጥፎም ሆነ መልካም ዕጣ ክፍል የሚሰጠው ከፈጣሪ ነበር፡፡ እናም የማትጋፋውን፣ የማትከሰውን፣ የማትሞግተውን ስጦታ ተቀብለህ ትኖራለህ፡፡ ዛሬ ዛሬ ግን ዕጣ ክፍላችን የሚወሰነው በማንጋፋቸው ምድራዊ ኃላፊዎች ሆኗል፡፡ ትክክል አይደለም ብለህ ትከሳለህ ግን ትሸነፋለህ፡፡ ኧረ ሕግ ተጥሷል ብለህ ትሟገታለህ ግን ትረታለህ፡፡ አንተ ዘንድ ካለ መቶ እውነትና ማስረጃ ይልቅ ኃላፊዎች ጠረጴዛ ላይ የወደቀች አንዲት ስንጥር ውሸት ሕይወትህን ታጨልማለች፣ ጥንካሬህን ትጋፋለች፣ ተስፋህን ትበትናለች፡፡ ያኔ… እውነት፣ እውቀት፣ ዕምነት ቅንነት፣ ግልጽነት ዋጋቸው ረክሶ፣ ክብራቸው ተገሶ፣ በነጠፉበት ለት፣ መጮህ ምን ሊፈይድ፣ ምን ሊያመጣ መላ፣ እህህን ስንቅ አድርጎ፣ ከመብሰክሰክ ሌላ፣ ከመቃጠለ ሌላ…ብለህ መቆዘም ዕጣ ክፍልህ ይሆናል፡፡ እናም ‹‹መልካም አስተዳደርን እናሰፍናለን›› የሚል መፈክር ባየህ ወይ በሰማህ ቁጥር በአንተ ሕይወት ላይ የተለጠፈ ስላቅ ቢመስልህ አያስደንቅም፡፡ ያላዩት አገር አይናፍቅምና፡፡ ከላይ የዘረዘርኩትን ሐሳብ ያነሳሁት ያለምክንያት አይደለም፡፡ ከአንድ ወር በፊት ወደ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ባቀናሁበት ወቅት ለጉዳዬ የተሰጠኝ ምላሽ ከምንዘምርለት የመልካም አስተዳደር መዝሙር ጋር የተፋታ ሆኖ ስላገኘሁት እንጂ፡፡ ነገሩ እንዲህ ነው፡፡ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በ2008 ዓ.ም. የትምህርት ዘመን የአሥራ ሁለተኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከተፈተኑት ተማሪዎች መካከል ከፍተኛ ነጥብ ያላቸውን ተማሪዎች ተቀብሎ በሳይንስና በኢንጂነሪንግ የትምህርት ዘርፍ በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲና በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ለማስተማር ማስታወቂያ ያወጣል፡፡ ሁለቱም ዩኒቨርሲቲዎች ተወካዮቻቸውን በበርካታ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በመላክ የሚያስተምሩትን የትምህርት ዓይነት የሚገልጽ በራሪ ወረቆቶች እንዲበተን ያደርጋሉ፡፡ ጉዳዩ የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲን የሚመለከት በመሆኑ የበተነውን በራሪ ወረቀት ለግንዛቤ ይሆናችሁ ዘንድ ላስቃኛችሁ፡፡ ዩኒቨርሲቲው በራሪ ወረቀቱ ላይ፣ በ“Applied Natural Science” ዘርፍ “Biomedical Engineering, Biotechnology, Industrial Chemistry, Space Technology /Areas of Study” ለማስተማር የተዘጋጀ መሆኑን የሚገልጽ ዝርዝር አውጥቷል፡፡ ይኼንን ወረቀት ያዩና በአሥራ ሁለተኛ ከፍል መልቀቂያ ፈተና ከ400 እስከ 565 ነጥብ ያመጡ ተማሪዎች ከወላጆቻቸው፣ ከመምህራኖቻቸውና ከጓደኞቻቸው ጋር በመመካከር፣ እንዲሁም ፍላጎታቸው ግምት ውስጥ በማስገባት ተመዘገቡ፡፡ የመግቢያ ፈተናም ተቀብለው 38 ተማሪዎች አለፉ፡፡ ነገር ግን የተማሪዎቹ ቁጥር ማነስ ያሳሰበው የሚመስለው ዩኒቨርሲቲ ሌላ ማስታወቂያ በብዙኃን መገኛዎች አስነገረ፡፡ በዚህ ጊዜ የዘረዘራቸው የትምህርት ዘርፎች ግን በመጀመርያው በራሪ ወረቀት ላይ የቀረቡት አልነበሩምና ተማሪዎቹ ትምህርት ከመጀመራቸው በፊት ዩኒቨርሲቲውን ስለሁኔታው ግልጽ እንዲያደርግላቸው ጠየቁ፡፡ የዩኒቨርሲቲው አስተዳደርም ተማሪዎቹን ሰብስቦ፣ ‹‹እናንተ ከፍተኛ ነጥብ ያላችሁና ተወዳድራችሁ የገባችሁ ናችሁ፡፡ ይኼንን ያደረግንበት ምክንያት የተመረጡ ተማሪዎችን ሳይንቲስት ለማድረግ በማሰብ ነው፡፡ ሳይንቲስት ለመሆን ደግሞ የመጀመሪያ ዘርፍ ዲግሪ ሊኖራችሁ ይገባል፡፡ በዚያው በመቀጠል ሁለተኛ ዲግሪያችሁን (Master’s Degree) በራሪ ወረቀቱ ላይ በተገለጸው መሠረት ይሰጣችኋል፤›› በማለት ትልቅንና የሚያስጎመዠውን ተስፋ መገቧቸው፡፡ ንጋትን የዘነጋ ባዶ ተስፋ አንድ በተሰጠጣቸው ተስፋ ሁሉም ተማሪዎች ተደሰቱ፡፡ ፈጣን ምላሽ በማግኘታቸውም ረኩ፡፡ አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የገቡበትን ቀን መረቁ፣ አወደሱ፡፡ በደስታ የተዋበ ተስፋቸው ፍሬ ያፈራ ዘንድ ጠንክረው መሥራት እንዳለባቸው ለራሳቸው ቃል ገቡ፡፡ በመምህራኖቹ ዘንድ ‹‹እንደ ዘንድሮ ዓመት ጎበዝ ተማሪ ገብቶ አያውቅም፤›› እስኪባል ድረስ በሞራል መሥራትን ተያያዙት፡፡ ግና… ደስታና ሞራላቸው ከአንድ ሴሜስተር የዘለለ ዕደሜ ለመቁጠር አልታደለም፡፡ እውነትና ንጋት እያደር ጠራና ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ ዩኒቨርሲቲው አዲስ በራሪ ወረቀት በተነ፡፡ በራሪ ወረቀቱም ላይ የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በመጀመርያም ሆነ በሁለተኛ ዲግሪ የሚያስተምረው Applied Biology, Applied Pysics, Applied Chemistry, Applied Geology, “Applied Mathematics” መሆኑን የሚገልጽ ነበር፡፡ ይህ በራሪ ወረቀት ለተማሪዎች መርዶ ነጋሪ ነበርና ተደናገጡ፡፡ ወረቀቱ የተበተነው አማራጮች ሁሉ በተሟጠጡበት ወቅት በመሆኑ ሐዘናቸውን አከበደው፡፡ ‹‹…እኛ ከፍተኛ ነጥብ ያለን ተማሪዎች በመሆናችን ከሕክምና ጀምሮ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች መመደብ ስንችል ሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲን አምነን መጥተን እንዴት እንታለላን? ይኼ ምርጫ መቅረብ የነበረበት መጀመርያ ነበር፡፡ የሕገ መንግሥቱን አንቀት 12 ንዑስ አንቀጽ አንድ ላይ ‘የመንግሥት አሠራር ለሕዝብ ግልጽ በሆነ መንግድ መከናወን አለበት’ በማለት የሚለውን ሕግ በአደባባይ መጣስ ከአንድ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም የሚጠበቅ ነው ወይ?›› በማለት በተለያዩ ደረጃ ላያ ያሉ ኃላፊዎችን አነጋገሩ፡፡ የዩኒቨርሲው አመራሮች የሰጡት መልስ ግን እጅግ የሚያሳፍር በአመራር ላይ ካለ ‹‹ምሁር›› የሚጠበቅ አልነበረም፡፡ ‹‹‹…የመጀመርያውን ወረቀት ያዘጋጀው ሰው ሞቷል፡፡ … በራሪ ወረቀቱ ላይ የእኔ ፎቶ የለም እኔን አትጠይቁኝ፡፡ ብትፈልጉ ተማሩ ባትፈልጉ ከስድስቱ በአንደኛው በር መውጣት ትችላላችሁ፡፡ እኛ የምናስተምራችሁ በመጀመርያ ዲግሪ ብቻ ነው፤›› የሚሉ ሥነ ምግባር የጎደላቸው፣ እውነት የጠማቸው፣ ከኢትዮጵያዊ ባህላችን ጋር አብረው የማይሄዱና የተሳከሩ መልሶች ነበሩ፡፡ ተማሪዎቹ በዩኒቨርሲቲው መልስ አዘኑ፡፡ ከትልቁ የትምህርት ተቋም በተነገረው ትንሽ መልስ አፈሩ፡፡ በአንድ ሴሚስተር ውስጥ ፍየልና ቅዝምዝም በሆኑት ሁለት መልሶች ተገረሙ፡፡ ‹‹….መንግሥት ባለበት አገር፣ የሕገ መንግሥት የበላይነት በተረጋገጠበት አገር፣ የሰብዓዊ መብት በተከበረባት አገር እንዴት ያልፈለግነውን፣ ያልመረጥነውን፣ ቀድሞ ያልተነገረንን ትምህርት ለመማር እንገደዳለን?...›› በማለት ቅሬታቸውን ለማቅረብ ተወካዮቻቸውን ወደ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ላኩ፡፡ አቤቱታቸውን ካላቸው መረጃና ማስረጃ ጋር አያይዘው አቀረቡ፡፡ የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የበላይ ኃላፊዎችም የቀረበላቸውን ቅሬታ ተቀብለው፣ ‹‹ዩኒቨርሲው የሚያስተምረው መጀመርያ በበተነው በራሪ ወቀት ላይ የተዘረዘሩትን የትምህርት ዓይነቶች መሆኑን ነው እኛም የምናውቀው፡፡ አሁን እናንተ ባሳያችሁን በራሪ ወረቀት ላይ ያሉትን የትምህርት ዓይነቶች አናውቃቸውም፡፡ ስለዚህ በአስቸኳይ ከዩኒቨርሲቲው ጋር ተነጋግረን መልስ እንሰጣችኋለን፤›› ብለው የግል ሞባይል ስልክ ቁጥራቸውን ሳይቀር ሰጥተውና አጽናንተው መለሷቸው፡፡ ቁም ነገርን የተራበ ባዶ ተስፋ ሁለት የተማሪዎቹ ተወካዮች አዲስ የተገነባላቸውን ተስፋ ተቀብለው ለጓደኞቻቸው አካፈሉ፡፡ ‹‹እልፍ ቢሉ እልፍ ይገኛል›› የተባለበት ዘመን ላይ አለመሆናቸውን ስላላወቁ የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱን መልስ ናፈቁ፡፡ በተሰጣቸው ስልክ ቁጥር ከሻይ ወጪያቸው ቀንሰው ደጋግመው ደወሉ፡፡ አዲስ ተስፋም ከመሥሪያ ቤቱ ደረሳቸው፡፡ ‹‹ከአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ጋር በእናንተ ጉዳይ ተነጋግረን በመጀመሪያው በራሪ ወረቀት ላይ የተጠቀሱትን የትምህርት ዘርፎች ለማስተማር እንደማይችል ነግሮናል፡፡ ስለዚህ ሦስት አማራጮች አሏችሁ፡፡ ወደ አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ መቀየር፣ አዳማ ባለው የትምህርት ዘርፍ መቀጠል የሚፈልጉትን ማስቀጠል፣ ወደ ኢንጂነሪንግ ዘርፍ መቀየር የሚፈልጉትን መቀየር፡፡ ከእነዚህ የምትፈልጉትን እንደትመርጡ ወስነናል፡፡ ውሳኔውን ለዩኒቨርሲቲው የላክን ስለሆነ ይነግሯችኋል ጠብቁ፤›› ተባሉ፡፡ ማለቂያ የሌለው ባዶ ተስፋ ሦስት ተማሪዎቹ ዩኒቨርሲቲውን ደጋግመው ቢጠይቁም ውኃ ቢወቅጡት ዓይነት ሆነባቸው፡፡ ይባስ ብሎ ሁለተኛ በዚህ ጉዳይ ላይ መነጋገር እንደማይፈልጉ ከማስፈራሪያ ጋር ገለጸላቸው፡፡ በመልሱ ያልተደሰቱት ተሪማዎች ተወካዮቻቸውን ከመላክ ይልቅ፣ ሁሉም ተሰብስበው ቢሄዱ ተደማጭ እንሆናለን ብለው በማስብ ወደ ሰላሳ የሚጠጉ ተማሪዎች ከአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ተነስተው ወደ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አቀኑ፡፡ አቤቱታቸውን ለሁለተኛ ጊዜ በማቅረብም አስቸኳይ መልስ እንዲሰጣቸው ጠየቁ፡፡ ሚኒስቴሩም እንዲያውቁት አደረጉ፡፡ ጥያቄያቸውን የተቀበለው አካልም በአስቸኳይ መልስ እንደሚሰጣቸውና አንድ ተወካይ ወደ አዳማ መጥቶ እንደሚያነጋግራቸው ቃል ገብቶ መለሳቸው፡፡ ተሰፋ በሰጠህ ቁጥር ዕዳ እየገባህ መሆኑን አትርሳ የሚለውን አባባል የዘነጋ ባዶ ተስፋ አራት ቀን አልፎ ቀን ቢተካም የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ውሳኔ ለተማሪዎቹ ሊቀርብ አልቻለም፡፡ ይመጣል የተባለው ተወካይን የበላው ጅብ አልጮህ አለ፡፡ ከእንግዳው ይልቅ ዩኒቨርሲቲው ቀረበና ‹‹ጥያቄያችሁ የፖለቲካ ፍላጎት ባላቸው ሰዎች የሚመራ መሆኑን ደርሰንበታል፡፡ የጠየቃችሁት የትምህት ዘርፍም በዓለም ላይ የሌለ ስለሆነም አርፋችሁ ብትማሩ ይመረጣል፡፡ ከዚህ ውጪ ትምህርታችሁን እየተዋችሁ ለአቤቱታ የምትሯሯጡ ከሆነ ዩኒቨርሲቲው ለማባረር ይገዳደል፤›› በማለት ገለጸላቸው፡፡ ሁሉ በጁ፣ ሁሉ በደጁ የሆነው ዩኒቨርሲቲ በሥነ ዜጋ ትምህርቱ የሕገ መንግሥቱን አንቀጽ ስምንት ንዑስ አንቀጽ ሦስት፣ ‹‹ማንኛውም ሰው በኃይል ተገዶ ወይም ግዴታ ለሟሟላት ሲባል ማንኛውንም ሥራ እንዲሠራ ማድረግ የተከለከለ ነው›› የሚለውን ሕግ ባስተማረበት ክፍል ተማሪዎች የማይፈልጉትን፣ በጭራሽ ያልመረጡትን ትምህርት በግዳጅ ሊያስተምር መነሳቱ የትኛውን ሕግ ተግባራዊ እያደረገ ይሆን? ወይስ ጌታዋን የተማመነች…ሆኖበት? አቤቱታቸውን ሰምቶ፣ ብሶታቸውን አዳምጦ ትክክለኛውን ፍርድ የሚሰጥ አካል ያጡት ተማሪዎች ይመለከተዋል ወዳሉት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሳይንስ፣ የመገናኛ ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ችግራቸውን በደብዳቤ አቀረቡ፡፡ ደብዳቤአያቸውን የተቀበለው አካልም ‹‹በአምስት ቀናት ውስጥ መልስ ይሰጣችኋል ጠብቁ፤›› አላቸው፡፡ የተባሉት አምስት ቀናት አለፉ፡፡ ያልተጠቀሱት አሥር ቀናት ተደገሙ፡፡ ያልታሰቡት አሥራ አምስት ቀናት ተቋጩ፡፡ መልሱ ግን እንደ መንግሥተ ሰማያት ራቀ፡፡ ‹‹የዘገየ ፍርድ እንደተከለከለ ይቆጠራል ያሉት ተማሪዎች እንባቸውን ያብስላቸው ዘንድ ወደ ዕንባ ጠባቂ ቢሮ ማመልከቻቸውን አቀረቡ፡፡ ይኼ ጽሑፍ እስከተጻፈበት ጊዜ ድረስ መልስ በመጠባበቅ ላይ ይገኛሉ፡፡ ይታያችሁ መንግሥታችን የመልካም አስተዳዳር ዕጦት አንኳር ችግር መሆኑን ተቀብሎ ለመቅረፍ በሚሯሯጥበት በዚህ ጊዜ፣ ተበደልን ላሉ ተማሪዎች ፍትሕ የሚሰጥ አካል እንዴት ይጠፋል? ይህ በእንዲህ እያለ የልጆቻቸውን አጣብቂኝ ውስጥ መግባት ያሳሰባቸው ጥቂት ወላጆች ጥያቄው የልጆቻችን ብቻ ሳይሆን የእኛም ነው በማለት ጣልቃ ለመግባት ተገደዱ፡፡ ልጆቻችንን እንደየአቅማችን ከአሥራ ሁለት እስከ አሥራ አምስት ዓመት አስተምረን፣ ደረሱንልን ብለን ዓይን ዓይናቸውን ስናይ እንዴት በመንግሥት ተቋም ለዚያውም በአደባባይ ይታለላሉ? በማለት ጥያቄያቸውን አንስተው ወደ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሄዱ፡፡ ይመለከታቸል የተባሉ ሁለት የሥራ ኃላፊዎችን አነጋገሩ፡፡ አንደኛውን ኃላፊ በስልክ ነበርና ያገኙት፣ ‹‹የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የራሱ አስተዳደር ያለው ስለሆነ እኛ ጣልቃ አንገባም፡፡ እናንተ ወላጆች ሄዳችሁ ለምኑት፤›› አላቸው፡፡ ወላጆች ግን፣ ‹‹ልጆቻችን ለምነው ሳይሆን በብቃታቸው ተፈትነው፣ አልፈው የገቡ በመሆኑ ማንንም ለመለመን ህሊናችን አይፈቅድም፡፡ ችግር በልመና የሚፈታ ከሆነ የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱን ለተማሪዎቹ ያንን ሁሉ ተስፋ መስጠት ለምን መረጠ?›› በማለት ሳይስማሙ ቀሩ፡፡ ይታያችሁ የተጭበረበሩ ተማሪዎችን መብት ለማስከበር ልመና አንዱ የአሠራር ሥልት የሆነበት ዘመን? አውቆ የተኛን ለምኖ መቀስቀስ አዲስ የሳይንስ ግኝት ይሆን? መልካም አስተዳዳር ሲያወሩት የቀለለ፣ ሲተገብሩት ግን ከጂብራልተር አለት የከበደ የሆነባቸው ወላጆች ወደ ሌላው ኃላፊ ቢሮ አመሩ፡፡ የሚመለከታቸውን ኃላፊም በግንባር ቀርበው ጉዳያቸውን አስረዱ፡፡ ኃላፊው፣ ‹‹የተማሪዎቹ ጥያቄ የፖለቲካ ችግር ባለባቸው ሰዎች የሚመራ፣ የጠየቁት ትምህርትም በዓለም ላይ የሌለ ነውና እናንተ ወላጆች አትግቡበት፡፡ እኛ ከዩኒቨርሲቲው ጋር በመነጋገር እንፈታዋለን፤›› በማለት ዩኒቨርሲቲው የሰጠውን መልስ ደገሙላቸው፡፡ ወላጆች ግን ተማሪዎቹ ያነሱት ጥያቄ የመብት ጥያቄ ነው፡፡ ጥያቄያቸው ‹‹እኛ የመጣነው በመጀመርያው በራሪ ወረቀት ላይ የሰፈሩትን የትምህርር ዓይነቶች ለመማር ነው፤›› የሚል ነው፡፡ ይኼ መብት ነው፡፡ መብት የማይሆነው ዩኒቨርስቲው የማያውቀውን ትምህርት እንዲያስተምራቸው ሲጠይቁ ነው፡፡ ነገር ግን ልጆቹ የጠየቁት ዩኒቨርሲቲው አስተምራለሁ ብሎ የዘረዘረውን የትምህርት ዘርፍ እንጂ የራሳቸውን ምናብ አይደለም፡፡ አንዳንዶቹ የትምህርት ዓይነቶች እኮ በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የሚሰጡ ናቸው፡፡ (እዚህ ላይ በገባው ቃልና በዘረዘረው የትምህርት ዘርፍ መሠረት እያስተማረ ያለው የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ሊመሰገን፣ ሊወደስ ይገባዋል ቃል የዕምነት ዕዳ መሆኑን አስመስክሯልና) እንደተባለው የፖለቲካ ችግር ያለበት ተማሪ ካለ በሕግ አግባብ መየጠቅ እንጂ፣ በፖለቲካ አሳቦ የመብት ጥያቄ አለመመለስ ከመልካም አስተዳር ችግሮች አንዱ መሆኑን መረዳት ይገባል፡፡ ለመሆኑ ጥፋቱ የማን ነው? የሚያስተምሩትን ትምህርት ባትዘረዝር ኖሮ ልጆቻችን በትምህርት ሚኒስቴር ይመደቡ ነበር፡፡ እናንተንም የመጀመርያ ምርጫቸው አያደርጉም ነበር በማለት ወላጆች በተሰጣቸው መልስ ሳይስማሙ ቀሩ፡፡ የተሻለና የመጨረሻው አማራጭ አድርገው የያዙት ሚኒስትሩን ማነጋገር ነበርና በጸሐፊያቸው በኩል ቀጠሮ እንዲያዝላቸው ጠየቁ፡፡ ይሁን እንጂ ሚኒስትሩ የበታች ኃላፊዎቹ ከሰጡት መልስ ውጪ የተለየ መልስ እንደሌላቸው ወላጆችን ማናገር እንደማይፈልጉ ገለጹ፡፡ በዚህ ጊዜ የፍቅር እስከ መቃብር የበዛብህን ግጥም ለማስታወስ ተገደድኩ፡ …ዳሩ ዳኛ የለም ልተወው ግድ የለም፡፡… ግን ደግሞ መተው ፈሪነት ነው፡፡ ያለነው በአፄው ዘመን ባይሆንም፣ ብታንኳኳ ወይ ብትቆረቁር የመልካም አስተዳዳር በር ከተዘጋ ቢከራከርም፣ ያንተ እውነት ለዕምነት ባይታደልም የቢሮክራሲን ውጣ ውረድ ለመፋለም አንድ ቀሪ መንገድ አለ፡፡ የግል ሚዲያ፡፡ እናም እውነቱን ሕዝብ እንዲያውቀው በማሰብ ምርጫዬን የግል ጋዜጣ አደረግኩ፡፡ በመግቢያዬ ላይ የመልካም አስተዳደር፣ ግልጽነትና ተጠያቂነት ከሪፖርት ማድመቂያነት ያለፈ አቅም የሌላቸው መካን ቃላት ሆነዋል ያልኩት ያለምክንያት አይደለም፡፡ ‹‹ግልጽነትና ተጠያቂነት ያለው አሠራር በማስፈን መልካም አስተዳደርን ዕውን እናደርጋለን›› የሚለው መፈክር ከመድረክ ያለፈ ሠፈርና ዕደሜ የለውም፡፡ ቢኖረውም ኖሮ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በነፃነት በሚርመሰሙሱባት አገር ተበድያሁ ብሎ ቅሬታ ያቀረበ ሰው ችግሩ ይፈታለት ነበር እንጂ፣ ወደ ፖለቲካ ችግር አይላከክም ነበር፡፡ ምናልባት የምናወራለት መልካም አስተዳዳር ለጎረቤት አገሮች ከሆነ ሐሳቤን አንስቻለሁ፡፡ እንደኔ ዕምነት ሰዎች የሚጠዩቁት ጥያቄ በትክክል መሆኑን ውስጣቸው እያወቀው እውነተኛውን መልስ ቢሰጡ ሌሎችን ያስቀይማል ብለው ሲያስቡ ወይም በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ራሳቸው የችግሩ አካል መሆናቸውን ሲያውቁ፣ ለማድበስበስ በማሰብ መልሳቸው በቁጣና በሰበብ አስባብ የተሰናከለ ይሆናል፡፡ ለዚያም ነው ተማሪዎች ያነሱት ጥያቄ መልስ ያጣው እንጂ የአልበርት አንስታይን ሐሳብ ሆኖባቸው እንዳልሆነ በእርግጠኝነት መናገር ይቻላል፡፡ እነዚህ ልጆች ዜጎች ናቸው፡፡ ከተሳሳቱ ፊት ለፊት ተነጋግሮ ማሳመን፣ ማረም፣ ካላወቁ ማሳወቅ፣ መንገዳቸውን ከሳቱ መመለስ ከዩኒቨርሲቲው የሚጠበቅ ተግባር ነው፡፡ የወላጅን ቦታ የተካው ዩኒቨርሲቲው ቀናውን መንገድ ሊያሳየቸው፣ መልካሙን ጎዳና ሊጠቁማቸው ሲገባ ባልወለደ አንጀቱ ተጋግዞ ተስፋቸውን ማጨለም ለምን እንደመረጠ ግልጽ አይደለም፡፡ እዚህ ላይ ተማሪዎቹ ወደ ዩኒቨርሲቲው የገቡት በትምህርት ሚኒስቴር በዕጣ ከመመደብ ይልቅ የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የዘረዘራቸው የትምህርት ዓይነቶች አጓጉተዋቸው እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ዳሩ ምን ያደርጋል ጉጉት ብቻ ሆኖ ቀረ፡፡ በሌላ በኩል ዩኒቨርሲቲው በሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሥር ሲሆንና አዲስ ፕሮግራም ሲጀምር መንግሥት ከፍተኛ በጀት እንደመደበለት እየታወቀ ያላሟላቸው ነገሮች ካሉ ተማሪዎችን ከመቀበሉ በፋት እንዲያሟላቸው ማበረታታት ሲገባ፣ የቆፈረውን ጉድጓድ እንዲያረዝመው ማበረታታት ለምን እንደመረጠ ግልጽ አይደለም፡፡ የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱም ቢሆን የተማሪዎቹ ጥያቄ ትክክል ካልሆነ ቁርጥ ያለ መልስ ሰጥቶ ትምህርታቸውን እንዲቀጥሉ ማድረግ፣ ጥያቄያቸው ትክክል ከሆነ ደግሞ ውሳኔውን አሳውቆ የሚስተካከልበትን መንገድ መፈለግ ሲገባው ‹‹ተማሪዎቹም ስህትት ሠርተዋል፣ ዩኒቨርሲቲውም አጥፍቷል›› በሚል የዋለለ መልስ የተማሪዎቹን ዕደሜ በአንድ ዓመት መቀነስ አግባብነት ያለው አካሄድ አይመስለኝም፡፡ ዕድልና ዕድሜ መጠባበቂያ የላቸውም፡፡ ቆመው አይጠብቁም፡፡ እናም ከእጅ እንዳመለጠ ስኒ አቅልሎ ማየት አገሪቱን ለመቀየር ‹‹ቆርጦ›› ከተነሳ መሥሪያ ቤት የሚጠበቅ አይደለም፡፡ በየመሥሪያ ቤቱ የሚያጋጥሙ የመልካም አስተዳደር ህፀፆች አገር አቀፍ ችግርን የመውለድ አቅም እንዳላቸው መገንዘብ ብልህነት ነው፡፡ ዛሬ ተስፋ የቆረጡ ተማሪዎች ነገ ስደትን ቢመርጡ፣ ዛሬ በዩኒቨርሲቲውና በተባባሪዎቹ ሰንካላ ምክንያት ትምህርት ያቆሙ ወጣቶት ከዚህ ዓይነት ዓይን ያወጣ ማታለል አንደበት በሌለው ባህር መበላት ይሻላል ብለው ቢወስኑ ማንም አይጠቀምም፡፡ ተቋሞቻችን አገር ወዳድ ዜጎችን የሚያፈሩ እንጂ በማጭበርበር ገብተው፣ በማጭበርበር የተካኑ ትውልዶችን መፈልፈያ መሆን የለባቸውም፡፡ ስለሆነም የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱም ሆነ የአዳማ ዩኒቨርሲቲ ቆም ብለው ሊያስቡ ይገባል፡፡ አጀማመራቸውን ለምን ፈተና በዛበት ብለው ራሳቸውን መጠየቅ ብልጠት ነው፡፡ የፖለቲካ ሰበብ ወንዝ ቀርቶ መንገድ እንደማያሻግር መረዳት አለባቸው፡፡ ፖለቲካ ላይ የሚለጠፍ ችግር የጧት ጤዛ ነው፡፡ ሲያረፋፍድ የሚረግፍ፡፡ መፍትሔው ግልጽነትና ተጠያቂነት የተጎናፀፈ አሠራር ማስፈን ነው፡፡ በሌላ በኩል ጉዳዩ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ የሚመለከታቸው የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ችግሩ በግልባጭ እስኪደርሳቸው መጠበቅ የለባቸውም፡፡ ባሉበት መንቀሳቀስና የጉዳዩን አሳባቢነት አጣርተው ችግሩ በቀጣይ የሚመጡ ተማሪዎች ላይ እንዳይደግም ማድረግ አለባቸው፡፡ የተመደበው በጀት የአገሪቱን ዕድገት በማፋጠን በኩል በትክክል እየሰጡ መሆናቸውን ማጣራት፣ የተማሪዎቹ ክትትልና እርካታ ምን እንደሚመስል ማየት ይገባል፡፡ የዩኒቨርሲቲው የትምህርት ሥርዓት በሚሊዮኖች ብር የሚቆጠር ችግር እንደተተበተበው የፋይናንስ ሥርዓት ከመዝረክረኩ በፊት ሁለት ጊዜ ማሰብ ከትናንት አዙሪት መውጣት ነው፡፡ አለበለዚያ በትምህርት ሚኒስቴር ሥር ካሉ ዩኒቨርሲቲዎች በምን ተለየና ራሱን ችሎ ለመቆም መንግሥት ፈቀደለት የሚል ጥያቄ በአንድ ወቅት መጠየቁ አይቀሬ ይሆናል፡፡ እርግጠኛ ነኝ ያኔ ችግሩ የፖለቲካ ችግር ነው አይባልም፡፡ በመጨረሻም ትናንት በሊቢያ በረሃ ውስጥ ታስረው በመማቀቅ ላይ ላሉት ኢትዮጵያውያን እንደጮህን ሁሉ ዛሬ አማራጮቻቸውን በጠራራ ፀሐይ ተቀምተው ያለፈቃዳቸው በግዳጅ ያልፈለጉትን ትምህርት እንዲማሩ ለተፈረደባቸው ተማሪዎች የዜግነት ግዴታችንን ልንወጣላቸው ይገባል፡፡ በተለያዩ ምክንያቶች ትምህርት የሚያቋርጡ ተማሪዎች ቁጥር አሳሳቢ በሆነበት በአሁኑ ወቀት በዩኒቨርሲቲውና በሳይንስና ቴክኖሎጂ ውሳኔ አዝነው ትምህርታቸውን ለማቋረጥ የተገደዱ ተማሪዎች ሕይወት ሊከነክን ይገባል፡፡ ይህን ስናደርግ የመልካም አስተዳዳር ዕጦትን የማንሸከም መሆናችንን አስመሰከርን ማለት ነው፡፡ መልካም አስተዳዳር ከሰማይ የሚወርድ ህብስተ መና አይደለም፡፡ በየረጃው ያሉ ኃላፊዎች የልጆቻቸውና የወገኖቻቸው በስቃይ የተሞላ ሕይወት አሳስቧቸው ትክክለኛውን ውሳኔ የሚሰጡበት የህሊና ፍርድ እንጂ! ከአዘጋጁ፡- ጽሑፉ የጸሐፊውን አመለካከት ብቻ የሚያንፀባርቅ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

