Quantcast
Channel: ዓለማየሁ ጉጀ
Viewing all 88 articles
Browse latest View live

ውሉ ያልተገኘው የቱሪዝም ልቃቂትና የቁጥቁጥ ውጤቶች

$
0
0

 

በልዑል ዘሩ

የቱሪዝም ኢንዱስትሪውን አገራዊ ፋይዳ ስንዳስስ በመጣንበት ውልክፍክፍ መንገድ ከመዘነው ዋጋ የለውም፡፡ ወይም የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሪፖርቶች ወይም የቱሪዝም ትራንስፎርሜሽን ምክር ቤት ስብሰባን ከተከታተልን የቁጥቁጥ ‹‹ውጤቶች›› ውጣውን ይቀራሉ፡፡

ከዚያ ይልቅ አገሪቱ ያሏት የተፈጥሮና ሰው ሠራሽ ሀብቶችና ዕምቅ መንፈሳዊና ቁሳዊ ቅርሶች ሚዛን ላይ ሊቀመጡ ግድ ይላል፡፡ እንደ አገር ባለፉት 25 ዓመታት በአንፃራዊነት የተገኘው ሰላምና የተዘመገበው ዕድገት (በተለይ የመሠረተ ልማት፣ የኃይል አቅርቦት፣ የሆቴሎችና የአስጎብኚ ድርጅቶች መጠንና ጥራት) ሊታይ ይገባል፡፡ ከዚህ ባለፈ የአገራችን ሕዝብ 100 ሚሊዮን መድረሱ ብቻ ሳይሆን፣ ነባሩን እንግዳ ተቀባይነትና መንፈሳዊ ገጽታ ካስታወስነው የልብ ቁጭት ማጫሩ አይቀርም፡፡

በቱሪዝም መስክ ዓለም እየተጠቀመበት ካለው ትሪሊዮን ዶላር አንፃር በአገራችን ያለው ብጣቂ ፍሰት (በዓመት ከሦስት ቢሊዮን ዶላር በታች) አያኩራራንም፡፡ በተለይ እንኳን ምሥራቁና ምዕራቡን ዓለም ይቅርና በአፍሪካ ያውም በጎረቤት የምሥራቅና የደቡብ ምሥራቅ አፍሪካ አገሮች (ኬንያ፣ ኡጋንዳ፣ ታንዛኒያ፣ ሩዋንዳና ደቡብ አፍሪካ. . .) ገቢ አንፃር ስንመዝነውም ገና ተራራውን የመውጣት ብርቱ ኃላፊነትና ትጋት ይጠብቀናል፡፡ በተለይ የመንግሥት ሸክሙ ደግሞ ከመርግ የከበደ ነው፡፡

የተቀናጀና የተመቻቸ የቱሪዝም አብዮት እንዴት?

ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ‹‹በተበጣጠሰ መንገድ›› ቱሪዝምን ለማሳደግ ከመዳከር በመውጣት፣ የአገሪቱ ቱሪዝም ኢንዱስትሪ ካለበት አዝጋሚ ጉዞ እንዲላቀቅ ጥረት ተጀምሯል፡፡ ለዚህ አንዱ ማሳያ በጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ የሚመራው ‹‹የኢትዮጵያ ቱሪዝም ትራንስፎርሜሽን ምክር ቤት›› መቋቋሙ ነው፡፡ ይህ ምክር ቤት እስካሁን የተለያዩ ተግባራትን ያከናወነ ሲሆን፣ በቅርቡ እንደተዘገበው ‹‹ኢትዮጵያ የ13 ወር ፀጋ›› (13th Months of Sunshine) የሚለውን የቱሪዝም መለያ (ብራንድ) ‹‹ኢትዮጵያ ምድረ ቀደምት›› (Ethiopia Land of Origins) በማለት ቀይሮታል፡፡ የአገሪቱ የቱሪዝም አባት የሚባሉትን አቶ ሀብተ ሥላሴ ታፈሰ ዕውቅና ከመስጠት ባሻገር የዘርፉን አንቀሳቃሾች በተቀናጀ መንገድ ችግራቸውን (የመልካም አስተዳደር፣ የብድር፣ የፀጥታና ደኅንነት እንዲሁም የገጽታ ግንባታ) ለመቅረፍ የጀመራቸው ሥራዎች እንዳሉ ይደመጣል፡፡

ይሁንና አገሪቱ የብዝኃ ባህል፣ ልዩ ልዩ እምነቶች፣ ታሪክና የተፈጥሮ ሀብቶች ባለቤት ከመሆን ባለፈ ከትልቁ የራስ ዳሸን ተራራ እስከ አፋር ዝቅተኛው ቦታ (ዳሎል) የታደለች ነች፡፡ በአየር ንብረት ክልልና በተፈጥሮ ሀብት ስብጥርም ከታደሉ ጥቂት የዓለም አገሮች አንዷ እንደሆነች ተገንዝቦ በተከታታይ ማስተዋወቅና ራስን መሸጥ፣ ቱሪዝምን በሁሉም መስክ ማበረታታት እየተቻለ አይደለም፡፡ አዳዲስ የባህልና ቱሪዝም ውጤቶች (Products) ይዞ ወደ ገበያ በመቅረብ ረገድም ውስንነት አለ፡፡

በተለይ እንደ አገር የዚህች አገር ዜጎች የቱሪዝም መስኩን ዕምቅ አቅሞች አሟጦ ለመጠቀም ያላቸው ተነሳሽነትና መቀናጀትም እዚህ ግባ የሚባል አይደለም፡፡ እውነት ለመናገር ከተፈለገ የፖለቲካ እሰጥ አገባውን (ጥላቻና የቂም በቀል ሽኩቻው) ክፉኛ አጥሎባታል ለማለት ይቻላል፡፡ በሠለጠነው ዓለም በውጭ የሚኖሩ ዜጎች ‹‹የአገር ዲፕሎማት ናቸው›› የሚባሉበት መተማመኛ፣ በእኛ አገር የሚሠራ አይመስልም፡፡

ለአባባሉ ጥሩ ማሳያ የሚሆኑት በድህነትም ሆነ የተሻለ ገቢ ለማግኘት የሚሰደዱ ሰዎች በውጭ አገር የሚደርስባቸው ምሬትና እንግልት ብቻ አይደለም፡፡ ይልቁንም ‹‹ከአገር ውስጥ ይቅል በውጭ መማርና መሥራት ይሻለኛል›› ብሎ የሄደው፤ በትጥቅም ሆነ በፖለቲካ ትግል የተሸነፈው ወይም ያኮረፈው በሚሊዮን የሚቆጠር ኃይል የአገሩን ገጽታ ለማጠልሸት ወደ ኋላ የማይል መሆኑ ነው፡፡ ከ30 ዓመታት በፊት የነበረን የድርቅና የጦርነት ምሥል ግድግዳው ላይ ሰቅሎ የቀረና የንግግሩ ማጣፈጫ የሚያደርግ ‹‹ኢትዮጵያዊ›› ቁጥሩ ትንሽ አይደለም፡፡ አገርንና ፖለቲካን ነጣጥሎ ሳይመለከት ‹‹የኢሕአዴግ ኢትዮጵያ›› እያለ በወገኑ ላይ ጥላሸት የሚቀባ ስንቱ ነው?

ከዚህ አንፃር ሲታይ የትራንስፎርሜሽን ምክር ቤቱም ሆነ ራሱ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ስለመቀናጀት ሲያስቡ ይህንንም ማየት አለባቸው፡፡ ጠንካራ ብሔራዊ መግባባት (ለእኔ ወደ ዕርቅ የቀረበ መደማመጥ ሊፈጠር ይገባል) ሳይኖር አንዱ በውስጥም በውጭም የአገር ገጽታ እያፈረሰ፣ ሌላው የቱሪዝም ቢሮዎች ‹‹ገነባን›› ቢል ፍሬ ሊያፈራ አይችልም፡፡ እዚህ ላይ ዕውን የአገሪቱ አስጎብኝ ድርጅቶች (በተለይ አንዳንዶቹ)፣ ሆቴሎችና ተያያዥ አገልግሎት ሰጪዎች ለአገር ስምና ለገጽታ ተጨንቀው ነው እንግዳን የሚያስተናግዱት ማለት ያስፈልጋል፡፡ ከቱሪዝም ብራንድ ጀምሮ በአገራዊ ቅርሶችና ታሪክ ላይ ያለን አረዳድና እምነት አገርን ያማከለና የተዋሀደ ነው (አንድ አስጎብኝ የአፄ ምኒልክ ሐውልት ለውጭ እንግዳ ሲያስረዳ የሰማሁት እስካሁን አግራሞትን ይጭርብኛል)፡፡

በመሠረቱ የራሷ ፊደል፣ ቋንቋና ዜማ ያላት አገር (በውስጥ ሁላችንም የምንኮራባቸው ሀብቶች ባይመስሉም)፣ ከአሥር የማያንሱ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) የተመዘገቡ ቁሳዊና መንፈሳዊ ቅርሶችን ታጥቀን፣ በዓደዋ የጥቁር ሕዝቦች ድል፣ ቀዳሚነታችን በሰው ልጅ መገኛነት እየተወሳ፣ እንደ ኢትዮጵያ አየር መንገድ ያለ የቱሪዝም ዓርማ ገንብተን፣ የአፍሪካ መዲና ሆነን. . . በዓመት አንድ ሚሊዮን ቱሪስት መሳበ አቃተን ሲባል የሚገኘው አንዱ ክፍተት፣ ይኼው የተቀናጀና የተዋሀደ አገራዊ ገጽታን የመገንባት ተነሳሽነት መጉደል ነው የሚል እምነት አለኝ፡፡ በነገራችን ላይ በ2008 ዓ.ም. 910 ሺሕ የውጭ ቱሪስቶች ወደ አገር ውስጥ የገቡ ሲሆን፣ 3.4 ቢሊዮን ዶላር እንደገባ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል፡፡ ይህ አኃዝ በዘንድሮው አገራዊ ሁኔታ መሽቆልቆሉም ተገምቷል፡፡

ከዚህ እውነታ አንፃር የሚመለከታቸው መንግሥታዊ አካላት ብቻ ሳይሆኑ ሁሉም መንግሥታዊ መዋቅር፣ በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ የሚኖረው ዜጋና  ምሁራንና ልዩ ልዩ የኅብረተሰብ ክፍሎችን ሊያሳልፍ የሚችል የቱሪዝም አብዮት መቀስቀስ ያስፈልጋል፡፡ ለዚህም ከወዲሁ እርሾውን አጠናክሮ መጀመር ጎን ለጎን አንድ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ማኅበረሰብም ለመገንባት እንደሚያግዝ መገመት ይገባል፡፡

ያልተነካው የአገር ውስጥ ጎብኚ አቅም

እንደ የዓለም ጉዞና ቱሪዝም ምክር ቤት (WITC) መረጃ ቱሪዝም በአሁኑ ወቅት ለ300 ሚሊዮን ሰዎች የሥራ ዕድል የፈጠረ ነው፡፡ ቱሪዝም በባህሪው ብዙ ሠራተኞችንና የሥራ ዕድሎች የሚፈጥር (Labor Intensive) በመሆኑ፣ ለወጣቶችና ለሴቶች ከፍተኛ የሥራ ዕድል መፍጠር ያስችላል፡፡ በዚሁ መረጃ መሠረት እ.ኤ.አ. በ2020 የዓለም ጎብኚዎች ቁጥር ከ1.6 ቢሊዮን በላይ፣ ኢንቨስትመንቱና የገንዘብ ፍሰቱም ከ15 ትሪሊዮን ዶላር በላይ ይሆናል፡፡ ከዚህ ግዙፍ ሀብት ምን ያህል ሊገኝ ነው? ጥያቄው፡፡

በእርግጥ የቱሪዝም መስህብና የኢንዱስትሪው ገቢ ሲባል ከውጭ ወደ ውስጥ የሚወጣውን ጎብኚ ብቻ አይደለም፡፡ ይልቁንም የአገር ውስጥ ጉብኝት ባህል ቢጠናከር በመስኩ ከፍተኛ የሥራ ዕድል ይፈጠራል፡፡ ተጨማሪ በቢሊዮን የሚገመት ሀብትም ሊገኝ ይችላል፡፡ የእርስ በርስ ትውውቁና አንድነቱም እየጎለበተ ይሄዳል፡፡ አሁን የሚታየው ግን መንግሥት በፈየዳቸው ዓውደ ጥናቶችና ዓውደ ርዕዮች፣ እንዲሁም ፌስቲቫሎች (የብሔር ብሔረሰቦች ቀን፣ የከተሞች ቀንና የአርሶ አደሮች ቀን. . .) እና የፕሮጀክት ምርቃቶች ያለፈ ማኅበራዊ የጉብኝት ተነሳሽነት አልተጠናከረም፡፡ ምናልባት በአንዳንድ ሃይማኖት ተከታዮች እየተጠናከረ የመጣው መንፈሳዊ ጉዞ እንደ መልካም ጅምር ሊታይ ይችል ይሆናል፡፡

ይህን ድፍረት የተሞላበት ትችት የምንሰነዝረው በፍጥነት እያደጉ ከመጡት ታዳጊ አገሮች አንፃር ያለንበትን ሁኔታ ለመመዘን ነው፡፡ በቀዳሚነት ቻይናን መጥቀስ ይቻላል፡፡ ‹‹World Ometres›› የተባለ ድረ ገጽ በቅርቡ ባወጣው መረጃ መሠረት፣ ከ1.4 ቢሊዮን በላይ ሕዝብ ያላት ቻይና በአገርህን እወቅ ክበባት በአሥር ሚሊዮን የሚቆጠሩ በማደራጀት በንግድ፣ በጉዞ፣ በጉብኝትና በገጽታ ግንባታ ሥራ ላይ አሰማርታለች፡፡ ምሁራኑም የአገር ገጽታ በመደገፍና ሙያዊ እገዛ በማድረግ ወደ ተጠቃሚነት ያሸጋግሯቸዋል፡፡ የአገር ውስጡ ጉበኝቱም መቶ ሚሊዮኖችን በማነቃነቅ እስከ 24 በመቶ የአገሪቱን የቱሪዝም ገቢ የሚሸፍን ሆኗል፡፡

130 ሚሊዮን የሚደርስ ሕዝብ ያላት ጃፓንም ‹‹ባህል፣ ተፈጥሮና ወዳጅነት›› በሚባል መሪ ሐሳብ ጠንካራ ብሔራዊ መግባባት የአገርህን ዕወቅ ባህል ገንብታለች፡፡ የአገሬው ሕዝብ አይደለም ድንቅ ቅርፅና ባህልን መጎብኘት ይቅርና ተራራ መውጣት፣ በረዶ መንሸራተትና በፍል ውኃ መታጠብ. . . የዕለት ተዕለት ሕይወቱ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ቅርስና ታሪክ በከፍተኛ እንክብካቤና አድናቆት ከትውልድ ወደ ትውልድ በማስተላለፍ ብቻ ሳይወሰን፣ የትም አገር የረገጠ ጃፓናዊ ‹‹አገሬን ጎብኙልኝ?›› ብሎ ሳይቀሰቅስ መመለስ ነውር አድርገውታል፡፡ ጃፓኖች የማስታወቂያና የገጽታ ግንባታ ሥራቸው ልምድ የሚቀሰምበት ነው፡፡

የህንድና የመካከለኛው ምሥራቅ አገሮች (በተለይ አብዮትና ጦርነት ያልመታቸው) የአገር ውስጥ ቱሪዝም ብርታት እንተወውና የደቡብ አፍሪካን እንኳን ብንፈትሽ ‹‹ግሩም›› የሚባል ነው፡፡ ከ55 ሚሊዮን ከማይበልጠው የአገሪቱ ሕዝብ ውስጥ በየዓመቱ እስከ አምስት ሚሊዮን የሚደርሱ የአገር ውስጥ ጎብኝቶች (ያውም ቅርሳቸው በፓርክና በዱር እንስሳት ወይም በመናፈሻ ላይ ያተኮረ ነው) ይንቀሳቀሳሉ፡፡ በዚህም በአሥር ሺዎች ለሚቆጠሩ ዜጎች የሥራ ዕድል ከመፍጠር ባሻገር ከዘርፉ ቢሊዮን ዶላሮችን ይሰበሰባሉ፡፡

እንግዲህ እነዚህን አብነቶች ማንሳታችን የአገራችን የአገር ውስጥ ጉብኝት አለመጠናከር ለማንሳት ቢሆንም፣ በቀጣይ ከዚህ ችግር መውጣት እንደሚያስፈልግ ለመጎትጎትም ነው፡፡ ‹‹ቱሪዝም የኢትዮጵያን ድንቁርናና ኋላ ቀርነት በግልጽ ለውጭ አገር ሰዎች ከማሳየት የዘለለ ፋይዳ የለውም፤›› ከሚለው ወግ አጥባቂ መሳፍንትና ምሁራን አስተሳሰብ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣውን ዘርፍ የልቃቂቱን ውል ለመፈለግም ነው፡፡

እንዲያውም ለነገሩ ዓለም በመረጃ አንድ መንደር ሆና የቴክኖሎጂ ተጠቃሚነትና የመሠረተ ልማት አመቺነቱ እያደገ፣ በዘርፉም ሆነ በሌሎች መስኮች ዩኒቨርሲቲዎች እየተስፋፉ. . . ለምን መፈላለግና ‹‹ልየው›› ማለት ራቀን? ምናልባት የሕዝቡ የገቢ አቅም ዝቅተኛ ነው ቢባል እንኳን ከነፍስ ወከፍ ገቢ ማደግም በላይ በቅንጦት የሚኖረውና ከፍተኛ  ገቢ ያለው አንዳንዱ የከተማ ነዋሪ ጋር እንኳን የመጎብኘት ባህል አላደገም (ከአዲስ አበባ ሶደሬና ላንጋኖ ለሽርሽር ከመሄድ የዘለለ አይደለም)፡፡

ከዚህ አንፃር ከትምህርት ቤቶች ጀምሮ በዩኒቨርሲቲዎች (በእነዚህ መስኮች እስከ 27 ሚሊዮን ሕዝብ እንደተሰማራ ይታወቃል) ከመንግሥት መሥሪያ ቤቶች፣ ከግል ኩባንያዎችና ድርጅቶች፣ እንዲሁም ከልዩ ልዩ ማኅበራዊ ግንኙነቶች (ዕድር፣ ዕቁብና መንፈሳዊ ማኅበራት) ጭምር ጉዳዩን እንዲያስቡበት ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ ለዚህ ደግሞ የፌዴራል መንግሥትና ክልሎች ብቻ ሳይሆኑ የተለያዩ የዘርፉ አንቀሳቃሾች (ባለሆቴሎች፣ ቱር ኤጀንቶችና አስጎብኚዎችም) በተቀናጀ መንገድ የማበረታቻ ሥርዓት መዘርጋት አለባቸው፡፡ ከሌሎች አገሮች ልምድ መውሰድም ያስፈልጋል፡፡

ማጠቃለያ

በኢትዮጵያ ‹‹የቱሪዝም ኢንዱስትሪው አላደገም›› የሚል ጭፍን ድምዳሜ የለኝም፡፡ በአገሪቱ መንግሥት የገጽታ ግንባታና ዲፕሎማሲም ይባል በነበሩን ዘመን ተሻጋሪ ቅርሶችና ታሪኮች ምክንያት ቢያንስ መቶ ሺዎች የውጭ ሰዎች ጎብኝተውናል፡፡ አሁንም የእኔ መሞገቻ ግን ካሉን በርካታ ቅርሶችና ከሌሎች አገሮች አንፃር ሲነፃፀር ጥቅሙ አይበቃንም ነው፡፡ በርካታ አሥር ሺዎች ወጣቶችና ሴቶችን በዘርፉ ልናሰማራበት ሲገባ ውሉ እንዳጠፋባት ልቃቂት እዚያም እዚህም ከመጎልጎል አልፈን፣ በውል እየተረተርነው አይደለም የሚል መከራከሪያ ላይ ነኝ፡፡ ከዚህ አንፃር እንደ መፍትሔ፡-

  • ዓለም አቀፍ የቱሪዝምና የጉዞ ንግድ ትርዒትን ማሳደግ በቀዳሚነት ሊሠራበት ይገባል፡፡ ይህን ዕድልም በውስን በጀት በውጤታማነት ለመጠቀም ቅድመ ዝግጅትና ብቃት ያለው የሰው ኃይል መጠቀም ያስፈልጋል፡፡ ከዚህ ቀደም በጀርመን በርሊንና በእንግሊዝ ለንደን በኋላም በቻይና ቤጂንግ ከተማ የተካሄዱ ተሳትፎዎች ነበሩ፡፡ ግን ምን ያህል ከፖለቲካ ትብት አውጥተን፣ በአቅምና ተወዳዳሪነት ተጠቀምንባቸው? ምንስ ትርፍ አገኘን?  የተማርነውስ? ብሎ በመፈተሽ በቀጣይ መጠናከር ይገባል፡፡
  • ማስተዋወቅና ራስን መሸጥ ላይ ዓለም አቀፍ ገበያን መቀላቀል ያስፈልጋል፡፡ ጎረቤቶቻችን እነ ኬንያና ኡጋንዳ ሳይቀሩ ሲኤንኤንና አልጄዚራን በመሰሉ ተፅዕኖ ፈጣሪ ጣቢያዎች ማስታወቂያ ይሠራሉ፡፡ ይህን አልፎ አልፎ ካልሆነ በስተቀር የኢትዮጵያ አየር መንገድ እንኳን ብዙም ሲገፉበት አይታይም፡፡ እርግጥ በጃፓንና በቅርቡ በአሜሪካ የተደረጉ የቢዝነስ መድረኮች የሚዲያ ሽፋንም አግኝተዋል፡፡ ግን በተጨባጭ ራሳችንን የምንሸጥበት ምቹ ሁኔታና ማበረታቻዎችን የምናስተዋውቅበት ሥልትን ማጠናከር ሥልጣኔ ነው፡፡
  • በውስጥ የሆቴልና አስጎብኝዎቻችን ደረጃና መጠንም ይበልጥ መሻሻል አለበት፡፡ በእርግጥ በአንደኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን በርካታ ድርጅቶች ተፈጥረዋል፡፡ ለምሳሌ ባለፈው ዓመት ደረጃ ከወጣላቸው የመዲናችን ሆቴሎች ግን አራት ሆቴሎች ብቻ ባለ አምስት ኮከብ ሲሆኑ፣ 13 ባለ አራት፣ 25  ባለ ሦስት፣ 19 ባለ ሁለት ኮከብ ሲሆኑ፣ ቁጥራቸው ትንሽ የማይባሉ ከዜሮ በታች ሆነዋል፡፡ ይህ ቁጥር ደግሞ ከእነ ግብፅ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ሞሮኮ፣ ኬንያ፣ ሞሪሺየስና ኡጋንዳ እንኳን ያነሰ ነው፡፡ ስለዚህ የመስኩ ዋነኛ ችግር የሆነውን ጥራትና ተወዳዳሪነት በተለይ በሰው ኃይልና አቅርቦት ረገድ ማረም ያስፈልጋል፡፡
  • የአገር ውስጥ ጉብኝትን የማጠናከሩ ጉዳይም ከላይ በተጠቀሰው መንገድ የብሔራዊ መግባባትና የአብሮነት እሴትንም ለመፍጠር በሚደረግበት ደረጃ  መጎልበት አለበት፡፡ እዚህ ላይ መንግሥትና ባለድርሻ አካላት አዲስ ዓይነት መላ ሊያበጁ ይገባቸዋል፡፡ ከዚህ አንፃር ክልሎች በዘርፉ የጀማመሯቸውን የተናጠል እንቅስቃሴዎች በማቀናጀት፣ ዘርፉ በምሁራንና በጥናት እንዲመራ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ ቱሪዝም ከፖለቲካ ልዩነትም በላይ አገራዊ አንድነትና ኅብረት እንደሚፈልግ ተረድቶ መነሳትም ለነገ የሚባል ጉዳይ አይደለም፡፡

     ከአዘጋጁ፡ጽሑፉ የጸሐፊውን አመለካከት ብቻ የሚያንፀባርቅ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

 

Standard (Image)

‹‹እነሆ መንገድ ለኢትዮጵያ››ን እንደ ገመገምኩት

$
0
0

በመታሰቢያ መላከ ሕይወት ገብረ ክርስቶስ

 

የመጽሐፉ ርዕስ ‹‹እነሆ መንገድ ለኢትዮጵያ›› የሚል ሲሆን መጽሐፉ በዋናነት የሚያጠነጥነው በአንድ ሐልዮት (Theory) ዙርያ ነው፡፡ ይኼም ሐልዮት የልቦና ውቅር ለውጥ (Paradigm Shift) የተሰኘ ነው፡፡ መጽሐፉ በ188 ገጾች ብቻ የተጻፈ ሲሆን፣ በውስጡ ግን እጅግ በበርካታ መረጃዎችና ለውጥ አምጪ አስተሳሰቦች የታጨቀ ነው፡፡ ነገር ግን የልቦና ውቅር ለውጥ የሚለውን ሐልዮት ለመተርጎም አንባቢ የግድ አንድ መቶ ገጾችን መጓዝ ግድ ይለዋል፡፡

ፕሮፌሰር ዳንኤል ቅጣው ይኼንን ቲዎሪ ሲያብራሩት ገጽ 101፣ ‹‹የልቦና ውቅር ለውጥ (Paradigm Shift) የምንለው ጉዳይ ሰፊ መሠረት ያለውና ጥልቅ የሆነ ጽንሰ ሐሳብ ነው፡፡ የልቦና ውቅር ማለት አንድ ሰው ከወላጆቹ፣ ከቤተሰቡ፣ ከማኅበረሰቡ፣ ከመምህራኑና ከአካባቢው ጭምር የሚያገኘው ይዞት የሚያድገውና የሚዋሀደው ማንነቱ ነው፤›› ይሉናል፡፡

እኔም ራሴ (የዚህ ጽሑፍ አቅራቢ) ይኼንን ቃል ከዚህ በፊት ሰምቼው ስለማላውቅ ለመረዳት ትንሽ ጊዜ ወስዶብኝ ነበር፡፡ ዋናው ቁም ነገር ግን ይኼ አስተሳሰብ በፕሮፌሰሩ ዕይታ (እኔ እንደሚገባኝ) በአገራችን ኢትዮጵያ አሁን ላለብን መሠረታዊ ችግር እንደ ዋነኛ ምክንያት ያስቀመጡት ይመስለኛል፡፡

ጸሐፊው በመጽሐፋቸው ውስጥ እጅግ የተለሳለሱ አማርኛዎችን ብቻ በመጠቀም ለማቅረብ ሞከሩ እንጂ፣ መሆን የነበረበት የልቦና ውቅር ለውጥ በዋናነት ከከፍተኛ የመንግሥት አመራሮች መጀመር እንዳለበት አስረግጠው መጻፍ ነበረባቸው፡፡ በዓለማችን በየትኛውም አገር የተመዘገበ ሥልጣኔ የልቦና ውቅር ለውጥ ከመንግሥት እስከ ታችኛው የኅብረተሰብ ክፍል ሳያካሂዱ ሥልጣኔ የመጣበት ሁኔታ የለም፡፡ ጸሐፊው ዘርዘር ባለ ሁኔታ የሲንጋፖርን ልምድ ያካፈሉን ሲሆን፣ የልቦና ውቅር ለውጥ በማምጣት አሁን በዓለማችን ታላቅ ሥልጣኔ እያመራች ስላለችው ቻይና ምንም ሳይሉን አልፈዋል፡፡

ያም ሆነ ይህ መጽሐፉ በአሁኑ ወቅት ለማንም ኢትዮጵያዊ ከመንግሥት ባለሥልጣን እስከ አንደኛ ደረጃ ያለ ተማሪ ሰብዕና ላይ ከፍተኛ ለውጥ ሊያመጣ የሚችል መጽሐፍ በመሆኑ፣ ማንኛውም ሰው አንብቦ በሕይወቱ ላይ አንድ ተጨባጭ ለውጥ ለማምጣት ቢጥር መልካም ነው እላለሁ፡፡

በተለይ ወላጆችና አስተማሪዎች መጀመርያ ራሳቸው በማንበብና ለልጆቻቸው ለተማሪዎቻቸው በማስረዳት ከተጠቀሙበት ጠቀሜታው እጅግ ትልቅ ነው፡፡

የመጽሐፉ የመጀመርያው ክፍል በአመዛኙ ምክር አዘል ትምህርቶችን የያዘ ሲሆን፣ ቁም ነገሮችና ሳይንሳዊ ትንታኔዎች የሚጀምሩት ወደ መሀል ገባ ሲባል ነው፡፡  

በዓለማችን ከተካሄዱት አብዮቶች አንዱና ትልቁ በቻይና የተካሄደው የባህል አብዮት ሲሆን፣ ይኼ አብዮት በቻይናውያንና ከዚያም በመላው ደቡብ ምሥራቅ እስያ አብዮቱ እንዲቀጣጠል ታላቅ አስተዋፅኦ ያበረከተ ነው፡፡ ይኼ አብዮት የቻይና ሕዝብ የልቦና ውቅር ለውጥ ለማምጣትና አሁን ቻይና የደረሰችበት የዕድገት ደረጃ እንድትደርስ ታላቁን መሠረት የጣለ እንደሆነ ይታመናል፡፡ በመሆኑም ይኼ ክስተት የዚህ ታላቅ መጽሐፍ አካል መደረጉ ጠቃሚ ነው የሚል ዕምነት አለኝ፡፡

ከዚህ ቀጥሎ መጽሐፉ ውስጥ ካሉ ይዘቶች ጠቀስ ጠቀስ እያደግረኩ ልለፍ፡፡ መጽሐፉ ገና ሲጀምር በህንዳዊው ማሕተማ ጋንዲ ጥቅስ ነው የጀመረው ‹‹አቅጣጫው የተሳሳተ የተጣደፈ ሥራ ፍፃሜው ከንቱ ድካም ነው፡፡›› ይኼ አባባል አገራችን አሁን ያለችበትን ሁኔታ በጥሩ መንገድ የሚገልጽ ይመስለኛል፡፡ በአገራችን በአሁኑ ጊዜ በርካታ ነገሮች እየተሠሩ ነው፡፡ ነገር ግን ሕዝባዊ እርካታንና ማኅበራዊ ለውጥ እያመጡ አይደለም፡፡ ይኼ ማለት እየሄድንበት ያለውን ወይም የመረጥነውን አቅጣጫ በሁሉም መስክ ቆም ብለን ለመመርመር የምንገደድበት ወቅት ላይ ነን፡፡ አለበለዚያ ሄደን ሄደን በጥቅሱ እንደተገለጸው ከንቱ ወደ ሆነ ውጤት ነው የምንደርሰው፡፡

‹‹ቀበቶውንና የጫማ ክሩን ከመጀመርያው በትክክል ያላሰረ ሯጭ ዕጣ ፈንታው መሀል መንገድ ላይ ቆሞ እንደገና ለማጥበቅ መሞከርና ውጤቱም ሽንፈት ይሆናል›› (ገጽ 32)፡፡

‹‹ሥራን ከጅማሬው በትክክል መሥራት ሁልጊዜም በትክክል መሥራት የሚለው ጽንሰ ሐሳብ ከልጅነት ጀምሮ ዳብሮና ጎልቶ ባህል መሆን የሚገባው ጉዳይ ነው›› (ገጽ 33)፡፡

‹‹ብልሆች ከሌሎች ይማራሉ ሞኞች ከራሳቸው ስሕተት ሊማሩም ላይማሩም ይችላሉ›› H.Bohn (ገጽ 74)፡፡

‹‹ዓለም የውድድር መድረክ መሆኗ ይታወቅ፡፡ እያንዳንዷ ሰከንድም በለውጥ ሕግ ውስጥ እያለፈች ነው›› (ገጽ 77)፡፡

‹‹ገፊ ምክንያቶች የተባሉት የመጀመርያው ደንበኛው የመጠየቁ ጉዳይ ነው፡፡ ደንበኛ ሁሌ የሚፈልገውን ይጠይቃል፡፡ በዚህም ምክንያት ደንበኛ ገበያውን ይመራዋል ማለት ነው፡፡

ዛሬ ውድደርን በድል መወጣት የማሸነፍ ጉዳይ ሳይሆን በገበያ ውስጥ ለመቆየትና የህልውና ጉዳይ ነው፡፡ የውድድሩ ሕግ ደግሞ የሚመራው በአነስተኛ ዋጋ ከፍ ያለ ጥራትና መልካም አገልግሎት በፍጥነት በማቅረብ ላይ የተመሠረተ ነው›› (ገጽ 78)፡፡

‹‹ደካሞችንና ሰነፎችን አቅፎ በመያዝና በመደገፍ አገር አታድግም፡፡ ሰውን የሚያከብር ደግሞ ራሱም በምላሹ ይከበራል፡፡ ዋናው ጉዳይ የሰው ሀብት ልማት ነው›› (ገጽ 88)፡፡

‹‹ጥራትና ምርታማነት በአመለካከት ለውጥ ላይ የተመሠረተ እንጂ የአንድ ሰሞን ሙከራ ድርጊት አይደለም፡፡ እንደ ግለሰብም እንደ ተቋምም ሆነ እንደ አገር ቁርጠኛና ጠንካራ ውሳኔ በየረጃው መወሰኑ የግድ ነው፡፡ በሲንጋፖርም የተሳካ የዕድገት ጉዳይ ላይ ደተደረገው ጠንካራ ውሳኔዎችን በየደረጃው ያለማወላወል በመውሰድ ነው›› (ገጽ 94)፡፡

‹‹ሲንጋፖሮች በሃያ ዓመታት ውስጥ ሦስቱንም ዋና ዋና የለውጥ አንኳሮች አሳክተው ነው ለስኬት የበቁት›› (ገጽ 97)፡፡

‹‹ትልቁ ችግር ሰዎች አዲስ ሐሳብን እንዲቀበሉ ማድረግ ሳይሆን አሮጌውን እንዲጥሉ ማድረግነው›› John M.Keynes (ገጽ 100)፡፡

ይኼ አባባል አሁን ባለው የአገራችን ተጨባጭ ሁኔታ ትልቅ ቦታ ሊሰጠው የሚገባ ነው፡፡ እኛ ኢትዮጵያውያን ለዕድገት የማይመቹ በርካታ ጎታች ባህሎችን ይዘን ሥልጣኔ በብድር ገንዘብ ለመገንባት እየሞከርን ነው፡፡ ይኼ አካሄድ ያለ ጥርጥር እጅግ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ነው የሚከተን፡፡

አሁን ሥልጣን ላይ ያለው መንግሥት የኢትዮጵያን ሕዝቦች የልቦና ውቅር የሥልጣኔ ሕጎች ከሚያዙት የልቦና ውቅር ጋር እንዲጣጣም ማድረግ ካልቻለ፣ በዜጎች ሕይወት ላይ ለውጥ ሊያመጣ የሚችል ዕድገት ሊመጣ እንደማይችል መገንዘብ አለበት፡፡ ምክንያቱም ሁሉም አመርቂ ዕድገት ያስመዘገቡ አገሮች የሄዱበት ሒደት ይኼ በመሆኑ፡፡

አቶ በረከት ስሞኦን ‹‹የሁለት ምርጫዎች ወግ›› በሚለው መጽሐፋቸው ላይ የኢትዮጵያ ሕዝብ በዓመት ከ100 ቀናት በላይ በበዓላት እያሳለፈ ዕድገት ሊመጣ እንደማይችል ጠቁመው ነበር፡፡ የሚገርመው እኚህ ሰው ይኼንን የጻፉት ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጎን ቁጭ ብለው ቤተ መንግሥት እያሉ ነው፡፡ በአገሪቱ ወሳኝ ሥልጣን ለረጅም ዓመታት የያዘ ሰው እንዲህ ዓይነት አስተያየት መስጠት ይችላል ወይ?