Standard (Image)

መንግሥት በአግባቡ ሥራውን የሚያከናውነው ራሱን ሲያፀዳ ብቻ ነው

$
0
0

በልዑል ዘሩ

ሪፖርተር ጋዜጣ ቅጽ 21 ቁጥር 1686 ሰኔ 19 ቀን 2008 ዕትም እጄ ገብቶ ነበር፡፡ ጋዜጣው እንደተለመደው ሁሉ ገዥው ፓርቲ ኢሕአዴግን ‹‹የቤት ሥራዎችህን በአግባቡ ከውን!›› ሲል አጥብቆ ያሳሰበበትን ርዕሰ አንቀጽ ይዟል፡፡ በመልካም አስተዳደር ችግሮች፣ ከሕዝብ ጋር ስለመታረቅ፣ መንግሥታዊ የአፈጻጸም ብቃት፣ ድርቅና የጎርፍ አደጋ፣ እንዲሁም የኢትዮ ኤርትራ ግጭት ላይ ያተኮሩት ምክረ ሐሳቦች ልባም ከተገኘ ብዙ የሚያሠሩ ጭብጦችን ይዘዋል፡፡

እኔም በግል እምነቴ ከእነዚህ ነጥቦች ጋር የተሳሰሩና የተለዩም ቢሆኑ የመንግሥት የቤት ሥራዎች ናቸው የምላቸውን ነው ለመተንተን የወደድኩት፡፡ እነዚህን ወቅታዊ ፈታኝ ሁኔታዎች መንግሥት አያውቃቸውም የሚል መነሻ ባይኖርም፣ ተግባር ገብቶ በግልጽነትና በድፍረት መከወን ላይ ያለውን እግር መጎተት ግን ያቁም፣ ያስተካክል በሚል ሥሌት ነው የምሞግተው፡፡

የመልካም አስተዳደር ጉዳይ

የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዓመቱ መጨረሻ ስብሰባ ላይ ሲናገሩ፣ ‹‹መልካም አስተዳደር በአንድ ጀንበር የሚረጋገጥ አይደለም፡፡ ዘንድሮ ግን ጉዳዩን አጀንዳ አድርገን ትግል በመጀመራችን ቢያንስ ሙስና፣ ብልሹ አሠራርና ደካማ የአገልግሎት አሰጣጥ እንዳይባባስ አድርገናል፡፡ ለቀጣይ ንቅናቄም መነሻ አሠራር መዘርጋት ጀምረናል፤›› ብለዋል፡፡

የዘንድሮ የመልካም አስተዳደር ‹‹ትግል›› በአዲስ አበባ፣ በአማራ፣ በድሬዳዋ፣ በኦሮሚያ፣ በትግራይና በደቡብ ክልሎች ብቻ ከአምስት ሺሕ በላይ መካከለኛና ዝቅተኛ የመንግሥት መካከለኛና ዝቅተኛ ሹመኞችን ከኃላፊነትም አስነስቷል፡፡ ከእነዚህ መካከል ወደ ወህኒ የተወረወሩም አሉ፡፡ ግን ድምር ውጤቱ ምን አስገኘ? ትግሉስ ምን ደረጃ ላይ ቆሟል መባል ይኖርበታል፡፡

አንዳንድ ተገልጋይ ዜጎችና ባለሀብቶች እንደሚናገሩት አሁንም በአንዳንድ መሥሪያ ቤቶች ሌብነቱና መደራደሩ አለ፡፡ (በተለይ መሬት፣ ገቢ፣ ንግድና ብቃት ማረጋገጥ…) የመሳሰሉት ዘርፎች ላይ ‹‹የሽያጭ ማጣሪያ›› የሚመስል መቀባበል እንደ ደራ ነው፡፡ በእርግጥ ለዚህ ችግር አለመቀረፍ ጉቦ አቀባዩ የኅብረተሰብ ክፍል ዋነኛ ተጠያቂ መሆኑ ባይቀርም፣ የሕዝብ ሀብት ቅርጥፍ አድርገው በልተው በሞቀ ሁኔታ የሚኖሩ ባለሥልጣናት ሁኔታ ሌላውንም እንዳደፋፈረው ይገመታል፡፡

ከመንግሥት ሥልጣናት ጋር ዝምድና፣ ሽርክናና ቅርርብ ምክንያት የሚገኙ የጨረታ ሥራዎች፣ የመሬት፣ የቤት፣ የብድር አቅርቦትና መሰል ‹‹ምቹ ሁኔታዎች›› ሁሉ የፍትሐዊነት ተጠየቅን ያስነሳሉ፡፡ ለእነዚህ ከሕዝብ ዓይንና ጆሮ ያልተሸሸጉ ድርጊቶች ‹‹ለምን!?›› የሚል ሞጋችና ታጋይ ከጠፋ ውርደትን የሚያስከትሉ ናቸው፡፡

የመልካም አስተዳደር ትግል መጀመርን በማሳበብ የውሳኔ ሰጪነት ፍርኃት ስለመንገሡም ይነገራል፡፡ ጥቃቅኑ ውሳኔ ሁሉ በኮሚቴና በስብሰባ ከመፈጸም አንስቶ ቀን ከሌት በግምገማ ተጠምዶ መዋል መደበኛ ሥራው ላይ የሚያሳድረው ጫና ቀላል አይሆንም፡፡ ከዚሁ ባልተናነሰ የማሻሻያ ዕርምጃው ግለትና ጥንካሬም ቢሆን ከቦታ ቦታ (ከክልል ክልል) የተለያየ ነው፡፡ በእያንዳንዱ የሥራ ኃላፊና ፈጻሚ ውስጥ ያለው የባለቤትነት ስሜትም ቢሆን የነጠፈና የተቀዛቀዘ ሆኖ ይታያል፡፡

እዚህ ላይ በጥብቅ መፈተሽ ያለበት የሲቪል ሰርቪሱ የመፈጸምና የማስፈጸም አቅምና ጥንካሬ ጉዳይ ነው (ይህ ነጥብ በሪፖርተር ርዕሰ አንቀጽም ላይ ተነስቷል)፡፡ ከፌዴራል እስከ ወረዳና ቀበሌ ባሉት የመንግሥት መዋቅሮች ጠንካራና ተወዳዳሪ ሙያተኛና የሥራ ኃላፊዎች ሊኖሩ ይገባል፡፡ የአገር ፍቅር ስሜት (ከመንደርተኝነትና ቡድንተኝነት የፀዳ) እና ሥነ ምግባርም ወሳኝ ጉዳዮች ናቸው፡፡

እነዚህ እውነታዎች መጓደላቸውን በርካታ ማሳያዎች መጥቀስ ይቻላል፡፡ የዋና ኦዲተር ሪፖርት የዘረዘራቸው ተቋማትና የሕዝብ ሀብት፣ በስኳር ኮርፖሬሽን፣ በውኃና መስኖ፣ በቤቶች ልማት፣ በጥቃቅንና አነስተኛ ዘርፍ የቆጠራና የምርመራ ውጤቶች ላይ የታየውን ገመና ታዝበናል፡፡ እንደ አገር ‹‹ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ›› በሚመስሉ ሪፖርቶች እየተጀቦኑ በጥቂት ታታሪ መሪዎች ጥረት ብቻ አገርን ለመቀየር ማሰብ የሚሆን ጉዳይ አይደለም፡፡ መጨናገፉም አይቀርም፡፡

ከእነዚህና ከሌሎች በርካታ እውነታዎች አንፃር መልካም አስተዳደርን ይበልጥ ለማጎልበት ገና ብዙ ሥራ ያስፈልጋል፡፡ የሰው ለውጥ ብቻ ሳይሆን የሥርዓት ማሻሻያ፣ የፖሊሲ ክለሳ ካስፈለገም መታየት አለበት፡፡ የአሿሿምና የምደባው ጉዳይም ከጠባቡ ክብ (Circle) ወጥቶ በአገራዊ ስሜት ወቅቱና መድረኩ የሚጠይቃቸውን ሰብዕናዎች እንዲያስብ ካልተደረገ፣ እየተቧደነ የመዝረፍንም ሆነ ሕዝብ የማስመረሩን በረራ የሚገታ ፍሬን መያዝ የሚቻል አይሆንም፡፡

ሕዝብ ይደመጥ፣ ይሳተፍ

ኤሕአዴግ (አሁን ያለው መንግሥት) ይመሰገንባቸው ከነበሩ ነገሮች አንዱ ሕዝብ የማማከርና የማሳተፍ ጥረት የማያደርግ መሆኑ ነበር፡፡ ይህ በተለይ ከትጥቅ ትግሉ አንስቶ እስከ ምርጫ 97 ድረስ ‹‹የተሻለ›› ነበር የሚሉ ሰዎችን አዳምጣለሁ፡፡ ከዚያ ወዲህ ግን መንግሥት ወደ ሕዝብ የሚወርደውና የሚያማክረው ለምርጫ ሰሞን ብቻ ነው ይባላል፡፡ ይህን ለማረጋገጥም አስገዳጅና የተፅዕኖ ውሳኔዎችን ‹‹በመጫን›› ጭምር ሕዝብ ላይ የሚያሳርፈው ምርጫው ካለፈ ከጥቂት ወራት አንስቶ መሆኑ ነው፡፡

ለአብነት ያህል ባሳለፍነው በጀት ዓመት በኦሮሚያ ክልል የልተገመተ የሕዝብ ቁጣ ቀስቅሶ ሥርዓቱን ጥያቄ ውስጥ ያስገባው ጣጣ የመጣው በሕዝብ ውይይት ባልዳበረው የ‹‹ጋራ ማስተር ፕላን›› ጉዳይ ነው፡፡ ራሱ የክልሉ መንግሥት ባለሥልጣናትና የኦሕዴድ ካድሬዎች ባላመኑበትና በጥርጣሬ ባዩት ፕላን ‹‹ትግበራ›› ስም ሕዝቡ እስከ መገንፈል ደርሷል፡፡ ሕይወትና ንብረት ጠፍቷል፡፡

በተመሳሳይ ወቅቶች በአዲስ አበባ ከተማና ዳርቻ የሚገኙ ሕገወጥም ይባሉ ሕጋዊ ነዋሪዎችን የማስነሳቱ ሥራ ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ በተለይ በመንግሥት መዋቅር ውስጥ በተወሸቁ ቀማኞች ጭምር ተታለው በሕገወጥ መሬት ላይ ግንባታ ያከናወኑና ሀብታቸውን ያፈሰሱ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ሁኔታ አሳሳቢ ነው፡፡ በእርግጥ መንግሥት ሕገወጥነትን የመከላከል ከፍተኛ ኃላፊነት እንዳለበት ይታወቃል፡፡ ግን ገና በእንቁላሉ ጊዜ ሕዝቡን እያሳተፈ ሊያርመው በተገባ ነበር፡፡

ከቅርብ ወራት ወዲህ በሰሜን ጎንደርና በትግራይ ክልል ድንበርተኛ ሕዝቦች መካከል የተነሳው የ‹‹ወልቃይት ጉዳይ››ም ቢሆን የተፍታታ ምክክርና መተማመን የተደረገበት አይመስልም፡፡ ከዚያ ይልቅ የፖለቲካ ትርፍ ያስገልኛል ያለው ሁሉ እየተነሳ ላገኘው ማኅበራዊ ድረ ገጽና ሚዲያ ሲረጨው የሚውለው ‹‹ወሬ›› የሕዝቡን ቀልብ እየሰነገው ይገኛል፡፡ ወልቃይትና አካባቢውን አንድ የልማት ኮሪደር አድርጎ የትግራይም ይሁን የአማራ ክልል ሕዝብ በጋራ እንዲጠቀሙበት ማድረግ ሲቻል፣ ‹‹በእኔ ነው›› ንቁሪያ ይኼ ሁሉ መከራር የሥርዓቱን አደጋ ላይ መውደቅ አመላካች ነው የሚሉም እየበዙ ነው፡፡

አገሪቱ ባፀደቀችው ሕገ መንግሥት መሠረት የሚከናወን የማንነት ጥያቄ፣ የፖለቲካ ምኅዳር ማስፋት፣ ሰላማዊ ሠልፍ የማድረግ፣ የሐሳብ ነፃነት፣ የመደራጀት ጉዳይ … መመለስ ያለባቸው በሕገ መንግሥቱ መሠረት ብቻ ነው፡፡ በዚህ ረገድ ክልል ከክልል የጋራ አረዳድና ውሳኔም ያለ አይመስልም፡፡ ጣልቃ ገብነትና ተፅዕኖ ያለበት አካሄድም እንዳይኖር ጥንቃቄ መደረግ ይኖርበታል፡፡

‹‹ኢትዮጵያ ውስጥ ዴሞክራሲን የማሳደጉ ጉዳይ የህልውና ጉዳይ ነው›› ሲባል አፍአዊ ሊሆን አይገባም፣ መሆንም አይችልም፡፡ ከ80 በላይ ብሔሮችና ቋንቋዎች፣ በርከት ያሉ የሃይማኖት ዓይነቶች፣ ብትንትኑ የወጣ አመለካከትና ፍላጎት እንዲሁም የታሪክ መጓተት በረበበበት ሁኔታ ብድግ ብሎ ‹‹ቻይናን›› ልሁን ማለት የሚመከር አይደለም፡፡ ያውም ባለፉት 25 ዓመታት ዴሞክራሲን እየተለማመደ የመጣ ዜጋ ባለበት፣ የዓለም መረጃ ሁኔታም ሁሉን እንደ ወንፊት የሚያንዠቀዥቅ በሆነበት አግባብ ፈጽሞ ሊታሰብም አይችልም፡፡

ይህ ቢሆንም ልማትን ለማምጣት በመታተር ብቻ የዴሞክራሲ መረጋገጥን ማሰብ ያዳግታል፡፡ ገንዘብና መሣሪያ ያለው መንግሥትና ገዢው ፓርቲ ብቻ ‹‹ይደመጥ›› ወደሚል ዝንባሌ እንዳይኬድም ዙሪያ ገባውን ማጤን ያስፈልጋል፡፡ በውጭም ሆነ በአገር ውስጥ በየጥጋጥጉ ያለውን አስተሳሰብ ንፋስ እንዲመታው ማድረግ፣ ሕዝብ አቋሙን እንዲገልጽበት ማስቻል ከሥርዓት መሻገት ያድናል፡፡ የፖለቲካ መታደስና የመነቃቃት አማራጭ መኖር አለበት፡፡

ሕዝብ በሚከፍለው ግብር፣ ለልማት በሚያወጣው ገንዘብ፣ ጉልበትና ዕውቀት ላይ ሁሉ እየተማመነ መኖር ይገባዋል፡፡ ‹‹የግዳጅ ቋንቋ›› የተቀላቀለባቸው የአንዳንድ የመንግሥት ኃላፊዎች ንግግርና ተግባራት ‹‹የደርግነት›› ባህሪዎች ናቸው፡፡ ተሳዳቢነትና ኃይል መድረሻቸው ጥላቻና መቃቃር ነው፡፡ ፍቅር፣ አንድነት፣ ሰላምና እኩልነትን መስበክ ብቻ ሳይሆን በተግባር ማሳየት የቻሉ መንግሥታትና የመንግሥት መሪዎች ይበልጥ ሕዝባዊና ተፈላጊ ናቸው፡፡ ከእነዚያ መማር ሕዝብ አድማጭና አሳታፊነትን ያጎናፅፋል፡፡

የአገር ሉዓላዊነትና ቀጣናዊ ጉዳይ

አገራችን ያለችበት ቀጣና ለሽብርተኝነት አደጋ የተጋለጠ፣ በቀይ ባህር አካባቢ ለጦር የታጠቁ አገሮች የፍጥጫ የስበት ማዕከል፣ የዓባይ ተፋሰስ የቅርብ ጊዜ ትኩሳት፣ አገሪቱን እንቅልፍ የማያስተኛ መሆኑ ተደጋግሞ ተወስቷል፡፡ ከዚህ አንፃር ከመካከለኛው ምሥራቅ እስከ ምዕራባውያን፣ ብሎም ከሩቅ ምሥራቅ እስከ ሰሜን አፍሪካ አገሮች በበጎም ሆነ በመጥፎ ትኩረት የሚስብ አካባቢ ውስጥ ነው ያለነው፡፡

ኢትዮጵያ ደግሞ ካላት ስትራቴጂካዊ ጂኦፖለቲካ ባሻገር እስከ 100 ሚሊዮን እየተቃረበ ባለው ሕዝቧ፣ እስከ ትሪሊየን ብር አጠቃላይ ምርት ማካበት የጀመረች መሆኗ ትኩረትን ይስባል፡፡ ለ15 ዓመታት ባለሁለት አኃዝ ብቻ ሳይሆን ከዓለም ፈጣን ዕድገት ተርታ የተመደበው የኢኮኖሚ ጉዞ አባባሉን ያረጋግጣል፡፡ አገሪቱ በንግድ፣ በኢንቨስትመንትና በቱሪዝም መስክ ሌላውን ዓለም ለመሳብ የምትከተለው ሥልትም ሆነ በአብዛኛው ‹‹በሰጥቶ መቀበል›› መርህ የሚመራው ዲፕሎማሲ፣ ከየአቅጣጫው ብዙዎችን የመሳቡ ሚስጥርም ይኼው ነው፡፡

ይህን ብሩህ የሚመስል ተስፋ የሚያደበዝዙ በቅርብ ርቀት ቀውሶች ግን አሉ፡፡ አንደኛው የኢትዮ-ኤርትራ የድንበር ፍጥጫና መቆራቆስ ነው፡፡ የተለያዩ የፖለቲካ ተንታኞች ደጋግመው እንደሚወተውቱት ከኤርትራ መንግሥት ጋር የተፈጠረው አለመግባባት ዘላቂ መፍትሔ ሊያገኝ ይገባል፡፡ ካልሆነ ግን ‹‹እኔ ከሞትኩ …›› ባዩ ሻዕቢያ ኢትዮጵያን እንደ ጠላት ለሚመለከት የትኛውም ወገን መሸጋገሪያና አጋር እየሆነ አገሪቱን ከማድማት የሚቆጠብ አይደለም፡፡ ይኼንን በተለያዩ ጊዜያት ከሳዑዲ ዓረቢያና ከኢራን ጋር ባሳየው ሽርክና ብቻ ሳይሆን በዚህ ክፍለ ዘመን ሥርዓቱን በነፍጥና በኃይል ለማውረድ የሚፋለሙ ዜጎችን በማስታጠቅና በማሰማራት አሳይቷል፡፡ የፊት ለፊት ትንኮሳ የሞከረባቸው፣ የዕገታና የዘረፋ ድራማዎችን የተወነባቸው ጊዜዎች እንደነበሩም በመንግሥት በኩል ተገልጿል፡፡ ስለዚህ በቀዳሚነት ይህ ‹‹ተከድኖ ይብሰል›› የተባለ የኢትዮ-ኤርትራ አጀንዳ ሊቋጭ ይገባል፡፡

ሌላኛው ተግባር የኢትዮ-ሶማሊያ ጉዳይ ነው፡፡ እርግጥ ነው ኢትዮጵያ በሶማሊያ በኩል እየመጣ የነበረውን ግብረ ሽብርና ጥቃት ለመመከት ብሎም የሶማሊያን የሽግግር መንግሥት በእግሩ ለማቆም ላለፉት ስምንት ዓመታት ገደማ ከፍተኛ መስዋዕትነት ከፍላለች፡፡ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅትና በአፍሪካ ኅብረት ዕውቅና ጭምር ጦሯን አስገብታም እስካሁንም አላወጣችም፡፡

ይህ ታሪካዊ ሁነት ግን መቋጫ ሊያገኝ ይገባል፡፡ አንደኛው የአገራችን ወታደሮች እስካሁንም ካልቆመው ጥቃትና ግብረ ሽብር ጉዳት መጠበቅ አለባቸው፡፡ ሌላው ግን ለዓመታት በአንቀልባ ተይዞ በእግሩ ያልቆመው የዚያች አገር ሰላም ሕዝቡን በንቃት ባሳተፈ መንገድ እንዲፈታ ዕድሉን ለእነሱው መስጠት አስፈላጊ ይሆናል፡፡ ሸማቂውን ወገን የሚደገፉ ሶማሊያውያን መኖራቸውም አይቀርምና ከአገራችን ጋር ቂምና ቁርሾ እንዳይዙ አድርጎ ፋይሉን መዝጋትና ጦሩ በአገሩ ሆኖ ሉዓላዊነቱን እንዲያስከብር መታሰብ ይኖርበታል፡፡

የደቡብ ሱዳን ውስጣዊ ትርምስ ማገርሸቱም ለኢትዮጵያ መንግሥት ሌላ የቤት ሥራ ይዞ መጥቷል፡፡ አንደኛው ከወራት በፊት በድንበር አካባቢ በሚኖሩ ዜጎች ላይ የደረሰው ዓይነት የግድያና የዘረፋ ተግባር እንዳይፈጸም ጥበቃ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ ሌላኛው ግን የደቡብ ሱዳን መንግሥት ወደተበታተነና የከሰረ ‹‹መንግሥት›› ደረጃ ከወረደ ሕገወጥ ስደት፣ ሕገወጥ መሣሪያ ዝውውርና ተዛማጅ ወንጀሎች መናኸሪያ የመሆን ዕድል ነው ያለው፡፡

ይህንን ችግር ለመቅረፍ የኢትዮጵያ መንግሥት የጀመራቸው የዲፕሎማሲና የሰላም ማስከበር ጥረቶች አሉ፡፡ ግን ከዚህም በላይ ዓለም ችግሩን እንዲያውቀው ማድረግና የጋራ ድንበሩን በተጠናከረ አኳኋን መጠበቅ ያስፈልገዋል፡፡ በነገራችን ላይ ‹‹ኢትዮጵያ የአፍሪካ ትልቋ የስደተኞች መሰብሰቢያ›› ከሚለው ሞገስ ጀርባም ከየአገሩ የሚመጣው ስደተኛ ጎርፍ በአገር ደኅንነት፣ በኑሮ ውድነትና በሕዝቦች የዕለት ተዕለት ኑሮ ላይ ያለው ተፅዕኖ ሊፈተሽና ሊጤን ይገባዋል፡፡

የመጨረሻው መመለስ የለበት የጎረቤት አገር የቤት ሥራ የኢትዮ-ሱዳን ድንበር አጀንዳ ነው፡፡ የኢሕአዴግ ተቃዋሚዎች ‹‹የኢትዮጵያ መንግሥት ለሱዳን መሬት ሰጠ፣ ለመልካም ወዳጅነት ሲባል የአገር ጥቅም አሳልፎ ሰጠ…›› ሲሉ ይደመጣል፡፡ ይህን አባባል መንግሥት ‹‹ሐሰት ነው›› ቢልም ሱዳን ትሪቡንን የመሳሰሉ የካርቱም ጋዜጦች ግን ብዙ ሐተታዎችና ዜናዎችን ጽፈውበታል፡፡ የሁለቱ አገሮች የጋራ ድንበር ኮሚሽንም ያዝ ለቀቅ እያደረገ ጉዳዩን ለዓመታት እየፈተለው መጥቷል፡፡

ምንም ተባለ ምን ግን መንግሥት በታሪክ የሚያስወቅሰውን ብቻ ሳይሆን፣ የአገሪቱን ጥቅም አሳልፎ የሚሰጥ ዕርምጃ ሊወሰድ እንደማይችል ይታመናል፡፡ ሥራው የሚፈልገውን ጥንቃቄ ማድረግም ተገቢ ይሆናል፡፡ ከዚህ ተነጥሎ የማይታየው የታላቁ ህዳሴ ግድብና የኢትዮ-ሱዳን-ግብፅ ከላይ ከላይ ለስላሳ የሚመስል ግንኙነት እንደ ዓሳ አበላል በብልኃትና በዕውቀት መያዝ ይኖርበታል፡፡ ይኼኛው የቤት ሥራም ቢሆን ቀላል ግምት የማይሰጠው ከባድ የአገር ሸክም ነው፡፡

በአጠቃላይ መንግሥት የቤት ሥራዎቹ ብዙ ናቸው፡፡ ዋና ዋናዎቹን ጠቅልለን ያነሳናቸው ብቻም አይደሉም፡፡ እነዚህን ጉዳዮች ግን ብቻውን ለመወጣት መሞከር በአንድ እጅ ማጨብጨብ ነው፡፡ ስለሆነም በየደረጃው ሕዝቡ በአገሩ ጉዳይ ይሳተፍ፣ ይምከር፣ ይወስን፡፡ ራሱን ካሸሸውና ከቀበረው ፖለቲከኛ በስተቀር ወደ ውይይት መምጣት የሚሻውም ይደመጥ፡፡ የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብና ወዳጅ አገሮች ምክርም በፋይዳው ልክ ይተግብር፡፡ ግን እነዚህን ሁሉ ተግባራት በአግባቡ ማከናወን የሚቻለው መንግሥት ራሱን ሲያፀዳ ብቻ ነው፡፡

ከአዘጋጁ፡- ጽሑፉ የጸሐፊውን አመለካካት ብቻ የሚያንፀባርቅ ሲሆን፣ ጸሐፊውን በኢሜይል አድራሻቸው Lzerugmail.comማግኘት ይቻላል፡፡ 

 

Standard (Image)

ግጭቶች የሚቆሙት ዴሞክራሲያዊ ውይይቶች ሲለመዱ ብቻ ነው

$
0
0

ኢትዮጵያ ውስጥ ዓይናችን የሚያየው ዕድገት፣ ተስፋ ሰጪ ለውጥና አበረታች የኢኮኖሚ ትራንስፎርሜሽን አለ፡፡ በዚያው ልክ በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግጭት፣ አለመግባባት፣ የሰው ሕይወትና የንብረት ውድመት እየተከሰተ ነው፡፡ ፖለቲካው ተረጋግቶ ከርሟል ሊባል አይችልም፡፡ ይልቁንም በበርካታ አካባቢዎች ነውጦች በስፋት ታይተዋል፡፡

በቅርቡ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረበው የተጣራ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ጉዳይ ሪፖርት ብቻ፣ በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች ከ300 በላይ ያልታጠቁ ዜጎች ሕይወት አልፏል፡፡ ከአሥር በላይ የፀጥታ ኃይል አባላት ሕይወትም እንዲሁ፡፡ በአካል ጉድለት፣ በንብረት ውድመት የሚጋለጠው ችግርም ከተለመደው ጊዜ የባሰ ነው፡፡ መደማመጥ ጠፍቶ ግጭት በነገሠበት በዚህ ወቅት መፍትሔ ካልተፈለገ አያያዛችን አያምርም፡፡

በዚሁ ዓመት በጋምቤላ ክልል፣ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ቡለን አካባቢ፣ በደቡብ ክልል በኮንሶ ልዩ ዞን የተከሰቱ ሌሎች ግጭቶች የሰው ሕይወት አጥፍተዋል፡፡ ቀላል የማይባል የንብረት ውድመትን፣ የዜጎችን መደናገጥና መፈናቀልን አስከትለዋል፡፡

ይኼው አደጋ አሁንም አልበረደም፡፡ ከሰሞኑ በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን ጎንደር፣ ደባርቅና ዳባት ከተሞች ላይ ከፍተኛ ውጥረት ነግሷል፡፡ በተለይ በጎንደር ከተማ የዜጎችንና የፀጥታ ኃይሎችን ሕይወት የቀጠፈ ግጭት ተከስቷል፡፡ ከሁሉም በላይ በማንነታቸውና በብሔራቸው ምክንያት የግጭቱ ሰለባ የሆኑ የአገሪቱ ዜጎች ንብረት ወድሟል፡፡ ተዘርፍል፡፡ ይህ ከፍተኛ ሊባል የሚችል የማንቂያ ደወል ለኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊያንን ምንን ይነግራል? ተብሎ በጥልቀት ምክክር ካልተጀመረበት ከፍተኛ አደጋ ከፊታችን መደቀኑ አይቀሬ ነው፡፡ ስለዚህ መነሻውን አንዳንድ በአንድ መመልከት ያስፈልጋል፡፡

ፌዴራሊዝሙ ለጥላቻ አቀጣጣዮች እየዋለ ነው

አስከፊው የደርግ አምባገነናዊ ሥርዓት ከተወገደ በኋላ ሥልጣን የያዘው ኢሕአዴግ መራሽ መንግሥት ፌደራላዊ ሥርዓትን ለማስፈን ሞክሯል፡፡ ይሁንና ይህ ሥርዓት ብሔርና ቋንቋን መሠረት አድርጎ የተገነባ እንደመሆኑ በአገሪቱ አንድነት ላይ የፈጠረው ጫና አለ የሚሉ ወገኖች አሉ፡፡ በተቃራኒው ደግሞ ለዘመናት በአሀዳዊ ሥርዓት ታስረው የቆዩትን ብሔር ብሔረሰቦች የእኩልነት መብት ይበልጥ አጎናጽፎአቸዋል የሚሉም ይገኙበታል፡፡

እውነታው ግን ከዚህ ፌደራል ሥርዓት ትግበራ በኋላ የብሔር ብሔረሰቦች መፋጠጥና መጠራጠር ያለጥርጥር ተባብሷል፡፡ በቅርቡ አንድ ታዋቂ ብሎገር ‹‹አካሄዳችንን በጊዜ ስላላረምነው ምድራችን ሩዋንዳ ሩዋንዳ ስላለመሽተቷ ምን ዋስትና አለን?›› ማለቱን ያጤኑዋል፡፡

በአንድ በኩል በብዙ መስዋዕትነትና ትግል ይህን የአገሪቱ የለውጥ ተስፋ በግንባር ቀደምነት ያመጣው የትግራይ ሕዝብ በጅምላ ‹‹ወያኔ›› እየተባለ ነው፡፡ ጉዳቱ ስም ስለወጣለት አይደለም፡፡ ይልቁንም ከሥርዓቱ ዋነኛ ተጠቃሚ እንደሆነ ከመደረጉ ባሻገር፣ የሌላውን ሕዝብ ጥቅምና ሀብት በልዩነት እንደሚወስድ ተደርጎ ፕሮፓጋንዳ ይነዛበታል፡፡ ለዚህ ደግሞ ዋነኞቹ አቀንቃኞች ከሥርዓቱ ጋር የመረረ ፀብ አለን የሚሉ ፅንፈኛ ወገኖች ናቸው፡፡ አንድን ሕዝብ ለይቶ በጠላትነት መፈረጅ ፀረ ዴሞክራሲ አመለካከት ከመሆኑም በላይ፣ ኃላፊነት የማይሰማቸው ግብዞች ተግባር ነው፡፡