‹‹የልቦና ውቅር ለውጥና ትራንስፎርሜሽን ይመሳሰላሉ፡፡ የቢራቢሮን ሕይወት ዑደት ብንመለከት መጀመርያ እንቁላል፣ ቀጥሎ ዕጭ፣ ከዚያ አባጨጓሬ ቢሆን ለውጡ ቀጥሎ በርካታ እግሮች ያሉት አባጨጓሬ በመጨረሻ ወደ አስደናቂ በአየር የሚበር ቢራቢሮነት ይለወጣል›› (ገጽ103)፡፡

‹‹አንድ ሰው ከልቦና ውቅር ውጪ አልወጣም ካለ የልቦና ውቅር ሽባነት ያግጥመዋል ማለት ነው፡፡ የልቡና ውቅር ልምሻ ደግሞ ለማንኛውም ለግልና የጋራ ሕይወት መስተጋብር ስኬት ከፍተኛ ጠንቅ ነው›› (ገጽ 105)፡፡

 ‹‹አዕምሮን በአንድ አቅጣጫ ላይ ቸንክሮ ከዚያ ውጪ ሌላ አማራጭ የለም ብሎ መደምደም የልቡና ውቅር ልምሻነት ያስከትላል›› (ገጽ 107)፡፡

‹‹የልቡና ውቅር የፈቃድ ውሳኔ ጉዳይ ነው እንጂ የተፈጥሮ ጉዳይ አይደለም፡፡ እኛ ሁላችን አመለካከታችንን በመቀየር ሙሉ ሰዎች ሆነን አገራችንን ወደ ከፍተኛ ደረጃ ልናደርሳት እንችላለን›› (ገጽ 109)፡፡

የዚህ ጽሑፍ አዘጋጅ አስተያየት

የልቦና ውቅር ለውጥ በአንድ አገር ወይም ማኅበረሰብ እንዴት ሊከሰት ይችላል የሚለው ጉዳይ በበቂ ሁኔታ የተብራራ አይመስለኝም፡፡ በእኔ እምነት የልቦና ውቅር ለውጥ በአንድ ማኅበረሰብ አንደኛ አስገዳጅ በሆነ መልኩ (እነ ቻይና እንዳደረጉት)፣ የሕዝብን አስተሳሰብ ባህል የአኗኗር ዘይቤ አስተዳደግ በመቀየር ማምጣት የሚቻል ይመስለኛል፡፡ ሌላው ሁለተኛው መንገድ ትውልድን በትምህርት በማነፅና አዝጋሚ በሆነ መንገድ በረዥም ጊዜ ጉዞ የመለወጥ መንገድ ሲሆን፣ ሦስተኛው መንገድ ኅብረተሰቡ ራሱ ትክክለኛው ወቅት ሲመጣ ከዓለም አቀፍ ኅብረተሰቡ ጋር በተለያዩ መንገዶች በሚደረግ ግንኙነት ምክንያት እስኪለወጥ ዝም ብሎ የመጠበቅ ተግባር ይመስለኛል፡፡

ከላይ ከተጠቀሱት ሦስት አማራጮች በአንድ ኅብረተሰብ ውስጥ ፈጣን ዕድገት ለማየት ምርጫው ሥልጣን የያዘው መንግሥታዊ አካል በመሆኑ፣ ከዚያ ውጪ ያለ ማንኛውም ኅብረተሰብ ሊኖረው የሚችል ተሳትፎ ወይም ተፅዕኖ የመፍጠር አቅም አናሳ ይመስለኛል፡፡

‹‹የሕይወት አጋጣሚ ዝም ብሎ እንዲመራ ከፈቀድንለት በተዘዋዋሪ ሌሎች በእኛ ሕይወት ውስጥ እንዲመሩን ፈቀድንላቸው ማለት ነው፡፡ በሰው ሕይወት ላይ ይመወሰንን ሥልጣን ያገኙ ሰዎች ደግሞ ያሻቸውን የማድረግ ሥራ ለመከወን ዕድል ይሰፋላቸዋል፡፡ በዚያው መጠንም በግልም በቡድንም እንደ አገር የሚደርሰው አካላዊ ክስተት የከፋ ይሆናል›› (ገጽ 121)፡፡

ስለዚህ ዕርምጃ መውሰድ አስፈላጊ ነው፡፡ የምንወስደው ዕርምጃ ደግሞ ቆራጥ ዕርምጃ ሲሆን ውጤቱ ያማረ ይሆናል፡፡ ዛሬ በአገራችን ቆራጥ ዳኞች፣ መምህራን፣ ወታደሮችና አስተዳዳሪዎች ያስፈልጉናል፡፡

‹‹ጉዳዩ እንደ ትራፊክ መብራቶች ነው፡፡ የትራፊክ መብራቶች አረንጓዴ፣ ቢጫና ቀይ ናቸው፡፡ አረንጓዴ የሆነው ምሳሌ እኛ የምንችለውና የተሻለ አድርገን የምንሠራው ነው፡፡ ቢጫው ደግሞ ልንሠራው እንችላለን ነገር ግን አርኪና አጥጋቢ አድርገን መሥራት ያልቻልነው ነው፡፡ ቀይ መብራት ግን እኛ የማንችለውና የማንሠራው ነው፡፡ ብንሠራውም እንኳ ውጤቱ ጥሩ አይሆንም፡፡ ስለዚህ በዚህ ጊዜ ይኼን አልችልም፣ ከእኔ የተሻሉ ሰዎች ይሥሩት ብለን ለሌሎች ማስተላለፍ ይኖርብናል›› (ገጽ 128)፡፡

‹‹ለምሳሌ በእኛ የወጣትነት ዘመን በንጉሡ ሥርዓት ላይ ድንጋይ ወርውረናል፡፡ ባህር ማዶ ተምረን በመጣንበትና እጅግ መሥራትና ለአገር መጥቀም በሚገባን የደርግ ዘመን በ‹‹በጎመን በጤና›› ዘይቤ ከሥርዓቱ ርቀን ኖርን፡፡ እንዲሁም አሁን በሥልጣን ላይ ያለው መንግሥት የአንድ ወጣት ዕድሜ አሳልፏል፡፡ በዚህ ጊዜ ዳር ቆመን ተመልካች ከሆንን የእኛ ለአገርም ይሁን ለወገን የመሥሪያ ጊዜያችን አልቋል ማለት ነው›› (ገጽ 134)፡፡

ሠለጠኑ ወደሚባሉ አገሮች ዓይናችንን ብንወረውር ከላይ የተዘረዘሩትን የሙሉ ሰው ባህርያት የመግለጫ ሰብዕናዎች በአብዛኛው አዳብረዋቸዋል፣ የጋራ ፀባይ አድርጓቸዋል›› (ገጽ 139)፡፡

‹‹አሁን እያነሳነው ያለው ትልቅ የለውጥ ጉዳይ ከዛሬ ሰላሳና ከዚያ በፊት በነበሩት ዓመታት አንስተነው ቢሆን የበለጠ ጥሩ ይሆን ነበር፡፡ ነገር ግን ያኔ አልተጀመረም ተብሎ ዛሬ አይታለፍም፡፡ ሁለተኛው ምርጡ ጊዜ አሁን ነው ብለን መጀመር አለብን›› (ገጽ 146)፡፡

በጣሊያን አገር በትምህርት ላይ ሳለሁ ጣሊያኖችን በጥቂቱም ቢሆን ጠጋ ብዬ ለማወቅ ዕድሉን አግኝቻለሁ፡፡ እነሱ ዛሬ የተባለ ገንዘባቸውን እንደ አምላክ ነበር የሚያዩት፡፡ ጣዖታቸው ነበር፡፡ ሊሬ ስንት ሺሕ ዘመን የሠራ የጣሊያኖች ገንዘብ ነበር፡፡ አውሮፓን የገዛ ነው ብለው የሚመፃደቁበትም ነበር፡፡ ወደ ጀርመኖች ስንመጣ ጀርመኖች ማርክ የተባለ ገንዘባቸውን እንደዚያው ነበር የሚያዩት፡፡ ነገር ግን የዓለም ሥርዓት ሲቀየርና ኢኮኖሚያዊ መዋቅር ሲቀየር ተረዱት፡፡ በአንድ በኩል የምዕራቡ ዓለም በሌላ በኩል ደግሞ የእስያ አገሮች ታላላቅ የኢኮኖሚ ዋልታዎች ሚዛኑን ከግራ ቀኝ ሲወጥሩ፣ አውሮፓውያን ግፊቱን ለመቋቋም ወደ አዲሱ አስተሳሰብና ዘመን መሸጋገር ነበረባቸው፡፡ አውሮፓውያን አንድ ሆነው እስካልቆሙ ድረስ በአዲሱ የውድድር ሥርዓት መቀጠል እንደማይችሉ በመገንዛባቸው ወደ አንድ ወጥ ስምምነት ደረሱ፡፡

ይኼ ሁኔታ ምን ያህል የልቦና ውቅር ለውጥን በአንደ ጊዜ ማምጣት እንደቻሉ የሚያሳይ የሚያስገነዝብ ነው፡፡ በነገራችን ላይ አውሮፓውያን ከ4,000 ዓመት በላይ በመካከላቸው እርስ በርስ መራራ ጦርነት ያካሄዱ ሕዝቦች ናቸው፡፡

የዚህ ጽሑፍ አዘጋጅ

በአጠቃላይ ፕሮፌሰሩ እያስተማሩን ያሉት እጅግ በርካታ ጠቃሚ ጉዳዮችን ነው፡ በዓለም ላይ ያሉ ድንበሮች እየደፈረሱ አገሮች ተጠጋግተውና ተደጋግፈው መራመድ ካልቻሉ የመጨረሻው ውጤት ውድቀት ብቻ እንደሆነ እያስተማሩን ነው፡፡ እኛ ኢትዮጵያውያን እጅግ አሳሳቢ እንደ ድህነት፣ ኋላቀርነት፣ የሥርዓት ዕጦት፣ የንዘብ፣ ወዘተ ችግሮት አሉብን፡፡ ከዚህ በፊት ያልነበሩ ምንም የማይጠቅሙንን ለምሳሌ በብሔሮች መካከል የሌለን ድንበር ፈጥረን በዚሁ ምክንያት እርስ በርስ እያጣላን ስንገኝ፣ ሌሎች አገሮች ድንበሮቻቸውን አፍርሰው የጋራ ኢኮኖሚ አስተሳሰብ እያዳበሩ እያካሄዱ ያሉበት ወቅት ላይ ነን፡፡

ፕሮፌሰር በትንተናቸው እስካሁን የተጓዝነው ጉዞ ጠቀሜታው እንዳለው አልቆጠሩትም፡፡ እነሆ አንድ ብለን እንጀምር እያሉ ነው፡፡ ሰሚ ካገኙ እኔም ይኼ ጉዳይ ሁሌም እያሳሰበኝ ስለነበር የ2000 ዓ.ም. አዲስ ዓመት ሲከበር ‹‹ምንይልክኢዝም›› በሚል ርዕስ ከፕሮፌሰሩ አስተሳሰብ ጋር የሚቀርረብ መጽሐፍ አሳትሜ ለንባብ አብቅቼ ነበር፡፡

ለማንኛውም ውድ አንባቢያን መጽሐፉ ባጭሩ በዚህ መልኩ ለመዳሰስ ሞክሬያለሁ፡፡ የተረፈውን አንብባችሁ ተረዱ፣ በጣም ጠቃሚ መጽሐፍ ነው፡፡

ማንም ሰው ምንም ያድርግ በየትኛውም መንገድ መራመድ እንዳለበት አቅጣጫውን ማወቅና ምርጡን መንገድ መምረጥ የግድ ይላል፡፡ አለበለዚያ እንደነ ሊቢያ፣ ሶሪያ፣ የመን፣ ኢራቅ ዓይነት ውዥንብር ውስጥ ገብተን አገራችንን ማፈራረስ ብቻ ነው፡፡ በአሁኑ ዘመን ግሎባላይዜሽን የሚባል ጎርፍ አለ፡፡ ይኼንን የጎርፍ አቅጣጫ ተከትለን ብቻ ነው መሄድ ያለብን፡፡ አለበለዚያ ጉዞው ሁሉ ውጤት አልባ ነው የሚሆነው፡፡

ከአዘጋጁ፡-ጽሑፉ የጸሐፊውን አመለካካት ብቻ የሚያንፀባርቅ ሲሆን፣ ጸሐፊውን በኢሜይል አድራሻቸው metasebyamelaku@gmail.comማግኘት ይቻላል፡፡      

 

 

 

 

 

   

 

 

 

Standard (Image)

ጊዜ የማይሰጡና አስቸኳይ ተግባራዊ መፍትሔዎችን የሚፈልጉ የአክሲዮን ማኅበራት ችግሮች

$
0
0

 

በሺፈራው ተስፋዬ

ከዕፍታው የቀረበ ማስታወሻ ይህ ጽሑፍ በአገር አቀፍ ደረጃ በአክሲዮን ማኅበራት ላይ ሊሠራ ለታሰበው ጥናት የመነሻ መሠረት እንዲሆን እየተሠራ ካለው የመጀመሪያ ደረጃ ጥናት (Preliminary Study) ግኝቶች ውስጥ፣ ጊዜ የማይሰጡና አስቸኳይ መፍትሔዎች የሚያስፈልጋቸውን ወሳኝ የአክሲዮን ማኅበራት ችግሮችንና የመፍትሔ አቅጣጫዎችን ነቅሶ በማውጣትና በማሳየት፣ የሚመለከታቸው ባለቤቶችና ባለድርሻ አካላት በሙሉ እስካሁን ከታየው ወይም ከደረሰው በላይ ከባድ ጉዳት ከመድረሱ፣ ከፍተኛ የዜጎችና የአገር ሀብትም ከመባከኑ ወይም ከመውደሙ በፊት ተገቢውን ወቅታዊ ዕርምጃ እንዲወስዱ ለማስታወስ ወይም ለማሳሰብ የቀረበ የመጀመሪያ ደረጃ ጥናት ዕፍታ ነው፡፡

ደረጃውን የሰቀለው የ1952 ንግድ ሕግና አዲሶቹ ሙከራዎች

 የአክሲዮን ማኅበራትን የሚመለከቱ ድንጋጌዎች በ1952 ዓ.ም. በታወጀው የንግድ ሕግ ውስጥ በአንቀጽ 6 ሥር የተካተቱ ናቸው፡፡ በአጠቃላይ ሕጉ ሳይሻሻል፣ የአፈጻጸም ደንብና መመርያ ሳይወጣለት በመጪው መስከረም 58ኛ ዓመቱን ያከብራል፡፡ በእርግጥ ቀደም ሲልም ሆነ በቅርብ የንግድ ሕጉን በተለይም የአክሲዮን ማኅበራትን ድንጋጌዎች ለማሻሻል ጥረቶች እንደነበሩ ይነገራል፣ እንዳሉም ይታወቃል፡፡ ቀደም ሲል የተደረጉትን የማሻሻያ ረቂቆች ለጊዜው ማግኘት ያልተቻለ ሲሆን፣ በቅርቡ የቀረቡትን የመጀመሪያ ደረጃ ረቂቆች ለማየት ተችሏል፡፡ ሁለቱም ጥረቶች በርካታ ጠቃሚ ጉዳዮችን ያነሱና የያዙ ቢሆንም፣ ከዚህች አጭር ጽሑፍና ከትኩረቱ ውሱንነት አንፃር ጥቂት ጉዳዮችን ብቻ በማሳየት ማለፍ ተመርጧል፡፡

በቀድሞው ፍትሕ ሚኒስቴር አመራር ከተለያዩ መሥሪያ ቤቶች በተውጣጡ የሕግ ባለሙያዎች ተረቆ የቀረበው ረቂቅ፣ ቀደም ሲል ከተሠሩት ጥናቶች ላይ ትምህርት አልወሰደም፡፡ የራሱም የሆነ መሠረታዊ ጥናት የለውም፡፡ እስከ ዛሬ ያጋጠሙትና ወደፊት ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮችን ከግንዛቤ ሳያስገቡ፣ በአጠቃላይ ሁኔታዎች ግምገማ (General Situational Analysis) ላይ የተመሠረተ በመሆኑ፣ አንዳንድ ረቂቅ ሐሳቦች ያሉትን ችግሮች የሚያባብሱና ከጥቅማቸው ይልቅ ጉዳታቸው ሊያመዝን እንደሚችል በቀላሉ መረዳት ይቻላል፡፡ የመነሻ ሐሳቦቹ ግምታዊ፣ ንድፈ ሐሳባዊና በግል ገጠመኝም ከችግሮቹ ጋር የመተዋወቅ ዕድል ያልነበረ ስለሚመስል፣ በችግሩ ለቆሰለ ሰው፣ በሰው ቁስል እንጨት እንደ መስደድ ዓይነት ተደርጎ ሊታይ ይችላል፡፡ ከፍተኛ ቀውስ ውስጥ የገቡት አክሲዮን ማኅበራት በተግባር (Defacto) በአንድ ሰው ተመሠርተው፣ ምንም ዓይነት ትርጉም ያለው ተሳትፎና ሥርዓት በሌለበት ሁኔታ ሆኖ እያለ፣ አክሲዮን ማኅበራት በአንድ ግለሰብ ይደራጁ የሚል ሕግ ተረቆ ቢፀድቅ ምን ውጤት እንደሚኖረው በጉዳዩ ላይ ትንሽ ቅርበት ያለው ሰው ወይም ትንሽ ማሰላሰል የሚችል ውጤቱን በጥልቀት መረዳት ይችላል፡፡

የአክሲዮን ማኅበራት አባላት ያልሆኑ ሰዎች የቦርድ አባል እንዲሆኑ የሚለውም ሐሳብ ዓላማ፣ ግብና ውጤት ምን እንደሆነ ለመረዳት ያስቸግራል፡፡ ምክንያቱም ባለሙያ ካስፈለገ በቅጥር ወይም በአማካሪነት ወይም በአክሲዮኑ ማስገባት እየተቻለ ማለት ነው፡፡ የመተዳደሪያ ደንብ እንዳይቀርብ ማለት በፍጹም ተቀባይነት አይኖረውም፡፡ ምክንያቱም እንኳን ደንብ ሳይቀርብ ቀርቶ፣ ደንቡ ቀርቦም በሥውር የሚሠራው ተገቢ ያልሆነና ሕገወጥ ሥራ ዓይነቱና ይዘቱ ተዘርዝሮ አያልቅም፡፡ ስለሆነም ግለሰብ የራሱን የግል ተቋም እንጂ የሕዝብ ኩባንያ ማቋቋም የለበትም፡፡ በአንድ በኩል ከላይ የተገለጡት ዓይነት ከባድ ችግሮችን የሚፈጥሩ ረቂቅ ድንጋጌዎች ሲኖሩ፣ በሌላ በኩል ደግሞ ማሻሻያ ተብሎ የቀረበው የአርትኦት (Editing) ሥራ  ይመስላል፡፡ የንግድ ሕግ ማሻሻል በሕግ ባለሙያዎች ብቻ የሚሠራበት ስፋትና ጥልቀት ባለው አገራዊ ጥናት ላይ ለምን እንዳልተመሠረተም ግልጽ አይደለም፡፡ ጥራት ያለው ሥራ ለመሥራት አቋራጭ መንገድ ያለ አይመስልም፡፡ መሥራት ያለበትን ወሳኝ ሥራ መሥራት ግድ ነው፡፡ አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ በተለይ አክሲዮን ማኅበራትን በተመለከተ የንግድ ሕጉን በሚገባ መረዳትና ካለው ተጨባጭ ችግሮች አንፃር ያለውን ትርጉምና አንድምታ በመመርመር፣ በውስብስብ ችግሮች ውስጥ ተዘፍቀው መራመድ ያቃታቸውንና ሀብታቸው፣ ዕድላቸው፣ ድርጅታቸው እየወደመ ያሉትን ለመታደግ የሚያስችል መመርያ በማዘጋጀት፣ በዘመቻ መልክም ቢሆን ጥረት ማድረግ ጊዜ የማይሰጥ በመሆኑ በአስቸኳይ መሥራት ሁለገብ ጠቀሜታ ይኖረዋል፡፡

በንግድ ሚኒስቴር የተረቀቀው ረቂቅ የተሻለ ለችግሮቹ ቅርበት ያለውና መፍትሔም ለመስጠት የሞከረ ነው፡፡ ይህም መሥሪያ ቤቱ ለችግሩ ካለው ቅርበት የተነሳ እንደሆነ ለመረዳት አያዳግትም፡፡ ቢሆንም ረቂቁ ብዙ መዳበር አለበት፡፡ ችግሮቹን ለይቶ ከዚያ አንፃር የሕግ መፍትሔ ማስቀመጥ ብቻ ሳይሆን የችግሮቹን መነሻ መሠረትና አማራጭ መፍትሔዎችን፣ በአክሲዮን የውስጥ ሥርዓትና በሕግ አስከባሪ አካላት መካከል፣ በሚዛናዊነት ማከፋፈልና አፈጻጸሙን ማሳለጥ ያስፈልጋል፡፡ የዚህ ረቂቅ ትልቁ ፈተና፣ የንግድ ሕጉ የአፈጻጸም ደንብ ይሁን ወይስ ይህን እንደ አዋጅ ወስዶ ሌላ የአፈጻጸም ደንብና መመሪያ ይዘጋጅ የሚለው ነው፡፡ ውሳኔው የመሥሪያ ቤቱ ሲሆን የዚህ ጽሑፍ አቅራቢ የግል አስተያየት ቀደም ሲል የቀረበው ነው፡፡

በንጉሠ ነገሥቱ መንግሥት ዘመን የተረቀቁት የንግድ ሕጉን የመሳሰሉት፣ በተለይ አክሲዮን ማኅበራትን የተመለከቱትን ድንጋጌዎች ከ57 ዓመታት በኋላ እንኳ ሕጉን በአግባቡ ማዳበርና ማሻሻል ቀርቶ፣ በአግባቡ ለመረዳትና ለመተግበር አለመቻላችን የሕጉ ጥራትና ደረጃ የላቀ እንደነበረ ያሳያል፡፡ በእርግጥም በዚያን ዘመንም ሕጉ አገሪቱ ከነበረችበት በመቶ ዓመት የቀደመ ነው ሲባል እንደነበረ ይነገራል፡፡ ቢሆንም በዘመናዊ ሕግ አገሪቱን የማዘመኑ ህልም የተሳካ አይመስልም፡፡

የአክሲዮን ማኅበራት የላቀ ሚና በልማት ውስጥ በመርህ ደረጃ የልማት አከናዋኝ አካላት በሆኑት በመንግሥት፣ መንግሥታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች፣ በኅብረት ሥራ ማኅበራት፣ በግል፣ በኅብረተሰብ ምሥረታ ድርጅት፣ በልማት ድርጅቶች፣ በጥቃቅንና አነስተኛ፣ ወዘተ በሁሉም የሚቻለው ሁሉ መሠራት አለበት፡፡ ነገር ግን በትክክል ከተሠራ በዘላቂነት፣ በተደራሽነት፣ መሠረታዊ ለውጥ በመምጣት፣ ከፍተኛ ካፒታል በመፍጠር፣ ከፍተኛ የሥራ ዕድል በመፍጠር፣ ግብር በአግባቡ በመክፈል፣ በግልጽ አሠራር፣ የሌሎችን የልማት አከናዋኞች ሥራ በማገዝና በማመቻቸት፣ ለዴሞክራሲያዊ ቢዝነስና ተቋም አመራር በማለማመድና በማሠልጠን፣ ትርጉም ያለው ሁለንተናዊ ለውጥ በማምጣት፣ ወዘተ በመሳሰሉት መመዘኛዎች ማወዳደር ከተቻለ የአክሲዮን ማኅበራት ሚና የላቀ መሆኑን ማረጋገጥ ይቻላል፡፡ በተለይ በምዕራባውያን አገሮች እስከ አሥር ሚሊዮን ባለአክሲዮን ዜጎችን በአንድ አክሲዮን ውስጥ ብቻ በማሳተፍ ተፅዕኖና ልዩነት ፈጣሪ የቢዝነስ ተቋም መሆናቸው ይታወቃል፡፡

ህንድን የመሳሰሉ እየተመነደጉ ያሉ አገሮች የአክሲዮን ማኅበራትን ዕምቅ ሀብት አሟጦ ለመጠቀም “Corporate Ministry” የሚባል የመንግሥት ተቋም መሥርተው እየሠሩ ነው፡፡ ከአፍሪካ ደቡብ አፍሪካ፣ ናይጄሪያና ኬንያ የመሳሰሉት ይህን ተቋም በሚገባ እየተጠቀሙ እንደሆነ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡ በእኛ አገር በዚህ ረገድ ሕጉ ከተደነገገ ከግማሽ ምዕተ ዓመት በላይ ቢሆንም፣ በተግባር የሚታየው ገና ጅምር ሲሆን፣ የችግሩ ውጥንቅጥነት እጅግ ያስደነግጣል፣ ያስፈራራልም፡፡ የደርግ ሶሻሊስት ርዕዮተ ዓለም ለአክሲዮን የማያመች እንደሆነ የሚታወቅ ሲሆን፣ ያለፉት 26 ዓመታትም አክሲዮን ማኅበራት ተገቢ ቦታቸውን አግኝተዋል፣ ምቹ ሁኔታዎችም ተፈጥሮላቸዋል፣ መሥራት የሚችሉትን ያህልም ሠርተዋል ማለት አይቻልም፡፡ በዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ውስጥ ለጥቃቅንና አነስተኛ የዕድገት ግብ ሲቀመጥላቸው፣ አክሲዮን ማኅበራት ግን ስማቸውም እንኳን ሊጠቀስ አልበቃም፡፡ በሌላ በኩል ዜጎች አክሲዮን ማኅበራት አመቺ ሆነው ስላገኙዋቸው፣ በራሳቸው ተነሳሽነት ያለውን ሕግ በመጠቀም በሺሕ የሚቆጠሩ አክሲዮን ማኅበራትን አቋቁመዋል፡፡ ቢሆንም አመቺ የመንግሥት ፖሊሲ፣ ስትራቴጂና ወቅታዊ ሕግና አፈጻጸም ባለመኖሩና ከሁሉም በላይ ከተወሰኑ አክሲዮን ማኅበራት መሥራቾች፣ ቦርድና ማኔጅመንት በሚመነጩ ችግሮች የተነሳ በዜጎችና በአገር ሀብት፣ የዕድገት ዕድልና ተስፋ ላይ ወደር የሌለው ወንጀል ተፈጽሟል፡፡

ከአክሲዮን ማኅበራት ልማትና ጥፋት ጋር ተያይዞ የሚወደሱና የሚከሰሱ አካላት ቀደም ሲል እንደተመለከተው አክሲዮን ማኅበራት ለአጠቃላይ አገራዊ ልማትና ብልጽግና ትልቅ ሚና ስለሚጫወቱ፣ መሥራቾች ትልቅ ክብርና ምሥጋና ይገባቸዋል፡፡ ክብርና ምሥጋናም ብቻ ሳይሆን ፍትሐዊ ተጠቃሚም መሆን አለባቸው፡፡ በተለይ ምሥረታው የሚጠይቀው ትግልና መስዕዋትነት በአግባቡ ዋጋ ሊሰጠው ይገባል፡፡ ከዚህ ውጭ ለሕዝብ ቃል ገብተው፣ በሕግ መሠረት ተቋቁመው፣ የሕዝብ ሀብት ከሰበሰቡ በኋላ፣ በትክክል ሥራውን ሠርተው ሁሉንም ተጠቃሚ እንደማድረግ ፈንታ የራሳቸውን አሻንጉሊት፣ ተላላኪና አቀባባይ ቦርድና ማኔጅመንት በሥውር ወይም በግልጽ ሰይመው፣ ሁሉን ነገር ለራስ በማድረግ ስግብግብነትና እንዳረጀች ድመት የፈጠሩትን ሁሉ እንብላ ካሉ፣ ወደር የሌለው ጥፋት መሆኑ አይቀርም፡፡ አንዳንድ ጊዜ መሥራቾች የቦርድ ሰብሳቢና የማኔጅመንት አመራርም በመሆን ሥርዓቱንና ሥራውንም ያበላሹታል፣ ሀብቱንም ይዘርፉታል፡፡ ይህ በጊዜያዊና በትንሽ ጥቅም ታውሮ ራስን እንደ ማጥፋት ይቆጠራል፡፡

አንዳንድ ጊዜ ራሳቸው ሁሉንም ቦታ ባይዙም ደካማ ተወካዮቻቸውን ሥልጣን ላይ ያስቀምጡና በሕግና በሥርዓት መሥራት ቀርቶ ተቋሙን ማፍረስ፣ ሥራውን ማበላሸት፣ ሀብቱን መዝረፍ ዋና ሥራ ይሆናል፡፡ ይህ ችግር እንዳይጋለጥ በአክሲዮን ድምፅ ሽፋን መስጠትና የከፍተኛ ባለአክሲዮኖችንም ድምፅ በምሣ ግብዣና በተሳሳተ መረጃ እየጠፋ ባለው ሀብታቸው ላይ የጥፋት ውሳኔ ተባባሪ ለማድረግ ይሞክራሉ፡፡ ትክክለኛውን የአክሲዮን ልማት ሥራ ማከናወን የማይችሉ ቦርድና ማኔጅመንት፣ በእንደዚህ ዓይነት የጥፋት ሥራ ላይ በመሠማራት የዜጎችና የአገር ሀብት፣ የልማት ዕድል እንዲባክን ያደርጋሉ፡፡ በዚህ ዓይነት እየወደመ ያለው የአክሲዮን ማኅበራት ሀብት ምን ያህል እንደሆነ በትክክል መገመት ያስቸግራል፡፡ ሕግና መንግሥት ባለበት አገር እንደዚህ ዓይነት ወደር የሌለው ጥፋት ለዓመታት ሲካሄድ ቆይቷል፡፡ በዚህም የተነሳ በዜጎችና በኅብረተሰቡም ላይ በቀላሉ የማይጠገን ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል፡፡ ስለሆነም ዜጎች ሀብታቸውን፣ ዕውቀታቸውን ጉልበታቸውን አስተባብረው ልማት እንዲያከናውኑና እምነትም እንዲያዳብሩ፣ በሕግና በመንግሥት ላይም እምነት እንዲኖራቸው፣ ኩባንያዎችን ተቆጣጥረው (Company Capture) አድርገው ጥፋት የሠሩት መሥራቾች፣ ቦርድና ማኔጅመንት ለጥፋታቸው በሕግ ሊጠየቁና ፍትሕም ሊበየን የግድ ይሆናል፡፡

የቦርድ አባላትና የማኔጅመንት ምርጫ መመዘኛዎች አንዳንድ የዋህ የሚመስሉ ብልጣ ብልጦች፣ ከፋይናንስ ዘርፍ ውጪ ባሉ አክሲዮን ማኅበራት የቦርድና የማኔጅመንት ምርጫ የቢዝነስ ባለሙያ እንዲሆን ሕጉ አያስገድድምና የሙያ መመዘኛ ማስቀመጥ ሕገወጥ ነው፣ የባለአክሲዮኑንም የመመረጥ መብት ይረግጣሉ ይላሉ፡፡ ይህ የአክሲዮን ማኅበራትን ሥራና የሕጉን ድንጋጌ ይዘትና ፍላጎት በሚገባ ካለመረዳትና የቦርድና የማኔጅመንት ወንበር ላይ ተዘፍዝፎ የሚጠበቅባቸውን ሥራ ሳይሠሩ ወፍራም ደመወዝና ጥቅማ ጥቅም ለማግኘት ከሚቋምጡ ወገኖች፣ ወይም ሁኔታውን በጥልቀት ከማይረዱ ወገኖች የሚሰጥ የዋህ አስተያየት ነው፡፡ አክሲዮን ማኅበራት በብዙ ካፒታል፣ በከፍተኛ ድርጅት የላቀ የሙያ ሥራ የሚያከናውኑ ቦርድና ማኔጅመንት የቢዝነስ ተቋማትን፣ በከፍተኛ የቢዝነስ ሳይንስና ጥበብ የሚመሩበት ነው፡፡ ከፍተኛው አመራር (Top Business Management) ቦርድ ሲሆን፣ መካከለኛው አመራር (Middle Management) ፕሬዚዳንትና ዋና ሥራ አስኪያጅ ተብሎ የሚጠራው ነው፡፡ ሁለቱም ቢዝነስ ፖሊሲ፣ ስትራቴጂ፣ ዕቅድና ቁጥጥር እንዲሁም የምዘናና የግምገማ (Business Analyis and Evaluation) ለመሥራት የላቀ የቢዝነስ ዕውቀት የሚያስፈልጋቸው መሆኑን ሕግ መደንገግ አይጠበቅበትም፡፡ ምክንያቱም ይህ ጉዳይ በእንግሊዝኛው “It Goes Without Saying” እንደሚባለውና በአማርኛው ደግሞ “ሳይታለም የተፈታ ነው” እንደሚባለው በመሆኑ ነው፡፡

ሕግ እንደ ድርሰት ወይም እንደ ታሪክ ዝርዝሩን ሁሉ እንዲጽፍ መጠበቅ የለበትም፡፡ የቢዝነስ ኩባንያን የሚያክል ትልቅ ተቋም መሥርቶ በቢዝነስ ማይማን (Business Ignorant) እንዲመራ በማድረግ ሀብቱንና የሥራ ዕድሉን እንዲጠፋ የሚያደርግ፣ ጤናማ አዕምሮ ያለው ባለሀብት ይኖራል ተብሎ አይታሰብም፡፡ ሁሉም መብትና ግዴታ እንዳለበትና ቢዝነስ የመምራቱን ግዴታ በብቃት መወጣት የማይችል ሁሉ፣ መብት አለኝ ብሎ ሊከራከር አይችልም፡፡ መብት አለን ብለው ቦርድና ማኔጅመንት ወንበር ላይ ተዘፍዝፈው ተቋሙ እጃቸው ላይ እየጠፋ ለምን የቢዝነስ ፖሊሲ፣ ስትራቴጂ፣ ዕቅድ፣ ወዘተ አውጥታችሁ አትተገብሩም ሲባሉ፣ በጉባዔ አዳራሽ ብቻ ሳይሆን በጋዜጣም ላይ ወጥተው ይህን መሥራት አይጠበቅብንም በማለታቸው መሳቂያና መሳለቂያ ሆነዋል፡፡ መቶ በመቶ ያተርፍ የነበረውን ኩባንያ በአሥር ሚሊዮኖች የሚቆጠር ኪሣራ ውስጥ ያስገቡበት ተጨባጭ መረጃ አለ፡፡ ስለሆነም ቦርድና ማኔጅመንት ሥልጣን ላይ ለመውጣት መብቱን ለመተግበር (Exercise) ለማድረግ ኃላፊነትን በብቃት ለመውጣት መቻልና ግዴታን በሚገባ መውጣት ቅድመ ሁኔታ መሆኑ ግድ ነው፡፡

ነገር ግን የቢዝነስ ባለሙያና ሙያ አስፈላጊና ጠቃሚ እንጂ በራሱ ብቻውን በቂ አይሆንም፡፡ ባለሙያው ቅን፣ የሚታመን፣ ሀቀኛ፣ ኃላፊነት የሚሰማውና ግዴታውን በሚገባ የሚወጣ መሆን አለበት፡፡ እነዚህ የማኅበራዊ ካፒታል እሴቶች ሲሆኑ ችግር ያለባቸው አክሲዮን ማኅበራት ውስጥ ዶክተር ሳይንቲስቱ፣ የተከበሩ አዛውንቱ፣ ጎልማሳው ባለሙያ ካለምንም ይሉኝታ ነጭ ውሸት ይዋሻሉ፣ የተሰጣቸውን እምነትና አደራ ይበላሉ፣ በኃላፊነት ስሜትና በታማኝነት ከመሥራት ይልቅ እጅግ የወረደ ተግባር ውስጥ ይገኛሉ፡፡ ስለሆነም ለቦርድና ለሥራ አስኪያጅነት የሚመረጡ ሰዎች በጥንቃቄ መመረጥና ውጤት ካላስገኙና ችግር ከፈጠሩ ካለምንም መዘግየት በተሻለ መተካት አለባቸው፡፡ ጥፋት ከሠሩም ሳይዘገይ በሕግ ፊት ማቅረብ እንደሚገባ የንግድ ሕጉ ደንግጓል፡፡

አፍራሽ ማነው? አድራጊው ወይስ አጋላጩ? ይህ ጥያቄ ችግሮች በከፋባቸው አክሲዮን ማኅበራት ውስጥ መነሳቱ የተለመደና የሚያጋጥም ነው፡፡ ጥያቄው የውጭውን አዳማጭ ብቻ ሳይሆን የውስጥ ባለቤቶችንና ባለድርሻ አካላትንም ግራ ሲያጋባ ይታያል፡፡ ምክንያቱ ደግሞ የመረጃዎቹ በግልጽ አለመቅረብና በግልጽ ውይይት በመመዘኛና በመረጃ ላይ ተመሥርቶ ቀርቦ ተመርምሮ ውሳኔ ካለመስጠትና በይፋ ካለመግለጽ የሚመነጭ ነው፡፡ አፍራሽ የሚለው ፍረጃ በተለይ ከቦርድና ከማኔጅመንት በተቃዋሚዎቻቸው ላይ የሚቀርብ ሲሆን፣ በሌላ አቅጣጫ ደግሞ በአክሲዮን ማኅበራት ውስጥ ችግሮችና ጥፋቶች እንዳሉ የተገነዘቡና እንዲስተካከልም የሚገፉ ባለአክሲዮኖች በበኩላቸው ቦርድና ማኔጅመንትን በድክመትና በጥፋት ማጋለጥ፣ ሲበዛም በአፍራሽነት መፈረጅ የተለመደ ነው፡፡

በእርግጥ ለማፍረስ ቅርበትና ሥልጣን ያለው ቦርድና ማኔጅመንቱ ሲሆን፣ ድክመቱንና ጥፋቱን የሚቃወሙት ሲቻል በጉባዔ ላይ፣ ካልተቻለም በብዙኃን መገናኛ ማቅረብና ማጋለጥ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ይህ ጉዳይ የጅቡንና የአህያዋን ተረት ይመስላል፡፡ ጅቡ ከላይ እየጠጣ ከታች የምትጠጣዋን አህያ ውኃውን አደፈረሽብኝ ብሎ ነገር እንደፈለጋት ዓይነት መሆኑ ነው፡፡ ለማንኛውም የአፍራሽነትን ክስ ብያኔ ለመስጠት ጭብጥ ይዞ ከግራ ቀኙ የሚቀርበውን መረጃና ማስረጃ በሚገባ መረዳት፣ መመርመርና እውነቱን አንጥሮ ማውጣት ግድ ይሆናል፡፡ ቢሆንም ቦርድና ማኔጅመንት እውነቱን ከመጋፈጥ ይልቅ የድብብቆሽ ጨዋታ መጫወትና እውነትን በመደበቅና የእነሱን ጥፋትና መገለጫ፣ ለሌላው ሲሰጡ የሚያሳይ የአንድ አክሲዮን ሁኔታ እነሆ የቦርዱ ሰብሳቢ ለብቻው፣ አምስት የቦርድ አባላት ሳያውቁና ሳይፈቅዱ እንዲያውም እየተቃወሙ 105 ሠራተኞች አባረዋል፡፡ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች ተዘግተው ሠራተኞች ተባረዋል፡፡ የትምህርት ክፍሎች ተዘግተውና መምህራን ተባረው፣ ተማሪዎችም ተበትነዋል፡፡ ካለምንም ጥናት ከገቢ ጋር የማይገናኝ የደመወዝ ጭማሪ በማድረግ ተቋሙን ለአደጋ አጋልጠዋል፡፡ ከሕጉና ከአሠራር ውጪ ከፍተኛ ገንዘብ እንዲወጣ ተደርጓል፡፡ ይህን የሠሩት የቦርዱና የማኔጅመንት መሪዎች ሥራቸውን የሚቃወሙትን በአፍራሽነት ሲፈርጁ፣ ተቃዋሚዎች በበኩላቸው አመራሩን በአፍራሽነት ከሰዋል፡፡ ታዲያ አፍራሹ ማነው? አድራጊው ወይስ አጋላጩስ?

የአክሲዮን ማኅበራት (Public Companies) ተወካዮች (ቦርድና ማኔጅመንት) የሥልጣን ገደብና ተጠያቂነት በአክሲዮን ማኅበራት አሠራር ቦርድ በጠቅላላ ባለሀብቱ በቀጥታ ተወክሎ የቢዝነስ ማኔጅመንቱን በበላይነት የሚመራ ሲሆን፣ ማኔጅመንቱ ደግሞ በቀጥታ በጠቅላላ ባለሀብቱ ባይወከልም፣ ጠቅላላ ባለሀብቱንና ኩባንያውን በመወከል ይዋዋል፣ ሥራዎችን ይሠራል፡፡ በዚህ ዓይነት አሠራርና ሒደት ማኔጅመንቱ ሥልጣኑን ያገኘው በቀጥታ ከወካዩ ማለት ከጠቅላላው ባለሀብት እንዳገኘው ይቆጠራል፡፡ ይህ ማለት ማኔጅመንት የቦርዱ ብቻ ሳይሆን በተመሳሳይ ሁኔታ የኩባንያው ወይም የጠቅላላው ባለሀብት ተወካይ ማለትም ተተኪና ተወካይ ስለሚሆን ቀጥታ ሕጋዊ ግንኙነትና ውጤት ይኖራል ማለት ነው፡፡ ማኔጅመንት በውክልና ሥልጣኑ በመሥራት የመዋዋል፣ የመሥራትና የማሠራት፣ ሥራዎችን በሚሠራበት ጊዜ በሕግ፣ በውልና የሥራው ፀባይ ከሚጠይቀው ውጭ በመውጣት የወንጀልና የፍትሐ ብሔር ጥፋቶችን በሚሠራበት ወቅት፣ ተጠያቂነቱ በራሱ በማኔጅመንቱ እንጂ ኩባንያውን ጠቅላላ ባለሀብቱን የሚመለከት አይሆንም ወይም መሆን የለበትም፡፡

በተለይ በጥፋቱ ኩባንያው ወይም ተቋሙ ተጎጂ በሚሆንበት ወቅት (በፍትሐ ብሔርም ሆነ በወንጀል) ተጠያቂነቱን ማኔጅመንቱ በግል መውሰድ አለበት እንጂ ጉዳት ደርሶበት እያለ፣ በተጨማሪ በተደራራቢ የማኔጅመንቱ ጥፋትና ጉዳት የሚሸከምበት ወይም የሚሸፍንበት ምክንያት አይኖርም፡፡ ለምሳሌ ማኔጅመንት ከሕግና ከቅን ልቦና ውጪ ግልጽ የሆነ ጥፋት በሠራተኛው ላይ ፈጽሞ እያለና በዚህም ኩባንያውም ተጎጂ በሚሆንበት ጊዜ፣ በፍርድ ቤት የሚወሰነውን ቅጣት ወይም ካሣ በቀጥታ ራሱ ማኔጅመንቱ መሸፈን አለበት፡፡ አሁን እንደ ሚታየው እኔ ምን ቸገረኝ፣ ወጪውን የሚሸፈነው በኩባንያው ነው እየተባለ የሚሠራውን ኃላፊነት የጎደለውሥራ ዋጋ መክፈል ያለበት ማኔጅመንቱ ነው፡፡ በወንጀል (በሙስናና በደረቅ ወንጀል) በኩባንያው ሀብት፣ መብትና ጥቅም ላይ ለተከናወነውም ድርጊት በቀጥታና በግል መጠየቅ ያለበት ራሱ ማኔጅመንቱ መሆን አለበት እንጂ፣ ኩባንያው/ባለሀብቱ መሆን የለበትም፡፡

አሁን እየታየ ያለው ኃላፊነትና ተጠያቂነት የጎደለው አሠራር ፍጹም ሕጋዊና ፍትሐዊ አይደለም፡፡ ማኔጅመንት በማናለብኝነትና በሕገወጥነት በሠራተኞች ላይ ለሚፈጽመው ሕገወጥ ሥራ በተለይም ቦርዱ ሕገወጥ ነው እያለ፣ ማኔጅመንት የሚያደርሰው ጉዳት ሲኖርና ጉዳዩ ፍርድ ቤት ሲሄድ የፍርድ ቤት ወጪዎች፣ የጠበቃ ወጪ፣ የጥፋትና የቅጣት ወጪዎች በኩባንያው ላይ ለሚደርሰው የገጽታ ብልሽት ዋጋውን መክፈል ያለበት ማኔጅመንቱ በግል መሆን አለበት፡፡ ኩባንያው/ጠቅላላው ባለሀብት ተደራራቢ የማኔጅመንት በደሎችን የሚቀበልበት ምንም ዓይነት ሕጋዊ ምክንያት ሊኖር አይችልም፣ አይገባምም፡፡ ይህ ጉዳይ በግልጽና በዝርዝር አዲስ በሚሻሻሉት ሕጎችና የአፈጻጸም ደንቦችም ውስጥ መካተት ይኖርበታል፡፡ ምክንያቱም ሕጋዊና ፍትሐዊ ሥርዓት እንዲሰፍን ሁሉም የየድርሻቸውን ሲወስድና የሚከፍለው ዋጋ ሲሰማው ጥፋት ከመሥራቱ በፊት ሁለት ጊዜ ማሰብ ይጀምራልና ነው፡፡

ከአዘጋጁ፡- ጽሑፉ የጸሐፊውን አመለካከት ብቻ የሚያንፀባርቅ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

 

Standard (Image)

አዲሱ የውጭ አገር የሥራ ሥምሪት አዋጅ አተገባበር መዘግየት ያመጣው ጦስ!

$
0
0

 

በመላኩ ገድፍ

ዓለም አንድ መንደር በሆነችበት በ21ኛ ክፍለ ዘመን ማንኛውም ሕጋዊ የሆነ የአንድ አገር ዜጋ በየትኛውም የዓለም ክፍል ተዘዋውሮ የመሥራትና የመኖር መብት እንዳለው ይታወቃል፡፡ ይህ ዓለም አቀፋዊ የሆነው የፍልሰት ሒደትም ዋነኛ ምክንያቱ የተሻለ ኑሮና ሕይወት ከመሻት የሚመጣ የሰው ልጆች ያልተገደበ ፍላጎት የሚያመነጨው ክስተት ነው፡፡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት በአሁኑ ወቅት ፍልሰት ከፍተኛ በሆነ ደረጃ እየጨመረ ሲሆን፣ ሕገወጥ ስደትም የአንበሳውን ድርሻ ይይዛል፡፡ ሕገወጥ ስደት ዜጎች ምንም ዓይነት ሕጋዊ የመኖሪያ ሰነድ ሳይኖራቸው ወደ አንድ ሉዓላዊ አገር በሕገወጥ መንገድ ድንበር ጥሰው በመግባት የሚኖሩበት ሒደት ነው፡፡ ዓለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት በተለያየ ጊዜ የሚያወጣቸው ሪፖርቶች እንደሚያሳዩት፣ የሕገወጥ ስደተኞች ቁጥር በሚገርም ፍጥነት እያሻቀበ ይገኛል፡፡

ድርጅቱ ለሕገወጥ ስደት ዋነኛ ምክንያቶች የመልካም አስተዳደር ዕጦት፣ ፍትሐዊ ያልሆነ የሀብት ክፍፍል፣ የሰላም ዕጦት፣ በቂ የሆነ የሥራ ዕድል አለመኖርና የሕገወጥ ደላሎች መስፋፋት መሆናቸውን ያብራራል፡፡ በመሆኑም ይህንን የዓለማችን አንገብጋቢ የሆነውንና የብዙ ሺሕዎችን ሕይወት በመቅጠፍ ላይ የሚገኘውን ሕገወጥ የሰዎች ዝውውር ለመግታት፣ በቀዳሚነት አገሮች የራሳቸው የሆነ የውጭ አገር የሥራ ሥምሪት አዋጅ ሊኖራቸው ግድ ይላል፡፡ አገራችን ኢትዮጵያም ቀደም ሲል በሥራ ላይ የነበረውን የውጭ አገር የሥራ ሥምሪት አዋጅ ቁጥር 632/2001 ሰፊ ክፍተት አለበት በማለት ወደ ዓረብ አገሮች ለሥራ የሚጓዙ ዜጎች ላይ የስድስት ወራት የጉዞ ዕገዳ ከተጣለ ዓመታት ያለፈ ሲሆን፣ አዲሱ አዋጅ ደግሞ የካቲት 11 ቀን 2008 ዓ.ም. በተወካዮች ምክር ቤት ፀድቋል፡፡ ይሁን እንጂ እስከ ዛሬ ድረስ ዕገዳው ተነስቶ ሕጋዊ የሆነ የሥራ ሥምሪት ማድረግ አልተቻለም፡፡ መንግሥት በፊት የነበረውን የተካው አዲሱ የውጭ አገር የሥራ ሥምሪት አዋጅ ቁጥር 923/2008 ከዚህ በፊት የነበሩ ችግሮችን መፍታት የሚያስችል፣ የዜጎችን መብትና ፍላጎት የሚያስከብር፣ እንዲሁም የባለ ድርሻ አካላትን ኃላፊነት በግልጽ የሚደነግግ ነው በማለት በተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን በመለፈፍ ነው፡፡ እስካሁን ግን ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከተው የመንግሥት አካል (የሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር) አዋጁ ወደ ሥራ የሚገባበትን ቁርጥ ያለ ጊዜ መወሰን አልቻለም፡፡ 

በዚህ ምክንያትም ዜጎች በሕገወጥ መንገድ ወደ ተለያዩ ዓረብ አገሮች እየሄዱ ለከፍተኛ ችግር መዳረጋቸው በየቀኑ በሚዲያዎች የምንሰማውና የምናየው ጉዳይ ሆኗል፡፡ ዕገዳው ከተጣለ ጀምሮ ኢትዮጵያውያን በተለያዩ መንገዶች ወደ ዓረብ አገሮች እየተመሙ ይገኛሉ፡፡ የመጀመሪያውን ድርሻ የሚይዘው ዜጎች በሕገወጥ ደላሎች አጉል ተስፋ ተታለውና ብዙ ገንዘብ በመክፈል ባህር አቋርጠው የሚሄዱበት ሲሆን፣ በዚህ መንገድ የሚጓዙ ስደተኞች በብዛት ካሰቡት አገር ሳይደርሱ ለውኃ ጥም፣ ለረሃብ፣ ለአስገድዶ መድፈርና በተለያዩ ችግሮች የአውሬ ቀለብ ሆነው ይቀራሉ፡፡ ይህን ሁሉ ስቃይ አልፈው በሕገወጥ መንገድ ወደ ዓረብ አገሮች የሚገቡ ዜጎችም የተረጋጋ ሕይወት ሳይኖሩ፣ በአሠሪዎቻቸው መብታቸው እየተጣሰ የሰቆቃ ሕይወት ይኖራሉ፡፡

በሌላ በኩል ዜጎች በሕገወጥ መንገድ ወደ ዓረብ አገሮች የሚያደርጉት ጉዞ ሕጋዊ ሽፋን ተሰጥቶት በቦሌ በኩል የሚካሄድ ሲሆን፣ ሒደቱም ሕገወጥ ደላላው ከዓረብ አገሮች ካሉት ወኪሎች ጋር በሚያደርገው ስምምነት ነው፡፡ ደላላው የተለያዩ ሴት ወጣቶችን የተዛባ መረጃ በመንገር በአጭር ጊዜ ውስጥ ሕይወታቸውን መቀየር እንደሚችሉ በማሳመን ተጓዦችን ይመለምላል፡፡ በመቀጠልም ለጉዞ የሚያስፈልጉ ነገሮችን ፖስፖርትን ጨምሮ እንዲያዘጋጁ ያደርጋል፡፡ በሌላ በኩል ዓረብ አገር ያለው ደላላ በበኩሉ የቪዛውን ጣጣ ጨርሶ በአጭር ጊዜ ውስጥ ልጆቹ ከላኪና ከተቀባይ አገሮች ኢምባሲዎች ዕውቅና ውጪ ወደ ሥራ ይሰማራሉ፡፡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ከሆነ፣ በዚህ መንገድ ወደ ዓረብ አገሮች የሚሄዱ ሠራተኞች ለዘርፈ ብዙ ችግሮች ይዳረጋሉ፡፡ የመጀመርያው ችግር ሠራተኞች ይዘውት የሚሄዱት የጉዞ ሰነድ ትክክለኛ አለመሆኑ ነው፡፡

በተለይ ከሕክምና ውጤቶች ጋር በተያያዘ ብዙዎች ለደላላና ለተለያዩ ወጪዎች ያወጡትን ገንዘብ እንኳን ያስመልሱ፣ በኪሳራ ከብዙ እንግልት በኋላ ወዲያውኑ ይጠረዛሉ፡፡ ይህ የሚሆነውም የሕክምና ውጤቱን ሪፖርት የሚሠራው ጤና ጣቢያ ሰዎች ጥቅምን የሚያሳድዱ እንጂ ሙያዊ ኃላፊነታቸውን የማይወጡ በመሆናቸው ነው፡፡ በተለይ በመርካቶና በአውቶቡስ ተራ አካባቢ የሚገኙ አንዳንድ ክሊኒኮች ከዓረብ አገሮች ኤምባሲዎች ፈቃድ አለን በማለት ምንም ዓይነት የምርመራ መሣሪያዎች ባልተሟሉበት ሁኔታ ለተጓዦች የሕክምና ምርመራ ያደርጋሉ፡፡ ይህ ብቁ ባልሆኑ ባለሙያዎችና ባልተሟሉ የላብራቶሪ መሣሪያዎች የሚደረግ የምርመራ ውጤትም በተጓዦች ላይ የሚያስከትለው ችግር በቀላሉ የሚታይ አይደለም፡፡ ከሁለት ወራት በፊት ሰው ልቀበል የአገር ውስጥ በረራ ተርሚናል ውስጥ ያገኘኋቸው ከሳዑዲ ዓረቢያና ከኩዌት የተጠረዙ ወጣት ሴት እህቶቻችን የዚህ ችግር ሰለባ ነበሩ፡፡

ስልክ አስደውለን በማለት የቀረቡኝ እነዚህ ልጆች ከክልሎች እንደመጡ አለባበሳቸውንና የንግግር ዘይቤያቸውን ሰምቶ መገመት ይቻላል፡፡ ዓይኖቻቸው ብዙ ከማልቀሳቸው የተነሳ ቀልተዋል፡፡ ብርዱና የረሃብ ስሜቱ ተደማምሮ ፊታቸውን አጠውልጎታል፡፡ ‹‹ማሽላ እያረረ ይስቃል›› እንዲሉ በጉዞ ላይ ያሳለፉትን አጋጣሚ እያወሩ በጥቂቱ ፈገግ ይላሉ፡፡ በነበረን ቆይታ የተፈጠረውን ችግር እንዲያስረዱኝ ጠየቅኳቸው፡፡ ዕድሜዋ 17 መሆኑን የነገረችኝ የሳዑዲ ተመላሿ ልጅ የሄደችበትን ሁኔታና የተመለሰችበትን ምክንያት ስታስረዳኝ ድንገት ከገረጡ ዓይኖቿ የሚወጡ እንባዎች ጉንጮቿን አቋርጠው እየፈሰሱ ነበር፡፡ ሲቃ በተናነቀው ድምፅ ንግግሯን ቀጠለች፡፡ የመጣችው ከኦሮሚያ ክልል ገጠራማ አካባቢ ሲሆን፣ አባቷ በልጅነቷ ስለሞተ እናቷ እንደ አባትም እንደ እናትም ሆና ሌሎች እህትና ወንድሞቿ ጋር ተቸግራ አሳድጋታለች፡፡ ትምህርትም እንደ እኩዮቿ በተገቢ ሁኔታ ባይሆንም እስከ ስምንተኛ ክፍል ተምራለች፡፡ የስምንተኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ተፈትናም ወደ ዘጠነኛ ተዛውራለች፡፡ ነገር ግን የዘጠነኛ ክፍልን ለመማር በአካባቢው የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ባለመኖሩ ወደ ሌላ ቦታ መሄድ ነበረባት፡፡ ይህንን ለማድረግ የአሳዳጊ እናትዋ አቅም አልፈቀደምና ትምህርቷን ለማቋረጥ ተገደደች፡፡ ጓደኞቿ በተሳካ ሁኔታ ትምህርታቸውን ሲቀጥሉ የእሷ ቤት መቀመጥ አንገበገባት፡፡ ይህ ሁኔታም ድንገት ዓረብ አገር የመሄድን ሐሳብ ወለደላት፡፡

በአካባቢዋ ብዙ ሴት ተማሪዎች ትምህርታቸውን መቀጠል እየቻሉ በሕገወጥ ደላሎች ተታለው ትምህርታቸውን አቋርጠው ይሄዳሉ፡፡ እሷ ግን ምንም አማራጭ ስላልነበራት ወደ ዓረብ አገር መሄድ መወሰኗ ትክክል ነበር ብላ ታምናለች፡፡ ሰዎቹ ልጅቷ የተመለሰችበትን ምክንያት በግልጽ ባይነግሯትም ቅሉ፣ ችግሩ ግን በተሳሳተ የሜዲካል ምርመራ ውጤት ምክንያት እንደሆነ ሳትሸሽግ ነግራኛለች፡፡ እንደ ልጅቷ እምነት ችግሩ የተፈጠረው የሜዲካል ምርመራ የሚሰጠው የሕክምና ተቋም ሕጋዊ አለመሆኑንና መሥፈርቱን የሚያሟላ የላብራቶሪ መሣሪያ የሌለው ከመሆኑ ጋር እንደሚሆን ትናገራለች፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ከዚህ የተላከው የሜዲካል ውጤትና እዚያ ደርሳ ስትመረመር የተገኘው ውጤት ፍፁም የተለያየ መሆኑ ነው፡፡

ከደቡብ ክልል የመጣችው ዕድሜዋ 25 ዓመት መሆኑን የነገረችኝ ፈርጣማዋ ወጣት ወደ ኩዌት ለሥራ ስትሄድ ይህ ሁለተኛ ጊዜዋ ነው፡፡ የተመለሰችበት ምክንያትም የሁለት ወር ነፍሰ ጡር ሆና በመገኘቷ ሲሆን፣ እንደ ልጅቷ ገለጻ ስህተቱ የተሠራው የሜዲካል ምርመራ ባካሄደችበት ጊዜና በረራ ባደረገችበት ጊዜ መካከል የሦስት ወር ልዩነት በመኖሩ ልትሄድ ስትል በድጋሚ ምርመራ ባለማድረጓ ምክንያት የመጣ ነው ባይ ነች፡፡ በሌላ በኩል በሕገወጥ መንገድ ባህር አቋርጣ ሳዑዲ ዓረቢያ ለሥራ የገባችዋ ወጣት በየትና እንዴት ሳዑዲ እንደገባች የምታውቀው ነገር የላትም፡፡ በጉዞ ወቅት ብዙ አስቸጋሪ ስቃዮችን ተጋፍጣ እንዳለፈኝ ትናገራለች፡፡ አብረዋት ጉዞ የጀመሩ ጓደኞቿ የት እንደደረሱ አታውቅም፡፡ ሕገወጥ ደላሎች በራሳቸው ሕገወጥ የጉዞ መረቦች እንደፈለጉ ይቀባበሏቸዋል፡፡ መሀሉ አይነገርም. . . እንዲሉ ለመናገር የሚቀፉ ብዙ ድርጊቶች በሕገወጥ ስደተኞች ላይ ሲፈጸሙ አስተውላለች፡፡

ሳዑዲ ዓረቢያ ከገባች አንድ ዓመት ቢያልፋትም ያሰበችውን ሳታሳካ በፖሊሶች ተይዛ  ሁለት ወር ከታሰረች በኋላ ወደ እናት አገሯ ተመልሳለች፡፡ በአጠቃላይ እነዚህ ልጆች ዕድል ብሎ በሰላም ወደ አገራቸው ይመለሱ እንጂ፣ በዚህ መንገድ የሚሄዱ ብዙ ወገኖቻችን ሕገወጥ ከመሆናቸው ጋር ተያይዞ በእስር የሚማቅቁ፣ በድብደባ አካላቸው የጎደለ፣ በአሠሪዎቻቸው አስገድዶ መደፈር የደረሰባቸው፣ ከፎቅ የሚወረወሩ፣ በአሠሪዎቻቸው የሠሩበትን ክፍያ የተከለከሉ፣ ብሎም ለአዕምሮ ሕመም የተዳረጉ ቡዙዎች መሆናቸው የማይካድ ሀቅ ነው፡፡ ዘወትር በማኅበራዊ ሚዲያዎች የሚለቀቁ ተንቀሳቃሽ ምሥሎች እንደሚያሳዩት፣ ኢትዮጵያውያን ከሌሎች የሩቅ ምሥራቅ አገር ዜጎች በተለየ ሁኔታ ከፍተኛ የመብት ጥሰት ይፈጸምባቸዋል፡፡ ለዚህ ሁሉ የመብት ጥሰት ዋነኛ ምክንያት አሠሪዎች ኢትዮጵያውያኑ ሠራተኞች ሕገወጥ መሆናቸውን ስለሚያውቁ፣ ሠራተኞቹን ኃላፊነት በጎደለው መንገድ እንደፈለጉ ለማሠራትም ሆነ ከዚያ ያለፉ ድርጊቶችን ይፈጽሙ ዘንድ የልብ ልብ ይሰማቸዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በዓረብ አገሮች የሚገኙ ኢትዮጵያ ቆንስላ ጽሕፈት ቤቶች ስደተኞች ለሚያሰሙት የድረሱልኝ ጥሪ ጆሮ ዳባ ልበስ ማለታቸው ሁኔታውን ከጊዜ ወደ ጊዜ እያባባሰው ይገኛል፡፡ ስደተኞች በማኅበራዊ ሚዲያ እንደሚገልጹት ከሆነ በዓረብ አገሮች የሚገኙ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎች ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን ይጠራጠራሉ፡፡ ሕጋዊም ሆኑ ሕገወጥ ስደተኞች ከአሠሪዎቻቸው የመብት ጥሰት ሲደርስባቸው ወደ ቆንስላው አቤት ማለታቸው አይቀርም፡፡ ይሁን እንጂ ኤምባሲዎች አስቸኳይ መፍትሔ አይሰጡም፡፡ ይልቁንም በብዛት ስደተኞች የሚደርስባቸውን የመብት ጥሰት ተቋቁመው እንዲኖሩ የሚገፋፉ ናቸው፡፡

በዓረብ አገሮች ያሉ የኢትዮጵያ ቆንስላዎች የዜጎቻቸውን መብት ለማስከበር የሚያችል የተደራጀና ወጥ የሆነ አሠራር የላቸውም፡፡ በዚህ ምክንያት በዓረብ አገሮች የሚሠሩ ብዙ ኢትዮጵያውያን በቆንስላዎቹ ምንም ዓይነት እምነት የሌላቸው በመሆኑ፣ የሚደርስባቸውን በደል እየተቋቋሙ የነገ ህልማቸውን ለማሳካት ሕይወታቸውን በሰቆቃ የተሞላ ሆኗል፡፡ በኩዌት የኢትዮጵያ ኤምባሲ በቅርቡ በፌስቡክ ገጹ ላይ የለቀቀው ተንቀሳቃሽ ምሥል እንደሚያሳየው፣ አንዲት ኢትዮጵያዊት ሠራተኛ አሠሪዎቿ ያለምንም ክፍያ ለአምስት ዓመታት እንዳሠሯት ትናገራለች፡፡ ልጅቷ እንደምትናገረው አሠሪዎቿ ከማንም ጋር እንዳትገናኝ በማገት ለአምስት ዓመታት ያለ ምንም ሰባራ ሳንቲም ሲበዘብዟት ኖረዋል፡፡ እንደዚህች እህታችን ዓይነት ስደተኞችና ለብዙ ዓመታት አግተው ካሠሯቸው በኋላ ከተጠያቂነት ለማምለጥ ከፎቅ የሚወረወሩ፣ አላስፈላጊ ድብደባ፣ እንዲሁም የአስገድዶ መደፈር ወንጀል የሚፈጸምባቸው እህቶቻችን ምን ያህል እንደሆኑ ቤት ይቁጠረው፡፡

በአጠቃላይ ለእነዚህ ሁሉ ዘርፈ ብዙ ችግሮች መነሻው በአገሮች መካከል ለሚደረግ የሥራ ውል ስምምነት አገሮቹ የዜጎቻቸውን መብትና የሥራ ፍላጎት የሚያስከብር የሥራ ሥምሪት አዋጅ አለመኖሩ፣ ቢኖርም ተፈጻሚነቱ የላላ መሆኑ ነው፡፡ ከላይ ለመጥቀስ እንደተሞከረው አገራችን ኢትዮጵያ ‹‹ሠርገኛ መጣ በርበሬ ቀንጥሱ›› እንዲሉ ከሁለት ዓመት በፊት ሳዑዲ ዓረቢያ ሕገወጥ ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን በኃይል ከአገሯ ማስወጣቷን ተከትሎ፣ የስድስት ወራት የውጭ አገር የሥራ ሥምሪት ላይ ዕገዳ በመጣል አዲስ የውጭ አገር የሥራ ሥምሪት አዋጅ አውጥታለች፡፡ ይህ አዋጀ በፍጥነት ወደ ሥራ ባለመግባቱ ምክንያትም ከሳዑዲ ዓረቢያ በኃይል ከተባረሩት ስደተኞች ውስጥ ብዙዎቹ በባህር በር እያቋረጡ በሕገወጥ መንገድ ወደ መጡበት ሳዑዲ መመለሳቸውን፣ መገናኛ ብዙኃን መግለጻቸው ይታወሳል፡፡

ሳዑዲ ከአራት ዓመት በፊት ሕገወጥ ኢትዮጵያውያንን በኃይል ብታስወጣም ቅሉ፣ በሕገወጥ መንገድ ወደ አገሯ የሚገቡትን ግን ማስቆም አልቻለችም፡፡ በዚህ የተነሳም በቅርቡ ለሦስት ወራት የሚቆይ የምሕረት አዋጅ በማውጣት አገሯን ለቀው ይወጡ ዘንድ እያሳሰበች ትገኛለች፡፡ ‹‹አለባብሰው ቢያርሱ ባረም ይመለሱ›› እንዲሉ ኢትዮጵያም ከዚህ ቀደም ይሠራበት የነበረውን የውጭ አገሮች ሥራ ሥምሪት አዋጅ ክፈተት ያለበት በመሆኑ፣ ይህንን ክፍተት ለማሻሻልም አዲስ የሥራ ሥምሪት አዋጅ ወጥቶ  ወደ ሥራ ባለመገባቱ ለሕገወጥ ስደት በር በመክፈት በብዙ ሺሕ የሚቆጠሩ ዜጎች በሕገወጥ መንገድ ወደ ተለያዩ አገሮች ገብተዋል፡፡ አዲስ አድማስ ጋዜጣ የዓለም አቀፍ የስደተኞችን ድርጅት ሪፖርት ጠቅሶ እንደዘገበው፣ ባለፉት ስድስት ወራት ከ40 ሺሕ በላይ ኢትዮጵያውያን በጦርነት እየታመሰች ወዳለችው የመን መሰደዳቸውን ያመለክታል፡፡ ስለሆነም አዲሱ የሥራ ሥምሪት አስፈላጊው ዝግጅት ተደርጎበት በፍጥነት ወደ ሥራ የማይገባ ከሆነ፣ ብዙ ወገኖች የበረሃ ሲሳይ መሆናቸው ይቀጥላል፡፡ የበረሃውንና ስቃይና መከራ አልፈው ወደ ዓረብ  አገሮች የሚሄዱ ዜጎች (አብዛኞቹ ወጣት ሴቶች) ከፎቅ መወርወር፣ አካል መጉደል፣ በሽተኛ መሆን፣ ሞት፣ አስገድዶ መደፈር፣ የሠሩበትን ደመወዝና ያፈሩትን ጥሪት ሳይዙ ባዶ እጃቸውን መባረር የተለመደ ሆኗል፡፡ ይህንን ችግር ይቀርፋል ተብሎ የተዘጋጀው አዲሱ የውጭ አገር የሥራ ሥምሪት ረቂቅ አዋጅ የሠራተኞችን መብት፣ ደኅንነትና ክብር ለማስጠበቅ ከበፊቱ በጣም የተሻለና ጠበቅ ያለ መሆን አለበት፡፡ በአዋጅ የተጠቀሱት ደንቦችም በሁሉም ባለድርሻ አካላት ዘንድ ተፈጻሚነት ይኖራቸው ዘንድ የጠነከረ ክትትልና ምዘና መካሄድ አለበት፡፡ በላኪና በተቀባይ አገሮች መካከል ባሉ ኤጀንሲዎች መካከል ጥብቅ የሆነ ግንኙነት እንዲፈጠር ከመቼውም በላይ አዋጁ ተግባራዊ ይሆን ዘንድ፣ በኢትዮጵያና በሌላኛው ተቀባይ አገር መካከል የጋራ ወጥ የሆነ ስምምነት መኖር አለበት፡፡ ለምሳሌ ወደ አንድ አገር ለሥራ የሚሄዱ ዜጎች የሥራ ልምዳቸውንና የትምህርት ደረጃቸውን ግምት ውስጥ ያስገባ የደመወዝ እርከን መኖር አለበት፡፡ በዓረብ አገሮች የሚሠሩ ዜጎች እንደሚናገሩት በሕጋዊ መንገድ ለሥራ ወደ አገሪቱ ከገቡ በኋላ፣ አሠሪዎቻቸው የሚከፍሏቸው ወርኃዊ ደመወዝ አነስተኛ በመሆኑ የተሻለ ክፍያ ለመፈለግ ከአሠሪዎቻቸው በመጥፋት በሕገወጥ መንገድ ሌላ የሥራ ቦታ ይቀይራሉ፡፡

ይህ ጠፍተው የሚሠሩበት አሠሪም ሕገወጥ መሆናቸውን ስለሚያውቅ በተለየ ሁኔታ የዜጎችንን መብት እንዲጥስ ያበረታታዋል፡፡ ሠራተኞቹም ዘወትር ከአገሪቱ ፖሊስ ጋር ሌባና ፖሊስ ሲጫወቱ የተረጋጋ ሕይወት ካለመኖራቸው ባለፈ፣ ለእስርና ለድብደባ የሚጋለጡ የትየለሌ ናቸው፡፡ ስለሆነም ይህንን መሰሉን ችግር ለማስወገድ ላኪና ተቀባይ አገሮች ወቅታዊ ሁኔታዎችን ግምት ውስጥ ያስገባ የደመወዝ የክፍያ እርከን ሊያወጡ ይገባል፡፡

በሌላ በኩል መረጃዎች እንደሚያመለክቱት በአብዛኛው በውጭ አገሮች በተለያዩ የሥራ መስኮች በተሰማሩ ዜጎች ላይ የሚደርሱ ችግሮች ከዕውቀትና ከክህሎት ክፍተት ጋር የሚገናኙ ናቸው፡፡ ስለሆነም አዲሱ የውጭ አገር የሥራ ሥምሪት አዋጅ ለሥራ ወደ ውጭ የሚሄዱ ዜጎችን ሄደው ለሚሠሩበት የሥራ መደብ በቂ የሆነ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ሥልጠና ከመስጠት ባለፈ፣ ለሥራው ብቁ መሆናቸውንን መመዘን አለበት፡፡

በተጨማሪም በአሠሪኛ በሠራተኛ መካከል በሚፈጠር አለመግባባት ላይ ሊሠራ የሚገባ አካል መቋቋም አለበት፡፡ በተቀባይ አገሮች የሚኖሩ የኢትዮጵያ ቆንስላዎች ይህንን ኃላፊነት በተገቢው ሁኔታ መወጣት አለባቸው፡፡ በተለያዩ የመረጃ ምንጮች በተለይም በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ እንደምናየው በዓረብ አገሮች የሚሠሩ ሴት እህቶቻችን ከሌሎች ዜጎች በተለየ ሁኔታ ከፍተኛ የሆነ የመብት ጥሰት በአሠሪዎቻቸው ይፈጸምባቸዋል፡፡ ይህ የሚሆነውም በአገሮቹ ውስጥ የሚገኙ ቆንስላ ጽሕፈት ቤቶች የተፈጠረውን ችግር አጣርተው ሕጋዊ የሆነ ዕርምጃ ካለመውሰዳቸው የሚመጣ ነው፡፡ ስለሆነም በአሠሪና በሠራተኛ መካከል ለሚኖረው አለመግባባት መፍትሔ ለመስጠት፣ ከአገናኝ ኤጀንሲዎች በተጨማሪ ኢምባሲዎችም ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከት ይጠበቅባቸዋል፡፡

ከአዘጋጁ፡- ጽሑፉ የጸሐፊውን አመለካከት ብቻ የሚያንፀባርቅ ሲሆን፣ ጸሐፊውን በኢሜይል አድራሻቸው   mellegedif@gmail.comማግኘት ይቻላል፡፡      

 

 

Standard (Image)

የመድን ሸፍጥ

$
0
0

በኢዮቤድ ጥበቡ ልሳነወርቅ

የአለቃ ደስታ ተክለ ወልድ የአማርኛ መዝገበ ቃላት "ሸፈጠ - ሰፈጠ ማለት - ካደ፣ ከዳ፣ ዓበለ፣ አሞኘ፣ አቄለ፣ አታለለ፣ ሸነገለ፤ ነው ይላል፡፡ "ሸፍጥ - ስፍጠት- አሉታ፣ ክዳት፣ የሆነውን የተደረገውን አልሆነም፣ የለም፣ አልተደረገም፣ አይደለም ማለት"መሆኑንም  ይገልጻል፡፡ የኦክስፎርድ መዝገበ ቃላት በበኩሉ "Fraud"የሚለውን የእንግሊዝኛ ቃል "wrongful or criminal deception intended to result in financial or personal gain"ሲል ይተረጉማል፡፡  አባባሉም ወደ አማርኛ  ሲመለስ "የፋይናንስ ወይም ግላዊ ትርፍ ለማግኘት ሲባል ሕጋዊ ያልሆነና የተሰሳተ የወንጀል ተግባርን መፈጸም"ማለት ነው፡፡ ስለዚህ "ሸፍጠኛ ሰው"የሆነውን የተደረገውን አልሆነም፣ የተደረገውን አልተደረገም ብሎ ክዶና ዓብሎ የሚፈጽመው የወንጀል ድርጊት ስለሆነ፣ የዚህ ጽሑፍ አቅራቢ በእንግሊዝኛ ልሳን "Insurance Fraud"የሚለውን ባማርኛ "የመድን ሸፍጥ"ብሎ ተርጉሞታል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በሥሩ የሚገኙትን የፋይናንስ ተቋማት ለመቆጣጠር የሚያወጣቸው መመርያዎችና ትዕዛዞች (Directives) የሚጻፉት በእንግሊዝኛ ልሳን  ነው፡፡ ማዕከላዊ ባንኩ "Insurance and Reinsurance Business Fraud Monitoring Directives SIB/39/2014"በሚል ርዕስ ያወጣው መመርያ ለዚህ ጽሑፍ መነሻ  ሲሆን፣ የመመርያው ርዕስ ወደ አማርኛ  ሲመለስ "በመድንና በጠለፋ መድን ሥራ ላይ የሚፈጸምን ሸፍጥ ለመቆጣጠር የወጣ መመርያ ቁ. SIB/39/2014"ይላል፡፡

 መመርያው ተራ ቁጥር 2.5 ላይ፡- "Fraud means an act or omission by shareholders, directors, employees, customers, policyholders, insurance auxiliaries committed with the intention of gaining dishonest and unlawful advantage for the party committing fraud or for other parties"በማለት "የመድን ሸፍጥ"ትርጉምን አስቀምጧል፡፡ ይኼም አባባል ወደ አማርኛ ሲመለስ "ሸፍጥ ማለት፣ በባለአክሲዮን፣ በዳይሬክተር፣ በሠራተኛ፣ በደንበኛ፣ በመድን ውል ባለቤት፣ በመድን ረዳት  ለሸፍጡ ፈጻሚ ወይም ለሌሎች ሕጋዊ ያልሆነ ጥቅም ለማስገኘት በማሰብ የሚፈጽመው ወይም የማይፈጽመው ደርጊት ነው፡፡"

በመመርያው ተራ ቁጥር አራት ላይም እንደተመለከተው መድን ሰጪዎችና  የጠለፋ መድን ሰጪዎች  የመድን ሸፍጥን ለመለየት፣ ለመቀነስና  ሪፖርት ለማድረግ የሚያስችል በግልጽ የተብራራ ፖሊሲና የአፈጻጸም መመርያ አውጥተው በቦርድ ዳይሬክተሮቻቸው እንዲያፀድቁና ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክና ለሠራተኞቻቸው እንዲያስታውቁ ያዛል፡፡ በተጨማሪም መድን ሰጪዎችና የጠለፋ መድን ሰጪዎች የአወቃወርና የአሠራር ሲስተም አዘረጋጋቸው የተፈጸሙትንና የተሞከሩትን የመድን ሸፍጦች ለቦርድ ዳይሬክተሮች፣ ለማኔጅመንትና ለሌሎች ለሚመለከታቸው ሁሉ ለማሳወቅ የሚያስችሉ የግንኙነት መስመሮች መዘርጋታቸውን እንዲያረጋግጡ፣ የተፈጸሙና የተሞከሩ የመድን ሸፍጦችን ለብሔራዊ ባንክ በየ15 ቀኑ እንዲልኩ ይገልጻል፡፡ መመርያው ሌሎችንም በዚህ ጽሑፍ ውስጥ ያልተጠቀሱትን የአፈጻጸም ሥርዓቶችን ይዟል፡፡

በአጠቃላይ "የሸፍጥ"ድርጊት በማታለል የግል፣ ወይም የጋራ ጥቅም ለማግኘት በሕግ፣ ወይም በሥራ የተሰጠ ኃላፊነትን አለመወጣት፣ ወይም ጉዳት ማድረስን የሚያስከትል ሲሆን፣ "የመድን ሸፍጥ"ስንል ደግሞ ከላይ እንደተገለጸው አንድ ሰው በሸፍጥ ከመድን ውል  የማይገባውን "የገንዘብ ጥቅም ወይም ወሮታ" (Financial Benefit or Advantage) ለማግኘት፣ ወይም ሌላ ሰው የሚገባውን ጥቅም እንዳያገኝ በማድረግ የሚፈጸም  የወንጀል ተግባር መሆኑን ለመገንዘብ እንችላለን፡፡