በሌላ በኩል በፌደራል ሥርዓቱ ‹‹መብትህን አስከብርልሃለሁ›› ቅስቀሳ ስም፣ የቀድሞዎቹ ሥርዓቶች የወጡበት ማኅበረሰብ የጥላቻ ቅስቀሳ ተካሂዶበታል፡፡ በተለይ አንዳንድ በመንግሥትና በገዥው ፓርቲ ውስጥ ተወሽቀው ‹‹አማራ›› እና ‹‹ነፍጠኛ›› የሚባለውን መገለጫ እያቀለቀሉ በንፁኃን ዜጎች ላይ ሳይቀር ጉዳት እንዲደርስ ያደረጉት ያልተቋረጠ ቅስቀሳ ከፍተኛ ዋጋ አስከፍሏል፡፡

በደቡብ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች ለሚነሳው ግጭት መንስዔውም ‹‹ማንነት›› እና ጥቅም ነው፡፡ ሲዳማው ከወላይታው፣ ኮንሶው ከጋሞው የሚገናኝበት ቤተሰባዊ ገመድ እየላላ በሥልጣን፣ በኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ሒሳቡን ሲያወራርድ ማየት በእጅጉ አስከፊና አሳዛኝ ነው፡፡

ከዚህ አንፃር አሁን ኢትዮጵያ የምትከተለው ፌደራላዊ ሥርዓት በሁለት መንገዶች ችግር ላይ ወድቋል፡፡ በአንድ በኩል ሥርዓቱን የተቃወሙ ያሉ የውስጥም ሆኑ የውጭ ኃይሎች ጠባብነትን ዋነኛ የፖለቲካ መሣሪያ ማድረግ ጀምረዋል፡፡ ይህ ከዚህ ቀደም በአሀዳዊነትና ‹‹ትምክህት›› ሲወቀሱ የነበሩ የፖለቲካ ኃይሎች (ኅብረ ብሔራዊ አደረጃጀቶችን) ሳይቀር እየሳበ ሲመስል ይበልጥ ያስደነግጣል፡፡ ‹‹ኢትዮጵያ››ን አስቀድመው ብዙ የደከሙትን ሁሉ የብሔር ካባን ደርበው እንዲባዝኑ ማድረጉ በራሱ የሚፈጥረው ነገር አለ፡፡

በሌላ በኩል ራሱ መንግሥታዊ ሥርዓቱ ከብሔራዊና አገራዊ ይልቅ አካባቢያዊና ብሔረሰባዊ ትርጉሙ ላይ ለ25 ዓመታት የዘለቀበት መንገድ ችግር ላይ ወድቋል፡፡ ማንነትና ብሔር ይጨፍለቅ እንኳን ባይባል አገር ከምትባለው የጋራ ሀብት በላይ መቀንቀኑ፣ በማንነት ላይ የተመሠረተ የብሔራዊ መገለጫ መሰጠቱ፣ ከዕድርና ከማኅበር አንስቶ ባንኩ፣ ፓርቲው፣ አክሲዮኑ፣ ደብሩና አጥቢያው ሁሉ ብሔር ተኮር መሆኑ ቀስ በቀስ እየፈጠረ ያለው ፍጥጫ ከፍተኛ ነው፡፡

ከዚህ አንፃር የፌደራል ሥርዓቱ የቆመበት መሠረት በጥልቀት ከልብ መፈተሽ አለበት፡፡ ዛሬ በሕዝብም ይባል በፖለቲካ ፓርቲዎች ደረጃ የሚታየው የመነጣጠልና የጥላቻ ዝንባሌ ነገ በክልል መንግሥታት ደረጃ ዕውቅና ቢሰጠውስ? በራሱ በመንግሥት ሥልጣን ላይ ባሉ አካላት የሐሳብ ክፍፍል ቢያስነሳስ? እነዚህ ሁሉ መተንበይ ያለባቸው ክስተቶች ናቸው፡፡ ዛሬ እንደ ዋዛና ቀላል የሚመስሉ ጉዳዮች ሁሉ ነገ በተለያዩ አገሮች እንደታዩ አስከፊ ክስተቶች መነሻ እንዳይሆኑም መሥጋት ተገቢ ነው፡፡

ከእነዚህ እውነታዎች አንፃር የፌደራል ሥርዓቱን እንከኖች መፈተሽ ተገቢ ነው፡፡ የጠባብነትና የትምክህት ዝንባሌውን መርምሮ መግደልም ተገቢ ይሆናል፡፡ ከሁሉም የፖለቲካ ኃይሎች ጋር በአገራዊ ጉዳይ ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ ምክክር መጀመርም ያስፈልጋል፡፡ ከሁሉ በላይ የሕዝቡን የመቻቻልና የኑሮ አንድነት መጠገን ተገቢና አስፈላጊ ነው፡፡ ለነገ የሚባል ሥራም አይደለም፡፡

የሕዝብ ጥያቄዎች በቂ ምላሽ ይፈልጋሉ

በመላው አገራችን በተለያዩ መንገዶች የሚነሱ የሕዝብ ጥያቄዎች በተለያዩ ምክንያቶች እንደሚነሱ ይታወቃል፡፡ እነዚህን ጥያቄዎች በሰላማዊና በዴሞክራሲያዊ መንገድ የመመለስና ዘላቂ መፍትሔ የመስጠት (በተቻለ መጠን) ጉዳይ ደግሞ፣ የመንግሥትና የገዥው ፓርቲ ዋነኛ ኃላፊነት ነው፡፡ የሁሉም የፖለቲካ ኃይሎችና የምሁራን ቀዳሚ አጀንዳ መሆን አለበት፡፡

ከዚህ አንፃር ባሳለፍነው በጀት ዓመት በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልል መንግሥት ‹‹ከዳር ዳር›› በሚባል ደረጃ የተነሳ የሕዝብ ጥያቄ በቂ መልስ አላገኘም፡፡ በአሁኑ ጊዜ ከሞላ ጎደል በክልሉ ምንም እንኳን ሁከትና አመፅ ጋብ ቢልም፣ የአዲስ አበባና (ፊንፊኔ) የአጎራባች ከተሞች ማስተር ፕላን፣ የባለሀብቶች የኢንቨስትመንት የመሬት ሊዝና የካሳ ጉዳይ አሁንም ብዙ ሥራ የሚጠይቅ ጉዳይ ነው፡፡

ከዚህ ጥያቄ ጋር በተያያዘ በተነሳ ሁከትም ይባል በሕዝባዊ እምቢተኝነት የተሳተፉ ዜጎች (በተለይ ወጣቶች) እንደታሰሩም ይታወቃል፡፡ እነዚህን ኃይሎች በሆደ ሰፊነት አስተምሮና መክሮ በጊዜ መፍታት ይገባል፡፡ በግርግሩ ለሞቱና ለተጐዱ ዜጎችም የፖለቲካ መጠቀሚያ እንዳይሆኑ የሚያደርግ የማነጋገርና የማካካስ ሥራ ያስፈልጋል፡፡ ይገባልም፡፡ ከሰሞኑ የቆሻሻ አወጋገድ ጋር እየተሰማ ያለው ችግርም በዴሞክራሲያዊ መንገድ መፍትሔ ያስፈልገዋል፡፡

የአማራና የትግራይ ብሔራዊ ክልል መንግሥታትና ያደናገረውና ሕዝቡንም ወደ ፍጥጫ እያስገባ ያለው ‹‹የወልቃይት የማንነት ጥያቄ›› ግልጽና የማያሻማ መፍትሔ ማግኘት ይኖርበታል፡፡ በተለይ የማንነት ጥያቄን በቀላሉ ለመመለስ የሚችለውና እየፈጸመ ለመጣው ኢሕአዴግ መራሹ መንግሥት ጉዳዩ የሚከብደው ሊሆን አይገባም፡፡

በአንድ በኩል ማንነትን ከሥልጣን፣ መሬትን ከመሰል ሀብት ጋር ማያያዝ ሊኖር ይችላል፡፡ በሌላ በኩል ለዘመናት አብሮ በኖረ ሕዝብ መሀል ሲቀነቀን የከረመው ብሔር ተኮር ቅስቀሳ ሰው ማንነቱን እንዲሻ ክፉኛ ሊገፋው እንደሚችል መታመን አለበት፡፡ ስለዚህ በትግራይ፣ በአማራ፣ በኦሮሚያም ሆነ በደቡብ ክልሎች የሚነሱ የሕዝብ የማንነት ጥያቄዎች መልስ የሚያገኙበት አልያም ጠንካራ ኅብረ ብሔራዊ አንድነት እንዲፈጠር ሥራው ከወዲሁ መጀመር አለበት፡፡

ምላሽ የሚሹት ጥያቄዎች ግን እነዚህ ብቻ አይመስሉም፡፡ ከዚህም በላይ ናቸው፡፡ በተለይ ከፖለቲካና ከዴሞክራሲ ምኅዳር ማስፋት ጀምሮ በፖለቲካ መዘዝ የታሰሩ ዜጎች፣ የተሰደዱና የተፈናቀሉ ሁሉ በአገራቸው ጉዳይ ያገባናል የሚሉበት መንገድም መከፈት አለበት፡፡ ኢሕአዴግ መራሹ መንግሥት በኢትዮጵያ የህዳሴ ጉዞ ውስጥ እየተጫወተ ያለውን ጉልህ ሚና ማስመር የሚችለውም በዚህ መንገድ ብቻ ነው፡፡

ግለሰቦች፣ ተቃዋሚዎችና ትክክልም ይሁንም አይሁንም ፕሮፓጋንዲስቶች ስህተት ሊፈጽሙ ይችላሉ፡፡ አክራሪና ጽንፈኛ ወይም አፍራሽ የሚባል አስተሳሰብም ሊያራምዱ ይችላሉ፡፡ መንግሥት ግን የሕዝብና የአገር ኃላፊነት አለበትና ሆደ ሰፊ፣ አስተዋይና አስታራቂ ሊሆን ይገባል፡፡ ለውይይት፣ ለድርድርና ሰጥቶ ለመቀበል በሩን ክፍት ማድረግም ኃጢያት ሊሆን አይገባም፡፡

ኢትዮጵያ በዚሁ መንግሥት ጥረት ዓለም አቀፍ ተሰሚነትን ይበልጥ አግኝታለች፡፡ ዲፕሎማሲያዊ ተቀባይነት ብቻ ሳይሆን ከሁሉም የውጭ ኃይሎች ጋር ለመደራደርና ለመወያየት የሚያስችሉ መርሆዎችንም አጥብቃ እንደያዘች ይታመናል፡፡ ይህንን ለአገሪቷ ሕዝቦች ጥያቄ ወይም ለኢትዮጵያዊያን ፖለቲከኞች ሐሳብ አለማዋል ግን ‹‹የውጭ አልጋ የውስጥ ቀጋ›› ሲባሉ የነበሩትን የቀደምት አገዛዞች ስያሜ የሚያላብስ ነው፡፡

የሕዝብ ጥያቄ በሁሉም ደረጃ ምላሽ ማግኘት አለበት ሲባልም ግጭት ስለተነሳና የአድማ ጥያቄ ስለሆነ ብቻ አይደለም፡፡ ይልቁንም የእያንዳንዱን ዜጋ ቅሬታ መንግሥት ሊመልስ ይገባል በማለት የሚቀርቡ የልማት፣ የመልካም አስተዳደርና የሰላም ጥያቄዎች ምላሽ ይፈልጋሉ፡፡ ባለሀብቱ በየትኛውም የአገሪቱ ጫፍ ዋስትናን ይሻል፡፡ ዜጎች ተንቀሳቅሰውና ሠርተው የመለወጥ መብታቸው ሊከበር ግድ ይላል፡፡

በአጠቃላይ አገራችን የሁላችንም ቤት ነች፡፡ በዘር፣ በቋንቋና በፖለቲካ አመለካከት እየተባላን መልሰን ወደ አዘቅት እንድንገባ አያስፈልግም፡፡ ከሁሉም በላይ ዜጎች የሚገለሉበት (Marginalization) እና የሚሸሹባት፣ አንዳንዶችም እንደፈለጉ የሚፈነጩባት አገር እንዳትሆን መሥራት ያስፈልጋል፡፡ ለዚህ ደግሞ ጊዜው ረፈደ ሊባል አይችልም፡፡ ሁሉም በጋራና በትጋት መነሳት ይጠበቅበታል፡፡ ከሁሉም በላይ ግን እዚህ አገር ዴሞክራሲያዊ ውይይት ሊለመድ ይገባል፡፡ እያቆጠቆጡ ያሉ ግጭቶች የሚቆሙት ዴሞክራሲያዊ ውይይቶች ሲለመዱ ብቻ ነው፡፡

ከአዘጋጁ፡- ጽሑፉ የጸሐፊዋን አመለካካት ብቻ የሚያንፀባርቅ ሲሆን፣ ጸሐፊዋን በኢሜይል አድራሻቸው Hirotdd@gmail.comማግኘት ይቻላል፡፡ 

             

Standard (Image)

የፌዴራል ሥርዓቱ ማሻሻያዎችን አይፈልግም!?

$
0
0

በያሲን ባህሩ

‹‹የፖሊሲ ማሻሻያ ማድረግን እንደ ሞት ሽረት የሚቆጥሩ መንግሥታት በተፈጠሩበት ቆዳ ተጠቅልለው የሚሞቱ ናቸው፡፡ አንድ አገር ወይም ሕዝብ የሚመራበት ፖሊሲ፣ ስትራቴጂዎችና ርዕዮተ ዓለማዊ ፍልስፍናዎች እንደ ተጨባጩ ዓለማዊ ሁኔታ ወይም ሕዝቡ ከደረሰበት የግንዛቤና የውጤት ደረጃ አንፃር መቃኘት አለባቸው፡፡ ይህን ማድረግ አለመቻል ነው ጉዞን የሚያደናቅፈው፤›› ይላሉ ቤንጃሚን ፍራንክሊን የተባሉ የሥነ ጽሑፍና የሥነ መንግሥት ሊቅ፡፡

ለዛሬ የጽሑፌ መግቢያ የአውሮፓዊው ሊቅ አባባልን የገለጽኩት ወድጄ አይደለም፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአገራችን እየታየ ከመጣው የመንግሥትና የሕዝብ አለመግባባት፣ ቀላል በማይባል ሁከትና ግጭት የተነሳ የሕዝብ ጥያቄ ብሎም ‹‹ጽንፈኛ›› የሚባለው የውጭ ተቃዋሚ ኃይል ይበልጥ እየተደመጠ መምጣት አሳሳቢ እየሆነ በመምጣቱ ነው፡፡

‹‹ይህ ታዲያ በዴሞክራሲ ሥርዓት ውስጥ ምን ችግር አለው? መንግሥት የጊዜ ጉዳይ እንጂ ውጤት ካላመጣ ተቀባይነት ሊያጣ ይችላል…›› የምትሉ ወገኖች ትኖራላችሁ፡፡ እኔ እንደ አንድ ዜጋ ሐሳቡን የማነሳው ግን ለ25 ዓመታት አገሪቱን በተለያዩ ውጣ ውረዶች ውስጥ አሳልፎ እዚህ ያደረሳት መንግሥት ሊቀየር ይችላል በሚል ሥጋት አይደለም፡፡ ይልቁንም ከረጅም ጊዜ የእርስ በርስ ጦርነት፣ ኋላቀርነትና ድህነት በኋላ ቀና ማለት የጀመረ ሕዝብና አገር ጅምር ጉዞ እንዳይደናቀፍ ነው፡፡