በጸሐፊው አመለካከት ከሌሎች የሸፍጥ ወንጀሎች ይልቅ "የመድን ሸፍጥ"በድርጊቱ ፈጻሚዎች ላይ የሚያስወስደው ዕርምጃ በአንፃራዊ መልኩ የቀለለ፣ የሚሰጠው ጥቅም ግን ከፍተኛ ነው፡፡  አብዛኞቹ መንግሥታትም ለመድን ሸፍጥ የሚያደርጉት የሕግ ጥበቃ ዝቅተኛ መሆኑን (Low Legal Priority)ነው፡፡  በሁሉም አገሮች የመድን ሸፍጥ በአገር ኢኮኖሚ ላይ ከባድ ጉዳት እያደረሰ በወንጀሉ ቁጥጥርና ክትትል ረገድ እንደ ሌሎች ወንጀሎች እምብዛም ክብደት ስለማይሰጠው የመድን ሸፍጠኞች ወንጀሉን ለመፈጸም እንደሚበረታቱ አያሌ በውጭ አገሮች የተደረጉ ጥናቶች ያስረዳሉ፡፡  ስለዚህም የመድን ሸፍጥ  በዓለም ላይ  እጅግ እየተስፋፋና እየበዛ በመሄድ ላይ ይገኛል፡፡

በፋይናንስ ላይ ትኩረት የሚያደርገው "ኢንቬስቶፔዲያ"የተባለው መዝገበ ቃላት  በእንግሊዝኛ ልሳን ለመድን ሸፍጥ የሰጠው ትርጉም ለአረዳድ ቀላል ስለሆነ እንደሚከተለው በአማርኛ ልሳን እንጠቅሰዋለን፡፡ "የመድን ሸፍጥ በመድን ውል ሻጭ (በመድን ሰጪ እና በጠለፋ መድን ሰጪ)፣ ወይም በመድን ገዥ  (በመድን አመልካችና በመድን ገቢ) የሚፈጸም ወንጀል ነው፡፡ በመድን ውል ሻጭ በኩል የሚፈጸመው የመድን ሸፍጥ የመድን ሥራን ለመሥራት ፈቃድ ሳይኖር ውሎችን መሸጥ፣ የዓረቦን ተመንን ያለማስመዝገብ፣ የኮሚሲዮን ጥቅም ለማግኘት ውሎችን ግልጽ ከማድረግ ይልቅ  ማደበላለቅንና ማደናገርን ይጨምራል፡፡ በመድን ገዥዎች በኩል ደግሞ፣ የተጋነኑና የማይገቡ የካሣ ጥያቄዎችን ማቅረብ፣ የተሳሳተ የጤና መረጃ መስጠት፣ ውል የሚጀምርበትን ቀን የኋሊት መጠምዘዝ፣ ቫያቲካል ሸፍጥ፣ ሐሰተኛ የሞት መረጃ ማቅረብ፣ ጠለፋ፣ አፈናና ግድያ፣ ወዘተ ይጨምራል" (http://www.investopedia.com/terms/i/insurance-fraud.aspተመልከት)፡፡

"ቫያቲካል ሸፍጥ (Viatical Fraud)"

በሰሜን አሜሪካ ከሕይወት መድን ውል ጋር የተያያዘ ስምምነት ማለትም "ቫያቲካል ሴትልመንት" (Viatical Settlement)፤ ወይም "ላይፍ ሴትልመንት" (Life Settlement) የሚባል አሠራር  ከተጀመረ  ዕድሜው ገና  33 ዓመት ነው፡፡  ከላይ በተጠቀሰው መዝገበ ቃላት የመድን ሸፍጥ ትርጉም ውስጥ በእንግሊዝኛው ልሳን "ቫያቲካል ሸፍጥ"በሚል የተገለጸው ወንጀል በአገራችንም ሆነ በሌሎች ታዳጊ አገሮች የሚታወቅ ስላልሆነ፣ ምን ዓይነት ወንጀል እንደሆነ በቅድሚያ አንባቢያን እንዲረዱ ማድረግ ተገቢ ነው፡፡

በመሠረቱ አንድ ሰው "የዕድሜ ልክ የሕይወት መድን ዋስትና (Whole Life Insurance)"የሚገዛው እሱ ሲሞት ተጠቃሚ ያደረገው/ጋቸው ሰው/ሰዎች (Beneficiaries)  የመድን ዋስትና ጥቅሙን  እንዲያገኙ ለማድረግ ነው፡፡ ስለሆነም "የቫያቲካል ሴትልመንት"ስምምነት የሚደረገው የዕድሜ ልክ የሕይወት መድን ዋስትና ውል ኖሯቸው በተለያዩ የማይድኑ በሽታዎች የተለከፉና የመሞቻ ጊዜያቸውን የሚጠባበቁ ሰዎች፣ ከሕልፈተ ሕይወታቸው በፊት የሕይወት መድን ውላቸው የሚያስገኘውን "የሞት ጥቅም" (Death Benefit)  ለሦስተኛ ወገን በቅናሽ ሸጠው በሚያገኙት ገንዘብ ቀሪ ሕይወታቸውን በገንዘብ ዕጦት ምክንያት ከሚደርስባቸው ጎስቋላ ኑሮ ተላቀው በደስታ እንዲኖሩ ለመርዳት ታስቦ የታቀደ ምግባረ ሠናይ ተግባር ነው፡፡

"የቫያቲካል ስምምነት"በራሱ (Perse) የመድን ውል  ሳይሆን በመድን ውል ላይ የተመሠረተ "መድን መሰል" (Quasi-insurance) ሕጋዊ ስምምነት ነው፡፡ በመሠረቱ  የሕይወት መድን ዋስትና ውል  የመድን ገቢው "የግል ንብረት" (Private Property) ስለሆነ እንደማንኛውም ንብረት ከፈለገ ሊሸጠው፣ ሊለውጠው፣ ወይም የውሉን ጥቅሞች ለሌላ ሦስተኛ ወገን ሊያስተላልፍ  ይችላል፡፡ ስለዚህ መድን ገቢው የሕይወት መድን ውሉን ያስተላለፈለት ሰው የውሉ ተጠቃሚ ሆኖ ተመዳኙ ሲሞት ጥቅሙን ሊያገኝ ይችላል፡፡ በአንፃሩ ደግሞ ማንኛውም ሰው ከፈለገ መዋዕለ ንዋዩን ሕጋዊ በሆነ  "የኢንቨስትመንት መስክ" (Investment Vehicle) ላይ አፍስሶ "የመዋዕለ ንዋይ ጥቅም" (Investment Benefit) ተጠቃሚ ሊሆን ይችላል፡፡ ስለዚህ "በቫያቲካል ሴትልመንት"የሕይወት መድን ውሉን የሚሸጠው በእንግሊዝኛው ስያሜ "ቫያተር" (Viator) ተብሎ የሚጠራ ሲሆን፣ በስምምነቱ ገንዘቡን አፍስሶ የመድን ውሉን የሚገዛውና መድን ገቢው/ተመዳኙ ሲሞት የመዋዕለ ንዋይ ጥቅሙን የሚቀበለው ሦስተኛ ወገን ሰው መጠሪያው ያው "ኢንቨስተር"ነው፡፡  ሁለቱን ተዋዋይ ወገኖች ማለትም ቫያተሩንና ኢንቨስተሩን የሚያቀራርቡት ደግሞ ኮሚሽን ከኢንቨስተሩ የሚከፈላቸው "አዋዋዮች" (Brokers) ናቸው፡፡

በአገረ አሜሪካ  በሕይወት መድን ውል ላይ መዋዕለ ንዋያቸውን የሚያፈሱ  "ስምና ክብራቸውን የሚጠብቁ" (Reputable Viatical Funding Firms) ኩባንያዎች የመኖራቸውን ያህል፣  በአንፃሩ ደግሞ አደገኛ ሸፍጠኞችም ይገኛሉ፡፡ በዚህ ምክንያት ብዙ የሰሜን አሜሪካ ክፍለ አገሮች "የቫያቲካል ሸፍጥ"መረን እየለቀቀባቸው በመሄዱ፣ ምክንያት ደርጊቱን ለመቆጣጠር የሚያስችላቸውን ሕጋጌዎች አውጥተው ይቆጣጠራሉ፡፡  በዚህ ረገድ "የኒውዮርክ ክፍለ ሀገር"ግምባር ቀደም ተጠቃሽ ነው፡፡ "የቫያቲካል ሴትልመንት"ተግባር የተጀመረው እ.ኤ.አ. በ1980 ዓ.ም. አጋማሽ ገደማ ሲሆን፤ አነሳሱም በዋናነት ኤችአይቪ ኤድስ በብዙ ሕመምተኞች ላይ ላስከተለው የኑሮ ቀውስ መፍትሔ ለመሻት ነበር፡፡ በዚያን ወቅት በኤችአይቪ ኤድስ ቀሳፊ በሽታ የተለከፉ ሕሙማን ለተወሰነ አጭር ጊዜ ብቻ በሕይወት እንደሚኖሩ ይገለጽ ስለነበር፣ አብዛኞቹም ከላይ እንደተገለጸው ያለቻቸውን አጭር ቀሪ ሕይወት በመልካም ሁኔታ ለመኖር በገንዘብ ዕጦት የሚቸገሩ ነበሩ፡፡ ምክንያቱም ሥራቸውን መሥራት ስለማይችሉ ገቢያቸው ይቋረጣል፣ ጥሪት ያላቸውም ቢሆኑ በሕክምና ወጪ ጨርሰውት ሊሆን ይችላል፡፡ በአንፃሩ ደግሞ እነዚህ ሕመምተኞች ለወራሾቻቸው፣ ወይም ተጠቃሚዎች አድርገው በውሉ ውስጥ ለሰየሟቸው ሰዎች እነሱ ከሞቱ በኋላ፣ በርከት ያለ "የሞት ጥቅም" (Death benefit)  የሚሰጡ የሕይወት መድን ውል ያላቸው ናቸው፡፡

ስለዚህ፣ "ከራስ በላይ ንፋስ"እንዲሉ አዳዲስ ሥራ ፈጣሪዎችና አማካሪዎቻቸው "የመዋዕለ ንዋይ ምንጭ"ከሆኑ ደርጅቶችና ማኅበረሰቦች (Funding Frms/Agencies)  ጋራ በመመካከር የሕይወት መድን ዋስትና በእጃቸው ላይ እያለ በገንዘብ ዕጦት ኑሮአቸው ለተጎሳቆለ ሕመምተኞች መፍትሔ ለመሻት ተነሳሱ፡፡ መፍትሔ ሆኖ የተገኘውም ከላይ እንደተገለጸው፣ ሕመምተኞቹ የሕይወት መድን ዋስትና ውላቸውን ለሦስተኛ ወገን  ኢንቨስተሮች በተወሰነ  ቅናሽ ሸጠው በሚያገኙት ገንዘብ እስከ  ሕልፈተ ሕይወታቸው  ድረስ በደስታ ተመችቷቸው እንዲኖሩ ለማድረግ ነው፡፡ የቫያቲካል ስምምነት መሠረተ ሐሣብም በተመሳሳይ ሁኔታ በዕድሜያቸው የገፉ ሰዎችም እንዲጠቀሙበት ተደርጓል፡፡ እነሆ አስከ ዛሬ ድረስ በልዩ ልዩ ደዌ ተይዘው መሞቻ ቀናቸውን የሚጠባበቁ፤ ወይም በዕድሜያቸው የገፉ ሰዎች (በሰሜን አሜሪካ የኒውዮርክ ክፍለ ሀገር ሕግ እንደሚደነግገው ዕድሜያቸው ከ65 በላይ የሆኑ አዛውንቶች) ጠቀም ያለ የሞት ካሣ ጥቅም ሊከፍል የሚችለውን የሕይወት መድን ውላቸውን ለሦስተኛ ወገን ኢንቨስተር በቅናሽ እየሸጡ፣ በገንዘብ ዕጦት ምክንያት ከተጋረጠባቸው የኑሮ ቀውስ ተላቀው ቀሪውን ሕይወታቸውን በጥሩ ሁኔታ እንዲያሳልፉ ይረዳቸዋል ማለት ነው፡፡

የቫያቲካል ሸፍጠኞች ቫያተሩ ሊያገኝ የሚችለውን ጥቅም በማሳነስ የማይገባ ትርፍ መብላት፣ የመድን ውሉን ባለቤትነት በስማቸው ከተላለፈላቸው በኋላ በተለይም የአልጋ ቁራኛ ለሆኑት ሕመምተኞችና አዛውንቶች መጠነኛ ገንዘብ ብቻ በመወርወር ማታለል፣ አንዳንዴም ጨርሶ አለመክፈል፣ ወዘተ የመሳሰሉትን የወንጀል ተግባራት ይፈጽማሉ፡፡ ስለዚህ ሕመምተኞቹ መልካም ስም ካላቸው መዋዕለ ንዋይ አፍሳሾች  ጋር ከሸፍጥ ድርጊት የፀዳ ድርድር ማድረግ እንዲችሉና ቫያተሮቹ በሕይወት ከሚቆዩበት ጊዜ ጋር ተመጣጣኝ ጥቅም ማግኘት እንዲችሉ፣ ስምምነቱን መቆጣጠር የሚቻልበትን ሕግ በማውጣት የመድን ሸፍጠኞች በሕመምተኞች ወይም በዕድሜ የገፉት አዛውንቶች ላይ ሊያደርሱ የሚችሉትን ጉዳት ለመታደግ ተችሏል፡፡ ከላይ በመድን ሸፍጥ ትርጉም ላይ ለአብነት ከተጠቀሱት ወንጀሎች መካከል "ቫያቲካል ሸፍጥ"  ጎልቶ የተጠቀሰውም በዚህ ምክንያት ነው፡፡ "Vitical"የሚለው የእንግሊዘኛ ቃል የተወሰደው "Viticum"ከሚለው የላቲን ቃል ነው፡፡ የቃሉ ትርጉም በእንግሊዝኛ ልሳን "Provisions for a Journey"በአማርኛ ሲተረጎም "የጉዞ ስንቅ"ማለት ነው፡፡ በክርስትና ሃይማኖቶች ዕምነት፣ በተለይም ጸሐፊው በሚያውቀው የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ተከታዮች  ለሞት የተቃረበ ሰው በቅዱስ ቁርባን "የክርስቶስን ሥጋና ደም"ከተቀበለ "የጉዞ ስንቅ"ያገኛል ተብሎ ይታመናል፡፡ ስለዚህ ከዚህ ዓለም ወደ ዘለዓለማዊ ሕይወት ለመሸጋገር ብርታት እንደሚሰጠው ሁሉ በዚሁ ተምሳሌት በማይድን በሽታ ተለክፈው ወይም ዕድሜያቸው በመግፋቱ ምክንያት የመሞቻ ጊዜያቸውን የሚጠባበቁና የሕይወት መድን ዋስትና ውል ያላቸው ሰዎች የመድን ውሎቻቸውን ለኢንቨስተሮች ሸጠው እስከ ሕልፈተ ሕይወታቸው ድረስ ስንቅ የሚሆናቸው ገንዘብ  ያገኛሉ ማለት ነው፡፡ የመድንውል በባሕርዩ ለመድን ገቢውም ሆነ ለመድን ሰጪው "የብዝበዛ በር"   (Opportunities for Exploitation) ሊከፍት የሚችል ሥራ ስለሆነ፣ መንግሥታት ከሌሎች የንግድ ሥራዎች ይልቅ በጥልቀት የሚቆጣጠሩት ሥራ መሆኑን ቀደም ብዬ በዚሁ ጋዜጣ ላይ ባቀረብኳቸው ጽሑፎቼ ለማስገንዘብ ሞክሬአለሁ፡፡

"ጥምረትበመድንሸፍጥላይ" (Coalition Against Insurance Fraud)

የመድን ሸፍጥ መድን ገቢውም ሆነ መድን ሰጪው የማይገባቸውን የገንዘብ ጥቅም ለማግኘት ሲሉ የሚፈጽሙት ድርጊት መሆኑ ከላይ ተብራርቷል፡፡ በሰሜን አሜሪካ የሚገኘውና "ጥምረት በመድን ሸፍጥ ላይ"  የተሰኘው ድርጅት "የሸፍጥ"ዋነኛ ምክንያት የሰዎች ስግግብብነት መሆኑን አበክሮ ይገልጻል  (www.insurancefraud.org/)፡፡ ስለሆነም የመድን ሸፍጥ ዓይነቶችን ከዚህ ቀጥለን ለአብነት ያህል እንጠቅሳለን፡፡ 

  • በጣምየተለመደው የመድን ሸፍጥ ዓይነት የጉዳት ካሣን ማጋነን   (Inflating Loss) እና  ያልደረሰ ጉዳትን የደረሰ አሰመስሎ ለማሳመን የሚደረግ ጥረት ነው፡፡ ሁኔታውም በመድን ሳይንስ ሰብዓዊ/ሰዋዊ ጉዳት-አሥልጥ (Moral Hazard) በመባል ይታወቃል፡፡
  • በበለፀጉትአገሮች ያሉ መድን ሰጪዎች የሚቀርቡላቸው አንዳንድ የጉዳት ካሣ ማመልከቻዎች አጠራጠሪ መሆናቸውን ቢረዱም፣ አንከፍልም ብለው አቋም ቢይዙ ተጎዳን ባይ ሸፍጠኞች ወደ ፍርድ አደባባይ መሄዳቸው አይቀሬ ነው፡፡ ስለዚህ በእነዚህ አገሮች የፍርድ ቤት ክርክር ወጪዎች ከፍተኛ ከመሆናቸውም ባሻገር አጋጣሚው ለመልካም ስም ጎጂ ስለሆነ በፍርድ ቤት ክርክር ጊዜንና ገንዘብን ከማባከን ይልቅ፣ የካሣ ጥያቄዎችን ተቀብሎ ማስተናገዱን መድን ሰጪዎች ሊመርጡ ይችላሉ፡፡ እነዚህን በመሳሰሉ ምክንያቶች የመድን ሸፍጠኞች የሆኑ መድን ገቢዎችና አጋሮቻቸው (ለምሳሌ በሰሜን አሜሪካ የሚገኙ አንዳንድ የሕግ ጠበቆች) በአቋራጭ ጥቅም ለማግኘት ሰፊ ዕድል ያገኛሉ፡፡
  • የመድንሸፍጥ ወንጀል ሌላው ምክንያት  አንድን ንብረት ከትክክለኛው ዋጋ በላይ አብዝቶ የመድን ዋስትና መግባት ነው (Over Insurance)፡፡ የንብረቱ ትክክለኛ ዋጋ መድን ከተገባበት ዋጋ ያነሰ ከሆነ መድን ገቢው የበለጠ ጥቅም ለማግኘት ሲል ሆን ብሎ በንብረቱ ላይ ጉዳት አድርሶ በውጤቱ ለመጠቀም ይገፋፋል፡፡ ኢሕአዴግ ኢትዮጵያን በተቆጣጠረበት ጥቂት ጊዜ ውስጥ አንዳንዳንድ ሰዎች ወደ ኢትዮጵያ ያስገቧቸውን አሮጌ የጭነት ተሽከርካሪዎች በተጋነነ ዋጋ ለባንክ ብድር መያዣ በማድረግ የመድን ዋስትና ከገቡላቸው በኋላ፣ ተሽከርካሪዎቹን በዘዴ በማቃጠል ወይም ገደል በመክተት በርካታ የካሣ ጥያቄዎች መስተናገዳቸው የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው፡፡ ከዚህ ደርጊት በተገኘው ልምድ ባንኮች ለአሮጌ መኪኖች ብድር መስጠት አቁመው እንደነበር ይታወሳል፡፡
  • አንዳንድመድን ሰጪዎችም የመድን ዓረቦን ገቢያቸውን ለማሳደግ ሲሉ በተጋነነ መድን ማስገቢያ ዋጋ ዋስትና በመቀበል መድን ገቢዎችን የሚያበረታቱ ከሆነ፣ ይኼም ደርጊት ችግሩን አባባሽ ለመሆኑ አሌ አይባልም፡፡ ገበያ ለማግበስበስ ሲባልም በጣም በዝቅተኛ ዓረቦን ዋስትና ለመሸጥ መሞከርም በገበያ ውስጥ የሚፈጥረውን ቀውስ ያባብሳል፡፡  የመድን ሥራ በአግባቡ ቁጥጥር ካልተደረገበት ሀቀኝነት የጎደላቸው መድን ሰጪዎች ተገቢ ያልሆኑ ደርጊቶችን ሊፈጽሙ እንደሚችሉ ግልጽ ነው፡፡

የመድንሸፍጥ በሁለት ዓበይት ክፍሎች ይከፈላል

 1.  "ጠጣርየመድንሸፍጥ" (Hard Insurance Fraud) 

የመድን ካሣ ለመቀበል አንድ ሰው ሆን ብሎ በሕይወት በንብረት ላይ የሚያደርሰው ጉዳት ጥፋት (Loss) "ጠጣር የመድን ሸፍጥ"ነው፡፡ ለምሳሌ ሆን ብሎ  የተሽከርካሪ አደጋ መፍጠር፣ የሕይወት የመድን ለማግኘት ብሎ የመድን ገቢውን ነፍስ ማጥፋት፣ ንብረትን ሆን ብሎ በእሳት ማቃጠል፣ ከሌቦች ጋር በመሻረክ ንብረትን ሆን ብሎ ማሰረቅና የመሳሳሉት ጠጣር የመድን ሸፍጦች ተብለው ይፈረጃሉ፡፡  በተለይም በመጨረሻ ላይ የተጠቀሰውን ወንጀል ለመፈጸም በአንዳንድ የበለፀጉ አገሮች ውስጥ ተቧድነው ድርጊቱን የሚፈጽሙ ሰዎች ቁጥራቸው ብዙ ነው፡፡ በሰሜን አሜሪካ "የአምቡላንስ አሳዳጆች" (Ambulance Chasers) በመባል የሚታወቁት ጠበቆች የአደጋ ጉዳት የደረሰባቸውን ሰዎች እያሳደዱ ለራሳቸው ብዙ ጥቅም የሚያስገኝ ሥራ የሚፈጥሩ   መኖራቸው የአደባባይ ሚስጥር ነው፡፡

2.  "ልልየመድንሸፍጥ" (Soft Insurance Fraud)

ከጠጣር የመድን ሸፍጥ ይልቅ "ልል የመድን ሸፍጥ"ብዛቱ ከፍተኛ ነው፡፡ ይኼውም የካሣ ጥያቆዎቹ ሕጋዊ ሆነው ሳለ በተገኘው የአደጋ አጋጣሚ በመጠቀም የበለጠ የካሣ ክፍያ ገንዘብ ለማግኘት ሲሉ የጉዳቱን መጠን የሚያጋንኑ ልል ሸፍጠኞች አሉ፡፡  የመድን ዋስትና ሲገዙ ዝቅተኛ ዓረቦን ለመክፈል ሲሉም ሆን ብለው የተሳሳተ መረጃ ለመድን ሰጪው የሚሰጡት የልል መድን ሸፍጠኞች ናቸው፡፡  ለምሳሌ አንድ ሰው ዝቅተኛ ዓረቦን ለመክፈል እንዲችል የሕይወት መድን ማመልከቻ ሲሞላ ዕድሜውን ሆን ብሎ ማሳነስ፣ አደገኛ ሕመም ያለበት መሆኑን እያወቀ ምንም በሽታ የለብኝም ብሎ መረጃ መስጠት፣ ቀደም ሲል የገዛቸው የመድን ውሎች ካሉ እነሱን የሚመለከቱ  መረጃዎችን  እንዲገልጽ ሲጠየቅ መኖራቸውን ልቡ እያወቀ ምንም የሌለ መሆኑን በመገልጽ ሐሰተኛ መረጃ መስጠትና የመሳሰሉት፣ በዚህ ክፍል ውስጥ የሚመደቡ ሸፍጦች ናቸው፡፡ የሆነውንና የተደረገውን አልሆነም፣ የለም፣ አልተደረገም፣ አይደለም ማለት ሸፍጥ መሆኑ ከላይ ተገልጾአል፡፡

የመድን ሸፍጥ በኅብረተሰቡ ላይ ምን ጉዳት ያስከትላል?

ከታሪክ ማኅደራት ለመገንዘብ እንደሚቻለው የመድን ሸፍጥ የመድን አገልግሎትን ለሕዝብ መሸጥ ከተጀመረበት ጊዜ ጀምሮ የነበረና ዛሬም ያለ ነው፡፡ በዓለም ዙርያ በየዓመቱ "በሁሉም የመድን ዓይነቶች"ላይ በሚቀርቡ ሐሰተኛ የካሣ ክፍያ ጥያቄዎች አገሮቹን ለብዙ ቢሊዮን ብር ብክነት እንደሚዳርጋቸው አያሌ ማስረጃዎች አሉ፡፡ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ለኅብረተሰብ ጎጂ ከሆኑት ሸፍጦች መካከል ለአብነት ያህል ጥቂቶቹን ቀጥለን እንጠቅሳለን፡፡ 

(1)  የመድን የዓረቦን ተመን እንዲጨምርያደርጋል

የመድን ዓረቦን ተመን እንዲጨምር ከሚያደርጉት ምክንያቶች አንዱ የመድን ሸፍጥ ነው፡፡ የሐሰተኛ ካሣ ክፍያዎችንና ሌሎች ዓይነት የመድን ወጪዎችን  ለመዋጋት በተለይ በውጭ አገሮች የሚገኙ መድን ሰጪዎች ለበርካታ ዓይነት ወጪዎች ይዳረጋሉ፡፡ ወጪዎቹንም ለማካካስ ሲሉ መድን ሰጪዎች በዓረቦን ተመኖች ላይ ጭማሪ መጣላቸው አይቀሬ ነው፡፡ ለምሳሌ ተመዳኞች፣ የካሣ አስተዳደር ሠራተኞች፣ የጥገና ጋራጆችና የተሸከርካሪ መለዋወጫ መደብሮች ባለቤቶችና ሠራተኞች የማይገባቸውን የገንዘብ ጥቅም ለማግኘት በተናጠልም ሆነ በሽርክና የመድን ሸፍጥ የሚፈጽሙበት ዋና መስመር የተሸከርካሪ መድን ነው፡፡ የመድን ሸፍጥ ከተንሰራፋባቸው የመድን ዓይነቶች መካከል የሠራተኞች የጉዳት ካሣ መድን መሆኑ አይታበልም፡፡ በሐሰት አደጋ ደርሶብናል በሚሉና የካሣ ጥያቄ የሚያቀርቡ ሠራተኞች የመብዛታቸውን ያህል፣ አንዳንድ አሠሪዎችም የመድን ዓረቦን ለመቀነስ ሲሉ ትክክል ያልሆነና የተሳሳተ መረጃ ለመድን ሰጪዎች ስለሚሰጡ፣ ለዓረቦን ተመን ጭማሪ አስተዋፅኦዋቸው ከፍተኛ ነው፡፡ ስለሆነም መድን ሰጪዎች በዓመቱ መጨረሻ ላይ የመድን ዋስትናዎቹን "የጉዳት-ኪሣራ ቀመር" (Loss Ratio) በመድን ዓይነትም ሆነ በጥቅል ሲያሰሉት "የውል ውጤት ኪሣራ" (Underwriting Loss) ሊደርስባቸው ይችላል፡፡ ምክንያቱም መድን ሰጪዎች በገቢ መልክ ያገኙት ዓረቦን  በካሣ መልክ ከከፈሉት ወጪ ጋር ሲመዛዘን የካሣ ክፍያው መጠን ከበለጠ ዋስትናው አክሳሪ ይሆናል ማለት ነው፡፡ ስለዚህ፤ ክስረቱ ዳግም እንዳይከሰት ለመከላከል የሚቀጥለውን ዘመን ዓረቦን መጨመር ግድ ይሆንባቸዋል፡፡

በአገራችን ለቀላል ሕክምና ወደ ጤና ተቋማት የሄዱ ሠራተኞች በተመላላሽ ሊታከሙ ሲችሉ፣ የሕክምና መድን ዋስትና ያላቸው ከሆኑ ተኝተው እንዲታከሙ ማድረግ፣ ወይም የሕመም ዕረፍት ማግኘት ለማይገባቸው ታካሚ ሠራተኞች የሕመም ዕረፍት በመስጠት በሥራ ላይ ችግሮች ሲፈጠሩ ይስተዋላል፡፡ በውጭ አገር የሚገኙ መድን ሰጪዎችም ከዚህ ችግር የፀዱ አይደሉም፡፡ ለምሳሌ በጀርመን አንዳንድ የሕክምና ዶክተሮች በተመሳሳይ የመድን ሸፍጥ ላይ ተሠማርተው ስለተገኙ ክስ እንደቀረበባቸው በመዋዕለ ዜናዎች ተዘግበው እናገኛለን፡፡ በብዙ አገሮች የሚገኙ የአነስተኛና የመለስተኛ ደርጅቶች ባለቤቶችች የሕመም መድን ዋስትና ዓረቦን ከአቅማችን በላይ ሆነብን እያሉ የሚያሰሙት እሮሮ ዋና ምክንያቱ የመድን ሸፍጥ  መሆኑ አይካድም፡፡

(2)  የመድን ሸፍጥ የዕቃዎችና የአገልግሎቶችዋጋዎች እንዲንሩ ያደርጋል

የመድን ዓረቦን በንግድ ደርጅቶች ላይ ሲጨምር የንግድ ድርጅቶቹም በበኩላቸው ጭማሪውን በዕቃዎቻቸውና በአገልግሎቶቻቸው ዋጋ ላይ ያጣጡታል፡፡ የዚህ ደርጊት ውጤት በአጠቃላይ በሸማቹ ኅብረተሰብ ላይ ጫና ማስከተሉ በውጭ በተደረጉ አያሌ ጥናቶች ተረጋግጧል፡፡ በውጭ የሚገኙ ትልልቅ ድርጅቶች የንግድ ሥራ ሸፍጦችን ለመከላከል ከፍተኛ ወጪ ስለሚያወጡ፣ ይኼንኑ በዕቃዎችና በአገልግሎቶች ዋጋ ላይ በመጨመር እንዲሚያቻችሉትም ይታወቃል፡፡

(3)  የመድን ሸፍጥ በሰዎች ሕይወት የሚያስከትለው ጉዳት

የሕይወት መድን ተጠቃሚ የሆኑ ሰዎች መድን ገቢው ቶሎ ሞቶላቸው ካሣቸውን ለመቀበል ባላቸው ጉጉት ሆን ብለው የሰው ሕይወት ያጠፋሉ፡፡ በጥንት ጊዜ በሰሜን አሜሪካ የመድን ዋስትና በሰው ሕይወት ላይ ለመግዛት "የመድን መብት" (Isurable Interest) እንዲኖር በሕግ ከመደንገጉ በፊት በፔንሲልቫንይ ክፍለ ግዛት የሚኖር አንድ በጣም የደከመና ያረጀ ሰው ነበር ይባላል፡፡ ይኼንን ሰው ስድስት ጎረምሶች ሲመለከቱት በጥቂት ቀናት ውስጥ ሊሞት ይችላል ብለው በመመካከር፣ ሰውየው ሲሞት የሞት ካሣ ገንዘብ ጥቅም ለማግኘት በየወሩ ዓረቦን እየከፈሉ በሽማግሌው ስም የሕይወት መድን ዋስትና ይገዛሉ፡፡ ሰውየው ከዛሬ ነገ ይሞታል ብለው ጎረምሶቹ ሲጠብቁት አልሞት ስላላቸውና ዓረቦኑንም በየወሩ መክፈል ስለከበዳቸው ሽማግሌውን ሆን ብለው ይገድሉታል፡፡ ፖሊስ የሽማግሌውን አሟሟት ሲያጣራ ስድስቱን ጎረምሶች በድርጊቱ ስለጠረጠራቸው ወንጀሉን አጣርቶ ፍርድ ቤት በማቅረብ የጓጉለትን ገንዘብ ሰይበሉት በስቅላት ተቀጥተዋል፡፡ በግዛቱ ውስጥ የመድን መብት ሳይኖር ለራስ ጥቅም የሌላ ሰውን የሕይወት መድን ማስገባት የተከለከለውም ከዚህ የወንጀል ደርጊት በኋላ ነበር፡፡  የሕይወት መድን ዋስትና ያላቸው ተጋቢዎችም አንዱ የአንዱን ሕይወት፣ ሸሪኮች የተሻረኪውን ሕይወት ሆን ብለው በማጥፋት የመድን ገንዘብ ጥቅም ለማግኘት ወንጀል ሊሠሩ ይችላሉ፡፡ እንደነዚህ ለመሳሰሉ እኩይ ተግባራት የመድን ሸፍጠኞች ለገንዘብ ሲሉ የሌሎቸ ሰዎችን ሕይወት ያለአግባብ ይቀጥፋሉ፡፡  

      (4)  ሐሰተኛ የተሸከርካሪአደጋዎች 

በተለይ በውጭ አገሮች የመድን ሸፍጠኞች የመድን ካሣ ክፍያ ጥቅም ለማግኘት ብለው "በማስመሰል በሚፈጥሩዋቸው የተሽከርካሪ አደጋዎች" (Staged Auto Accidents) ንፁኃን ሰዎችን የአደጋ ሰለባዎች ያደርጋሉ፡፡ በዚህም ተግባራቸው በብዙ አገሮች ሸፍጠኞች ሆን ብለው በሰላም ከሚጓዙ ተሽከርካሪዎች ጋር ግጭት ይፈጥራሉ፡፡ ሆን ተብሎ የሚደረጉ ግጭቶች በሰሜን አሜሪካ "ግጭት ለጥሬ ብር" (Crash for Cash)  በመባል ይታወቃሉ፡፡ በዚህ ዓይነቱ የተሸከርካሪ ግጭት ቴክኒክ የተካኑ ሸፍጠኞች ከፊት ለፊት እየነዱ ድንገት ፍሬን በመያዝ ከኋላ እየተከተለ ያለው ሰላማዊ ተሽከርካሪ እንዲገጫቸው ያደርጋሉ፡፡ አንዳንድ ጊዜም የፀነሰችን ሴት ይዘው ድርጊቱን ስለሚፈጽሙ ሴትዮዋ ባትጎዳም ክፉኛ የተጎዳች በማስመሰል ስለምትንፈራፈር፣ ለሕክምና ዕርዳታ የተሠለፉ ሐኪሞች ሴትዮዋ መፀነሷን ሲረዱ ሕይወቷን ለማትረፍ ፅንሱን ሊያቋርጡት ይችላሉ፡፡ የግጭቱ ውጤት እዚህ ደረጃ ከደረሰላቸው ሸፍጠኞቹ በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠር ዶላር የመድን ካሣ ገንዘብ እንደሚያፍሱ ይታወቃል፡፡ በዚህ ዓይነቱ የፍርድ ቤት ክርክር የተካኑና ሆን ብለው የመድን ዋስትና ካሣዎችን ክርክር ለሚከታተሉ አያሌ ጠበቆችም ትልቅ ሲሳይ ይሆንላቸዋል፡፡

እ.ኤ.አ. በ1993ዓ.ም. በሰሜን አሜሪካ ኒውጀርሲ ክፍለ ግዛት "የመድን ሸፍጥ መርማሪዎች" (Insurance fraud Investigators) በከተማዋ ውስጥ በተለያየ ቦታ በሕዝብ ማመላለሻ አውቶብሶች ላይ ሆን ብለው "የማስመሰል/ተምሳሌታዊ ግጭት" (Staged Auto Accidents) እንዲደርስባቸው ያደርጋሉ፡፡ አደጋዎቹ በተፈጸሙባቸው ሥፍራዎች በግርግሩ አጋጣሚ ለመጠቀም ብዙ ሰዎች እየዘለሉ አውቶብሶቹ ውስጥ ገብተው አደጋ ደርሶብናል፣ ዕርዳታ አድርጉልን እያሉ መጮህ ይጀምራሉ፡፡ አንዳንዶቹም  መኪኖቻቸውን አያቆሙ አውቶብሶቹ ውስጥ የገቡ ናቸው፡፡ ሰዎቹ አውቶብሶቹ ውስጥ እየተንደረደሩ የገቡት የተጎዱ መስለው ያላግባብ የመድን ካሣ ክፍያ ለማግኘት በማሰብ  ነው፡፡ በተከታታይ ቀናትም በመቶዎች የሚቆጠሩ የካሣ ጥያቄ ማመልከቻዎች ለአውቶብሶቹ የመድን ዋስትና ሰጪ ኩባንያዎች ቀርቧል፡፡ አውቶብሶቹ የማስመሰል/ተምሳሌታዊ አደጋ እንዲደርስባቸው ሲደረግ በውስጣቸው ከመድን ሸፍጥ መርማሪዎቹና ከአሽከርካሪው  በስተቀር ማንም ሌላ ተሳፋሪ አልነበረም፡፡

ለጥናት ተብሎ በተደረገው በዚህ የማስመሰል/ተምሳሌታዊ አደጋ ከተገኘው አስገራሚ ውጤት በኋላ አሥራ ሰባት ድርጅቶች እያንዳንዳቸው 500,000 ዶላር በማዋጣት "ጥምረት በመድን ሸፍጥ ላይ" (The Coalition Against Insurance Fraud) በሚል ስያሜ "ፀረ መድን ሸፍጥ ተቋም"አቋቋሙ፡፡ የተቋሙም ዓላማና ተልዕኮ የመድን ሸፍጥን በትጋት መዋጋት ነው ፡፡  በከፍተኛ ሁኔታ እየተስፋፋ ያለውን የመድን ሸፍጥ ለመቋቋም ጥምረቱ የግልና መንግሥታዊ ደርጅቶችን በማስተባበር አያሌ ጥረቶችንም ያደርጋል፡፡ አባላቱም የመድን ሸፍጥ ብክነትን ለመቆጣጠር፣ የኅብረተሰብን ደኅንነት ለመጠበቅ፣ ብሎም "የመድን ሸፍጥ ወንጀለኞችን ለማንበርከክ ቆርጠን ተነስተናል" (Bring this Crime Wave to its Knees) ይላሉ፡፡ ሰሜን አሜሪካ በተሽከርካሪ መድን አደጋ ካሣ ክፍያ ላይ በየዓመቱ ብዙ ቢሊዮን ዶላር ኪሣራ እንደሚደርስባት ተቋሙ ሰፊ ዘገባ ማቅረቡም ይታወቃል፡፡

(5)  ሐሰተኛ  የእሳት አደጋዎች

ያላግባብ ገንዘብ ለማግኘት ካላቸው ፍላጎት አንፃር መድን በተገባላቸው ንብረቶች ላይ ማለትም መኖሪያ ቤቶችን፣ የንግድ ድርጅቶችን፣ ተሽከርካሪዎችን፣ ወዘተ ሆን ብለው እሳት የሚለኩሱ ተመዳኝ ሸፍጠኞችም አሉ፡፡ እሳት በተለኮሰባቸው ቤቶች፣ ደርጅቶችና ፋብሪካዎች ውስጥ የሚገኙ ሰዎች፣ ጎረቤቶች፣ እሳቱን ለመከላከል የተሰማሩ የእሳት አደጋ ሠራተኞች በድርጊቱ መጎዳታቸው አይቀሬ ነው፡፡ እነዚህን በመሰሉ አደጋዎች ምክንያት የሚወድሙት ንብረቶች የአገር ሀብት ናቸው፡፡ ብዙ ጊዜ በዚህ ተግባር ላይ የሚሰማሩ መድን ገቢዎች የሚያቀርቧቸው የመድን ካሣ ክፍያ ጥያቄዎች በጣም የተጋነኑ ናቸው፡፡ የወንጀል ደርጊቱም እንዳይደረስበት መረጃዎችን ለማጥፋት ቢጥሩም በፖሊስ ምርመራ ሲጋለጡ ይስተዋላል፡፡ ቅድመ ደርግ በአዲስ አበባ ከተማ አምባሳደር ቴአትር ሕንፃ ሥር ይገኝ የነበረ የምሽት ክበብ ላይ የእሳት አደጋ ደርሶበት የክበቡ ንብረት በሙሉ ተቃጥሎ ነበር፡፡  የመድን ካሣ ለማግኘት አስበው በቤንዚን የተሞላ ጀሪካን ክበቡ ውስጥ አስቀምጠው  እሳቱን ሆን ብለው ያቀጣጠሉትና በመጨረሻ ዘግተው የወጡት የክበቡ ባለቤት ናቸው፡፡ ክበቡን ባለቤቱ ማቃጠላቸውን መርማሪ ፖሊሶቹ የደረሱበት ቤንዚን የነበረበት ጀሪካን በእሳቱ ግሎ ሲፈነዳ ክዳኑ ተፈናጥሮ ጣሪያ ላይ በረጨው ቤንዚን መረጃ ፖሊስ ተጠራጥሮ ባደረገው ከፍተኛ የምርመራ ሥልት ነበር፡፡ ዓቃቤ ሕግ በሸፍጠኛው የክበቡ በባለቤት ላይ ክስ መስርቶ የዘጠኝ ዓመት እስራት እንዳስወሰነባቸው፣ በጊዜው በነበረው የፖሊስና ዕርምጃው ጋዜጣ ላይ ማንበቡን ጸሐፊው ያስታውሳል፡፡  

(6)  ሠራተኞችንከሥራ ያፈናቅላል

      አንዳንድ የመድን ሸፍጥ እንቅስቃሴዎችም ሠራተኞች ከሥራቸው እንዲፈናቀሉ ምክንያት ሆነው ይገኛሉ፡፡ ለምሳሌ በሰሜን አሜሪካ "ማርቲን ፍራንከል (Martin Frankel)"የተባለ ሸፍጠኛ ሰው "ፍራንክሊን አሜሪካን ላይፍ ኢንሹራንስ ካምፓኒ” የሚባል የሕይወት መድን ኩባንያ አቋቁሞ በሚስጥር የኩባንያውን ሀብት ወደ ግል ሒሣቡ በማዛወሩ ምክንያት ኩባንያውን አክስሮ እንዲዘጋ አድርጓታል፡፡ በዚያም ደርጊት ሳቢያ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሠራተኞች ከሥራቸው ተፈናቅለዋል፡፡

(7)  የመንግሥትንሀብት አቅጣጫ ያስለውጣል

የብዙ አገሮች መንግሥታት ሌሎች ወንጀሎችን ለመቆጣጠር የሚያውሉትን  ገንዘብ የመድን ሸፍጥን ለመቆጣጠር ይጠቀሙበታል፡፡ ደርጊቱ በተለይ የኢኮኖሚ ዕድገታቸው አናሳ የሆኑትን አገሮች አቅም በእጅጉ ይፈታተናል፡፡ ስለዚህም የፀረ-መድን ሸፍጥ ቢሮዎች ማቋቋሚያ በጀት፣ እንዲሁም የፖሊስንና የዓቃቤ ሕግ ቢሮዎችን ለማጠናከር ለሚወሰዱ ዕርምጃዎች አያሌ ወጪዎች ያስፈልጋሉ፡፡ የሰሜን አሜሪካ መንግሥት ለፌዴራልና ለክልል መንግሥታት በጤና ሕክምና ላይ የሚደረገውን ሸፍጥ ለመከላከል በየዓመቱ ብዙ ቢሊዮን ዶላር በጀት ይመድባል፡፡ በዚህ ረገድ የሌሎች አገሮችም ወጪዎች የናሩ መሆናቸው ግልጽ ነው፡፡ ስለዚህ በሌሎች ጠቃሚ ልማቶች ላይ የሚውለው የሕዝብ ሀብት ሸፍጠኞችን ለመዋጋት አቅጣጫ መቀየሩ አሌ አይባልም፡፡

የመድንሸፍጥ ስታትስቲካዊ መረጃ

በአገራችን በመድን ሸፍጥ የሚባክነውን የአገር ሀብት የሚገልጽ አስተማማኝ የሆነ  መረጃ  ስላልተገኘ፣ በዚህ ጽሑፍ ውስጥ ለማቅረብ አልተቻለም፡፡ ሆኖም የመድን ሸፍጥ "ኢኮኖሚያዊ ወንጀል" (Economic Crime) በመሆኑ በአንድ አገር ኢኮኖሚ ላይ  ምን ያህል ጉዳት እንደሚያደርስ ለአንባቢ ግንዘቤ ለማስጨበጥ ሌሎች አገሮች ያጠናቀሩትን ስታትስቲካዊ መረጃ ዝቅ ብሎ በሚገኘው ራሱ አስረጅ በሆነው ሰንጠረዥ አማካይነት ለአብነት ያህል ማቅረብ ተችሏል፡፡ መረጃው የተቀዳው "NHS Counter Fraud and Security Management Service, July 2006" - The International Fraud And Corruption Report - A study of selected countries (www.slideshare.net/…/the-international-fraud-and...) በሚል ርዕስ  ከተዘጋጀው ሪፖርት ላይ ነው፡፡ በሰንጠረዡ ውስጥ አገሮቹ ካላቸው የሕዝብ ብዛትና ዓመታዊ ገቢያቸው አንፃር በመድን ሸፍጥ ከሚባክነው ሀብታቸው ጋር ተነፃፅሮ ይታያል፡፡

 

 

አገር

 

የሕዝብ

ብዛት

 

ዓመታዊ ገቢ ምርት

(GDP)

 

በመድን ሸፍጥ

የሚባክነው ሀብት

 

ከዓመታዊ ገቢ ምርት  (%)

አውስትራሊያ

20.1 ሚሊዮን

8.1 ትሪሊዮን ዶላር

5.8 ቢሊዮን ዶላር

1.3

ካናዳ

31.0 ሚሊዮን

980  ቢሊዮን የካ. ዶላር

20  ቢሊዮን የካ. ዶላር

2.1

ፈረንሣይ

61.9 ሚሊዮን

1.7 ትሪሊዮን ዩሮ

መረጃ የለም

2

ጀርመን

82.5 ሚሊዮን

2.1 ትሪሊዮን ዩሮ

200 ቢሊዮን ዩሮ

9

አየርላንድ

4.02 ሚሊዮን

148.9 ቢሊዮን ዩሮ

6.31 ቢሊዮን ዩሮ

4

ሰሜን አሜሪካ

296 ሚሊዮን

11.7 ትሪሊዮን ዶላር

660 ቢሊዮን ዶላር

6

 

መደምደሚያ

የመድን ዓረቦን እንዲጨምር ከሚያደርጉት ምክንያቶች አንዱ የመድን ሸፍጥ መሆኑን ከላይ ተብራርቷል፡፡ ያላግባብ የሚከፈሉ የካሣ ክፍያዎችም ሆኑ በዚያ ዙርያ የሚከፈሉ ሌሎች ተመሳሳይ ወጪዎች እየተደማመሩ የመድን ጉዳት ክስረት አካፋይ ቀመሩን (Loss ratio) ስለሚያንሩት ወጪዎችን ለማጣጣት መድን ሰጪዎች ዓረቦን እንዲጨምሩ፣ ነጋዴዎች ደግሞ የመድን ዓረቦን ሲንርባቸው ወጪአቸውን በሸቀጦችና በዕቃዎች ዋጋ ላይ  እንደሚያጣጡ  ተገልጾአል፡፡ ስለዚህ የዓረቦን ተመን በናረ ቁጥር ኅብረተሰብ የመድን ዋስትና በተመጣጣኝ ዋጋ ማግኘት አዳጋች ይሆንበታል፡፡ ከዚህ አንፃር በጥቅሉ ሲታይ የመድን ሸፍጥ የሚጎዳው ከመድን ሰጪዎች ይልቅ የመድን ተጠቃሚውን ኅብረተሰብ እንደሆነ ግልጽ ነው፡፡ ምክንያቱም፣ ዓረቦን ቢወደድም "መድን አልባነት" (Uninsurance - the state of being uninsured) የሚያስከትለው የጉዳት ክስረት (loss)  ስለሚከፋ የሠለጠነ ኅብረተሰብ መድን ከመግዛት አይቆጠብም፡፡ በዓለም ዙርያ ከላይ የተጠቀሱትን የመድን ሸፍጥ ችግሮች ለመከላከል መንግሥታትና መድን ሰጪዎች ትልቅ ፈተና ተጋርጦባቸዋል፡፡ በአገራችንም ቢሆን የመድን ሸፍጥ ያው የሙስና ወንጀል ስለሆነ መንግሥት፣ መድን ሰጪዎችና ኅብረተሰቡ የችግሩን ስፋት በጥልቀት ተረድተው የመሸ ቢሆንም ሳይነጋ አጥብቀው  ሊዋጉት ይገባል፡፡

ከአዘጋጁ፡-  ጸሐፊው [BA, LLB (GD), Graduate Dipl. in Development Administration (India), ACII, Chartered Insurer (UK), ACS (USA)] ለረጅም ዓመታት በመድን ሥራ፣ በሥልጠና፣ በመድን ምርምርና ሥነ ጽሑፍ ሰፊ ልምድና ዕውቀት ያላቸው ሲሆኑ፣ የመድን ባለሙያዎች ማኅበር (SIP) የመጀመርያው ፕሬዚዳንት ነበሩ፡፡ ጽሑፉ የእሳቸውን አመለካከት ብቻ የሚያንፀባርቅ መሆኑን እየገለጽን፣ ጸሐፊውን በኢሜል አድራሻቸው eyosono@gmail.comወይም leeyobed@yahoo.comወይም በቴሌፎን ቁ. +251 0911 43 15 50 ማግኘት ይቻላል፡፡

 

 

 

Standard (Image)

መንግሥት ሙስናን ለመታገል ቁርጠኝነት ካለው የራሱን ጓዳ ይፈትሽ

$
0
0

 

የዕድገትና ትራንስፎሜሽን ዕቅዱ ሰነድ ላይ መልካም አስተዳደር ማስፈን፣ የኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከትና የእሱ መገለጫ የሆነውን ሙስና መታገል የሞት ሽረት ጉዳይ ነው መባሉን ያነበብኩ ይመስለኛል፡፡ ዕውን በአገሪቱ እየተካሄደ ያለው የሙስና ትግል መልካም አስተዳደርን ለማስፈን በሚያስችል ደረጃ ላይ ነው ወይ ቢባል እውነታው ግን ሌላ ነው፡፡ የንግድ ሚኒስትሩ ሰኔ 6 ቀን 2009 ዓ.ም. ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረቡት ሪፖርት ‘የኮንትሮባንድ ጉዳይ ላይ እርር ድብን ብሎ መድረክ ላይ የሚናገር የመንግሥት አመራር ራሱ በር ከፋች ነው'ያሉት ለዚህ ጽሑፍ መነሻዬ ነው፡፡

በእያንዳንዱ የፀረ ሙስና ትግል ሒደት ላይ የኮንትሮባንድ ነጋዴ አመራሮች ሚናን ለማሳየት እሞክራለሁ፡፡ የኮንትሮባንድ ነጋዴ አመራር በየመድረኩ ዜጎች ፊት ሆኖ ‘ኪራይ ሰብሳቢነትን ደፍቀን፣ መልካም አስተዳደር እንዲሰፍ አድርገን የኢትዮጵያ ህዳሴን እውን እናደርጋለን'እያለ ይደነፋል፣ ይፎክራል፡፡ ኪራይ ሰብሳቢነትንና ሙስናን ይረግማል፣ ያስረግማል፡፡ ይህ የመንግሥት ኃላፊ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ አስመጪና ላኪ ነው፣ የኮንትሮባንድ ንግድ ይፈጽማል፣ በዚህም በገበያ ውስጥ የዕቃ ዋጋ እንዲዛባ ያደርጋል፡፡ ግብርና ታክስ ያጭበራብራል፡፡ ሙስና ይሠራል፡፡ ሙስናን እንድትጠየፉ እያለ አመራር ይሰጣል፡፡ ኪራይ ሰብሳቢ ራሱ ሆኖ በጠራራ ፀሐይ የኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከትን እንታገላለን ይላል፡፡

ይህ እውነታ ባለበት የኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከትና የእሱ መገለጫ የሆነው ሙስን መታገል እንዴት ሆኖ የሞት ሽረት ጉዳይ ሊሆን ይችላል? እኔ ከእውነታው በመነሳት የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ አፈጻጸም ሒደት ላይ በሙስና ማደግ የሞት ሽረት ጉዳይ ነው ቢባል ትክክለኛ ይሆናል የሚል አስተሳሰብ አለኝ፡፡ የሙስና ትግል መካሄድ ያለበት ይህን እንዲያስተባብር በሕግ ሥልጣን በተሰጠው ተቋም ብቻ መሆን የለበትም፡፡ ሁሉም የመንግሥት ተቋማት ሚናቸውን በትክክል መወጣት ይኖርባቸዋል፡፡ ለዚህ ደግሞ የበግ ለምድ የለበሱ ግን በግ ነን የሚሉ ተቋማትን በሚመሩ ተኩላ የኮንትሮባንድ ነጋዴ አመራሮች ከሆነ፣ በአገሪቱ ውስጥ ሙስና አይጠሩም፣ መልካም አስተዳደርም በጭራሽ ሊሰፍን አይችልም፡፡

 በአገሪቱ ሙስናና ብልሹ አሠራር ትግል እንዲያስተባብር በሕግ የተዋቀረው የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ከሚያከናውናቸው ተግባራት ውስጥ የሙስና ወንጀል ምርመራ እንዲቀነስ የተደረገው፣ ከላይ እንደተገለጸው የኮንትሮባንድ ንግድ በሚያጧጡፉ ባለሥልጣናት ሥውር እጅ አማካይነት መሆኑ በጣም ግልጽ ነው፡፡ አሁን አሁን ያደረጉት ትክክል ነው እያልኩ ነው ራሴን እነሱ ቦታ ላይ አስቀምጬ ሳያው፡፡ ጥቅማቸውን የሚያስቀረውን ሕግ በማዳከም የሚፈልጉትን ጥቅም ማግኘት የሞት ሽረት ጉዳይ ስለሆነባቸው፣ ተግባሩ ግን ወዴት ይወስዳል የሚለውን ግን የተገነዙበት አይመስለኝም፡፡ ከሕዝብ ለዚያውም ከደሃው ሕዝብ ጉሮሮ ተነጥቆ የተወሰደው ሀብት በአንድ ቀን በጥቂት ደቂቃ ውስጥ ሊጠፋ እንደሚችል ግንዛቤ አለመያዛቸው ያሳዝናል፡፡

በዓለም ያሉት አብዛኛዎቹ የፀረ ሙስና ተቋማት የሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ትምህርት ማስተማር፣ ለሙስና ብልሹ አሠራር ተጋላጭ የሆኑ አሠራሮችን በመለየት መከላከል፣ የሙስና ወንጀል ጥቆማዎችን በመቀበል መመርመር ጎን ለጎን የሚከናወኑና በፍፁም የማይነጣጠሉ ናቸው፡፡ ደግሞ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀረ ሙስና ኮንቬሽን ይህን በግልጽ ይደነግጋል፡፡ በአገራችን ግን በእነዚህ ኮንትሮባንድ ነጋዴ በሆኑ የመንግሥት ኃላፊዎች ከሌሎች ኪራይ ሰብሳቢ ከሆኑ ባለሀብት ወዳጆቻቸው ጋር በማበርና በመመሳጠር የሙስና ወንጀል ጥቆማ መቀበልና ምርመራ የማካሄድ ሥራን ከኮሚሽኑ በመቀነስ ለፌዴራል ፖሊስ እንዲሰጥ አስደረጉ፡፡ ኮሚሽኑ በዚህ ሥራ ቢያንስ የዜጎችን ዕንባ የሚያብስና እሮሮ የሚያሰማ ተቋም ነበር፡፡ የሚገርመው ደግሞ ሕግ አውጭ አካል ውስጥም እነዚህ የመንግሥት አመራሮች መግባታቸው ነው፡፡ በሕግ አውጭ አካል ውስጥ ያሉትም ተባባሪና አጋር በመሆን በቅድሚያ የኮሚሽኑ ሥራ ጥላሸት እንዲቀባ ተግተው ሠሩ፡፡ ኮሚሽኑ ራሱ መርማሪና ከሳሽ ነው ብለው ነጠላ ዜማ አወጡ፡፡ የእነሱ አጫፋሪ የሆኑ የሚዲያ ሰዎችም ጉዳዩን አራገቡት፡፡ ቴሌቪዥን ነጠላ ዜማውን በተደጋጋሚ አስተላለፈ፡፡ መርማሪና ከሳሽ ሆኖ ያጠፋውን ጥፋት ግን መናገር አልቻሉም፡፡ ተው ስህተት ነው የምትሠሩት ሲባሉ ደግሞ አገሪቱ የእነሱ ብቻ እስከሚመስል ድረስ ደነፉ፣ አስፈራሩ፡፡

ቀጥሎም በ1996 ዓ.ም. ተካሄደ (በማን፣ እንዴትና መቼ የሚለው በዜጎች አልታየም) የተባለውን ጥናት ጠቅሰው የኮሚሽኑ የሙስና ወንጀል ምርመራ ሥራ ቆርሰው ወደ ሌላ ወረወሩት፡፡ ከኮሚሽኑ ተነጥቆ የሙስና ወንጀል ምርመራ ሥራ የተሰጠው ተቋም ምን ያህል ውጤታማ ነው የሚለውን ወደፊት ከመረጃዎች በማነፃፀር ለማቅረብ እሞክራለሁ፡፡ በመጋቢት ወር 2007 ዓ.ም. የግሉን ዘርፍ ያካተተ የኮሚሽኑ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 881/2007 ያወጣው ምክር ቤት፣ ልክ በዓመቱ የኮሚሽኑ ማዳከሚያ አዋጅ መጋቢት ወር 2008 ዓ.ም. በአዋጅ ቁጥር 943/2008 አወጀ፡፡  በሌላ በኩል እነዚህ አመራሮች ለኮሚሽኑ የቀረው የማስተማርና የመከላከል ሥራ የአገሪቱን የሙስና ችግር ለመቅረፍ ወሳኝና ቅድሚያ የሚሠጥ ሥራ ብለው ዘመሩ፡፡ መጀመሪያ መሠራት ያለበት ሥራ እሱ እያሉ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው መዘመራቸው ለእኔ አይገርምም፡፡

ዋናው መታየት ያለበት ከበስተጀርባቸው ያለው ሥውር የሙስና ወንጀል ሥራ የሆነው የኮንትሮባንድ ንግድ ነው፡፡ ‘ልጅ ለእናቷ ምጥ አስተማረች'ነው ነገሩ፡፡ እንዲያውም ከኮሚሽኑ አመራሮችና ሠራተኞች በላይ ስለመከላከልና ማስተማር የሚናገሩት እነዚህ አመራሮች ሆነው ተገኙ፡፡ ለማስተማር ለማስተማርማ የሃይማኖት ተቋማትም እኮ ስለሥነ ምግባር ብዙ ያስተምራሉ፡፡ ግን በሃይማኖት ተቋማት ውስጥ ስለሥነ ምግባር ትምህርት የሚሰጥ ቢሆንም፣ ስርቆት ደግሞ በብዛት አለ፡፡ ሃይማኖት ተቋማት ውስጥ ሙስና የሚሰሩት ፈሪኃ እግዚአብሔር የሌላቸው ሲሆኑ፣ ከኮንትሮባንድ ነጋዴ አመራሮች ግን የሚለዩት እኛን አትዩ በማለታቸው ነው፡፡ ቢያንስ ለመስረቀቸውን ንስሐ ገብተዋል፡፡ የኮንትሮባንድ ነጋዴ አመራሮች ግን እንደዚህ አይሉም፡፡ እነሱ ለራሳቸው በጣም ንፁህ ናቸው፡፡ ለፖለቲካ ድርጅታቸውና ለሕዝባቸው ሁሌም ሟች ነን ይላሉ፡፡ ግን አይደሉም፡፡ ሌቦች ናቸው፡፡

የፀረ ሙስና ኮሚሽን ከሚያከናውናቸው ሥራዎች አንዱ ሙስናና ብልሹ አሠራርን መከላከል ነው፡፡ አንዱን የማስፈጸም ክንፉ በሚሳይል የተመታው ፀረ ሙስና ኮሚሽን የተቀናጀ ሙስና የመከላከል ስትራቴጂ አስተገብራለሁ እያለ ሲዳክር ይታያል፡፡ አሠራሩ በአውስትራሊያ፣ በፊሊፕንስ፣ በጎሮቤታችን ኬንያ ጭምር ይተገበራል፡፡ አሠራሩ በአጭሩ ሲታይ የተዘጋጀውን የሙስና መከላከል ስትራቴጂ ሰነድ ለተቋማት አመራሮችና ሠራተኞች ግንዛቤ እንዲይዙ ይደረጋል፡፡ የተቋማት ሙስና መከላከል ፖሊሲ ይነደፋል፡፡ የተቋማት የሥጋት አካባቢዎች ይለያሉ፡፡ የሥጋት አካባቢ የመለየት ሥራ መሠራት ያለበት ለዚህ ሥራ በተዋቀረው ኮሚቴ አማካይነት ነው፡፡ የተለዩ የሥጋት አካባቢዎች የተቋሙን ሠራተኞችና የሕዝብ ክንፍ ይሁንታ ያገኛሉ፡፡ ለተለዩት የሥጋት አካባቢዎች የመከላከያ ስትራቴጂ ዕቅድ ይነደፋል፡፡ ዕቅዱ ለፀረ ሙስና ኮሚሽኑ ይላካል፡፡ የመከላከያ ስትራቴጂው የሚተገበረው ሥጋት ያለበት የሥራ ክፍል ይሆናል፡፡ አሁን እየታየ ያለው ስህተት ዕቅዱ የሥነ ምግባር መኮንን ዕቅድ እንዲሆን ማድረግ ነው፡፡ በመጨረሻም የመከላከያ ስትራቴጂው ያመጣው ለውጥ በተቋሙ አመራር፣ በሠራተኞችና በሕዝብ ክንፍ ዕውቅና ማግኘት አለበት፡፡

በመቀጠልም የፀረ ሙስና ኮሚሽኑ በስትራቴጂው ትግበራ ዓመት ውስጥ የመጣውን ለውጥ በመገምገም ከሙስና የፀዳ ተቋም የሚል ማረጋገጫ ይሰጣል፡፡ ይህ ሥራ የሚሠራው በተቋም ውስጥ ባሉት አመራሮች ቁርጠኝነትና በፀረ ሙስና ኮሚሽን ክትትልና ድጋፍ ነው፡፡ ኮሚሽኑ ሪፖርት ያዘጋጃል፡፡ የተወካዮች ምክር ቤትም እንደ ዋና ኦዲተር ሪፖርት ዓይነት ቢያንስ በዓመት አንድ ጊዜ በዚህ አፈጻጸም ዙሪያ የፀረ ሙስና ኮሚሽንን ሪፖርት ይገመግማል፡፡ ነገር ግን ኮሚሽኑ ይህን ቅዱስ ሐሳብ ይዞ ይነሳ እንጂ አንዳንድ ተቋማት ስትራቴጂውን ለማከናወን ፈቃደኞች አለመሆናቸውን የኮሚሽኑ የዘጠኝ ወራት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ያሳያል፡፡ እዚህ ላይ ኮሚሽኑ ያለው የሰው ኃይል ፍልሰት በጣም ከፍተኛ ከመሆኑ አንፃር ብቃትና ክህሎት ያለው የሰው ኃይል ስለማይኖረው፣ ይህን ስትራቴጂ አንዳንድ አመራሮችን በትክክል በማሳመን ለማስተባበር አቅም ያንሰዋል፡፡ የኮሚሽኑ ወዳጅና ደጋፊ የሆነ የመንግሥት አመራርና ባለሀብት ይኖራል ብዬ አላስብም፡፡ በተለይ አንዳንድ የመንግሥት ኃላፊዎች ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ኮሚሽኑን የሚያዳክሙ ተግባራትን ለመከወን ነቅተው ይጠባበቃሉ፡፡ የምርመራ ሥራም ተወስድቦታል፡፡ ደሃው ሕዝብ ኧረ ተው ቢል የሚሰማ ለም፡፡ መንግሥት ግን አገር መሪ በመሆኑ ሙስና ባይጠፋም እንዲቀንስ ከልብ ሊደግፍ ይገባል፡፡ ኮሚሽኑም ይህን የሚክድ አይመስለኝም፡፡

ታዲያ እንዴት ሆኖ ነው የትራንስፎሜሽን ዕቅድ ሊሳካ የሚችለው? ሌላው ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ በ2009 ዓ.ም. ቀንና ወሩን ባላስታውስም የሀብት አስመዝገቢዎች ሀብት ለሕዝብ ይፋ እንደሚደረግ፣ ሕዝቡም የተመዘገበውን ሀብት መጠን እያየ ልዩነት ካለ ጥቆማ ሲያቀርብ ዕርምጃ እንደሚወሰድ ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥተው ነበር፡፡ በአገራችን የሀብት ማሳወቅና ምዝገባ በሕግ ተደግፎ ሥራው ከተጀመረ ሰንብቷል፡፡ የሀብት ምዝገባ በፀረ ሙስና ኮሚሽን እየተሠራ እንደሆነ አውቃለሁ፡፡ ሀብታቸውን የሚያስመዘግቡ ሰዎች እነማን እንደሆኑና እነዚህ ሰዎች ሀብታቸውን ማስመዝገብ ሲገባቸው የደበቁት ካለ ይህን የሚያውቅ ሰው ለፀረ ሙስና ኮሚሽን ጥቆማ ካቀረበ፣ ጥቆማ የቀረበበት ሀብት እውነትነቱ ከተረጋገጠ አንድ አራተኛውን ጥቅም እንደሚያገኝ ሕጉ ይደነግጋል፡፡ ነገር ግን የተመዘገበው ሀብት እስከ ዛሬ ድረስ ለሕዝብ ዕይታ አለማቅረቡ እንቆቅልሽ ነው፡፡

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩም የተመዘገበው የአመራር ሀብት ለሕዝብ ይፋ ይሆናል ያሉትም ማንን አማክረው እንደሆነ ግልጽ አይደለም፡፡ ፀረ ሙስና ኮሚሽንም የተመዘገበውን ሀብት ለማሳየት በቅድሚያ የጀመርኩትን የአውቶሜሽን ማለትም የቴክኖሎጂ ልማት ሥራ ላጠናቅቅ ካለ ዓመታትን አስቆጥሯል፡፡ ሚዲያዎች ኮሚሽኑ ለምን የተመዘገበውን ሀብት ማሳየት እንዳልፈለገ በተደጋጋሚ ጠይቀው በቂ ምላሽ ሳያገኙ ሲሰለቻቸው፣ አሁን አሁን የተውት ይመስለኛል፡፡ ነገር ግን የተመዘገበ ሀብት ከማሳወቅ ጀርባ የኮንትሮባንድ ነጋዴ የመንግሥት አመራሮች ሥውር እጅ እንዳለ ይገመታል፡፡ ምክንያቱም የተዘመገበ ሀብት ይፋ ሲሆን ሀብት ያስመዘገባና ያላስመዘገበ፣ ወይም የተመዘገበና ያልተመዘገበ ሀብት መጠን ልዩነት በትክክል ሊታወቅ ስለሚችል ከወዲሁ በመፍራት እንዳይታይ እያደረጉ ነው የሚሉ ጉምጉምታዎች በዜጎች ዘንድ በስፋት አለ፡፡ በሌለ በኩል ኮሚሽኑም እንደ ሙስና ወንጀል ምርመራና ሀብት ማሳወቅና ምዝገባ ሥራዎችን እንዳይነጠቅ ሥጋት ስላለበት ድፍረት አጥቶ ይሆናል የሚሉም አልታጡም፡፡

ፀረ ሙስና ኮሚሽን ከሚሠራቸው ሥራዎች የሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ትምህርት መስጠት ሌለው የፀረ ሙስና ትግል ዘዴ ነው፡፡ የሙስና ወንጀል ምርመራ ሥራ በእጁ በነበረበት ወቅት ለሥነ ምግባርና ለፀረ ሙስና ትምህርት ጥሪ ሲደረግ፣ አብዛኛው ጥሪ የተደረገለት ሰው እየመጣ ሥልጠናውን ይወስድ ነበር፡፡ አሁን አሁን ግን ሰው አንድ ክንፉ በሚሳይል የተመታበትና የፈረሰ የፀረ ሙስና ኮሚሽን ምን ሊፈይድ ነው ሥልጠና የሚሰጠው የሚል አቋም በመያዝ ጥሪውን ተቀብሎ በመምጣት ሥልጠና ለመውሰድ በጣም ዳተኛ እየሆነ ይገኛል፡፡ ሌላው የሚዲያ ዳተኝነት ነው፡፡ በ2009 በጀት ዓመት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በመንግሥት ሚዲያ ላይ ያለውን ችግር በግልጽ በመገምገም ቀጣይ የማሻሻያ አቅጣጫ ማስቀመጡ በጣም ነበር ደስ ያለኝ፡፡ የመንግሥት ሚዲያዎች በተለይም ዋናው ቴሌቭዥን ጣቢያ የሥነ ምግባርና የሙስናን ጉዳይ እንዳይዘግብ በቦርድ የተከለከለ መሆኑን ከውስጥ አዋቂዎች ሰምቼአለሁ፡፡ ምናልባት በሚዲያ አካባቢ የኮንትሮባንድ ነጋዴ የሆኑ የመንግሥት አመራሮች መኖራቸው ስለሆነ አይገርምም፡፡ ስለዚህ መንግሥታችን በፀረ ሙስና ትግል ላይ ፅኑ አቋምና ቁርጠኝነት ካለው፣ በእነዚህ የኮንትሮባንድ ነጋዴ በሆኑ የመንግሥት አመራሮች የሚፈጸመውን የፀረ ሙስና ትግል የማዳከም ሥራ በትክክል ሊገነዘብ ይገባል፡፡ አመራሩ ለታችኛው ሠራተኞች አርዓያ መሆን ሲገባው ኮንትሮባንድ ነጋዴ ከሆነ፣ የታችኛው ሠራተኛም ድርሻውን መውሰድ ስለሚፈልግ በዚህ ሰበብ የሚጨፈለቀው ደሃው ዜጋ ምን ያህል እንደሚሆን መገመት ይቻላል፡፡

በተለይም በብዛት የዕለት አገልግሎት  የሚሰጥ ተቋም ውስጥ ሠራተኞች አርፍደው ሥራ ሲገቡ፣ ዜጎች በደላሎች አደራደሪነት አገልግሎት ለማግኘት ሲገደዱ፣ ሠራተኛው መረጃዎችን በማጥፋት ተገልገይ  ዜጎች አገልግሎቱን ለማግኘት በተደጋጋሚ እንዲመላለሱ ሲደረግ፣ አገልግሎቱን ለማግኘት ጉቦ ሲጠየቁ፣ በትውውቅ፣ በብሔርና በሃይማኖት አገልግሎት ሲሰጥ ዜጎች በመንግሥት ላይ እምነት ያጣሉ፡፡ በመንግሥት ላይ ጥላቻን ያሳድራሉ፡፡ አመራሩም በአንደበቱና በወረቀት ላይ ብቻ ሙስናን እንደሚጠየፍ እየተናገረ፣ እየረገመና እያስረገመ በተግባር ግን የኮንትሮባንድ ነጋዴ ሲሆን፣ በአንድ በኩል አገሪቱ ማግኘት ያለበትን ግብርና ታክስ ከማስቀረት በተጨማሪ ልማታዊ ነጋዴዎች ይደክማሉ፡፡ የተዳከመ ልማታዊ ነጋዴ ደግሞ ግብርና ታክስ መክፈል አይችልም፡፡ የሥራ አጥ ቁጥር በአገሪቱ በጣም እንዲጨምር ያደርጋል፡፡ በዚህም በዕድገትና ትራንስፎሜሽን ዕቅድ ሰነድ ላይ የተቀመጡ ግቦች ውጤታማ አይሆኑም፡፡ በአገሪቱ ሙስና ይስፋፋል፡፡ ዜጎች መብታቸውን በገንዘባቸው ለመግዛት ይገዳደሉ፡፡ ዜጎች በመልካም አስተዳደር ዕጦት ሲንገላቱ ይኖራሉ፡፡ ድሆች ነን፣ ደሃ ሆነን እንኖራለን፡፡ ጥቂቶች በጣም የተንደላቀቀ ኑሮ ይኖራሉ፡፡

ስለዚህ መንግሥት የፀረ ሙስና ኮሚሽን ያለበትን ችግር በቅርበት በመገምገም፣ የኮንትሮባንድ ነጋዴ በሆኑ አመራሮች በሥውር እጅ እንዲቀነስ የተደረገውን የሙስና ወንጀል ምርመራ ሥራ ወደ ቦታው በመመለስ፣ ሕዝቡ በፀረ ሙስና ትግል በነፃነትና በእምነት እንዲተሳተፍ በማድረግ፣ እንዲሁም በቦርድ የተከለከለው የሚዲያ የሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ዘገባዎች በግልጽነት በሚዲያዎች እንዲተላለፉ በማድረግ የተጀመረውን የአገሪቱን ህዳሴ ጉዞ ከልብ እውን እንዲሆን በማድረግ ከነበረብን ድህነት እንዲያላቅቀን በፈጣሪ ስም እጠይቃለሁ፡፡ መንግሥት ቁርጠኝነት እንዲኖረውና የኮንትሮባንድ ነጋዴ የሆኑ አመራሮቹን ጭምር ለመታገል ከፈለገ ውስጡን ደጋግሞ ይፈትሽ፡፡ ሙስናን ታግለን ህዳሴያችንን ዕውን እንደምናደርግ ፅኑ አቋም አለኝ፡፡ ሁሌም ከልማታዊ መንግሥታችን ጎን እቆማለሁ፡፡ ለዚህም ሙስናን በፅናት እታገላለሁ፡፡

ኮንትሮባንድን በንቃት በመከላከል የአገሪቱን የህዳሴ ጉዞ እናፋጥን!!

ከአዘጋጁ፡- ጽሑፉ የጸሐፊውን አመለካከት ብቻ የሚያንፀባርቅ ሲሆን፣ ጸሐፊውን በኢሜይል አድራሻቸው  geberealemu@yahoo.comማግኘት ይቻላል፡፡    

Standard (Image)

አቢጃታና ሻላን ከመጥፋት እናድን!