ከሁሉ በላይ በጭቆና ውስጥ እንኳን ለዘመናት ተቻችሎ፣ ተከባብሮና ተዋልዶ የኖረን የአንድ አገር ሕዝብ የሚነጣጥል አደጋ እንዳይሰነቀር ነው፡፡ በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየታየ እንዳለው ‹‹ቋንቋና ማንነት ተኮር የሆነውን ፌዴራላዊ ሥርዓት›› ተጠቅሞ ሕዝብን ከሕዝብ ለመነጠል የተጀመረውን ጽንፈኛና ዘረኛ አካሄድ ያለጥርጥር ቆም ብሎ ማሰብን ይጠይቃል፡፡ ሕዝቡ ለተዛባና አጥፊ አስተሳሰብ ተገዥ እንዳይሆን መንግሥትና ኃላፊነት የሚሰማቸው ወገኖች ሁሉ ጥረት እንዲያደርጉም ለማሳሰብ ነው፡፡

ኢትዮጵያ በሥራ ላይ ያዋለችው ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓት ‹‹ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ›› መሆኑ ብቻ ሳይሆን፣ የከተማ አስተዳደሮችን ጨምሮ አገሪቱን 11 ክልሎች እንዲኖራት አድርጓል፡፡ ከ700 በላይ ወረዳዎችና 17 ሺሕ የሚደርሱ ቀበሌዎች ከመኖራቸውም በላይ ከ80 የማያንሱ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦችን ዕውቅና የሰጠ ሥርዓት ነው፡፡

በዚህ ያልተማከለ መንግሥታዊ ሥርዓት በአገሪቱ ለዘመናት ተንሰራፍቶ የኖረው ‹‹አንድ አገር፣ ባንዲራ፣ ሃይማኖት፣ ቋንቋ…›› ወደሚል ጭፍለቃ ይደረግ የነበረው ጉዞ ተገትቷል፡፡ በዚህም ማንነታቸውና ታሪካቸው ተደፍቆ የኖሩ ሕዝቦች በነፃነትና በእኩልነት መንፈስ የመንቀሳቀስ ዕድል አግኝተዋል፡፡

ከሁሉ በላይ በራሳቸው ቋንቋ የመዳኘትና የመማር፣ እንዲሁም በየብሔሩ ተወላጆች የመተዳደርና የመመራት ጅምር ተፈጥሯል፡፡ ክልሎች በጋራ የገነቡት የፌዴራል መንግሥት (ከነስብጥር ችግሮቹ) አቋቁመው እየተዳደሩም ይገኛሉ፡፡

‹‹ይህ መንገድ ለ25 ዓመታት በማራመዱ የሕዝቦችን ፍትሐዊ ተጠቃሚነት፣ ተሳትፎና ኅብረ ብሔራዊ አንድነት አምጥቷል፤›› የሚሉ ወገኖች በአንድ በኩል አሉ፡፡ በሌላ ወገን ፌዴራላዊ ሥርዓቱ የአገሪቱን ሕዝቦች ነጣጥሏል፡፡ ጠባብነትና የጎሳ ፖለቲካ ተንሰራፍቷል፡፡ የአገሪቱ ድንበር፣ የወደብ ሀብትና የዜጐች ተዟዙሮ የመንቀሳቀስ መብት ለአደጋ ተጋልጧል የሚል ተከታታይ ጩኸትም አልቆመም፡፡

በእነዚህ ሁለት ጠርዞች መሀል ላይ ያለው መከራከሪያ ደግሞ የፌዴራል ሥርዓቱን ሳይኮንን ብሔርና ቋንቋ ተኮር መሆኑ ያለውን አደጋ የሚያቀነቅን ነው፡፡ ‹‹የኢትዮጵያ ሕዝብ ከዚህ በኋላ ወደ አሀዳዊነት ሊመለስ ባይችልም ጂኦግራፊ፣ ሥነ ልቦናና ማኅበራዊ ትስስርን የዘነጋ ቋንቋና ማንነት ተኮር አከላለል የጠባብነትና የጎሳ ፖለቲካ መባባስ ዕድል እያሰፋ ነው፤›› የሚል ነው፡፡

ይህን ሐሳብ እነ ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ካሉበት መድረክ አንስቶ ኢዴፓ፣ መኢአድና መሰል የተሻለ ተቀባይነት ያላቸው የፖለቲካ ድርጅቶች የሚያቀነቅኑት ነው፡፡ እንዲያውም በቅርቡ ‹‹ዘመን›› ለተሰኘው መንግሥታዊ መጽሔት ሐሳባቸውን ያካፈሉት ፕሮፌሰር በየነ፣ ‹‹እናንተ መድረክ ለምን አይዋሀድም ትላላችሁ፡፡ ለ25 ዓመታት አገር የመራው ኢሕአዴግ፣ ሰፊ ካፒታልና ከስድስት ሚሊዮን በላይ አባል ያለው ኢሕአዴግ እንኳን እስካሁን ከግንባርነት አልፎ አንድ ውህድ ፓርቲ መሆን አልቻለም፡፡ ይኼ ደግሞ አሁን ያለችው ኢትዮጵያ ውጤት ነው፤›› ነበር ያሉት፡፡

አደጋው ግን ይኼ ብቻ አይደለም፡፡ ብሔር ተኮር ፌዴራላዊ ሥርዓቱ በየዓመቱ ከፍተኛ ወጪ እየተመደበለት በፌስቲቫል መልክ በብሔራዊ ደረጃ እየተከበረ ነው፡፡ የኢትዮጵያ የፌዴራል ሥርዓት ተሞክሮ ከአገር አልፎ ለአንዳንድ የአፍሪካ አገሮች ‹‹ልምድ›› ይሆናል ተብሎም ዓለም አቀፍ መድረኮች ሳይቀሩ በአዲስ አበባ ተከፍተዋል፡፡ ኅትመቶች፣ ዶክመንተሪዎችና የተለያዩ ክርክሮችም ተካሂደውበታል፡፡

ያም ሆኖ ግን አሁንም ‹‹የማንነት ጥያቄ›› መንግሥት እንደሚለው ‹‹ተመልሶ ያለቀ ጉዳይ›› አልሆነም፡፡ ለአብነት በደቡብ ክልል (ኮንሶ፣ ጋሞጎፋ፣ ካፋ…)፣ በአማራ ክልል (የቅማንት)፣ በትግራይ (የወልቃይት) ተደጋግሞ የሚጮኽ ድምፅ አለ፡፡ አስከፊው ነገር በውህደትና በእኩልነት ላይ የተመሠረተ ‹‹ኅብረ ብሔራዊ›› ትስስር ይፈጠራል እየተባለ ዜጎች በብሔርና በሃይማኖት ሰበብ እየተገለሉና እየተሰደዱ ነው፡፡ በተለያዩ ጊዜያት የአማራ ክልል ተወላጆች በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች፣ የትግራይ ተወላጆችም በሰሜን ጎንደር በቅርቡ የደረሰባቸውን ጥቃት ያጤኑዋል፡፡

ብሔር ተኮር ፌዴራል ሥርዓቱ በተለያየ መንገድ በማንነታቸው የሚሰባሰቡ ዜጐችን አበራክቷል፡፡ ቀስ በቀስ እንኳን የፖለቲካ ድርጅትና የአክሲዮን ማኅበር ይቅርና ‹‹የፀበል ፀዲቅ ማኅበር›› እንኳን በብሔር የሚደራጅ ሆኗል፡፡ ዕቁብ፣ ቅሬና ደቦ ሳይቀሩ በመንደርተኝነት ተቃኝተዋል፡፡ ከሁሉ በላይ ሃይማኖትን ከብሔር፣ ጋብቻን ከዘር ሐረግ ጋር ለማስተሳሰር የሚያዳክሩንን ‹‹ተው!›› ያላቸው አልነበረም፡፡

በመንግሥት አሠራርና ሥርዓት ውስጥም ከፌዴራላዊ ሰንደቁ ይልቅ የክልል ባንዲራዎችና ኮፍያዎች በርክተው ይታያሉ፡፡ ከፌዴራሉ መንግሥት ቋንቋ ይልቅ የየብሔሩ ቋንቋዎች ይበልጥ ተፅዕኖ ፈጥረዋል፡፡ ከፌዴራል ፖሊስ ጀምሮ ‹‹የፌዴራል›› የሆኑ ሚዲያዎች፣ ስትራቴጂዎችና ዕቅዶች የተቀባይነት ደረጃቸው እየወረደ የመጣ መስሏል፡፡ ለዚህ አብነቱ አሁን በተጨባጭ በክልሎች እየታየ ያለው እውነታ ነው፡፡

አንዳንድ የፌዴራል መንግሥታት ጥናት ላይ ያተኮሩ ምሁራን ‹‹የኢትዮጵያ የፌዴራል መንግሥት ሥልጣን ሀብትና አቅም ወደ ክልሎች መከፋፈል አለበት፡፡ የተሰበሰበው ሥልጣንም ሊበተን ይገባል፤›› ሲሉ ይደመጣል፡፡ መሬት ላይ ያለው እውነት ግን ‹‹እንኳን ዘንቦብሽ›› የሚሉት ነው፡፡ ክልሎች በዚህም ደረጃ ‹‹ድንበሬ፣ ወሰኔ፣ የግል መሬቴ…›› የሚሉት ከአገር የወጣ አስተሳሰብ አየሩን ሞልቶታል፡፡

አዲስ አበባ ከመላው ኢትዮጵያ ሕዝቦች ሀብትነትም አልፋ የአፍሪካ መዲና ሆናለች፡፡ ይሁንና ከኦሮሚያ ክልል ፊንፊኔ ዙሪያ ልዩ ዞን ጋር እንኳን የሚያስተሳስራትን የጋራ ማስተር ፕላን መተግበር የማትችልበት ደረጃ ተፈጥሯል፡፡ ሌላው ቀርቶ መዲናዋ ለምትጠጣው ውኃና ለምትደፋው ቆሻሻ ‹‹ከሌላ አገር ጋር የመደራደር ያህል›› ሁኔታዎች እየከበዷት መጥተዋል፡፡ በዚህ ሁኔታ የከተማዋ የረጅም ጊዜ ጉዞም ቅርቃር ውስጥ እየገባ ይመስላል፡፡ ግን ለምን መባልም አለበት፡፡

የፌዴራል ሥርዓቱ ዜጐች በእኩልነትና በነፃነት አንድ ጠንካራ አገር የመገንባት ህልም ነው ሊኖረው የሚችለው፡፡ አሁን ባለው ሁኔታ ግን በየመንደሩ ተመሳሳይ ቋንቋ መናገር የሚችሉ ጥቂት ወገኖች ተሰባስበው ‹‹ማንነታችን ይታወቅ›› ነው እያሉ ያሉት፡፡ ከዚያም አልፎ ወደ ታሪክ መነጣጠቅ፣ ደምና አጥንት መቁጠር ለመግባት የተጀመረው ጥድፊያ አገር የሚያፈርስ ጅምር ነው፡፡ አንዱ ወደ ቀኝ ሌላው ወደ ግራ መዘረጣጠጥና መፈላቀቅ አገር ያፈርስ እንደሆነ እንጂ ሊገነባ አይችልም፡፡

በዚህ ላይ ‹‹ካልበላሁት ልድፋው›› ባዩ ፖለቲከኛ የብሔር ጥላቻን በጠባብነት መርዝ እየለወሰ በመዝራት ላይ ነው፡፡ የፌዴራል ሥርዓቱ ግብ ብዙ ‹‹አገሮችን›› መፍጠር የሆነ ይመስል እገሌ ይገንጠል፣ ከእነገሌ ጋር አንድ ነን እያለ ይለፍፋል፡፡ ይህ ሁሉ ቀዳዳ የተከፈተው ደግሞ ያለጥርጥር ጠንካራ ውህደት፣ ብሔራዊ መግባባትና ትስስር ባለመፈጠሩ ነው ባይ ነኝ፡፡

ሌላው በፌዴራል ሥርዓቱ አፈጻጸም ውስጥ አንድ ዓብይ ተግዳሮት ታይቶ መፈተሽ ያለበት ‹‹አንዱን ጥሎ ሌላውን አንጠልጥሎ›› የሚካሄደው መጋጋጥ ነው፡፡ በአገሪቱ ለብሔር፣ ለእምነት፣ ለፆታና ለዕድሜ ብዝኃነት የተሰጠውን ትኩረት ያህል ‹‹የአመለካከት ብዝኃነት›› እንደሌለ የመቁጠር ዝንባሌ እየገነገነ ነው፡፡ ይህ ደግሞ ከዴሞክራሲ ምሰሶዎች (የሐሳብ ነፃነት፣ መደራጀት፣ መቃወምና ድጋፍ ማድረግ…) ጋር ክፉኛ ሊጋጭ ይችላል፡፡

በአገሪቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ ከገዥው ፓርቲ ኢሕአዴግ አመለካከትና ፖሊሲ ውጪ የሚያራምዱ ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ ፖለቲካ አራማጆች እየተዳከሙ መጥተዋል፡፡ እርግጥ ለእነዚህ ኃይሎች መዳከምና መውደቅ ቀዳሚዎቹ ተወቃሾቹ ራሳቸው ቢሆኑም ፍርኃትን አስወግዶ፣ የመደራጀትና ሐሳብን የመግለጽ ልዕልና የማረጋገጥ ኃላፊነት የመንግሥትም ነው፡፡ ከሁሉ በላይ ‹‹ከልማታዊ ዴሞክራሲያዊ ፖሊሲ›› ውጪ ማቀንቀን ‹‹ኃጢያት›› ከመሰለ የሰላም በሮች ይዘጋሉ፡፡ የፀብ፣ የነውጥና የግጭት በሮች ይበረገዳሉ፡፡

የፌዴራል ሥርዓቱ የአመለካከትና የፖለቲካ ልዩነት ያለውን ዜጋ አቻችሎ ስለመያዝ ብቻ አይደለም መጨነቅ ያለበት፡፡ በብሔርና በማንነት ደረጃም ቢሆን ለዘመናት ተገፍቶ የኖረውን ሁሉ ዕውቅና እየሰጠ ሲያጎለብት፣ ብዙኃኑን አለመግፋቱና አለመድፈቁን እየፈተሸ ሊሄድ ይገባል፡፡

ከዚህ አንፃር በቀዳሚነት የኦሮሞና የአማራ ብሔሮች ቀድመው ይጠቀሳሉ፡፡ እነዚህ ሕዝቦች እስከ 68 በመቶ የአገሪቱን ሕዝብ ያህል ቁጥር ይይዛሉ፡፡ በቆዳ ሽፋን ረገድም ሰፊውን ድርሻ ከመያዛቸው ባሻገር በተማረ የሰው ኃይል፣ በሀብትና ዕምቅ የተፈጥሮ ሀብት ረገድ የአገሪቱ እምብርት ናቸው ቢባል ማጋነን አይደለም፡፡ ስለዚህ የእነዚህን ሕዝቦች ተጠቃሚነትና እኩልነት ብቻ ሳይሆን ‹‹እየተበደልኩ ነው›› የሚለውን ስሜት ተገንዝቦ መልክ ማስያዝ የሥርዓቱ ኃላፊነትና ግዴታ ነው፡፡

በነገራችን ላይ ‹‹ተበደልኩ›› የሚለው ስሜት የሚመነጨው በፍትሐዊ የሀብት ክፍፍል ከሌሎች ብሔሮችና ሕዝቦች ያነሰ ተጠቃሚ ስለሆኑ አይደለም፡፡ ይልቁንም ከብዝኃነት ወይም ከታሪክ አጋጣሚ ከነበራቸው የፖለቲካ ኢኮኖሚ ሥፍራ አንፃር አገራዊ ስሜታቸውን የማያጡበት ብልኃት መዘርጋት ያስፈልጋል፡፡ በተለይ በየትኛውም ብሔር ውስጥ ተሰንቅሮ የግል ፍላጎቱን ለማቀንቀን የሚሻው ጥገኛ ይልቅ፣ ይህን ክፍተት መሠረት አድርጎ ሕዝብን ለማነሳሳትና ሥርዓቱን ለማደፍረስ እንደማይመለስ መገመት ተገቢ ነው፡፡