$
0
0

በሮቤ ባልቻ

በቅርቡ በሪፖርተር ጋዜጣ ‹‹አቢጃታን ተዩው›› በሚል ርዕስ የቀረበውን መልዕክት ተመልክቼዋለሁ፡፡ መልዕክቱን ያቀረቡትን ሰለሞን ወርቁ የተባሉ ጸሐፊን አደንቃቸዋለሁ፡፡ አውቀውም ሆነ ሳያውቁ በአገር ተፈጥሯዊ ሀብት ላይ ጎጂ ውሳኔ የሚያሳልፉ፣ ግለሰቦችና መሥሪያ ቤቶች ዕርምጃዎቻቸውን መልሰው እንደሚያጤኑ ጸሐፊው ኃላፊነታቸውን ተወጥተዋል፡፡ ከአስተያየታቸውም እንደተረዳሁት ጉዳዩ በጎ ምላሽ  ካላገኘ፣ ለወደፊቱም ገንቢና ቀጣይ መልዕክቶች ይኖሩዋቸዋል ብዬ አስባለሁ፡፡

ይህ የአገርን ተፈጥሯዊ ሀብትና ሥነ ምድራዊ ገጽታ የሚጎዳ ጥናትና ውሳኔ ለአቶ ሰለሞን አስተያየት ብቻ የሚተው አይደለም፡፡ አሁን በአቢጃታና በሻላ ሐይቆች ላይ የተደቀነው አሳሳቢ ሁኔታ፣ ለዛሬውና ለነገው ትውልድ ጎጂ መሆኑን የሚያምን ዜጋ ሁሉ ድምፁን ሊያሰማበት የሚገባ ነው፡፡

ከጥቂት ዓመታት በፊት በሐሮማያ ሐይቅ መድረቅ መንስዔ ላይ ጥናት ያካሄዱ ባለሙያ ምክንያቶች ያሉዋቸውን ዝርዝሮችን ሲያቀርቡ፣ በብሔራዊ ቴሌቪዥን መከታተሌን አስታውሳለሁ፡፡

በሐይቁ ዙሪያ የነበሩ ተክሎችና ቁጥቋጦዎች ተመንጥረው አካባቢው መራቆቱን እንደ አንድ መንስዔ አውስተው ነበር፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የሐይቁ ውኃ ለከተማውና ለአካባቢው ፍጆታ ከአቅም በላይ አገልግሎት ላይ በመዋሉ እንደሆነም ገልጸው፣ ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮችን አንስተው እንደነበር ትዝ ይለኛል፡፡  

ዛሬ ጥፋት የተደቀነባቸውን አቢጃታና ሻላ ሐይቆች ስናነሳም ከሐሮማያ ሐይቅ የተለየ ዕጣ እንደማይጠብቃቸው ግልጽ ነው፡፡፡ ከመነሻው በአቢጃታና በሻላ ሐይቆች ዙሪያ መቋቋም የነበረበት የሶዳ አሾ ማምረቻ ፋብሪካ አይደለም፡፡ ለዘመናት ተፈጥሮ በአካባቢው ያለመለመቻቸው የግራር ዛፎችና ሌሎችም ተክሎች በይበልጥ እንዲለመልሙ መሠራት ነበረበት፡፡ የአካባቢው ተፈጥሮ ጥበቃ የሚጠናከርበትና ለቱሪስቶች ዕይታ የሚያመቹ መዝናኛዎች፣ መመልከቻዎችና ማረፊያዎች መዘጋጀት ነበረባቸው፡፡ ቀደም ሲል ተሠርተው አገልግሎት ላይ የነበሩና ዛሬም በመስፋፋት ላይ የሚገኙ የስምጥ ሸለቆ መዝናኛና ማረፊያ ሥፍራዎች በይበልጥ ተሻሽለው፣ ዓለም አቀፍ ደረጃ የጠበቁ እንዲሆኑ ማገዝና መደገፍ ይገባ ነበር፡፡ ይህ ሳይሆን ቀርቶ የአቢጃታን ሐይቅ ውኃ ሲጠቀም የነበረው ፋብሪካ፣ ውኃው በመቀነሱ ወደ ሻላ ሐይቅ ለመሸጋገር ጥናት በማድረግ ላይ ነኝ ማለቱ አስገራሚ ነው፡፡

አቢጃታና ሻላ ሐይቆች በአፍሪካም ሆነ በዓለም የሚታወቁባቸው የራሳቸው መለያ እንዳላቸው በአቶ ሰለሞን በዝርዝር ቀርቧል፡፡ አቢጃታ፣ ሻላና ጭቱ ሐይቆች ማረፊያ የሆኑት በአገራችን ለሚገኙ የአዕዋፍ ዝርያዎች ብቻ ሳይሆን፣ ከዓለም ዙሪያ ረዥም ርቀት አቋርጠው ለሚመጡ ተሰዳጅ አዕዋፍ ጭምርም እንደሆነ በጸሐፊው ተገልጿል፡፡ እነዚህ ሐይቆች 453 የተለያዩ የአዕዋፋት ዝርያዎች መያዛቸውንም በልዩነት አስቀምጠውታል፡፡ በሐይቆቹም በዓመት 5,000 ያህል ሻሎዎች እንደሚራቡባቸውም አስፍረዋል፡፡ 50,000 ፍላሚንጐዎችና 40,000 ያህል መንቁረ ግልብጥ አዕዋፋት በማረፊያነትና በመመገቢያነት እንደሚገለገሉባቸው አቶ ሰለሞን ጥሩ አድርገው ገልጸውታል፡፡

ከዚህ የምንገነዘበው ተፈጥሮ ሐይቆቹን ውብ አድርጎ እንደሰጠን ነው፡፡ በተፈጥሯዊ ውበቱ ላይ ደግሞ የተለያዩ ዝርያ ያላቸው አዕዋፋት ሠፍረውበታል፡፡ በቦታው ተገኝቶ የማየት ዕድል ያላገኘ ሰው እንኳን ጽሑፉን በማንበብ ብቻ በሐይቆቹ የሚኖረውን ትዕይንትና ውበት በዓይነ ህሊናው መመልከት ይችላል፡፡ ጊዜና ሁኔታ ሲፈቅድለትም ሄዶ ለመጎብኘትም ያስባል፣ ያቅዳል፡፡ ይህንን ተፈጥሯዊ ሀብት በዘላቂነት መጠበቅ ከተቻለ ደግሞ፣ በአግባቡ አስተዋውቆና የቱሪስት መስኅብ አድርጎ እንደ ሌሎች አገሮች ተጠቃሚ መሆን ይቻላል፡፡ በእኔ ግምት የሶዳ አሾ ፋብሪካው የሐይቁን ውኃ መጠቀሙ ብቻ ሳይሆን፣ በዙሪያው መቋቋሙ ራሱ በሐይቁ ላይ የሚያስከትለው ጉዳት ይኖረዋል፡፡ የጉዳቱን ዓይነትና መጠን ግን የመስኩ ባለሙያዎች አጥንተው ቢያቀርቡት ይመረጣል፡፡

ከሶዳ አሾ ፋብሪካው በተጨማሪ በባቱ (ዝዋይ) ከተማ የመስኖ ሥራ የሚያከናውኑ የአበባ፣ እርሻና የወይን እርሻ ድርጅቶች 6,000 የሚደርሱ የውኃ መሳቢያ ፓምፖች በመትከል የአቢጃታን ሐይቅ በመጠቀም ላይ እንደሚገኙ ምንጭ ጠቅሰው አቶ ሰለሞን አስፍረዋል፡፡ በእኔም አስተያየት ይህ ተግባር የአቢጃታን ሐይቅ ሞት እንደ ሐሮማያ ሐይቅ የሚያፋጥን ድርጊት ነው፡፡ አቶ ሰለሞንም ይህንኑ ጠቅሰዋል፡፡      

የአበባና የወይን እርሻዎቹ ገና ሲቋቋሙ በአቢጃታ ውኃ ላይ ተማምነው ሥራ መጀመር አልነበረባቸውም፡፡ ፈቃድ ሰጪው ክፍልም የኢንቨስትመንት ፈቃዱን ከሌላ አማራጭ ጋር ሊሰጣቸው ይገባ ነበር፡፡ ሁለቱም ድርጅቶች በተናጠል ወይም በጋራ በሌሎች አማራጮች ዙሪያ ጥናት እንዲያደርጉ ማሳሰብ ይቻል እንደነበር እገምታለሁ፡፡ ለእኔ የሚታዩኝ አማራጮች ጥልቅ ጉድጓዶች ቁፋሮ፣ በቅርበት ያሉ ወንዞችን አጎልብቶ መጥለፍና ውኃ ማቆር ናቸው፡፡ የዚህ ዘርፍ ባለሙያ ባልሆንም፣ እነዚህን አማራጮች በተናጠል ወይም በማዳበር እርሻዎቹ መጠቀም ይችሉ እንደነበር መገመት እችላለሁ፡፡፡ ከመነሻው ሌላ አማራጭ ሳይታይ ዝግጁ ሆኖ ያለን የተፈጥሮ ሀብት እንደ መጨረሻ መፍትሔ ወስዶ ለጥፋት መዳረግ ግን የሚደገፍ አይደለም፡፡ አማራጮች ቀርበውላቸው ባለሀብቶቹ ከአቢጃታ ሐይቅ ውጪ ሌሎቹን የማይቀበሉ ከሆነ፣ ስምምነቱ እዚያው ላይ መቆም ነበረበት፡፡ በአግባቡ ከሠራንበትና ጥቅም ላይ ካዋልነው፣ ዛሬ ለእኛ ነገ ደግሞ ለልጆቻችን የሚተርፍ ውብ ሀብት ከሚጠፋ የአበባ ልማቱና የወይን ምርቱ ቢቀር ይመረጣል፡፡

ዛሬም ቢሆን የአበባና የወይን እርሻዎቹ ሌሎች አማራጮች ከአሁኑ እንዲፈልጉ ቀጣይ ድርድር ማመቻቸት ይገባል፡፡ የሐይቁ ውኃ እየቀነሰ መጥቷል ተብሏል፡፡ እየቀነሰ ከመጣ ደግሞ ነገ መድረቁ የማይቀር ነው፡፡ ነገ ሲደርቅ እርሻዎቻቸው ሥራ ከሚያቆሙ ከአሁኑ በአማራጮች ዙሪያ ጥናት ማካሄድ ይኖርባቸዋል፡፡ ጥናታቸው ግን በቅርባቸው ወደሚገኙ ሌሎች ሐይቆች መሸጋገርን የሚጨምር ሊሆን አይገባም፡፡

አቢጃታንና ሻላን የመሳሰሉ ሐይቆች አካባቢ የማዕድን ቁፋሮና የማምረቻ ፋብሪካ ሲታሰብ፣ ጉዳዩ የሚመለከታቸው መንግሥታዊ መሥሪያ ቤቶች ተነጋግረውበት ይወስናሉ የሚል ግምት አለኝ፡፡

ለምሳሌ በተፈጥሮ ሀብት ላይ የሚያስከትለውን ጉዳት አስመልክቶ የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃና ልማት የሚመለከተው መሥሪያ ቤት፣ የማዕድን ኮርፖሬሽን፣ የዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ ባለሥልጣንና የኢንቨስትመንት ጉዳዮች የሚመለከተውን መሥሪያ ቤትና ሌሎችንም ማንሳት ይቻላል፡፡

ከእነዚህ ግዙፍ መሥሪያ ቤቶች ሶዳ አሾ ፋብሪካ በሐይቁ አካባቢ መቋቋሙና የሐይቁን ውኃ መጠቀሙ ተፈጥሯዊ ሚዛኑን ሊያዛባ እንደሚችል ገምቶ፣ አማራጭ ሥፍራ እንዲፈልግ የሚያደርግ ባለሙያና ክፍል እንዴት ይታጣል? በእርግጥ የዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ ባለሥልጣን ዕርምጃው በተፈጥሮ ላይ ጉዳት እንደሚኖረው አመልክቶ ሰሚ ማጣቱ ተጠቅሷል፡፡ የተቀሩት መሥሪያ ቤቶች ኃላፊዎችና ኤክስፐርቶቻቸው ሊከተል የሚችለው ጉዳት እንዴት አልታያቸውም? የአበባና የወይን እርሻዎቹስ ይህንኑ የሐይቅ ውኃ እንዲጠቀሙ እንዴት ተፈቀደ? ለምንስ ሌሎች አማራጮች አልቀረቡባቸውም?

ፋብሪካውና እርሻዎቹ የሚገለገሉበት የሐይቁ ውኃ እየቀነሰ ሲመጣ ፋብሪካው ወደ ሻላ ሐይቅ ለመሸጋገር ጥናት መጀመሩንስ እነዚህ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች እንዴት ያዩታል? ውብ የተፈጥሮ አካባቢዎችን ለተሻለ ልማት እንጂ፣ በቀጣይነት ለጥፋት የሚዳርግ ውሳኔ ውስጥ እንደማይገቡ ተስፋ ይደረጋል፡፡

የአቢጃታና የሻላ ሐይቆች ተፈጥሯዊ ውበት እንደተጠበቀ እንዲቆይና አዕዋፋቱም ቀጣይ ሕይወት እንዲኖራቸው በየኃላፊነታችንና በሙያችን ዕገዛ ማድረግ ይጠበቅብናል፡፡ አቢጃታ ሙሉ በሙሉ ከመድረቁ በፊት ፋብሪካውና የመስኖ እርሻ የሚጠቀሙ ድርጅቶች አማራጭ መፍትሔዎች ሊፈለግላቸው ይገባል፡፡ ወደ ሻላ ወይም ሌሎች የስምጥ ሸለቆ ሐይቆች ለመሸጋገር የሚደረግ ማንኛውም ጎጂ እንቅስቃሴ ቢገታ፣ የተፈጥሮ ሀብቶቹን ለመንከባከብ ድርሻ አለው ብዬ አምናለሁ፡፡

በስምጥ ሸለቆ ሐይቆች ዙሪያ አዳዲስና ዘመናዊ የቱሪዝም ማስፋፊያ ፕሮጀክቶች ይዘው የሚቀርቡ አልሚዎች እንዲበረታቱ ያስፈልጋል፡፡

ተፈጥሮን ስንደግፋትና ስንንከባከባት እሷም መልሳ ትክሳናለች፡፡ በግድ የለሽነት ያለበቂ ጥናት ስናጠፋት እሷም በተራዋ ምላሽ አላት፡፡ በሚከተለው ተፈጥሯዊ ጉዳትም መጪው ትውልድ ተወቃሽ ያደርገናል፡፡

አቢጃታ ሐይቅና ብርቅዬ አዕዋፋቱ ከጥፋት ድነው የልማትና የቱሪዝም ማዕከል እናድርጋቸው፡፡ ሻላ ላይ የታቀደው የአማራጭነት ትልምም ይቁም፡፡ ውብ የተፈጥሮ አካባቢዎችን መጠበቅና የበለጠ ምቹ አድርጎ መያዝም ሌላው የልማት ዘርፍ መሆኑ ይሰመርበት፡፡ ይህንን ማድረግ መቻል ደግሞ የአገራችንን ተፈጥሯዊ ሀብቶች ሚዛናዊ በሆነ መንገድ የመጠበቅ አንዱ አካል ነው፡፡

ከአዘጋጁ፡- ጽሑፉ የጸሐፊውን አመለካከት ብቻ የሚያንፀባርቅ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

         

Standard (Image)

አቢጃታ - በእኛ አገር ‹‹የሄደና የሞተ ነው የሚመሰገነው››

$
0
0

በሰለሞን ወርቁ

ከዕለት ወደ ዕለት ኩርማን የማይሞላ ውኃ እየቀረው የመጣው የአቢጃታ ሐይቅ በአፋጣኝ እንዲያገግም ካልተደረገ በአምስት ዓመታት ጊዜ ውስጥ ነጭ አሸዋና ትዝታው ብቻ ይቀራል፡፡ የሐይቁ ውኃ መቀነስና የአካባቢው መራቆት ምክንያት ያደረጉ በርከት ያሉ ጥናቶች በየጊዜው በተለያዩ ተቋማትና ግለሰቦች ተጠንተዋል፡፡ ጥናቶቹ የችግሮቹን መነሻ አንስተው በአጭር ጊዜ ውስጥ ሊወሰዱ ስለሚገባቸው ርምጃዎች የራሳቸውን የይሁንታ ሐሳብ ያቀርባሉ፡፡ በአንጻሩ ግን ይህንን ችግር ከወዲሁ ለመፍታትና ሐይቁንም ከአደጋ ለማዳን የተሞከረ አንድም ፍሬያማ ተግባር አይስተዋልም፡፡ ለችግሩ መንስዔ የሆኑና በቀጥታ የሚመለከታቸው ተቋማትና ድርጅቶች የተጠኑ ጥናቶችን መሠረት አድርገው አፋጣኝ ዕርምጃ ከመውሰድ ይልቅ ጥፋቱን ላለመቀበል እየተገፋፉ ይገኛሉ፤ ሐይቁም ሞቱን ለመቀበል ያጣጥራል፡፡ እነዚህ ድርጅቶች በሚያስጠኗቸው ጥናቶችም ለጥፋቱ ድርሻቸውን ለማሳነስና ሌላውን ኩነኔ ለማስገባት ከመሮጥ ይልቅ በተናጠል ያጠፉትን ሀብት በጋራ መክረው ማዳን እንደሚችሉ የተረዱ አይመስልም፡፡

ታደሰ ፈታሂ ካቀረቡት ‹‹ግሪኒንግ ኤ ሮፒካል አቢጃታ፣ ሻላ ሌክስ ናሽናል ፓርክ ኢትዮጵያ - ኤ ሪቪው›› በሚለው ጥናታቸው እንዳቀረቡት፣ ለአቢጃታ ሐይቅ ውኃ መቀነስ በምክንያትነት ከሚጠቀሱት ጉዳዮች አንዱ የቡልቡላ ወንዝ ሙሉ በሙሉ ወደ ሐይቁ መግባት በማቆሙ እንደሆነ ይታመናል፡፡ ይህ ከብዙዎቹ አንዱ ሲሆን ሌሎች ተደራራቢ ችግሮችም አልታጡም፡፡ ዝዋይ ሐይቅ በስተምሥራቅ ከመቂ ወንዝ፣ በስተምዕራብ ደግሞ ከከታር ወንዝ ግብሩን ይሰበስባል፤ ከዚያም የቡልቡላን ወንዝ በመጠቀም በተራው ለአቢጃታ ሐይቅ ግብር ያገባ ነበር፡፡ የላንጋኖ ሐይቅም ከሚያገኛቸው ገባር ወንዞችና ጅረቶች የፈቀደውን የውኃ መጠን በሆራ ቀሎ ወንዝ አማካይነት ለአቢጃታ ይለግስ ነበር፡፡ አሁን ይኼ ሁሉ ነበር ሆኗል፡፡ ትልቁ ችግር ያለው ሐይቁ በተፈጥሮው በወንዞች ልግስና ብቻ ህልውናው የቆመ ነገር እንደሆነ ተደርጎ የሚነገረው ጉዳይ፣ ጥፋተኛ አይደለንም ብሎ ለመሸሽ እንደ አማራጭ መወሰዱ ላይ ነው፡፡ የሐይቅ ተፈጥሮ ምንም ይሁን አግባብ ባለው መንገድ የያዘውን ሀብትና ውኃውን ተጠቅመንበት ቢሆን ኖሮ ይህ ችግር ባልተከሰተ ነበር፡፡   

ቡልቡላ ወንዝን ከመነሻው ተቀብሎ በደጁ ዙሪያ ያልለመደውና ከፍተኛውን ድርሻ እየተጠቀመ ያለው ‹‹ሸር ኢትዮጵያ›› (‘ሸር’ በእንግሊዝኛ መሆኑን ልብ ይበሉልኝ) ሲሆን፣ ከሱ የተረፈውንም ሌሎች ተቀብለው እየተጠቀሙት ይገኛሉ፡፡ ካለፈው ዓመት በፊት ወደ ሐይቅ ይገባ የነበረውም የወንዙ ተፋሰስ በሚለቀቀው ኬሚካል የተበላሸ ነበር፡፡ አሁን ከነጭራሹ ያም ቀርቷል፡፡ በአሁኑ ወቅት የእነዚህ ወንዞች ግብር የራቀው ይህ ሐይቅ ላለፉት ሃያ ሰባት ዓመታት ገደማ ለሶዳ አሽ ፋብሪካ ያለስስት ሀብቱን እየሰጠ ነው፡፡ በተለያየ መጠን በዙሪያው ለተቋቋሙ እርሻዎች መስኖ ያለማል፣ ለአካባቢው የቤት እንስሳትም ትሩፋቱን ቀጥሏል፣ አሁንም እንጥፍጣፊውን ልሰን ካልጨረስን ያሉት ከጎኑ አሉ፡፡ ቀደም ሲል ሐይቅ በዓሳ ምርቱ የሚታወቅ የነበረ ሲሆን፣ የዓሳ ዘር የሚባል የጠፋውና ምርቱም የተቋረጠው ከሶዳ አሽ ፋብሪካ መቋቋም ስምንት ዓመት በኋላ ነበር፡፡

ታደሰ ፈታሂ በጥናታቸው ያቀረቡት የሳተላይት ምስል እንደሚያስረዳው፣  አቢጃታ በ1966 ዓ.ም. ገደማ ከነበረው የውኃ ይዞታ ስፋት በ2000 ዓ.ም. ከአንድ መቶ ስኩዌር ኪሎ ሜትር በላይ የሚሆነውን ይዞታ አጥቷል፡፡ ከ1980 ዓ.ም. እስከ 2000 ዓ.ም. ባለው ጊዜ ውስጥ ብቻ የተከሰተው መቀነስ ሲሰላ ደግሞ ስድሳ ሰባት ስኩዌር ኪሎ ሜትር ያህል ቅነሳ አሳይቷል፡፡ በአሁኑ ወቅት የቀረው የውኃ ይዞታ ከፍተኛ ጨዋማነት ያለው በመሆኑና ቀደም ሲል የነበረው ከፍተኛ የአልጌ ሽፋን ጨርሶ በመጥፋቱ ምክንያት ሐይቁ ሕይወት አልባ እየሆነ መጥቷል፡፡ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ትንሹና ትልቁ ቆልማሚት /Greater and lesser Flamingos/ ማረፊያና መመገቢያ የነበረው ይህ ሐይቅ፣ አሁን እንደ ስባሪ የፊት መስታወት የሚመለከትበትና የሚመለከተው አጥቶ ሰማይ ሰማይ ያያል፡፡  

የአቢጃታ ሐይቅ ገባር የነበሩት ሆራ ቀሎና ቡልቡላ ወንዞች መድረቅ (በትላልቅ የመስኖ እርሻ መጠለፍ ምክንያት) የአቢጃታ ሐይቅን ህልውና ብቻ ሳይሆን ከመነሻቸው እስከ መዳረሻቸው ባለው የወንዙ አካባቢ የሚኖሩትን ማኅበረሰብ ህልውናም ተጋፍቷል፡፡ እኔ የምለው እዚህ አገር ወንዞቻችንን፣ ጅረቶቻችንንና ምንጮቻችንን እንደዚህ በነፍስ ወከፍ እንከፋፈል ካልን ምን ሊደርሰን እንደሚችል አስባችሁታል? እባካችሁ ይህን የንብረት ክፍፍል ነገር እንተወው፡፡ ፍትሐዊ የሆነ የሀብት አጠቃቀም ሲኖር ዘላቂ የሆነ የአረንጓዴ ልማት ግቡን ይመታል፡፡ በአንድም በሌላም መንገድ ሁላችንም የቆምነው ለዚህ እንደሆነ አምናለሁ፡፡   

የሆራ ቀሎና ቡልቡላ ተፋሰስ አካባቢ ኗሪዎች በወንዞቹ መድረቅ ምክንያት እየደረሰባቸው ከሚገኙት ችግሮች መካከል፣ አንድ፡- በቁጥቁጥ ይጠቀሙት የነበረው የወንዝ ውኃ በመድረቁ ወደ ሰማይ አንጋጠው ለእርሻቸው ወቅትን መጠበቅ ይዘዋል፡፡ ሁለት፡- ከብቶቻቸውን በአቅራቢያቸው ማጠጣት ባለመቻላቸው ርቀው በመጓዝ ለከፍተኛ እንግልት ተዳርገዋል፤ እንዲያውም አብዛኞቹ ወደ ሐይቆቹ በመሰማራት ሌላ ያልተገባ ጥፋት ማጥፋቱን ቀጥለዋል፡፡ ሦስት፡- የአቢጃታ ሐይቅ የውኃ ይዞታ የነበረው ቦታ ሙሉ በሙሉ በመራቆቱ ምክንያት ከፍተኛ አቧራ አካባቢውን በየጊዜው ስለሚሸፍነው ለጤና ችግር ተዳርገዋል፡፡ እነዚህ ችግሮች በአጭር ጊዜ እየተስተዋሉ ያሉ የአካባቢው መራቆት ያስከተላቸው ሲሆኑ፣ ይህ ሁኔታ በዚህ መልኩ ከቀጠለና የአቢጃታን ሐይቅ ማዳን ካልተቻለ ሁለንተናዊ ከሆነ የአየር ንብረት መለወጥ ሳንካ ባሻግር በአካባቢው ኗሪዎች ላይ ሊደርስ የሚችለው ችግር እጅግ ከፍተኛና አጠቃላይ ህልውናቸውን የሚጋፋ ሊሆን እንደሚችል አያጠያይቅም፡፡

ኢትዮጵያ በያዘችው የሽግግር ዕቅድ የአረንጓዴ ልማት ዓቢይ ጉዳይ ሲሆን፣ በዕቅዱ መሳካትም ከካርበን ልቀት የፀዳች መካከለኛ ገቢ ያላት አገር ለመሆን የታለመው ግብ ይሳከ ዘንድ ዛፍ መትከል ብቻውን በቂ አለመሆኑ ልብ ሊባል ይገባል፡፡ ፓርኮችም ከያዟቸው ብዝኃ ሕይወት ሀብት አንፃር ለዕቅዱ መሳካት ከፍተኛውን ድርሻ ይወስዳሉ፡፡ ከኢኮኖሚ ፋይዳው አንፃር እንኳ ብንመለከተው የአቢጃታ ሻላ ሐይቆች ብሔራዊ ፓርክ ተፈጥሯዊ ይዘቱን ጠብቆ በዓመት የሚያስገኘው ገቢ ሲሰላ ከ15.9 እስከ 308.5 ሚሊዮን ዶላር የሚገመት ነው፡፡ ዘላቂ የሚለው ቃል ከቃል የዘለለ ትርጉም ካልሰጠነው ልማታችንም ይህንን አቅጣጫ ካልተከተለ የምናጣው የተፈጥሮ ሀብታችንን ብቻ ሳይሆን አጠቃላይ ህልውናችንንም ጭምር ነው፡፡ እናም ስለ አቢጃታ፣ በሞቱ እጃችሁን የሰደዳችሁ ሁሉ ክርክሩን አሊያም ዝምታውን ትታችሁ ጊዜ ሳትሰጡ ለአንድ ዓይነት እልባት ዛሬውኑ ተነሱ፡፡ 

ከአዘጋጁ፡- ጽሑፉ የጸሐፊውን አመለካከት ብቻ የሚያንፀባርቅ ሲሆን፣ ጸሐፊውን በኢሜይል አድራሻቸው solwors@gmail.comማግኘት ይቻላል፡፡

 

 

 

          

       

 

Standard (Image)

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የፀረ ሙስና ኮሚሽንን ሊታደጉ ይገባል

$
0
0

 

በገደሙ ሁሉቃ

ሙስና ለአገር ኢኮኖሚ ዕድገት እንቅፋት ነው፡፡ ሙስና ጥቂቶች ተንደላቀው የሚኖሩበት ሲሆን፣ ብዙኃኑ ሕዝብ በድህነት እየማቀቀ እንዲኖር የሚያደርግ ነቀርሳ ነው፡፡ በአገራችን ሙስና የሚለው ቃል በግልጽ እየታወቀ የመጣው ከ1993 ዓ.ም. ወዲህ ቢሆንም ድርጊቱ ግን ለዘመናት የኖረ ነው፡፡ ነገር ግን ሙስና የሚለው ቃል በጣም የሚመች ባለመሆኑ ተቀባብቶና ተንቆለጳጵሶ ‹‹ኪራይ ሰብሳቢነት›› የሚል ስያሜ ያገኘው ደግሞ በእኛው አገር ከአቶ መለስ ዜናዊ ሞት በኋላ ነው፡፡ በእርግጥ ቤት፣ መሬትና ዕቃ የሚያከራይ ሰው ኪራይ ሰብሳቢ ነው፡፡ አንድ ጊዜ ጀግናው አትሌት ኃይሌ ገብረ ሥላሴ ‹እኔ ቤት ስለማከራይ እኔም ኪራይ ሰብሳቢ እባላለሁ ወይ?› ያለውን አስታውሳለሁ፡፡ ቢሮ ውስጥ አንዳንድ ወጣት ሠራተኞችም ቤተሰቦቻቸው ቤት ስለሚያከራዩ ቃሉን እንፈራለን ሲሉ ሰምቻለሁ፡፡ ኪራይ ሰብሳቢነት በአሁኑ ወቅት በአገራችን እንደ ግዑዝ አካል ተደርጎ እየተወሰደ ያለ ትልቅ ቃል ነው፡፡ ግን ሙስና የሚለውን ቃል ላለመጥራት የታለመ መሆኑን ማንም የተረዳው አይመስለኝም፡፡

በመሠረቱ የኪራይ ሰብሳቢነት ትርጉም እሴት ሳይጨምር ተጨማሪ ገቢ ማግኘት ወይም መፈለግ ሲሆን፣ የሙስና ትርጉም ደግሞ የመንግሥትን ሀብት ለራስ ጥቅም ማዋል ወይም ሌላ ሰው እንዲጠቀም ማድረግ ነው (የዓለም ባንክ ትርጉም ነው)፡፡ እሴት ሳይጨምር ጥቅም ማግኘት ወይም መፈለግ ማለት አንድ ሰው ወጪ ሳያወጣ ወይም ምንም ነገር ሳይጨምርበት ተጨማሪ ገቢ ማግኘት ወይም መፈለግና ሙስና ለእኔ በጣም የተለያዩ ናቸው፡፡ በተለይም በፍላጎትና አቅርቦት መካከል ልዩነት ሲፈጠር አንዳንድ ጊዜ ተጨማሪ እሴት ሳይጨመር ተጨማሪ ገቢ ሊገኝ የሚችልበት አጋጣሚ ብዙ ስለሚሆን ሙሉ ለሙሉ ሙስና ነው ለማለት ያስቸግራል፡፡ አጋጣሚውን መጠቀም የሚለውን ትርጉም ስለሚሰጥ፡፡ ሌለው ተቀጽላ በመጨመር የኪራይ ሰብሳቢነት አስተሳሰብ ወይም አመለካከት የሚባል ነገር አለ፡፡ ከላይ ከትርጉሙ አንፃር ሲታይ አንድ ሰው እሴት ሳይጨምር ተጨማሪ ገቢ ማግኘት ሲፈልግ፣ ይህ ሰው የኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከት ያራምዳል ይባላል፡፡ አስተሳሰብ ወይም አመለካከት መያዝ ለእኔ ችግር አይመስለኝም፡፡ አስተሳሰብ መያዝ ሕገ መንግሥታዊ መብትም ነው፡፡ ሙስና ግን የተለየ ነው፡፡ ሙስና ጉቦ፣ ማጭበርበር፣ ማዳላት፣ መስረቅ የመሳሰሉት ትርጉም ያለው ስለሆነ፣ በተለይም በመንግሥት ተቋማት ውስጥ ለሚሰጠው አገልግሎት የተሰጠውን ኃላፊነት በመጠቀም ከተገልጋይ ጉቦ መቀበል፣ የመንግሥት ሠነድ በማጭበርበር ገቢ ማግኘት፣ ሥልጣኑን ተጠቅሞ ዘመዶችን መጥቀምና የመንግሥት ንብረት መስረቅ ሙስና ነው፡፡ እዚህ ላይ ሥራን አርፍዶ የሚመጣ ኃላፊና ሠራተኛም ሙስና ሠርቷል ማለት ይቻላል፡፡ ኪራይ ሰብሳቢነት የሚለው ቃል ሙስና ለመሥራት ያሰበ ወይም የሠራ ሰው የዘየዱት ቃል ይመስለኛል፡፡ በአገራችን ሁለቱንም ቃላት በዝርዝር ለማስቀመጥ ሊሞክር እንጂ የጽሑፉ መነሻ ሌላ ነው፡፡ 

በአቶ መለስ ዜናዊ ሕይወት ዙሪያ በቅርቡ አንድ መጽሐፍ ገበያ ላይ ውሏል፡፡ በመጽሐፉ ውስጥ ከተጠቀሱት ርዕሶች ስለገንዘብ ስላላቸው አመለካከት ሳነብ የአሁኑን ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር አስታወስኩኝ፡፡ አቶ መለስ ዜናዊን የመሰለ ሰው ከእንግዲህ በኢትዮጵያ ይፈጠራል ቢዬ አላስብም፡፡ ምናልባት በአንድ ትውልድ አንድ ሰው ከተገኘም በጣም ጥሩ ነው የሚል አስተሳሰብ አለኝ፡፡ አቶ መለስ ስለገንዘብ ምንም ዓይነት ዕውቀት የላቸውም፡፡ ገንዘብ በኪሳቸው አይዙም፡፡ ደመወዛቸውን ሰው ይቀበልላቸዋል፡፡ ውጭ ሲሄዱ ወደ መዝናኛ አይሄዱም፣ ገበያ ሄደው ዕቃ አይገዙም፡፡ የተሰጣቸውን ሽልማት ለዕርዳታ ሰጥተዋል፡፡ ከዚህ አንፃር ለሙስና ትግል ባላቸው አመለካከት በጣም ጽኑ አቋም ያላቸው ንፁህ ኢትዮጵያዊ ናቸው በሚል ድምዳሜ ላይ ደረስኩኝ፡፡ ሙስናን ይፀየፋሉ፡፡ ለሕዝባቸው በጣም ያስባሉ፣ ይጨነቃሉ፡፡ ለሕዝባቸው ዝናብ እንዲዘንብ ሁሌም ይመኛሉ፡፡ ሕዝባቸው በልቶ እንዲያድር ይመኛሉ፡፡ ለራሳቸው ግን አልኖሩም፡፡ ፈጠሪ ነፍሳቸውን በገነት ያኑረው፡፡ በምድር ባይደላቸውም ፈጠሪ ያስብላቸዋል፡፡ ሙስና  ስለሚያስከትለው ጉዳት በተለየ ገንቢ አስተያየት ይሰጣሉ፡፡ ‹መንግሥት በአንድ እጅ ነው ሙስናን የሚታገለው› ይላሉ፡፡ የፀረ ሙስና ትግሉ ተጠናክሮ እንዲሄድ በቂ አመራር ይሰጣሉ፡፡ ለዚህም የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን እንዲቋቋም አድርገዋል፡፡ የፀረ ሙስና ኮሚሽኑ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ፍላጎት ስላላቸው፣ ለምክር ቤት ሪፖርት ሲያቀርቡ አንድም ቀን ስለሙስና ጎጂነት ሳይናገሩ አላለፉም፡፡ መቼም መቼም ቢሆን እንዲህ ለአገሩ ዕድገት ከልቡ የሚሠራ ሰው በፍፁም አናገኝም ያልኩት ለዚህ ነው፡፡

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ አቶ መለስን ተክተው ወደ ኃላፊነት ሲመጡ የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን የሥራ ኃላፊዎችን፣ የተወሰኑ ባለሀብቶችና ደላሎችን በሙስና ወንጀል እንዲከሰሱ ሲያደርጉ ብራቮ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን ብለን ነበር፡፡ በአንድ ወቅት ለፓርላማ ሪፖርት ሲያቀርቡ ፀረ ሙስናን በተመለከተ ራሳቸው ትኩረት አድርገው እንደሚከታተሉ ለሕዝብ ቃል ገብተው ነበር፡፡ ከዚህ ውጪ ባህር ዳርና መቐለ በተካሄደው የኢሕአዴግ ጉባዔዎች ላይ ስለሙስና ጎጂነት ትኩረት ሰጥተው አምርረው ይናገሩ ነበር፡፡ የፖሊሲ ጥናትና ምርምር ማዕከል ባካሄደው የጥናት ሪፖርት ይፋ ሲያደርግም፣ እንዲሁ በተወሰነ ደረጃ ስለሙስና አምርረው ሲናገሩ ነበር፡፡ በ2008 በጀት ዓመት መጀመሪያ ላይ ስለሙስና ሌላ ሐሳብ ይዘው ብቅ አሉ፡፡ ሙስናን ለማጥፋት በቅድሚያ የሥነ ምግባር ትምህርት በማስተማር የአመለካከት ለውጥ ማምጣት ያስፈልጋል አሉ፡፡ እንዲሁም የተቋማት አሠራሮች ለሙስና ተጋላጭ እንዳይሆኑ የሙስና መከላከል ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል አሉ፡፡  በ2009 በጀት ዓመት ግን ስለሙስና ጎጂነና በሙስና ላይ ስለሚወሰድ ዕርምጃ ላይ የተናገሩት ደግሞ የተለየ ነው፡፡ ‹ሙስና እንደተሠራ ይወራል፡፡ ነገር ግን ማስረጃ ማግኘት አይቻልም፡፡ የሙስና ችግር በትልቁ ይወራና ማስረጃ ሲባል አይጥ የምታህል ነች› አሉ፡፡ ቀጥሎም የመንግሥት ኃላፊዎች ሀብታቸውን እንደሚያስመዘግቡና የተመዘገበው ሀብት ለሕዝብ ይፋ ሲሆን፣ ሕዝቡ የተመዘገበውን እያየ በልዩነት ሪፖርት ሲያቀርብ ዕርምጃ ይወሰዳል ብለው ቃል ገቡ፡፡ ሲተገበር ግን አላየንም፡፡ ሙስና ላይ ምርመራ ለማካሄድ እንደ አሜሪካ ዓይነት ኤፍቢአይ (FBI) አቋቁመናል አሉ፡፡ ግን ነው ወይ? አይደለም፡፡ በ2009 በጀት መጨረሻ ሪፖርት ላይ ስለሙስና በዩኒቨርሲቲዎች የሚከናወኑ የሙስና ወንጀሎች በኤፍቢአይ (FBI) እንዲመራመሩ ይደረጋል አሉ፡፡ ምን ያህል ውጤታማ እንደሚሆኑ ወደፊት የምናየው ይሆናል፡፡ ነገር ግን በ2009 መጀመሪያ አካባቢ ሙስና በአገሪቱ በከፍተኛ ሁኔታ እያደገ መምጣቱን አንድ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ምሁር አስረግጠው ሲናገሩ ሰምተው ይሆን ወይ ብዬ አስባለሁ፡፡

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር የቀድሞውን ጠቅላይ ሚኒስትር ራዕይ ለማሳካት ተግተው እንደሚሠሩ ቃል ገብተው ነበር፡፡ የሕዝብ ነቀርሳ የሆነውን ሙስናን በፅኑ መታገል የአቶ መለስ ዜናዊ ራዕይ ነበር፡፡ እሳቸው ሙስናን በጽኑ ለመታገል ያዋቀሩት የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽንን ነው፡፡ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም  ግን ከሥነ ምግባርና ከፀረ ሙስና ሥራዎች ውስጥ የሙስና ወንጀል ጥቆማ የመቀበል፣ የመመርመር፣ የመክሰስ፣ የማስቀጣትና የተመዘበረ ሀብት የማስመለስ ሥራዎችን ለፌዴራል ፖሊስና ለጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ እንዲሰጥ አደረጉ፡፡ ምክንያቱ ግን ለሕዝብ ግልጽ  አይደለም፡፡ ለፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ የተሰጠውን የዓቃቤ ሕግ ሥራ የዚህ ጽሑፍ አቅራቢም መስጠቱ ትክክል ነው ብሎ ያምናል፡፡ የፌዴራል ፖሊስ በአገሪቱ ሰፊ አደረጃጀት ያለውና ከሕዝቡ ጋር ዕለት ተዕለት ቀጥታ ግንኙነት ያለው ተቋም ስለሆነ የሙስና ተጋላጭነቱ በጣም ከፍተኛ ነው፡፡ በትራንስፓራንሲ ኢንተርናሽናል የባሮሜትር ጥናትና የፌዴራል የሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን የሚያደርጋቸው ጥናቶች ፖሊስ ለሙስና ተጋላጭነቱ ከፍተኛ መሆኑን በግልጽ ያሳያል፡፡ በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በዓለም የፖሊስ አደረጃጀት በከፍተኛ ሁኔታ ለሙስና ተጋላጭ መሆኑን መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ግን ባልታወቀ ምክንያት ደፍረው የሙስና ወንጀል ምርመራ ሥራን ለፌዴራል ፖሊስ ሰጡ፡፡ የፌዴራል ሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ይህ ሥራ ሲያከናውን ከሕዝቡ የሚቀርበው የሙስና ወንጀል ጥቆማ እስከ 5,000 ድረስ ነበር፡፡ የፌደራል ፖሊስ ግን ይህን አላደረገም፡፡ ከውስጥ አዋቂ ምንጭ እንደተነገረኝ ከሆነ ከ1,000 ያልበለጠ የሙስና ወንጀል ጥቆማ መቀበሉን ሰምቻለሁ፡፡ ኮሚሽኑ በዓመት በሙስና ከተመዘበረ ሀብት እስከ ከሃምሳ ሚሊዮን ብር በላይ ያስመልስ እንደነበር መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ ፌዴራል ፖሊስ ግን ይህ ያህል ገንዘብ ማስመለሱን በሪፖርቱ ላይ አልገለጸም፡፡

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ከነበረበትና ለ15 ዓመታት ሲጠቀምበት ከነበረበት ሕንፃ እንዲወጣ አድርገዋል፡፡ ኮሚሽኑም የሙስና ወንጀል ምርመራ ሥራ ሲወስድበት የማስተማርና የመከላከል ሥራ ለማከናወን ከፍተኛ ዝግጅት በማድረግና ስትራቴጂና ሥልት በመቀየስ ወደ ሥራ በመግባት ላይ መሆኑን፣ የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ለማየት ችያለሁ፡፡ ኮሚሽኑ በዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ መነሻነት በፀረ ሙስና ትግል ላይ የኅብረተሰቡን ተሳትፎና ሚና የበለጠ ለማሳደግና ንቅናቄ ለመፍጠር እንዲያስችለው፣ ይህን የሚያስፈጽም የሰው ኃይል በማደራጀት የተለያዩ ተግባራት በማከናወን ላይ እንደሚገኝ አውቃለሁ፡፡ ከ900 በላይ የሙያ ማኅበራትን በማደራጀት እንቅስቃሴ ያደርጋል፡፡ የእነዚህ ማኅበራት ሥራ አስፈጻሚዎች በየሦስት ወራት የአፈጻጸም ግምገማ የሚያካሄዱት እዚሁ ኮሚሽኑ ሕንፃ ውስጥ ነው፡፡ ኮሚሽኑ ከሙያ ማኅበራትና ከመንግሥት ተቋማት ለተውጣጡ አካላት የሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ትምህርትና ሥልጠናዎችን የሚሰጠው በሕንፃው ውስጥ ነው፡፡ ለሠልጣኝ የምሳ መስተንግዶ የሚያደርገው በአነስተኛ ዋጋ በሠራተኞች መዝናኛ ክበብ ነው፡፡ ሕንፃውን ሲለቅ ግን እነዚህ ሥራዎች በኪራይ በሚያገኛቸው ሕንፃዎች ውስጥ የሚያከናውን ከሆነ ግን መንግሥት ለከፍተኛ ወጪ የሚዳርግ ይሆናል፡፡

ሌላው የሠራተኞች ቢሮ እጥረት ነው፡፡ ኮሚሽኑ ከ300 በላይ ሠራተኞች ያሉት ሲሆን፣ የቤቶች ኮርፖሬሽን ግን ቢበዛ 140 ሠራተኞች የሚይዝ ስለሆነ ኮሚሽኑ ለ160 ሠራተኞች ሌላ ቢሮ መከራየት ይጠበቅበታል፡፡ ሠራተኞችን በሁለት በተለያዩ ቦታዎች ማስተዳደር ከመርህ አኳያ አይመከርም፡፡ ይህ እንግዲህ ኮሚሽኑ የሙስና ወንጀል ምራመራ ከተወሰደበት በኋላ የመጣ ዕዳ ስለሆነ አሁን ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ኮሚሽኑን ሊታደጉት ይገባል፡፡ አባት የሌለው ተቋም እንዳይሆንና የአቶ መለስ ዜናዊን ራዕይ ለማሳካት ከልብ ከተነሱ የኮሚሽኑን ችግር ጆሮ ሰጥተው ማዳመጥ አለባቸው፡፡ ችግሩን መረዳትና ማቃለል ይኖርባቸዋል፡፡ የሕዝብ ተቋም ስለሆነ ማጠናከር አለባቸው፡፡

በአገሪቱ ባሉት ዘጠኙም ክልል መስተዳደሮች የሥነ ምግባርና  የፀረ ሙስና ኮሚሽኖች እሉ፡፡ የእነዚህ የክልል ሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽኖች አደረጃጀት የሙስና ወንጀል ምርመራና ዓቃቤ ሕግ ይዘው የተደራጁ ሲሆን፣ የፌዴራል የሙስና ወንጀል ሲቀነስበት የክልል የሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽኖች የያዙትን አደረጃጀት እንዳሉ ይዘው ነው ያሉት፡፡ ከአገራዊ የሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ትግል ውጤታማነት አኳያ ሲታይና የክልሎች የሙስና ወንጀል ምርመራ ሥራ ውጤት ብቻ ሲገመገም፣ ኮሚሽኑ የፌዴራል ፖሊስና የጠቅላይ ዓቃቤ ሕግን በመጠየቅና በማሳመን ሪፖርት ሊያቀርብ ይችላል፡፡ ዛሬ ያለው የመረጃ አያያዝ ችግር እንደተጠበቀ ሆኖ፡፡ ይህም የአገሪቱን የፀረ ሙስና ትግል ስትራቴጂና ሥልት የተለያየና ጉራማይሌ እንዲሆን አድርጎታል፡፡ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም አገሪቱ ወጥ የሆነ የፀረ ሙስና ትግል እንዲኖር ትኩረት መስጠት ይጠበቅባቸዋል፡፡

መነሻዬ ላይ ወዳነሳሁት ሐሳብ ልመለስና ኅብረተሰቡ ዘንድ ሙስናና ኪራይ ሰብሳቢነት አንድ ዓይነት እየሆነ እየተወሰደ ነው፡፡ የመንግሥት ኃላፊዎችና ሚዲያዎች ኪራይ ሰብሳቢነት የነገሠበት የሚሉ አባባሎችን በተደጋጋሚ ስለሚያስተጋቡ፣ ኅብረተሰቡም ሙስና የሚለውን ኪራይ ሰብሳቢነት በሚል በመተካት እየተረዳ ነው፡፡ ኪራይ ሰብሳቢነት ብቻውን ችግር አይደለም፡፡ የኪራይ ሰብሳቢነት አስተሳሰብ የያዘ ሰው አስተሳሰቡን ወደ ተግባር ሲለውጥ ግን ችግር ይሆናል፡፡ ከዚህ አንፃር ሕዝቡ ኪራይ ሰብሳቢነትንና ሙስናን ለይቶ ማወቅ ይኖርበታል፡፡ ሁሉም ሰው የተለያየ የኪራይ ሰብሳቢነት አስተሳሰብ ሊኖረው ይችላል፡፡ የተፈጥሮ ሕግ ስለሆነ ተጨማሪ እሴት ሳይጨምር ጥቅም የማይፈልግ የሰው ልጅ አይኖርም፡፡ መጠኑ ይለያይ እንጂ ሁሉም ሰው የኪራይ ሰብሳቢነት አስተሳሰብ ያራምዳል፡፡ ሙስና ግን ከዚህ የተለየ ነው፡፡ ሙስና በጥሬ ቃሉ ሌብነት ነው፡፡ ሙስና በአንድ ጉዳይ ላይ የመወሰን ኃላፊነት የተሰጠው ሰው ድርጊት ነው፡፡ የመንግሥት አገልግሎት በተለይም የአገልግሎቱ ፈላጊዎች ሲበዙበት፣ ወይም አገልግሎት ፈላጊው የሚጠበቅበትን ግዴታ ለማሟላት ሳይችል ሲቀር ክፍተቱን ለመሙላት ሲል፣ ወይም በተሰጠው ኃላፊነትን ተጠቅሞ በሚሰጠው አገልግሎት ላይ ተገልጋዮች ያለበትን ክፍተት በመጠቀም ሙስና ይሠራል፡፡ ከዚህ ውጪ ደግሞ በመንግሥት ንብረትና ሰነድ ላይ ያለውን ቅርበት በመጠቀም ሙስና ይፈጽማል፡፡ ስለሆነም በኪራይ ሰብሳቢነትና በሙስና መካከል ያለው ብዥታ ለኅብረተሰቡ ግልጽ ሊሆን ይገባል፡፡ ካልሆነም በኪራይ ሰብሳቢነት ጥላ ሥር ሆኖ ሙስና የሚለውን ስም ማጥፋት አይገባም፡፡ በጥቅሉ ሙስና ሌብነት ነው፡፡ መሸፋፈን አያስፈልግም፡፡

ስለዚህ መንግሥታዊ የአምስት ዓመቱ የዕድገትና ትራንስፎሜሽን ዕቅድ ላይ መልካም አስተዳደር ለማስፈን ኪራይ ሰብሳቢነትን መታገል የሞት ሽረት ጉዳይ የተባለው ሙስና ላይ ብዥታን ስለፈጠረ፣ ሙስናን መታገል በሚል ማስተካከል ያስፈልጋል፡፡ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም በኃላፊነት ዘመናቸው የአቶ መለስ ዜናዊን ራዕይ ዕውን ለማድረግ የገቡትን ቃል የሚያከብሩ ከሆነ፣ ሙስናን በፅኑ መታገል ይጠበቅባቸዋል፡፡ ሙስና በአገሪቱ ኢኮኖሚ፣ ልማት፣ ዕድገትና በሕዝቡ ኑሮ ላይ የሚያሳድረውን ተፅዕኖ በተለይ ሙስናን ፈጽመው ገቢ ያላቸው ሰዎች ገበያ ላይ የመግዛት አቅማቸው ከፍተኛ ስለሚሆን፣ ደሃው ሕዝብ ከእነሱ ጋር ተወዳደሮ ገበያ ውስጥ ግዥ መፈጸም ስለማይችል፣ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ይህንን ተረድተው በሕዝቡ ጎን ሊቆሙ ያስፈልጋል፡፡ ለዚህም የፌዴራል የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን በተሟላ የአመራር ብቃትና ክህሎት እንዲመራ ማድረግና ኮሚሽኑ አሁን እደረሰበት ካለው እንግልት ማላቀቅ ይኖርባቸዋል፡፡ ካልሆነ ግን የፌዴራል ሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ላለፉት 14 ዓመታት በተለይም አቶ መለስ በነበሩበት ዘመን ለሠራው ሥራ አሁን እየተቀጣ ነው ወደሚለው ድምዳሜ ይወስዳል፡፡

የኮሚሽኑ ሠራተኞች የታዘዙትን በማከናወናቸው ሞራላቸው ሊነካ አይገባም፡፡ የጠቅላይ ሚኒስትር መንግሥት ተቋሙን የማይፈልግ ከሆነ ደግሞ ለሕዝብ በግልጽ ይፋ በማድረግ መዝጋት አለበት፡፡ መንግሥት ይኼንን ያደርጋል የሚል እምነት ግን የለኝም፡፡ ለዚህ ያበቀኝ ግን አሁን እየተፈጸመ ያለው አዝማሚያ ለመዝጋት ነው እንዴ የሚያስብል ስለሆነ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ የፀረ ሙስና ትግል ውጤትን በሚገባ ይረዳል፡፡ የተማረ ሕዝብ አለን፡፡ የሚጎዳውንና የሚጠቅመውን ጠንቅቆ ያውቃል፡፡ በእርግጥ ኮሚሽኑ ራሱ የውስጥ ችግር ላይ እንደነበር እናስታውሳለን፡፡ ይህ ደግሞ ማረም የሚቻል የውስጥ ችግር ነው፡፡ ተቋሙ የሕዝብ ስለሆነ መፍረስ ግን የለበትም፡፡ ኮሚሽኑ በሕዝቡ ዘንድ መልካም ስም (Goodwill) አለው፡፡ በሕዝብ አዕምሮ ውስጥ ከነሕንፃው ገብቷል፡፡ ምንም ባይሠራ እንኳን ቢያንስ ሙስና የሚፈጽሙትን ሰዎች ለፀረ ሙስና እናገራለሁ እየተባለ እንኳን ለማስፈራራት ይጠቅማል፡፡ ፖሊስ ለዘመናት ከሕዝብ ጋር አብሮ የኖረ ስለሆነ ሕዝብና ፖሊስ በጣም ይተዋወቃሉ፡፡ ፖሊስ በአደረጃጀቱ ብዙ ስለሆነ ሙስና ውስጥ የመግባት ነገር የተለመደና የኖረ ነው፡፡ የተሃድሶና የኪራይ ሰብሳቢነት መፈክር በፖሊስ ቤት የተፈለገውን ያህል ውጤት ሊያመጣ አይችልም፡፡ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ለወደፊት ታሪካቸው ተጨማሪ ግብዓት እንኳን ሲሉ ኮሚሽኑ ቢያጠናክሩና ቢታደጉ ይሻላል የሚል አስተያየት አለኝ፡፡ ሕንፃውን ለኮሚሽኑ ይተውለት እላለሁ፡፡ የቤቶች ኮርፖሬሽንም  የመገንባት ‹ማንዴት› ስላለው የራሱን ሕንፃ መገንባት ይኖርበታል፡፡ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ውሳኔዎ በጉጉት ይጠበቃል፡፡

ከአዘጋጁ፡- ጽሑፉ የጸሐፊውን አመለካከት ብቻ የሚያንፀባርቅ ሲሆን፣ ጸሐፊውን በኢሜይል አድራሻቸው geberealemu@yahoo.comማግኘት ይቻላል፡፡

 

 

Standard (Image)

የአንድ የዑመር ኻያም ግጥም ሁለት ቁንጮ የአማርኛ ገጣሚዎች ምናብ

$
0
0

በሽብሩ ተድላ

ሁለት የታወቁ የአማርኛ የግጥም ደራስያን (ተስፋዬ ገሠሠና በዕውቀቱ ሥዩም) ለአንድ የዑመር ኻያም ግጥም በየፊናቸው የሰጡትን ትርጉም (ትርጉም ማለቱ አከራካሪ፣ አወዛጋቢ ቢሆንም) ወይም ዕይታቸውን ላካፍላችሁ፡፡

ተስፋዬ ገሠሠ ‹‹መልክአ ዑመር›› ብሎ በሰየማት በ1987 ዓ.ም. የታተመች ውብ የአማርኛ ግጥም መድበል ‹‹የቅኔው መጽሐፍ ሳይቀር ይያዝና›› በሚል ርዕስ ያቀረባት የዑመር ኻያም ግጥም ናት የዚህ ጽሑፍ መንስኤ የሆነች፡፡ ይህችኑ ግጥም በዕውቀቱ ሥዩም ‹‹የማለዳ ድባብ›› ብሎ በሰየማት በ2009 ዓ.ም. በታተመች የአማርኛ ግጥም መድበል ውስጥ ‹‹የምድረ በዳ በረከት›› በሚል ርዕስ አበርክቶልናል፡፡ የእኔ አስተያየት (ጽሑፍ) ያጠነጠነው በሁለቱ አንጋፋ ደራስያን፣ በአንድ ግጥም ዕይታ (ትርጉም) ላይ ነው፡፡

ይህንን ጽሑፍ ለማዘጋጀት ያነሳሳኝ የአለኝታ ደስታ ነው፡፡ ‹‹ማለት›› ብሎ የሚጀምር አረፍተ ነገር ስሰማ የምደነግጠውን ያህል፣ በወጣት ትውልድ የሚጻፉ የአማርኛ ግጥሞችን ሳነብ እረካለሁ፣ እኩራራለሁ፣ የባህል አለኝታዬ ካንቀላፋበት ይነቃል፣ ከሰመመን ይላቀቃል፣ ምንጩ አልደረቀም እላለሁ፡፡ ወጣት የአማርኛ ደራስያን (ገጣሚዎች) በርክተዋል፣ ብዙ ናቸው፤ የባህላችንም አለኝታዎች ናቸው፣ እኛ በርቱ እንበላቸው፣ ማበረታታቱ በተለይ የዕድሜ ባለፀጋዎች ኃላፊነት ነው ብዬ እገምታለሁ፡፡ ከዚህ አንፃር ታይታ፣ ይች የእኔ ጽሑፍ ለወጣት ደራስያን እንደ ማበረታቻ ትወሰድልኝ፣ ስለግጥም መወያየት ባህል ተንኳሽ ትሁንልኝ፡፡

ግጥም አጠር፣ መጠን ባለ መጠን የተለያዩ ትርጉሞችን ለመስጠት ያመቻል፤  በጣም ዝርዝር ከሆነ፣ ሌላ ፍች አያስፈልገውም ይሆናል፡፡ ምንም ‹‹ግጥም›› ‹‹የሥዕልን›› ያህል የተለያዩ ትርጉሞችን ለመስጠት ዕድልን ባያበርክትም፣ የምርጥ አጭር ግጥም፣ ፍችው (ትርጉሙ) የሚያበርክተው የጥበቷ ተቃራኒ ነው፣ ትርጉሙ መጠነ ብዙ ሊሆን ይችላል፡፡ በውስን ቃላት የተዋቀረ፣ ነጥሮ የወጣ፣ ብዙ ትርጉም ያለው ሲሆን፣ በአንፃሩ ያለ የሌለውን ማዕድ አድርጎ ያቀረበ ግጥም ግልብ ይሆናል፡፡ የዑመር ግጥሞች በአራት መስመሮች ነው የሚቋጩ፤ ስለሆነም ውብም፣ ፍልስፍና አዘልም ናቸው፡፡ እያንዳንዱ ትርጉመ ብዙ ሊሆንም ይችላል፡፡

አሁን ወደ ተነሳንበት ጉዳይ ልመለስ፡፡ ሁለቱ ታዋቂ ደራስያን (ተስፋዬ ገሠሠና በዕውቀቱ ሥዩም፣ በታሪክ አጋጣሚ ሁለቱም ወዳጆቼ ናቸው) በዕድሜ ይለያያሉ፣ በመሃላቸው ቢያንስ የ40 ዓመት ክፍተት ያህል አለ ብዬ እገምታለሁ፡፡ የሁለቱ ታዋቂ የግጥም ደራስያን፣ የስንኝ አወቃቀሮችም የተለያዩ ናቸው፡፡

የተስፋዬ ገሠሠ ሞቅ ደመቅ ያለ ነው፣ ፊት ለፊት ነው፣ የፈካ ነው፣ የሳቅ፣ የፈገግታ ምንጭ ነው፣ ሥዕላዊ ነው፡፡

ምሳሌ አንድ

የበረሃ ልጆች (ጎሕ ሲቀድ በምትባል የግጥም መድበል)

‹‹ለዘንፋላ ጡቶች ላረግራጊ ሽንጥ

ለለስላሳ ገላ ከንፈረ ምጥምጥ፤

ገንዘብ፤ ጤና ብቻ አይበቃም ድርጓቸው

ሕይወት፤ ጭንቀት፣ ጥበት፡-

ነፍስ ነው ግብራቸው!!››

(ለውቤ በረሃ ኮረዳዎች የተገጠመ ይመስላል)

ምሳሌ ሁለት

ግጥሞቹ ‹‹ዛሪያዊ›› ናቸው፣ ‹‹ኑረታዊ›› (Existential) ናቸው፡፡

ሕይወት ለመንግሥቱ ለማ

‹‹ . . .

አይመልሱትን ነገር የትናንቱንና የትናንቱን በስቲያ

አይናፍቁት ነገር ነገን ተነገወዲያ

ኧረ ወዲያ!  ወዲያ ወዲያ!

ሽህ ቅኔ ቢቀኙ

ሽህ ሚሾ ቢወርድ አዳሜ ቢንጫጫ

መንጌ ‹‹ስልቻ ቀልቀሎ፣ ቀልቀሎ ስልቻ!››

ኧረ ወዲያ! ወዲያ! ወዲያ!››

የበዕውቀቱ ሥዩም ስልት፣ አቀራረብ፣ ከሚታሰበው፣ ካነገብነው ነባር ግንዛቤ፣ የተገላቢጦሽ ነው፣ ነባራዊ ሁኔታዎችን የሚያናጋ፣ የሚያዛባ ነው፣ ዙሪያ ጥምጥም ዕይታን ያበረክታል፣ በእርሰ በርስ የማይዳሰሱ ገጽታዎች ያሉ አይመስልም፡፡

ምሳሌ አንድ

ፍግ ላይ የበቀለች አበባ (ስብስብግጥሞች በምትባል የግጥም መድበል)

‹‹አበባይቱም አለች፣

ፍግ ላይ የበቀለች

ምንድን ነው ጥበቡ?

ኔክታር ማጣፈጡ

አደይን ማስዋቡ፣

እኔም መለስኩላት፣

ይብላኝ ለንብ እንጂ ዝምብማ ይተጋል

ከቆሻሻ ዓለም ውስጥ ጣ'ምን ይፈልጋል፡፡››

ምሳሌ ሁለት

ዳዊት እና ጎልያድ

‹‹እግዜርና ዳዊት፣ አብረው ተቧደኑ

ብቻውን ታጠቀ፣ ጎልያድ ምስኪኑ

አንዳንዱ ተገዶ፣ ለሽንፈት ሲፈጠር

በጥቅሻ ይወድቃል፣ ስንኳንስ በጠጠር፡፡››

እኛ ‹‹ንብን›› ስናሞካሽ እርሱ ‹‹ዝንብን››፣ እኛ ‹‹ለዳዊት›› ስናዝን፣ እርሱ ‹‹ለጎልያድ›› ያደላል፡፡ ምን ያድርግ ከላይ የተወሰነበት ነው ብሎ ስኖቹ አስተካዥ ናቸው፡፡ ሰፊ አስተያየትንና ጥልቅ ግንዛቤን የተጎናጸፉ ናቸው፡፡

በሁለቱ መኻል ያለው የዕድሜ ልዩነት፣ የዕይታ ልዩነትን ሊያስከትል ይችላል አድማሳቸው፣ አቅጣጫቸው (በአጭሩ ወደ ግጥሙ የሚመለከቱበት መስኮት) አንድ አይሆንም፣ ዕድሜና ስልት ይለያዩዋቸዋል፡፡ ከላይ የሠፈሩት ግጥሞች፣ ስለደራስያኑ መጠነኛ ግንዛቤ ያስጨብጡናል ብዬ እገምታለሁ፡፡

ወደ ዋናው ጉዳይ ልመለስ፡፡ ግጥም ከአንድ የቋንቋ ጋን ወደ ሌላ የቋንቋ ጋን ሲገለበጥ ምን መስሎ ይገልበጥ ለሚለው? እያንዳንዱ አንባቢ ሊተችበት የሚችል ሁኔታ ነው፡፡ በባህል አባዜ ይታሰራል፣ በተሞክሮ ይገረገራል፣ በቋንቋ ቃላት ምንጭነትም (ባሕር አከል/ኩሬ መሰል) ይወሰናል፡፡

ግጥም ከመጀመሪያ ከተደረሰበት ቋንቋ ወደ ሌላ ቋንቋ ሲቀለበስ፣ ሲተረጎም፣ ውበቱ ለዛው የሚገለጠው በአካባቢ ዕይታ ስለሆነ፣ አዲሱ ቋንቋ የሚያስተናግደውን ባህል፣ ማኅበራዊ አስተሳሰብ፣ መዳሰስ ማካተት ይገባዋል፡፡ ደረቅ የግጥም ትርጉም፣ ለዛውን ይገፈፋል፣ ውብ ግጥምም አይሆንም፡፡ ይህች ጽሑፍ በዚህ ግንዛቤ ላይ የተመሠረተች ናት፡፡

የዑመር ኻያም (OMAR KHAYYAM) ግጥም ከፐርሽያን (ፋርስ) ቋንቋ በኤድዋርድ ፊትዝጀራልድ ወደ እንግሊዝኛ የተቀለበሰው (የእንግሊዝኛ ትርጉም - English translation of the original) እነሆ፡፡

Here with a loaf of bread beneath the Bough,

A Flak of wine, a Book of Verse-and Thou

Beside me singing in the Wilderness

 And Wilderness is Paradise enow.

የዑመር ኻያም ግጥም መልእክት እንደ ሽርሽር መውጣት ሆና፣ ስንቅንና አካባቢን (ቦታን) አገናዝበን እንድንመለከታት ትጋብዘናለች፡፡ ከዚያም ሁኔታዎችን ያገናዘበ ትርጉም፣ እይታና ስሜት ታበረክትልናለች፡፡ ሽርሸር ሲወጣም ትንሽ ዳቦ፣ አንድ ፋሽኮ ቪኖ (ወይን)፣ የግጥም መጽሐፍ ይዞ ሰወር አለ ቦታ፣ በዛፍ ሥር ተጠልሎ፣ ወዳጅን እያስዘፈኑ መደሰት ነው፡፡ የተያዘውንም ስንቅ እንዲሁም አካባቢውን፣ ብሎም የደስታው ምንጭ ምን እንደሆነ ማጤን ያሻል፣ አስተዋፅኦ ያደረጉ ይመስላል፡፡ ስንኙ በአራት መስመሮች (ሩብያት) የተወሰነ ነው፡፡

እንግዲህ የሁለቱን ቁንጮ የአማርኛ ደራስያን (ገጣሚዎች) አተረጓጎም ልመልከት፣ ስመለከት ግን፣ ከሦስት አቅጣጫዎች ብቻ እንዲሆን ወስኛለሁ፡፡ ያንን ያደረግኩበት ምክንያት ግንዛቤው ሳይኮላሽ መንዛዛቱ ይቀንሳል ብዬ ስለገመትኩ ነው፡፡ ሦስቱ አቅጣጫዎች (የግጥሙ መፈተሻ) እንሆ፡- ትርጉሞቹ ከዋናው (ከዑመር ግጥም) ጋር የይዘት ተመሳሳይነት፤ ትርጉም የተዋቀረባቸው ቃላት ብዛትና አካባቢውን አጢኖ ትርጉም ለምን ወይም ለማን ትኩረት እንደተሰጠ፣ ናቸው፡፡

እንግዲህ ትርጉሞችን አንድ ባንድ ላውሳ፡፡

በተስፋዬ ገሠሠ (1987 ዓ.ም.) መልክአ ዑመርበምትባል የግጥም መድበል እንደቀረበች፤

የቅኔው መጽሐፍ ሳይቀር ይያዝና

‹‹እንግዲህ ከዛፍ ሥር ጋደም ይባልና፣

የግጥም መጽሐፍ ሳይቀር ይያዝና፣

ፍትፍቱ ባገልግል፣ ጠላው በቅምጫና፣

ጠጁ በብርሌ ቡናው በጀበና፣

እጣኑ ከገሉ ቦለለል ይልና፣ እግር ባልዞረበት ሥውር አለ ስፍራ

ካጀብ ተለይቶ ከግርግር ርቆ ሆኖ ካንች ጋራ››

. . . .

ኸዚያ ወዲያማ፣

ኸዚያ ወዲያማ፣

ዝፈኝልኝ ነዋ እንጉርጉሮ በይ፣

‹‹አራዳም እንደሰው ይናፍቃል ወይ፣

አራዳ አራዳዬ አራዳ አራዳዬ፣

ሆይ-ሆይ! ገነት ማለት፣ ይች ናት ሆድዬ!››

    በዕውቀቱ ሥዩም (2009 ዓ.ም.) የማለዳ ድባብበምትባል የግጥም መድበል፣ ‹‹የምድረ በዳ በረከት›› በምትል ርዕስ እንደቀረበች፤

አንዲት ብርጭቆ ወይን፣

አንዲት ጤፍ እንጀራ፣ አንዲት አሪፍ ግጥም፣

እነዚህ ባሉበት በምድረ በዳ ላይ ቁጭ ብለሽ ከጎኔ፣

ሌላው ምን ይሠራል፣

ምድረ በዳው ሁሉ ዓደይ ለብሶ ያደርራል፡፡

ተስፋዬ ገሠሠ የአካባቢውን ድባብ በዝርዝር አስፍሯል፤ የግጥም መጽሐፍ፣ በዳቦ ፋንታ ፍትፍት በአገልግል፤ በወይን ፋንታ ጠጅ፣ ጠላ፤ እንዲሁም ዋናውን የሠፈር ባህል ቡና እና እጣንን ያካትታል፡፡ ዘወር ያለ ቦታንም ይመርጣል፣ ከግርግር ይሰወራል፣ ዛፍ ሥር ይጠለላል፡፡ እንጉሮውም ስለአራዳ ይሆናል፣ መኻል አዲስ አበባ፡፡

ዑመር ያወሳቸውን ሁሉ፣ ተስፋዬ ገሠሠ (ስንቅም ሆነ አካባቢ) አውስቷል፣ ያልነበረም ጨምሮበታል (ቡና፣ እጣን)፡፡ እይታውን አገር ቤት አስገብቶታል፡-

ዝፈኝልኝ ነዋ እንጉርጉሮ በይ፣

‹‹አራዳም እንደሰው ይናፍቃል ወይ፣

አራዳ አራዳዬ አራዳ አራዳዬ፣

ሆይ-ሆይ! ገነት ማለት፣ ይች ናት ሆድዬ!››

በተስፋዬ ገሠሠ ቅልበሳ የዑመር ግጥም ሙሉ በሙሉ አገራዊነት ተላብሳለች፡፡

በዕውቀቱ ሥዩም “ዊልደርነስ” (wilderness) ለሚለው ቃል የመጽሐፍ ቅዱስ ዓይነት ትርጉም ሰጥቶ “ምድረ በዳ” ብሎታል (ምሳሌ፤ ሙሴ በምድረ በዳ)፡፡ የቃሉ (wilderness) ተራ ትርጉሙ ዘወር ያለ፣ ጸጥ ያለ፣ ሰው የማይታይበት፣ ተፈጥሮ የገነነበት አካባቢ ነው፡፡ እንዲሁም የበዕውቀቱ እይታ የዑመርን ግጥም ይዘት ሙሉ በሙሉ አያካትትም፡፡ ለማካተት ከተሞከረበትም ገፅታ ሲታይ አቀራረቡ ከዑመር ካቀረበው ሁኔታ ጋር ይለያያል፡፡ ለምሳሌ ዑመር አንድ ፋሽኮ ቪኖ ሲያቀርብ፣ በዕውቀቱ አንድ ብርጭቆ ወይን ያቀርባል፣ ዑመር አንድ የቅኔ መጽሐፍ ሲያቀርብ፣ በዕውቀቱ አንዲት አሪፍ ግጥም ይላል፡፡ በዛፍ ጠለላ ስር ቆይታን አያመለክትም፤ እንዲያውም አካባቢውን “ምድረ በዳ” ያደርገዋል፡፡ ቆይታው በዘፈንም ሆነ በእንጉርጉሮ አልታጀለም፣ አልታጀበም፡፡

ይህም ሆን ተብሎ የተደረገ ይመስላል፣ አካባቢውን በጎላ መልኩ በአንድ ሌሊት ለመቀየር፣ አበባ አላብሶ ለማደር፡፡ የምድረ በዳው አበባ ለብሶ ማደር፣ ክስተቱን፣ ድርጊቱን፣ ሁኔታውን፣ ግሩም ድንቅ ያደርገዋል፣ ተዓምር ያስመስለዋል (ምደረ በዳን ባንዲት ሌሊት አስሽብርቆ ማደር)፡፡ ለምለም የሆነን አካባቢ፣ አበባ ቢጨምሩበት፣ አንፃራዊ መብቱ የጎላ አይሆንም፡፡ ኮረዳዋ በዑመር ጎኑ መገኘት ብቻ ደስታን ለዑመር ያጎናፅፈዋል፣ አካባቢው ራሱ መንግሥተ ሰማያት ይሆናል፣ ሌላው ምን ያደርጋል ብሎ ይደመድማል፡፡

በበዕውቀቱ የግጥም ቅልበሳው በአምስት መስመሮች ነው የተዋቀረ፣ “ሩብያትነቱን” ለጥቂት ነው የሳተ፡፡ በዚህ ዑመር ይደሰት ነበር ብዬ እገምታለሁ፣ የቃላት ቋት ለእርሱ፣ ለዑመር፣ “ሃራም” ስለነበረ፣ “የምን ጋጋታ ነው?"“እፍኝ ሙሉ ውብ ቃላት ይበቃሉ” ብሎ ያምን ነበር ብዬ ስለምገምት፡፡

በበዕውቀቱ እይታ ወይን (ቪኖም) የተያዘው በአንድ ብርጭቆ ነው፣ ዑመርና ወዳጁ ተራ በተራ ፉት ሊሉ ይሆናል፤ ያም የቅርበት፣ የፍቅር ሌላው መግለጫ ይሆናል፡፡ አንዲት አሪፍ ግጥም ነች የተሰነቀች፣ እሷው ናት በጋራ እምትነበነብ ማለት ነው፤ አንድ ብርጭቆ እንደመጋራቱ ሁሉ፡፡ የኮረዳዋ ከዑመር ጎን ሻጥ ማለት መንግሥተ ሰማያት እንደመግባት ያህል ይወሰዳል፡፡

ተስፋዬ “ሩብያቱን” በአሥራ ሁለት መስመሮች ይመነዝራል፡፡ ምነው የረፋድ መንገድ አደረግክብን? ብለን ልናማው እንችላለን፡፡ ቢሆንም ረፋድን በተዋበ አካባቢ ነው ያሳለፍነው፡፡ የተጓዝነው ብለን ልንጽናናም እንችላለን፡፡ እርሱም ጉዞውን ለማስዋብ ነው ባህላዊ ከባቢ ያሰፈርኩላችሁ ሊለን ይችላል፡፡

በዕውቀቱን ደግሞ ምነው ኮረዳዋን ብቻ የመንግሥት ሰማያት መጎናጸፊያ አደረግኻት፣ የአካባቢውን ድባብ ፋይዳ ቢስ አደረግኸው? ብለን ልንጠይቅ እንችላለን፣ በወቀሳ መልኩ፡፡ ዕድሜን አገናዝቦ፣ ያንን እርሱት፣ ተዉት! የምን ኮተት ማብዛት ነው? ሊለን ይችላል፡- ትኩስ ኃይል፡፡

የሁለቱም መልስ ተመሳሳይ ወይም አንድ ሊሆን ይችላል፡፡ እንደ ዕድሜያችን! ብለው ይመልሱ ይሆን? “እረጭ” በማለት ላይ ያለ ደም እና “ትኩስ” ደም መኻል ያለ ልዩነት ብለን ልንደመድም እንችል ይሆናል፡፡

ተስፋዬ ገሠሠ የዑመርን ግጥም ወደ አገር ቤት ሲያስገባት፣ ቡና አፍልቶ፣ እጣን አጢሶ ነው፣ የገጠመኝ ፀጋ፣ ዕድሜ ባስነገበው መስኮት ላይ ሆኖ አይቶ፡፡ በዕውቀቱ ሥዩም፣ ያለአካባቢ ድባብ (የዛፍ ጠለላም ሆነ፣ የጣን ጢስ፣ ቡና ሌላ፣ ሌላ)፣ የኮረዳዋ መገኘት ብቻ፣ መንግሥተ ሰማያት የመግባት ያህል ነው አለ፡፡ እንጉርጉሮም ሆነ ዘፈን አላስፈለጉም፡፡ ይባስ ብሎ፣ ቆይታን አንድ አዳር አከለበት፣ ዑመር ያላወሳውን (ምድረ በዳው አበባ ለብሶ ያድራል አለ፣ እዚህ አድራለች ማለት ነው፣ እርሷ በሌለችበት አዳር ይህ ተዓምር አይከሰትም ብሎ መገመት ይቻላል)፡፡ የኮረዳዋ እዚያ መገኘት እርካታ አበረከተ፣ ለዑመር ብቻ ሳይሆን ለአካባቢውም ጭምር፣ አካባቢውን አስሸበረቀው፣ አበባ አላበሰው፡፡

እንግዲህ ይህ ዓይነት ዘገባ፣ የሌሎች ተመሳሳይ ዘገባዎች መተንኮሻ እንደሚሆን ተስፋ አደርጋለሁ፣ ተስፋ የሁላችንም ከዛሬ ወደ ነገ መሸጋገሪያ ነው፤ ስለሆነም ተመሳሳይ ትችቶች በተለይ በወጣቱ ኃይል ይቀርባሉ ብዬ በተስፋ እጠባበቃለሁ፡፡     

ከአዘጋጁ፡- ጸሐፊው ሽብሩ ተድላ (ፒኤችዲ) የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የባዮሎጂና የፓራሲቶሎጂ ልሂቅ (ኢመረተስ) ፕሮፌሰር ሲሆኑ፣ በርካታ የጥናትና ምርምር ሥራዎቻቸውን አሳትመዋል፡፡ በቅርቡም ጥልቅ ማኅበራዊና ሰብአዊ (ሶሺያል ኤንድ ሂዩማኒስት) ጉዳዮችን በጥልቀት ያቀረቡበት ከጉሬዛም ማርያም እስከ አዲስ አበባ፡- የሕይወት ጉዞ እና ትዝታዬየተሰኘ መጽሐፍ ለኅትመት አብቅተዋል፡፡ ጽሑፉ የጸሐፊውን አመለካከት ብቻ የሚያንፀባርቅ ሲሆን፣ ጸሐፊውን በኢሜይል አድራሻቸው shibrut@gmail.comማግኘት ይችላል፡፡

 

 

 

Standard (Image)