የኢፌዴሪ (የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት) በሕገ መንግሥቱ አጽንኦት ሰጥቶ የደነገጋቸውን የሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ትኩረት ሰጥቶ መተግበርም ዋነኛው የሥርዓቱ ዋስትና ነው፡፡ በዚህች አገር ከ20 ዓመታት በፊት የወጣ ሕገ መንግሥትን ዛሬም ድረስ ‹‹በማስፈጸም አቅም ማነስ›› ሰበብ ተግባራዊ አለማድረግ ውጤቱ አደገኛ ነው፡፡

በመረጃ ነፃነት፣ በመደራጀት፣ ነፃ ማኅበራትን በማቋቋም፣ በዜጐች የትም ተዘዋውሮ የመሥራትና ሀብት የማፍራት መብት፣ በሰላምና ደኅንነት የመኖር መብት፣ ሃይማኖትን በነፃነት የማራመድ መብት፣ የሕግ የበላይነት፣ በየመስኩ የግልጽነትና ተጠያቂነት፣ የዜጐች ፍትሐዊ ተጠቃሚነት … (እንደመጣልኝ የዘረዘርኳቸው) ይበልጥ ተከብረው ሕዝቡ የፌዴራል ሥርዓቱን እንዲያምነው መሆን አለበት፡፡ እዚህ ላይ በፌዴራል ሥርዓቱ ስም በየክልሉና በየመንደሩ ፀረ ዴሞክራሲያዊነት፣ ሙስና፣ ኪራይ ሰብሳቢነት ካቆጠቆጠ መንገዱ ሁሉ ውድቀት ነው፡፡ የሕዝብ ቅያሜና ቁጣም ሊቀር አይችልም፡፡

በፖለቲካ ዓለም ውስጥ ‹‹ውሸት ሲደጋገም እውነት ይመስላል›› የሚለው ብሂል አይሠራም ባይባልም፣ ዋነኛው ሕዝብ ማሳመኛ ግን ተግባር ነው፡፡ አሁን ባለችው ኢትዮጵያ በሚገኙ አንዳንድ ክልሎች ሕዝቡን ፊት ለፊት ወርዶ በልበ ሙሉነት ማናገር የተሳናቸው ፖለቲከኞች ለምን በዙ? ፍትሐዊ የሀብት፣ የሥራ ዕድልና የሥልጣን ክፍፍልን ለማረጋገጥ የሚያስችል ዴሞክራሲያዊ ምክክር እንዴት እየነጠፈ ሄደ? በአገራዊና በብሔራዊ ጉዳይ በአንድ መንፈስ ‹‹ቀጭን ትዕዛዝ›› የሚያወርድ ለምን ጠፋ (ኢዴሞክራሲያዊ ባህሪ እንኳን ቢኖረው) ብሎ መፈተሽ ያስፈልጋል፡፡

ዛሬ በብሔር፣ በሃይማኖት፣ በአመለካከት… የቆዘሙና የተለያየ አቋም የሚያራምዱ ዜጐች መብዛታቸውን ማየት እየተቻለ ነው፡፡ እነዚህን ኃይሎች በበሰለ የፖለቲካ ድርድርና ዴሞክራሲያዊ ውይይት ወደ አገራዊ የጋራ አጀንዳ የሚያስጠጋ የስበት ማዕከል መፍጠር ይጠይቃል፡፡ ይህን ማድረግ የሚቻለው ደግሞ በፌዴራል ሥርዓቱ ውስጥ የታጨቁ የመርህና የአፈጻጸም ተግዳሮቶችን ደፍሮ በመቅረፍና የማሻሻያ ዕርምጃዎችን ፈጥኖ በመውሰድ ነው የሚል እምነት አለኝ፡፡ እናንተስ?!  

ከአዘጋጁ፡- ጽሑፉ የጸሐፊውን አመለካካት ብቻ የሚያንፀባርቅ ሲሆን፣ ጸሐፊውን በኢሜይል አድራሻቸው YasenB@yahoo.comማግኘት ይቻላል፡፡ 

 

 

    

  

Standard (Image)

ይድረስ ለአቶ ሞገስ ሀብተ ማርያም

$
0
0

እውነታውን ለምን ፈሩት?

 

በመድኃንዬ ላፍቶ

 

በኢሕዲሪ ምክትል ፕሬዚዳንት ሌተና ኮሎኔል ፍሰሐ ደስታ ‹‹አብዮቱና ትዝታዬ›› በሚል መጽሐፋቸው ላይ ተመርኩዘው በሪፖርተር ሐምሌ 10 ቀን 2008 ዓ.ም. ዕትም የጻፉትን ሐተታና ስሞታ በጥሞና አንብቤዋለሁ፡፡

በመጀመሪያ የተጠቀሰው መጽሐፍ ሀቅን ያቀፈ፣ እውነትን የተላበሰ ብቻ ሳይሆን በመሥሪያ ቤትዎ የተፈጸመውን ጥፋትና ግፍን ጨምሮ በአብዮቱ ውስጥ በማወቅም ሆነ በስህተት ስለተፈጸመው ሁሉ የይቅርታን መልዕክት የያዘ ነው፡፡ በመሆኑም መጽሐፉ ከፍተኛ ተቀባይነትና ተወዳጅነት ያገኘ መሆኑን ልገልጽልዎት እወዳለሁ፡፡ በመሠረቱ ረጅሙ ሐተታዎን ካነበብኩ በኋላ ሌተና ኮሎኔል ፍሰሐ ደስታ የእርስዎን ሳይሆን የራሳቸውን ትዝታ መጻፋቸውን አለመረዳትዎን ተገንዝቤያለሁ፡፡ ለማንኛውም ስለትችቱ የመጽሐፉ ባለቤት ተገቢ መልስ ይሰጡበታል ወይም ንቀው ይተውት ይሆናል፡፡ ይህንን ለሳቸው መተው ይሻላል፡፡

በበኩሌ ግን በጽሑፍዎ መግቢያ አካባቢ በእኛ የሰደድና የኢሠፓአኮ አባላት የነበርን የትግራይ ተወላጆች በሐሰት ተወንጅለን በማዕከላዊና በቤርሙዳ የደረሰብንን ግርፋት፣ ሰቆቃና ግድያ ሌተና ኮሎኔል ፍሰሐ በዝርዝር በመጻፋቸው ስህተት እንደሆነና ራሳቸውን ለመከላከል ያቀረቡት አስመስለው የሰነዘሩት ትችት አሳዝኖኛል፡፡ አለቃዎና ሌሎች የዚህ ወንጀል ተባባሪ የነበሩት በሕይወት ቢኖሩ የወሰዱት ዕርምጃ ትክክል መሆኑን ያስረዱን ነበር የሚል መልዕክትም ለማስተላለፍ ሞክረዋል፡፡ ሌተና ኮሎኔል ፍሰሐ በአብዮቱ ውስጥ የገጠማቸውን ሁኔታ ዘርዘር ባለ መልኩ በማቅረባቸውም ቅሬታዎን ገልጸዋል፡፡ እውነታውን ነው የፈሩት? ወይስ ለወረቀቱ ነው የተጨነቁት? በአብዮቱ ወቅት መሥሪያ ቤትዎ በንጹኃን ዜጎች ላይ የፈጸመውን ድርጊት ሕዝቡ እንዲያውቅ ለምን ተደረገ የሚሉ ይመስለኛል፡፡ የአብዮቱ ታሪክ አካል ነውና ዛሬም ነገም መጻፉ የማይቀር ነው፡፡

ይህንን ካልኩ በኋላ እኔ በአካል ባላውቅዎትም በደኅንነቱ መሥሪያ ቤቱ ሁለተኛ ሰው ስለነበሩ የመረጃ ዕውቀት ይኖርዎታል ብዬ እገምታለሁ፡፡ በመሆኑም በሌተና ኮሎኔል ፍሰሐ የቀረበውን ጽሑፍ እውነተኛነቱን ለማረጋገጥ ከፈለጉ ጥቂት ግን የማያወላዳ ማስረጃ ላቅርብልዎት፡፡ በመጀመሪያ ‹‹ሉዓላዊነትና ዴሞክራሲ በኢትዮጵያ›› በሚል ርዕስ በአቶ ገብሩ አሥራት በተጻፈው መጽሐፍ ከገጽ 159 እስከ 161 ያለውን ያንብቡ፡፡ በአጭሩ ‹‹ሕወሓት የውሸት የከተማ መዋቅር ሠርቶ የደርግ ታማኞችና ሕወሓትን ያውካሉ የተባሉትን የሕወሓት አባላት አስመስሎ የስም ዝርዝር ላከ፡፡ በዚህም መሠረት የደርግ የደኅንነት መሥሪያ ቤት የኢሠፓአኮና የደርግ ታማኞች የነበሩትን በራሱ እጅ አጠፋቸው፤›› በማለት በግልጽ አስቀመጥውታል፡፡ እዚህ ላይ መቐለ የነበሩ እሥረኞች በሕወሓት ነፃ የወጡት ከዚህ በኋላ መሆኑን ልብ ይበሉ፡፡

ሁለተኛ እርስዎ የተቃወሙት የሌተና ኮሎኔል ፍሰሐ ጥቂት ገጾችን ነው፡፡ ይህንን በተመለከተ የማዕከላዊ ምርመራ ሰነዶችን አገላብጦ፣ ግለሰቦችን ጠይቆ አቶ ግርማይ አብርሃ ‹‹ያመነም ያላመነም›› በሚል ርዕስ ዳጎስ ያለ መጽሐፍ ጽፏልና ያንብቡት፡፡ ሦስተኛ ፕሬዚዳንት መንግሥቱ ኮሎኔል ተስፋዬ ፍሰሐን የወያኔ አባል ነው እያለ ይጠረጥረዋል፣ ማስረጃ ግን ለማቅረብ አልቻለም ሲሉ ለገነት አየለ በሰጧት ቃለ መጠይቅ አረጋግጠዋል፡፡ በመጨረሻ ግን ታደሰ ገብረ እግዚአብሔር በግርፋት ማቆ በገመድ ታንቆ ከመገደሉ በፊት፣ ለአለቃዎና ለማዕከላዊ ምርመራ የጻፈውን 190 ገጽ ሰነድ ይመልከቱት፡፡ እነዚህን ካነበቡ በኋላ ብዕሬን ለምን አነሳሁ ብለው ይቆጭዎታል ብዬ እገምታለሁ፡፡ በተለይ የታደሰን ጽሑፍ ካነበቡ በኋላ እንደ አለቃዎ ‹‹የአዞ እንባ›› ሳይሆን ርህሩህ ከሆኑ እውነተኛ እንባ ያነባሉ፡፡

ኮሎኔል ተስፋዬ ማዕከላዊ እሥር ቤት ሊያነጋግሩን መጥተው ነበር፡፡ እኛም ‹‹በአንድ በኩል ሕወሓት ዓላማችንን ይቃወማሉ በማለት ሊገድለን ያሳድደናል፡፡ እኛ ለደርግና ለኢሠፓአኮ ታማኝ ስንሆን ደርግ ካልተገለበጠ በስተቀር እንዴት ለመታሰር በቃን? መንግሥት ያልደረሰበት ሴራና አሻጥር እየተሠራ ነውና ያጣሩልን፤›› ብለን ጠየቅናቸው፡፡ ‹‹አጣርቼ መልስ እሰጣችኋለሁ፤›› ብለውን ሄዱ፡፡ አውቆ የተኛ እንደሚሉት እስሩ ያነሰን ይመስል የተወሰን ሰዎች ፀሐይ ሳይሆን ብርሃን ተነፍገን በጨለማ ቤት ለሰባት ወራት ተዘጋብን፡፡ በኤሠፓአኮ መዋቅር አንድም የትግራይ ተወላጅ እንዳይኖር የሚል ፖሊሲ የነበረ ይመስል ቤርሙዳና ማዕከላዊ በእስረኞች ተጨናነቁ፡፡ ጥቂት ቆይቶ ታደሰ ገብረ እግዚአብሔርን ጨምሮ አምስት ሰዎች ተገደሉ፡፡ ዶ/ር መንገሻም ከግርፋቱ ብዛት እግራቸው ተቆራርጦ እሳቸውም አብረው ተገደሉ፡፡

ከግድያ የተረፍነው ደግሞ ኢሕአዴግ አዲስ አበባን ሲቆጣጠር ጠባቂዎቻችን ጥለውን ሲሄዱ ከወህኒ ወጣን፡፡ ብዙም ሳንቆይ ፀረ ሕወሓት ነበራችሁ ተብለን በኢሕአዴግ በቁጥጥር ሥር ዋልን፡፡ ከተለያየ እስር ጀምሮ ዕድሜ ልክ ተፈረደብን፡፡ የሁለት መንግሥት ሰለባ ሆንን፡፡ ይህ ራሱ ንጹኃን ሰዎች እንደፈለጋችሁ አስራችሁ እንዳሰቃያችሁ በቂ ማስርጃ ሊሆንዎት በተገባ ነበር፡፡ ዳሩ ያልተያዘ ግልግል ያውቃል ሆነና በኢሕአዴግ ዘመን በእስር ያሳለፍናቸውን ረዥም ዓመታት እርስዎ ሜዳሊያና ኒሻን፣ ሹመትና ሽልማት አድርገው ወስደውታል፡፡ በቁስላችን ለመሳቅና ለመሳለቅ በመፈለግዎ አምላክ ይቅር ይበልዎት፡፡

‹ጥርስና ከንፈር አብሮ ይደማል› እንደሚባለው ለአለቃ መከላከል ተገቢ ነው፡፡ አገር ያወቀውን ፀሐይ የሞቀውን ነገር ለመከላከል መሞከር ግን ትርፉ ትዝብት ነው፡፡ ‹‹ሙት ወቃሽ አያድርግኝ›› ይላሉ አበው ሲተርቱ ተናግሮ አናጋሪ እያለ ግን ሙት መወቀሱና መቀስቀሱ አይቀርም፡፡ ከአለቃዎ ጋር አብሬ ታስሬ ነበር፡፡ የመሥሪያ ቤታችሁ ባልደረቦች ለመጀመሪያ ጊዜ ፍርድ ቤት ስቀርቡ ኮሎኔል ተስፋዬ ሳይጠየቁ፣ ‹‹በእኔ መሥሪያ ቤት እኔ ሳላውቅና ሳላዝ አንድም ነገር አልተፈጸመም፣ ኃላፊነቱን በሙሉ እኔ እወስዳለሁ፤›› ብለው ተናገሩ፡፡ ዳኛውም ወቅቱ ሲደርስ ይህንን ይገልጻሉ ሲሉ መለሱላቸው፡፡

ወቅቱም ደርሶ የመሥሪያ ቤታችሁ ባልደረቦች የነበሩ መለዮ ለባሾች ለምስክርነት ሲጠሩዋቸው ግን በዓቃቤ ሕግ እንደሚለቀቁ ቃል ተገብቶላቸው ነው መሰለኝ፣ መጽሐፍ ቅዱስ ይዘው አላውቃቸውም ሲሉ ካዱ፡፡ በዚህ ብቻ አላበቁም፡፡ ወታደሮች መሆናቸውን እያወቁም፣ ወታደሮች አልነበሩም ስሉ መሰከሩ፡፡ እነዚህ ታዛዦች በእሳቸው ምስክርነት ዕድሜ ልክና ሞት ተፈረደባቸው፡፡ ሞት የተፈረደባቸው ኢሕአዴግ ይቅርታ አድርጎላቸው አሁንም በሕይወት አሉና ይጠይቁዋቸው፡፡ አለቃዎ ግን እነሱን ጭዳ አድርገው ሊወጡ ቋምጠው ነበር፡፡ ሌላም ሌላም አለ፡፡ ሆድ ይፍጀው!

በመጨረሻ እርስዎ በመሥሪያ ቤቱ ከፍተኛ  ባለሥልጣን ከነበሩ በማዕከላዊና በቤርሙዳ ይፈጸም የነበረውን ግፍ አያውቂም ነበር? በመሆኑም በመሥሪያ ቤትዎ የነበሩ ከአለቃ እስክ ምንዝር በኢሕአዴግ መንግሥት ቁጥጥር ሥር ሲውሉ እርስዎ የውጭ ዜጋ አይደሉ እንዴት ተረፉ? በትብብር ወይስ በድርድር? ‹‹መጫር ያበዛች ዶሮ የመታረጃዋን ቢላዋ ታወጣለች›› አሉ ቸር ይግጠመን!!!

ከአዘጋጁ፡- ጽሑፉ የጸሐፊውን አመለካከት ብቻ የሚያንፀባርቅ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

Standard (Image)

የሰንደቅ ዓላማ ፖለቲካ

$
0
0

በከበደ ካሳ

እስኪ አንድ የሚገርመኝን ነገር ላንሳ፣ ተሳስቼ ከሆነም አርሙኝ፣ የምወቅሳችሁ ወገኖች ተሳስታችሁም ከሆነ ለመታረም አትፈሩ።

አሁን ላነሳ የፈለግሁት ስለ ሁለት ሰንደቅ ዓላማዎች ነው። ርዕሴን የሁለትሰንደቅ ዓላማዎችወግልለው ፈልጌ ነበር። ቢሆንም ቅሉ እነዚህ ሰንደቅ ዓላማዎች አብረው ሊያወጉ የሚችሉበት ተፈጥሮ የላቸውምና ርዕሴን ቀይሬዋለሁ።

አንደኛው ሰንደቅ ዓላማ በጎንደርና በባህር ዳር ሠልፈኞች ይዘውት ያየነው ነው። አረንጓዴ፣ ቢጫና ቀይ ሆኖ መሀሉ ላይ ምንም ዓርማ የሌለበትን ማለቴ ነው። ይህ ሰንደቅ ዓላማ ጎንደር ከተማ አደባባይ ላይ የኢፌዴሪ ሰንደቅ ዓላማን በማውረድ እንዲውለበለብ ተደርጓል። ሌላው በተመሳሳይ ወቅት በኦሮሚያ ክልል አንዳንድ ከተሞች (አዲስ አበባን ጨምሮ) በተደረጉ ሠልፎች ላይ ሠልፈኞች ይዘውት የነበረው የኦነግ ባንዲራ ነው።

የኦነግ ባንዲራ በቃ የኦነግ ነው። ስሙም፣ ግብሩም፣ ዓላማውም ጥንቅቅ ተደርጎ የታወቀ የለየለት ባለቤት አለው። እኔን የሚገርመኝ ግን የዚያኛው ባንዲራ ባለቤት ማንነት ነው። በእርግጥ የእኛባንዲራዓርማየሌለውነውየሚሉ ወገኖች በአገር ውስጥም በውጭም እንዳሉ አውቃለሁ። ጥያቄዬ ግን‹‹እኛ››የምትሉት እናንተ ማን ናችሁ? የሚል ነው።

እንደሚታወቀው ሰንደቅ ዓላማ ከጀርባው ትልቅ መልዕክትን ያዘለና አንድን ፖለቲካዊ አስተሳሰብ የሚወክል ነው። የየትኛውም አገር ወይም የኅብረተሰብ ክፍል ባንዲራ ከዚያ አገር ሕዝብ ማንነትና ከሚከተለው የፖለቲካ ሥርዓት ጋር በእጅጉ የተቆራኘ ትርጓሜና ውክልና ይሰጠዋል። ሌላው ቀርቶ የኦነግ ባንዲራም ራሱን የቻለ መልዕክትና ዓላማ ያዘለ ነው።

እኔ አሁን ጥያቄ የማነሳው የዚህ ልሙጥ ባንዲራ ትርጓሜና መልዕክት ምንድን ነው? በማለት ነው። ትርጓሜው ይህ ነው፣ የሚወክለውም ይህንን ነው የሚለኝ ካለ በቅንነት ለመቀበልና የማላውቀውን ለመማር ዝግጁ ነኝ። እስከዚያው ግን እኔ የሚረዳኝን ላካፍላችሁ።

ይህ ባንዲራ ሕገ መንግሥታዊ ዕውቅና ካለው የኢፌዴሪ ባንዲራ የሚለየው መሀሉ ላይ ዓርማ ስለሌለው ብቻ ነው እንጂ በቀለም ተመሳሳይ ናቸው፡፡ አረንጓዴ፣ ቢጫ፣ ቀይ።  በሰንደቅ ዓላማ አዋጅ ቁጥር 654/2001 አንቀጽ 7 ላይ የቀለማቱን ትርጉም አስመልክቶ እንደተቀመጠው አረንጓዴው የሥራ፣ የልምላሜና የዕድገት ምልክት ሲሆን ቢጫው የተስፋ፣ የፍትሕና የእኩልነት ምልክት ነው። ቀዩ ደግሞ ለነፃነትና ለእኩልነት መስፈን የሚደረግ የመስዋትነትና የጀግንነት ምልክት ነው፡፡ በዚህ ላይ ልዩነት ያለ አይመስለኝም።

የልዩነት ነጥብ ሆኖ የሚታየው ዓርማው ነው። እዚህም ላይ ቢሆን ውይይት ሊያስነሳ የሚችለው ጉዳይ ዓርማው የያዘው መልዕክት እንጂ ሰንደቅ ዓላማ ላይ ዓርማ ማስቀመጥ በእኛ አገር ብቻ ሳይሆን፣ በብዙዎቹ የዓለም አገሮችም የሚደረግ በመሆኑ አከራካሪ ጉዳይ ሊሆን አይችልም፡፡ እንግዲህ በባንዲራችን ላይ ያለው ዓርማ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 3 ሥር የተሰጠው ትርጓሜ የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች፣ ሕዝቦችና ሃይማኖቶች በእኩልነትና በአንድነት ለመኖር ያላቸውን ተስፋ የሚያንፀባርቅ የሚል ነው። ይህ መቼም በእኩልነትና በአንድነት ለማያምን ካልሆነ በስተቀር ለማንም የሚያስከፋ ሊሆን አይችልም። እናም ዓርማው ያረፈበትን መደብ ተቀብሎ ዓርማውን መቃወም ማለት ዓርማው ያዘለውን የእኩልነትና አንድነት ተስፋ መቃወም ነው ብዬ አስባለሁ። አይደለም እንዴ?

ከዚህ አንፃር የኦነግን ባንዲራ እንመልከት። የኦነግ ባንዲራን ከኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ባንዲራም ሆነ ከፌዴራል መንግሥቱ ባንዲራ ጋር ብናነፃፅረው ልዩነቱ በዓርማ ብቻ ሳይወሰን የቀለምም ሆኖ እናገኘዋለን። ልዩነት እንዲህ ሲሆን ለክርክርም ይመቻል፣ ግልጽ ልዩነት። በታሪክ አጋጣሚ የተዛቡ ግንኙነቶች እንዳሉ ተቀብሎ እነዚህን ስህተቶች በማረም፣ የጋራ እሴቶቻችንን በማጎልበትና የጋራ ጥቅሞቻችንን በማሳደግ በአንድነት የመኖር ዴሞክራሲያዊ ብሔርተኝነትና ያለፈውን ቁስል ሁል ጊዜ እንዲያመረቅዝ እያደረገ ተገንጥሎ መኖርን በሚሻ ጠባብነት መካከል ያለ ግልጽ ልዩነት። እናም ኦነግ አንድነትን ሳይሆን መገንጠልን የሚሻ አካል በመሆኑ የአገሪቱን ባንዲራም ሆነ የክልሉን ዓርማ ያለመጠቀሙ፣ ብሎም የራሱን ባንዲራ መቅረፁ የሚጠበቅ ብቻ ሳይሆን ከባንዲራ አጠቃቀም መርህ አንፃርም ተገቢ ነው።

በከፊል ከላይ ካነሳሁት ጉዳይ ጋር የሚያያዘው ሁለተኛው ጥያቄዬ ልሙጡን ባንዲራ የእኛነውየሚሉ ወገኖች ይህን ባንዲራ ከየትኛው ሥርዓት ጋር እያስተሳሰሩት እንደሆነ እንዲነግሩኝ ነው። አንዳንድ ጸሐፊዎች እንደሚያስቀምጡት ኢትዮጵያ ከአሁኑ በፊት በተለያዩ የመንግሥት ሥርዓቶች ሰባት ጊዜ ያህል ብሔራዊ ባንዲራዋን ቀያይራለች። ይኼ ልሙጡ ባንዲራ ግን በየትኛውም ሥርዓተ መንግሥት ወቅት አገልግሎት ላይ አልዋለም። በየሥርዓቱ የነበሩ ሰንደቅ ዓላማዎች የጋራ የሆኑ ባህሪዎች ነበሯቸው፡፡ በመጀመሪያ ከጥንት እስከ አሁን በሁሉም ሰንደቅ ዓላማዎቻችን የነበሩት ቀለሞች አረንጓዴ፣ ቢጫና ቀይ ናቸው፡፡ በተጨማሪ ከ1890 በፊት ከነበረውና ከደርግ ውድቀት በኋላ በሽግግሩ ወቅት ለአጭር ጊዜ ከነበረው ሰንደቅ ዓላማ ውጪ በሁሉም ላይ ዓርማዎች ነበሩ፡፡

በአፄ ምኒሊክ ዘመነ መንግሥት በሰንደቅ ዓላማው ላይ ዘውድ የጫነ አንበሳ መስቀል ይዞ ይታይ ነበር፡፡ በአፄ ኃይለ ሥላሴ ዘመንም ይሄው አንበሳ ‹‹ሞዓ አንበሳ ዘእም ነገደ ይሁዳ›› የሚል ጽሑፍና ኮከቦች ተጨምረውለት እስከ ወታደራዊው የደርግ ሥርዓት ድረስ ቀጥሏል፡፡ ደርግ ሥልጣኑን እንደያዘ አንበሳው ላይ የነበረውን ዘውድ ያነሳ ሲሆን፣ በመስቀሉም ቦታ የጦር ጫፍ ምልክት አስቀምጧል፡፡ በ1979 ዓ.ም. ደርግ አንበሳውን ሙሉ በሙሉ በማውጣት በምትኩ ጦር፣ ጋሻ፣ ማረሻ፣ የስንዴ ዘለላና ሌሎች ምልክቶችን ያካተተ ዓርማ አስቀምጧል፡፡ ከኢሠፓ ምሥረታ በኋላም ሌላ ለውጥ በማድረግ፣ ‹‹የኢትዮጵያ ሕዝባዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ›› የሚል ጽሑፍና የኢሠፓ መገለጫ የሆነ አነስተኛ ዓርማ በውስጡ ያካተተ ዓርማ በሰንደቅ ዓላማው ላይ እንዲሰፍር አድርጓል፡፡

እንግዲህ ሰሞኑን የምናየው ባንዲራ ሙሉ በሙሉ የሚመሳሰለው ደርግ ከተገረሰሰ በኋላ በነበረው የሽግግር መንግሥት ወቅት ከነበረው ባንዲራ ጋር ብቻ ነው፡፡ በደርግ ውድቀት ማግሥት (በሽግግሩ ወቅት ማለቴ ነው) አገራችን ትመራበት የነበረው ገዢ አስተሳሰብ በመሠረታዊነት ከአሁኑ የፌዴራላዊ ሥርዓት የተለየ አልነበረም። በየጊዜው በማጥራት ውስጥ እያለፈ የጠራ መስመር ሆኖ የወጣው በኢሕአዴግ ውስጥ ከተካሄደው ተሃድሶ በኋላ ቢሆንም የመንግሥት አስተዳደር፣ አወቃቀርና ገዢው ፓርቲ የሚከተለው የፖለቲካል ኢኮኖሚ ደርግን ለማስወገድ በተደረገው ትግል ወቅት ተመልሶ ያደረ ነው። ስለዚህ አሁን አገሪቱ ከምትመራበት የፖለቲካ ሥርዓት ጋር ልዩነት ያላቸው አካላት ቢያደርጉ የሚያምርባቸውና የሚገባቸው ከቀደሙት ሥርዓቶች ዓርማዎች ውስጥ አንዱን መመለስ ወይም ደግሞ የራሳቸውን ዓርማ መሥራት ነው እንጂ፣ አሁን የሚያውለበልቡት ባንዲራ እነሱ ለያዙት ዓላማም የሚመጥን አይደለም።

ለነገሩ ይህ መፍትሔ ለእነሱም ከብዷቸው እንጂ ጠፍቷቸው አይደለም። የቀደሙት ሥርዓቶች ዓርማዎች ሲታዩ በግልጽ የገዥዎችን የበላይነትና እነርሱ ነን ብለው የሚያስቡትን ሥዩመ እግዚአብሔርነት የሚሰብኩ፣ ኋላ ላይ የመጡት ዓርማዎች ደግሞ በነፃ ፍላጎት ላይ የተመሠረተ የሕዝቦች አንድነትን ሳይሆን በኃይል የሚመጣን የግዛት አንድነት የሚናፍቁ ናቸው፡፡ እናም እነዚህን በልባቸው ያሉ ዓርማዎች አንግቦ አደባባይ መውጣት የዓርማዎቹን ባለቤቶች ታግሎ ከጣለው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር በቀጥታ የሚያላትማቸው መሆኑን ይረዱታል። ስለሆነም እንዲሁ በደምሳሳው ማጣፊያ የሚያጥራቸውን አጀንዳዎች በመቅረፅ የቻሉትን ያህል ኃይል ለማደናገርና ከጎናቸው ለማሠለፍ ይተጋሉ። ከሰሞኑ የታየውም ይኼው ነው።

ለዚህ ጽሑፍ የተነሳሳሁት ሠልፎቻችን ሕጋዊ ጥያቄዎችና ሕጋዊ ያልሆኑ ጥያቄዎች ተቀላቅለው ከሚተላለፉባቸው ወይም ደግሞ ሕጋዊ ጥያቄዎች በሕገወጥ አካሄድ ከሚቀርቡባቸው መገለጫዎች አንዱ ይኼው የባንዲራ ጉዳይ ስለሆነ እንጂ ከተሰለፍን አይቀር የምንጠይቃቸው፣ መንግሥትም ሊፈታቸው የሚገቡ ብዙ ችግሮች እንዳሉን ጠፍቶኝ አይደለም። በአካል ብቻ ሳይሆን በአስተሳሰብም የተሠለፍንበት ጎራ ከተደበላለቀ ግን ትርፉ ኪሳራ፣ መጨረሻውም የኋሊት ጉዞ ነው የሚሆነው።

ባነሳኋቸው ጥያቄዎች ላይ ምላሽ ያለው ሰው በኢሜይል አድራሻዬ ቢነግረኝ ወረታውን በምሥጋና እከፍላለሁ።

ከአዘጋጁ፡- ጽሑፉ የጸሐፊውን አመለካካት ብቻ የሚያንፀባርቅ ሲሆን፣ ጸሐፊውን በኢሜይል አድራሻቸው kebedememe@gmail.comማግኘት ይቻላል፡፡ 

 

 

Standard (Image)
Viewing all 88 articles
Browse latest View live