ልዕልት የሺመቤት ዓሊ ጋምጩ እጅግ ብዙ የተነገረላቸው ንጉሠ ነገሥት እናት ምንም ያልታወሱ የወሎ ልዕልት

$
0
0

በይኼይስ ምትኩ ኃይሌ

በየትኛውም ዘመን የሚነግሡ ነገሥታት ታሪክና ገድል ጠንካራና ደካማ ጎኖች በወቅቱ በነበሩት የታሪክ ጸሐፊዎች ተሰናድተው ለትውልድ እንዲተላለፉ ይደረጋል፡፡ አዲሱ ትውልድ በቀደመው ትውልድ የተሠሩትን ሥራዎችና ታሪካቸውን ለማወቅና ለመመራመር የታሪክ ሰነዶችን ማገላበጥ የግድ ይላል፡፡ ነገሥታት አንዳንዴ በሠሩት ሥራ ልክ አንዳንዴም ከሠሩት ሥራ በላይ ይነገርላቸዋል፡፡  በአገራችን ኢትዮጵያ ታሪክ በርካታ የነገሥታት ታሪክ ቢኖርም አንዳንዶቹ ከቆይታቸውና ከሥራቸው አንፃር ብዙ የተባለላቸውና የተጻፈላቸው ናቸው፡፡ ለምሳሌ አፄ ዮሐንስ የአገራቸውን ሉዓላዊነት ለመጠበቅ ከጣሊያኖች፣ ከግብፆችና ከደርቡሾች ጋር ባደረጉት ተጋድሎ ትውልድ ያስታውሳቸዋል፡፡ አፄ ምኒልክ የአፍሪካውያን ድልና ኩራት በሆነው የዓድዋ ድልና ዘመናዊነትን ለኢትዮጵያ ለማስተዋወቅ ባደረጉት አስተዋጽኦ ትውልድ ሁሌም ይዘክራቸዋል፡፡ አፄ ቴዎድሮስ የአገር አንድነትን ለመጠበቅ፣ ዘመናዊነትን ለኢትዮጵያ ለማስተዋወቅ በመሞከራቸውና የአገራቸውን ሉዓላዊነት ለመጠበቅ መቅደላ ላይ የሠሩትን ተጋድሎ በታሪክ ሁሌም ይታወሳሉ፡፡

በኢትዮጵያ ታሪክና የፖለቲካ ተሳትፎ ወይም አገሪቱን በመምራት ረጅም ዘመናት ያስቆጠሩት ተፈሪ መኰንን በኋላ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ በአገሪቱ ዘመናዊነትን ለማስፋፋት ባደረጉት ጥረት በተለይም ደግሞ የአፍሪካ አንድነትን ምሥረታና ተያያዥ ታሪኮች ጋር ሁልጊዜ ስማቸው ጎልቶ ይሰማል፡፡

በአዲስ አበባ ሰኔ 26 እና 27 ቀን 2009 ዓ.ም. በተካሄደው 29ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ስብሰባ ላይ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ለአፍሪካ አንድነት ምሥረታና ዕድገት ላይ ላደረጉት አስተዋጽኦ በኅብረቱ ግቢ ውስጥ የመታሰቢያ ሐውልት እንዲቆምላቸው ተወስኗል፡፡ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ በኢትዮጵያ ታሪክና የፖለቲካ ሕይወት ውስጥ ለበርካታ ዓመታት ቆይተዋል፡፡ በንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ ዘመን አልጋ ወራሽ በመሆን ለ13 ዓመታት ቢያሳልፉም ከንግሥቲቱ በበለጠ በአገሪቱ ፖለቲካ ውስጥ ወሳኝ ሚና እንደነበራቸው ሁሉም የታሪክ ጸሐፊዎች የሚስማሙበት ነው፡፡

ከ1923 እስከ 1967 ዓ.ም. በአገራችን የቅርብ ታሪክ ውስጥ ለረጅም ጊዜ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ነበሩ፡፡ ስለሆነም የኢትዮጵያ ታሪክ በተነሳ ቁጥር የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ታሪክ መነሳቱ የግድ ነው፡፡

እኚህ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ለ58 ዓመታት (1909-1967) ጉልህ ሚና የነበራቸው ንጉሠ ነገሥት ከተወለዱ ዛሬ 125 ዓመት ሆናቸው፡፡ የዚህ አጭርና ታሪካዊ ጥያቄ ያላት ጽሑፍ መነሻ የንጉሠ ነገሥቱን ታሪክ ለማውሳት አይደለም፡፡ ንጉሠ ነገሥቱ ብዙ ተጽፎላቸዋል፡፡ ብዙ ተነግሮላቸዋል፡፡ ብዙ ተዚሞላቸዋል፡፡ ሆኖም ግን እኚህ በአገራችን ታሪክ ግዙፍ ስፍራ ያላቸው ንጉሠ ነገሥት፣ በአፍሪካ አንድነት ቀዳሚ ሚና የነበራቸውና በዚህም ምክንያት አፍሪካውያን በአንድ ድምፅ ለሠሩት ሥራ ሐውልት እንዲቆምላቸው የወሰኑላቸውን ንጉሥ የፈጠረው ማሕፀን ግን ሲወሳ ወይም ታሪኩ ሲነገርለት አይሰማም፡፡

ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ከእናታቸው ከወ/ሮ የሺመቤት (የአባታቸውና የአያታቸው ስም ሳይጠቀስ) እና ከአባታቸው ከልዑል መኰንን ወልደ ሚካኤል ጉዲሳ ሐምሌ 16 ቀን 1884 ዓ.ም. በቀድሞ አጠራር በሐረርጌ ጠቅላይ ግዛት ጀርሳ ጎሮ ተወለዱ የሚለው ታሪክ በተደጋጋሚ ተጽፏል፡፡ አባታቸው ልዑል መኰንን ወልደ ሚካኤል ጉዲሳንም በተመለከተ በርካታ ገድሎቻቸውን፣ የሚወዱት ምግብና መጠጥ ሳይቀር ቁመናቸውና የሚለብሱት ልብስ ጨምሮ በፎቶ በማስደገፍ በተለያዩ የታሪክ ጸሐፊዎች ተመዝግበው ይገኛሉ፡፡

ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ሕይወቴና የኢትዮጵያ ዕርምጃበማለት በ1965 ዓ.ም. ባሳተሙት መጽሐፋቸው የልጅነት ሕይወታቸውን በተመለከተ ሲገልፁ፣ አባቴ ልዑል ራስ መኰንን የታላቁ የሸዋ ንጉሥ የሣህለ ሥላሴ ልጅ የልዕልት ተናኘ ወርቅ ልጅ ናቸው፡፡ በማለት ይቀጥሉና አባታቸውም የዶባና የመንዝ ባላባት ደጃዝማች ወልደ ሚካኤል ወልደ መለኮት ልጅ ናቸውይላሉ፡፡ ይህ ሌሎች የታሪክ ጸሐፊዎች ራስ መኰንን ወልደሚካኤል ጉዲሳ የሚለውን የአያታቸውን ስም ሙሉ በሙሉ የሚቀይር ነው፡፡ እንዴት ጉዲሳ ወደ ወልደ መለኮት እንደተቀየረ ግልጽ አይደለም፡፡ ይህንን ለታሪክ ተመራማሪዎች እተወዋለሁ፡፡

የወረኢሉ ታዋቂ የኦሮሞ ባላባት ከነበሩት ዓሊ ጋምጩ የሚወለዱት ልዕልት የሺመቤት ከሌሎቹ የአገራችን ባለ ታሪኮች አንፃር የተባለላቸው ወይም የተጻፈላቸው ነገር የለም ማለት ይቻላል፡፡ በርካታ የታሪክ ጸሐፊዎችን ያዘጋጁትን የታሪክ ሰነድ ስናገላብጥ የምናገኘው የንጉሡን ወይም የንጉሡን አባት ታሪክ እንጂ የልዕልቷን ታሪክ አናገኝም ወይም ቢገኝም እጅግ በጣም በጥቂቱ ነው፡፡

በተለይ የቀድሞ ታሪክ ጸሐፊዎች የልዕልቲቷን ታሪክ ሊጽፉ ቀርቶ አባት ወይም አያት የሌላቸው እስኪመስል ወይም የአባትና የአያታቸውን ስም ላለመጻፍ የተማማሉ እስኪመስል ድረስ ከስማቸው ውጭ የአባትና የአያት ስም ማለትም ዓሊ እና ጋምጩ የሚለውን አይጠቅሱም፡፡ ንጉሡ በጻፉት መጽሐፋቸው ላይ እንኳን የእናታቸው ሙሉ ታሪካዊ ዳራ ሊፃፍ ቀርቶ በአገራችን የስም አጠራር እንደሚደረገው የእናታቸውን አባትና አያት ስም አልተጠቀሰም፡፡ ይህ ለምን ሆነ ብዬ ሁል ጊዜ ራሴን ብጠይቅ መልስ ያላገኘሁለት ጥያቄ ነው፡፡ የታሪክ ባለሙያዎች መልስ እንደምትሰጡኝ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡

የሺመቤት ዓሊ ጋምጩ ማናቸው?

ልዕልት የሺመቤት እናታቸው ወ/ሮ ወለተጊዮርጊስ የምሩ ሲባሉ፣ አባታቸው ደግሞ ዓሊ ጋምጩ ይባላሉ፡፡ የተወለዱት በቀድሞ አጠራር በወሎ ጠቅላይ ግዛት ወረኢሉ አውራጃ (አሁን ደቡብ ወሎ ዞን ወረኢሉ ወረዳ) ዶሉ በሚባል ቦታ ነው፡፡ የዚህ ጽሑፍ አዘጋጅ ከ20 ዓመት በፊት በወረኢሉ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የታሪክ መምህር ሆኜ በማገለግልበት  ወቅት የአካባቢውን ታሪክ የያዘ አጠር ያለ ታሪካዊ የጥናት ጽሑፍ ለትምህርት ቤቱ አቅርቤ ነበር፡፡

ጥናት ከቀረበባቸው ታሪካዊ የአካባቢው ጉዳዮች አንዱ የልዕልት የሺመቤት ዓሊ ጋምጩ ታሪክ ነበር፡፡ የልዕልቷ ቤተሰቦች ማለትም ተወላጆቻቸው በማነጋገር ጥርት ያለና ታሪኩን እንደወረደ ለመጻፍ ተሞክሯል፡፡ የልዕልቷ አራተኛና አምስተኛ ተወላጆች በአካባቢው በሕይወት ስላሉ የሚያውቁትንና ከቀደምት ቤተሰቦቻቸው የተነገራቸውን ምንም ሳይሸራረፉ ቃል በቃል ነግረውኛል፡፡

የተወለዱበት ቦታ ሳይቀር በአካል በመገኘት አይቼዋለሁ፡፡ አሁን በምን ደረጃ ላይ እንዳለ ባላውቅም በወቅቱ እጅግ በጣም ትልልቅ ዕድሜ ጠገብ ዛፎችና በመፈራረስ ላይ የሚገኝ ቤትና አጥር ነበረው፡፡ ልዕልት የሺመቤትን የተመለከተ የሰነድ ማስረጃ ማግኘት ግን አልቻልኩም፡፡ ይህ ምናልባትም ልዕልቲቷ አካባቢውን በሕፃንነታቸው ስለለቀቁት ይመስለኛል፡፡ ዘውዴ ረታ ተፈሪ መኮንን ረጅሙ የሥልጣን ጉዞበሚባለው መጽሐፋቸው ገጽ 18 ላይ፣ ወ/ሮ ወለተ ጊዮርጊስ ከወረኢሉ ባላባት ከሼሕ ዓሊ የወለዷትን ሴት ልጅ ይዘው ወደ ሸዋ ለመመለስ የቻሉት አፄ ምኒልክ ከቴዎድሮስ አምልጠው ከተመለሱ ከአንድ ዓመት በኋላ ነው፡፡ በዚያን ጊዜ ሕፃኗ የሺመቤት የአራት ዓመት ልጅ ነበረች፤ይላሉ፡፡ ይህ የሚያመለክተው ልዕልት የሺመቤት አካባቢውን የለቀቁት በሕፃንነታቸው ስለነበር ታሪካዊ የሰነድ ማስረጃዎች በአካባቢው አለመገኘቱ ግልጽ ነው፡፡  

ልዕልት የሺመቤት፣ ሐሰን ዓሊና ስናፍቅሽ ዓሊ የሚባሉ ሁለት ወንድምና እህት ነበራቸው፡፡ ሆኖም ግን በእናት የሚገናኙ አይመስለኝም፡፡ የስናፍቅሽና የሐሰን ዓሊ ተወላጆች ወረኢሉና ጃማ ወረዳ በብዛት ስለሚገኙ የልዕልቷን ታሪክ መፃፍ ለሚፈልጉ ጥሩ አጋጣሚ ነው ብዬ አስባለሁ፡፡

በተለይ የስናፍቅሽ ዓሊ ልጅ የነበሩትና በኃይለ ሥላሴ ጊዜ የጃማ ወረዳ (በደቡብ ወሎ የሚገኝ ወረዳ ነው) አስተዳዳሪ የነበሩት ፊታውራሪ ከበደ ባንተ አይምጣ የአባቴ የቅርብ ጓደኛ ስለነበሩ ቤታችን እየመጡ ስለቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ቤተሰብና አንዳንድ ተያያዥ ጉዳዮች በተመለከተ ከአባቴ ጋር የሚያደርጉት ውይይትና ጭውውት ሁልጊዜ አስታውሰዋለሁ፡፡

የፊታውራሪ ከበደ ልጆች ጋር አብሮ አደጎች ስለሆንን ይኼንን የታሪክ ማስታወሻ ሳዘጋጅ ኑሮዋን ጃማ ወረዳ ያደረገችውን ልጃቸውን ወ/ሮ ተዋበች ከበደን በስልክ አናግሬአት ነበር፡፡ በማዘጋጀው ማስታወሻ ደስተኛ ብትሆንም የልዕልት የሺመቤት ዓሊ ጋምጩ ታሪክ አስታዋሽ ማጣቱ ግን ቅር እንዳሰኛት አልሸሸገችኝም፡፡

በቅርብ የታተመውና ፕሮፌሰር ፍቅሬ ቶሎሳ የኦሮሞ እና የአማራ እውነተኛ የዘር ምንጭ በሚለው መጽሐፋቸው ገጽ 241 ላይ፣ እናቱ (ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴን) የሺመቤት ዓሊ ጋምጩ በአባትዋ በኩል የወረሂመኑ ኦሮሞ ናት፡፡ በአዲሱ ግኝት መሠረት ይብረሁልሽ በተባለችው ሥልጤ ጉራጌ እናትዋ ‘ቂቶ’ ትባል የነበረችው አያትዋ ወ/ሮ ወለተ ጊዮርጊስ የወሎው ኦሮሞ ነብይ የሼሕ ሁሴን ጅብሪል ልጅ ናት፡፡ ይህ ማለት ሼሕ ሁሴን ጅብሪል የአፄ ኃይለ ሥላሴ ቅድመ አያት ናቸው ማለት ነው፤በማለት ጽፈዋል፡፡ ሆኖም ግን ይህ ፍጹም ስህተት የሆነ የታሪክ ግድፈት ነው፡፡ አፄ ኃይለ ሥላሴ ከሼሕ ሁሴን ጅብሪልም ሆነ ከወረሂመኑ ተወላጆች ጋር ምንም ግንኙነት የላቸውም፡፡

ይህ በዚህ እንዳለ ልዕልት የሺመቤት ዓሊን የሚያውቅና ስለ እሳቸው አንጀት አርስ ጽሑፍ የተጻፈው በፊታውራሪ ተክለ ሐዋርያት ተክለ ማርያም ነው፡፡ እኚህ ግለሰብ በልዕልቲቷ ቤት ያደጉ በመሆናቸው ደግነታቸውን፣ ባህሪያቸውን፣ መልካቸውንና ከዚያም ባሻገር  ዘግናኝ አሟሟታቸውንም ሒደት ጽፈውልናል፡፡ 

ፊታውራሪ ተክለ ሐዋርያት፣ የሕይወቴ ታሪክበሚባለውና በ1998 ዓ.ም. ቤተሰቦቻቸው ባሳተሙት መጽሐፍ ገጽ 32 ላይ፣ ተክለ ሐዋርያት ልዕልት የሺመቤትን መጀመሪያ ያዩዋቸው ቀን የነበረውን ሁኔታ ሲገልፁ ወ/ሮ የሺመቤት በጣም ወፍራም ብስል ቀይ ናቸው፡፡ ቆንጆ ናቸው፡፡ ሹሩባቸው በትከሻቸው ላይ ተንዘርፍፏል ይላሉ፡፡በእርግጥ ቁንጅናቸውን ለመመስከር የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴን መልክ ማየት በቂ ይመስለኛል፡፡

ራስ መኰንን ቤት አገልጋይ ሆኜ ቤተሰብ ነበርኩ የሚሉት ፊታውራሪ ተክለ ሐዋርያት ልዕልት የሺመቤት ደግና ሩህሩህ መሆናቸውንም በዚሁ ከላይ በተገለጸው መጽሐፋቸው በተደጋጋሚ ገልጸዋል፡፡ ፊታውራሪ ተክለ ሐዋርያት ሐረር በነበሩበት ወቅት በተፈጠረባቸው በሽታ ምክንያት የሰውነታቸውን መጎዳት ልዕልት የሺመቤት በማየታቸው በወቅቱ የተፈጠረው ሲገልፁ፣

እንኮዬ ተመዋረድ (የልዕልቲቱ አገልጋይ) መዳኔን ለእመቤቴ ነግራቸው ኖሮ አምጪው ብለዋት ወሰደችኝ፡፡ ባዩኝ ጊዜ ደነገጡ ‹‹ምነው አቡነ ተክለ ሃይማኖት! እንዴት ከሳ! አወይ ልጄን ክፉኛ ተጎድትዋል፡፡ አብሽሬ እባክሽ አብሊልኝ በቶሎ እንዲያገግም እንድታጎርሺው››ማለታቸውንና በዚሁ በተደረገላቸው ቤተሰባዊ እንክብካቤ ከበሽታቸው ማገገማቸውን ጽፈዋል፡፡

በመጨረሻም የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ታናሽ ወይም አሥረኛ ልጃቸውን ሲገላገሉ የተፈጠረውን የልዕልት የሺመቤት አሟሟት ገጽ 45 ላይ በዓይን ያዩትን በዝርዝርና ልብ በሚነካ ስሜት የጻፉትን እንዲህ አንብቡት፡-

መጋረጃ ተጥሎ እመይቴ ያቃስታሉ ከወደ ጀርባ ዞርኩና ወደ እመይቴ ተጠጋሁ፡፡ ከመሬት በላይ ከፍ አድርገው አስቀምጠዋቸዋል፡፡ እግሮቻቸውን አንፈራጠው ጋለል ብለው ተደግፈዋል፡፡ ምጥ ይዟቸዋል፡፡ አንዲት የአደሬ ሴት (ስሟ ተዘነጋኝ ቡሽሮ ነው ይመስለኛል) አዋላጃቸው ነች ተብላ አለቃ ሀብተ ማርያም አስመጥተዋል፣ ከእመይቴ እግሮች ስር ተቀምጣ ትጠባበቃለች፡፡ ሴቶቹ ከመጋረጃ ግቢ ሲያገኙኝ ጊዜ የተመዘዘ ካራ ሰጡኝ ከእመይቴ ራስጌ አቆሙኝ እንደዚህ የጎራዴውን ደንደስ ከጫንቃዬ ላይ አስደግፌ እጠባበቃለሁ፡፡ ሴቶቹ ይማጠናሉ ‹‹ማርያም ማርያም›› ይላሉ፡፡ እኔም እንደነሱ ልመናዬን አፋጠንኩ፡፡

ምጡ እመይቴን አልጎዳቸውም ሴቶቹ መማጠናቸውን ተዉና ድምፃቸውን በጣም ዝቅ አድርገው ተንሾካሾኩ ልጅ መወለዱን በመላ አወቅሁ፡፡ ነገር ግን ድምፁን አልሰማሁትም አዲስ የተወለደውን ልጅ ወደ ጓዳ ያሸሹት መሰለኝ፡፡ አለቃ ሀብተ ማርያም ወደ ጓዳው ውስጥ እየገቡ እየወጡ እየተመላለሱ ከሴቶቹ ጋር ይነጋገራሉ፡፡ በኋላ ልጁን ወዴት እንዳደረሱት ለማወቅ አልተቻለኝም፡፡ እንደዚህ እመይቴ ተገላግለው ጥሬ ቅቤ ከራሳቸው ላይ በጉሎ ቅጠል ለጠፉላቸው፡፡ እመይቴ ውኃ ለመኑ፡፡ ‹‹እባካችሁ ውኃ ስጡኝ›› አሉ፡፡ አለቃ ሀብተ ማርያም ወተት እንዲሰጧቸው አዘዙ፡፡ ወተቱን በቀመሱ ጊዜ እመይቴ ተቆጡ ‹‹በጦም አስገደፋችሁኝ አቡነ ተክለሃይማኖት ይወዱላችኋል›› እያሉ አማረሩ፡፡ አለቃ ሀብተ ማርያም ቄሶች አስገቡና እግዚአብሔር ይፍታ አሰኝተው ‹‹ንስሐ በኋላ መቀበል ነው እንጂ ምንም ኃጢአት የለበትም›› እያሉ አጽናኗቸው፡፡ ውድቅት አለፈ የእንግዴ ልጅ አልወርድ ብሎ አስቸገረ ማታ የተገላገሉ ከዶሮ ጩኸት በኋላ እንኳ ሳይወርድላቸው ቆየባቸው፡፡ ሊነጋ አቅራቢያ ተዳከሙ መናገር ያቅታቸው ጀመር ሰውነታቸው በጣም ወፍሮ ነበርና ጉዳት በዛባቸው፡፡ እየቆዩ ሴቶቹ ሁሉ ተጨነቁ ያለቅሳሉ እኔም እየተጨነቅሁ አለቅሳለሁ እንቅልፍና ድካም አልተሰሙኝም፡፡ አለቃ ሀብተ ማርያም ትዕዛዝ ሰጡ፡፡ አዋላጅዋ እጅዋን ትታጠብና ጣቶችዋን አስገብታ ቀስ ብላ የእንግዴ ልጁን ወደ ውጪ እየሳበች ታስወጣው ብለው አልጎመጎሙ፡፡ ሴቶቹ ይህን በሰሙ ጊዜ ፊታቸውን አኮማተሩ ለቅሶም አበረቱ፡፡ አዋላጅዋ እንደታዘዘቸው አደረገች እመይቴ ክፉኛ ተንሰቀሰቁ ድምፃቸውን ልቤን ነካው የባሰውን እንባዬ ፈሰሰ፡፡ እመይቴ ጮሁ ‹‹ኧረ ገደላችሁኝ፣ እባካችሁ ስለ አቡነ ተክለሃይማኖት ጥቂት አስተንፍሱኝ ምነው ጨከናችሁብኝ! ምን አልኳችሁ…›› አዋላጅዋ ፋታ አልሰጠቻቸውም ዝም ብላ ትጎለጉላለች እመይቴ ተዳከሙ ተዝለፈለፉ በዙሪያቸው ደጋፊዎች በዙ፡፡ ሊነጋ ነው ወፎች መንጫጫት ጀመሩ ጭለማው ሊገፍ ነው ጧት በማለዳ እመይቴ አረፉ፤ ይላሉ፡፡ 

ፊታውራሪ ተክለ ሐዋርያት ልዕልት የሺመቤት ከላይ በተገለጸው በዘግናኝ ሁኔታ በወሊድ ምክንያት ሕይወታቸው ማለፉን ቢገልጹም የተወለደው ልጅ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ይሁኑ ሌላ አልገለፁም፡፡ ዘውዴ ረታ፣ ተፈሪ መኮንን ረጅሙ የሥልጣን ጉዞበሚለው መጽሐፋቸው ላይ ልዕልቲቱ የሞቱት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ከተወለዱ በኋላ ቀጥሎ የተፀነሰውን ልጅ በሚወልዱ ጊዜ ነው ማለታቸውና በንጉሡ የተጻፈው ሕይወቴና የኢትዮጵያ ዕርምጃበሚለው መጽሐፍ ላይ፣ እናቴ ወ/ሮ የሺመቤት ገና የሠላሳ ዓመት ዕድሜ እያሉ በ1886 ዓ.ም. መጋቢት 6 ቀን አርፈው ሐረር በጥምቀተ ባሕር ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ተቀበሩ፣የሚለው ሲታይ ልዕልቲቷ ያረፉት ንጉሡ ከተወለዱ ከሁለት ዓመት ገደማ መሆኑን ያመለክታል፡፡

በታሪክ ውስጥ ጉልህ ስፍራ የነበራቸው ሰዎች በየትኛውም አገር እንደሚደረገው ሐውልት ይቆምላቸዋል፣ ሙዚየም ይዘጋጅላቸዋል፣ ይጻፍላቸዋል፡፡ አንዳንዴም ይዜምላቸዋል፡፡ ሆኖም ግን ልዕልት የሺመቤት በወረኢሉ ከተማ ከሚገኘውና ደርግ ‹‹ድል በዓል›› ብሎ የሰየመውና በኋላ ወደ ቀድሞ ስሙ ከተመለሰው ‹‹ልዕልት የሺመቤት›› ተብሎ ከሚጠራው መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ውጭ ለስማቸው መጠሪያ ምንም ዓይነት ማስታወሻ አይገኝም፡፡ በወቅቱ የታሪክ መምህር በነበርኩበት ወቅት ያየሁትና የተወለዱበት አካባቢ፣ ቤትና ግቢ አሁን በምን ሁኔታ ላይ እንዳለ አላውቅም፡፡ ሆኖም ግን በተቃራኒው ስለልጃቸው ታላቅ ሥራ ብዙ ተብሏል፣ ተጽፏል፣ ሐውልትም ሊቆም ነው፡፡ ሆኖም ግን ከዚህም ባሻገር ይህን በአገራችን ታሪክ ግዙፍ ስፍራ ያለውን ባለታሪክ ያፈራ ማሕፀን ብናስታውሰው፣ ብናወሳውና ብንጽፍለት ተገቢ ይሆናል እላለሁ፡፡ ቸር ሁኑ፡፡

በመጨረሻም ይህንን የታሪክ ማስታወሻ ስጽፍ ዋናው ዓላማዬ የተዘነጉትን ልዕልት ለማስታወስና የታሪክ ተመራማሪዎች ተገቢውን እንዲሠሩ ለማስታወስና ለመጠቆም ነው፡፡ 

    ከአዘጋጁ፡- ጸሐፊው በኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ የሕግ መምህር ሲሆኑ፣ ጽሑፉ የሳቸውን አመለካከት ብቻ የሚያንፀባርቅ ነው፡፡ ጸሐፊውን በኢሜይል አድራሻቸው yiheyis.lawoffice@gmail.comማግኘት ይቻላል፡፡

 

 

Standard (Image)

ነጠብጣቡን ማገናኘት.... የማዕድን ሀብት እንቆቅልሽ

$
0
0

 

ፓን አፍሪካዊነትን የሚያቀነቅነው ታዋቂው ኒው አፍሪካ መጽሔት እ.ኤ.አ. በየካቲት 2004 ዕትሙ "Solving The Great Conundrum...How African Can Own Its Natural Resources"በሚል ርዕስ በሰጠው የሽፋን ዘገባው የአፍሪካ ታላቁ እንቆቅልሽ፣ አፍሪካውያን እንዴት የተፈጥሮ ሀብቶቻቸው ባለቤት ይሆናሉ ብሎ ይሞግታል፡፡ የውጭ ኩባንያዎች አምስት በመቶ የሮያሊቲና ታክስ ብቻ፣ ከ90 እስከ 95 በመቶ የአፍሪካን የተፈጥሮ ሀብቶች ሲመዘብሩ ዓመታትን ያስቆጥራሉ የሚለው መጽሔቱ፣ ኩባንያዎቹ ለማዕድን ፍለጋ ሥራ የሚያወጡትን ወጪ በማጋነን የአኅጉሪቱ ሕዝብ በደኅንነት ሲማቅቅ ይቆያል ይለናል፡፡

የቀድሞው የላይቤሪያ ፕሬዚዳንት ቻርልስ ቴለር ወደ ሥልጣን በወጡ በሁለተኛው ዓመት እ.ኤ.አ. በ1997 የበላይቤሪያ አጠቃላይ የማዕድን ሀብቶች ክምችቶች በአየር ላይ እንዲነሱና ጥናት እንዲካሄድ አዘዙ፡፡ የፕሬዚዳንቱ ውሳኔ በአገሪቱ መንግሥት የማዕድን ሀብቶቹን ክምችት ለማወቅ ተስፋ ሰጪ ውጤቶች የተገኙበት ነበር፡፡ ምክንያቱም መንግሥት አገሪቱ ምን ዓይነት ማዕድኖች እንዳላት፣ በተጨባጭ የት የት እንደሚገኙና በምን ያህል መጠን እንደሚገኙ ማወቅ ተችሎ ነበር፡፡ ቻርስ ቴለር ወደ ሥልጣን ከመምጣታቸው ጥቂት ዓመታት በፊት በጆርጅ ቡሽ አስተዳደር ከፍተኛ ባለሥልጣናት የሚደገፍ አንድ የአሜሪካ ግዙፍ የነዳጅ ዘይት ኩባንያ፣ በላይቤሪያ የነዳጅ ዘይት ፍለጋ ላይ ተሰማርቶ ነበር፡፡ ኩባንያው ከላይቤሪያ  ለሚያወጣው የነዳጅ ሀብት ከእያንዳንዷ ዶላር አምስት ሳንቲም ለአገሪቱ ለመስጠት ፍላጎት ነበረው፡፡ ቻርልስ ቴለር ግን ስምምነቱን ማድረግ አልፈለጉም፡፡ ያ ግዙፍ የአሜሪካ ኩባንያ ስምምነቱን እንዲያደርጉ ደጋግሞ ግፊት ቢያደርግም በእንቢተኛነታቸው በመፅናታቸው፣ በእጅ አዙር እ.ኤ.አ. በ2004 በሴራሊዮን ልዩ ፍርድ ቤት የሴራሊዮን አማፂያንን በመርዳት  የሚል ክስ እንዲቀርብባቸው ምክንያት እንደሆነ  ይነገራል፡፡            

የቴለር ክስን ከመጋረጃው ጀርባ ሆነው ግፊት ይፈጥሩ የነበሩት ዩናይትድ ስቴትስና ብሪታኒያ ነበሩ፡፡ ይኼ ግዙፍ የአሜሪካ የነዳጅ ዘይት ኩባንያ  "የላይቤሪያን ነዳጅ ዘይት እኛ እንድናወጣ ከፈቀዱልን ለፍርድ እንዳይቀርቡ እናደርጋለን ...."የሚል መደለያ አቅርቦላቸው ነበር ይባላል፡፡ ከአገሪቱ የነዳጅ ዘይት ሀብት ገቢ ውስጥ ከያንዳንዷ ዶላር አምስት ሳንቲም ብቻ ማግኘት ፍትሐዊ አይደለም ብለው የሞገቱት ቴለር በኋላ ከመከሰስ አልዳኑም፡፡ ኩባንያው "ክቡር ፕሬዚዳንት ልንረዳዎት አንችልም፣ ልንከላከልሎት አንችልም ..."ነበር ያለው

ቴለር ከማዕድን ኩባንያዎች የሚገኘውን የማዕድን ትርፍ ለማሳደግ ያደረጉትን ቁርጠኛ ዕርምጃ የተቃወማቸው አንድ የውጭ ኩባንያ ከሥልጣን ለመወገዳቸው፣ ከሴራሊዮን ልዩ ፍርድ ቤት ወደ ሔጉ ዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት ከተላለፉ በኋላ ችሎት ላይ ቆመው ለምን ለእስር እንደተዳረጉ ይኼንን ታሪክ  አቀረቡ፡፡ ፍርድ ቤቱ በፀጥታ ተዋጠ፡፡ ታሪኩ በአጭሩ ቻርልስ ቴለር የሴራሊዮን  አማፂያንን "በመርዳትና በሌሎች ወንጀሎች"ፍርድ ቤቱ ጥፋተኛ መሆናቸውን አረጋግጫለሁ በማለት ለ50 ዓመታት በብሪታኒያ እስር ቤት እንዲማቅቁ ፈርዶባቸዋል፡፡

አንድ ዓይነት  ባይሆንም እ.ኤ.አ. በ1997 የኮንጎ ብራዛቪል ፕሬዚዳንት የነበሩት ሊዙባ ተመሳሳይ ዕጣ ገጥሟቸዋል፡፡ በዴሞክራሲያዊ ምርጫ ወደ ሥልጣን የመጡት ሊዙባ፣ የኮንጎ ብራዛቪል ሕዝብ በምርጫ የጣለባቸውን ኃላፊነት  በመጠቀም የቀድሞ ወታደራዊ አስተዳደር ከምዕራባውያን ግዙፍ የነዳጅ ዘይት ኩባንያዎች ጋር የገባውን ድርሻ ክፍፍል ምጣኔ በተመለከተ ለመደራደር ሐሳብ አቀረቡ፡፡ አገሪቱ ከነዳጅ ሀብቷ 15 በመቶ ብቻ ታገኝ ስለነበር ፕሬዚዳንት ሊዝቡ ይኼ ዝቅተኛ ድርሻ ወደ 33 በመቶ እንዲያድግ ለማድረግ ቆርጠው ተነሱ፡፡ ከአንድ የፈረንሣይ ግዙፍ የነዳጅ ዘይት ኩባንያ በስተቀር ሁሉም የነዳጅ ዘይት ኩባንያዎች ደስተኛ ነበሩ፡፡ የፈረንሣይ የነዳጅ ዘይት ኩባንያው ወዲያው ወደ ፈረንሣይ ፓሪስ  በማቅናት ለወቅቱ ለፕሬዚዳንት ጃክ ሺራክ መራሹ መንግሥት ድርጊቱ እንዲቆምና ፕሬዚዳንት ሊዝቡ እንዲንበረከኩ ፈረንሣይ እንድታደርግ ተማፀነ፡፡

ፕሬዚዳንት ሊዝቡ እ.ኤ.አ. በ1998 እንግሊዝ ለንደን ውስጥ ከኒው አፍሪካ መጽሔት ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንደተናገሩት፣ ፕሬዚዳንት ጃክ ሺራክ ወዲያው ወደ ፓሪስ አስጠርተዋቸው የቀድሞ መንግሥት ወታደራዊ መሪን ምክትል ፕሬዚዳንታቸውና የመከላከያ ዋና አዛዥ እንዲያደርጉ ቀጭን ትዕዛዝ  ሰጧቸው፡፡ ይኼ የፈረንሣይ ጣልቃ ገብነት ከኮንጎ ብራዛቪል ሕገ መንግሥት ጋር የሚጋጭ  ቢሆንም፣ ፈረንሣይ የፈለገችው የፈረንሣዩን ግዙፍ ነዳጅ ዘይት  ኩባንያ ጥቅም ለማስከበር የሚያስችላት ተቀናቃኝ ኃይል ወደ ሥልጣኑ ቁንጮ ማምጣት ነበር፡፡ ሊዝቡ የኮንጎ ብራዛቪል ሕገ መንግሥት እንደማይፈቅድ ለቀድሞው የፈረንሣይ ፕሬዚዳንት ጃክ ሺራክ ሲነግሯቸው፣ ሕገ መንግሥቱን አንቋሸው ውሳኔውን እንዲተገብሩ አዘዙ፡፡

ከጥቂት ሳምንታት በኋላ የሊዝቡ መንግሥት አልቆየም፡፡ በትንሽ "የእርስ በእርስ ጦርነት "ሥልጣኑን እንዲያጣ ተዳረገ፡፡ የቀድሞ መንግሥት ወታደራዊ መሪ አማፂ ወታደሮች መንግሥቱን እንዲጥሉ ያ የፈረንሥይ ግዙፍ የነዳጅ ዘይት ኩባንያ  ጀልባዎቹን እስከ መስጠት የዘለቀ ድጋፍ በማድረግ የፕሬዚዳንት ሊዝቡ መንግሥት እንዲወድቅ አደረገች፡፡ ፈረንሣይ ለኮንጎ ብራዛቪል ምክትል ፕሬዚዳንት እንዲሆን ያጨችው የቀድሞ መንግሥት ወታደራዊ አዛዥ ሥልጣኑን ተቆናጠጠ፡፡ ፕሬዚዳንት ሊዝቡ ከኮንጎ ነዳጅ ገቢ አገሪቱ 33 በመቶ ማግኘት አለባት ቢሉም፣ ይኼ ዕርምጃቸው ሥልጣናቸውን እንዲያጡ ዳረጋቸው፡፡ ፕሬዚዳንቱ የፈለጉት ድርሻ ተግባራዊ ሳይሆን ቀርቶ  20 በመቶ ኩባንያው በመክፈል የአገሪቱን ነዳጅ ሀብት መበዝበዙን ቀጠለ፡፡ ጉዳዩ በዚህ ተጠናቀቀ፡፡

ከሃያ አምስት ዓመት በፊት የሊዝቡ መንግሥት መገርሰስ ጋር የሚመሳሰል ድርጊት እ.ኤ.አ. በ1974 በኒጀር ተመሳሳይ ድርጊት ተከስቶ ነበር፡፡ በወቅቱ ኒጀርን ያስተዳድሩ የነበሩት ሀማኒ ዶሪ ልክ እንደ ኮንጎ ብራዚቪሉ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ተመሳሳይ ዕጣ  ገጥሟቸዋል፡፡ በወቅቱ ምዕራባውያን ዘመም በመሆኑ የሚታወቀው የኒጀር መንግሥት የኒጀር ዩራኒም ማዕድን በማውጣት ሥራ ላይ የተሰማራው  የፈረንሣይ ግዙፍ ማዕድን አውጪ ኩባንያ፣ ከዩራኒየም ገቢው ለኒጀር የሚሰጠውን አነስተኛ ምጣኔ እንዲያሻሽል መጠየቁን ተከትሎ ፈረንሣይ ጥርስ ውስጥ ገባ፡፡ "በሙስና ተንሰራፍቷል ..."ተብሎ መንግሥት እንዲወገድ ተደረገ፡፡ ታዋቂው አፍሪካዊ ጋዜጠኛ ባፉር አንኮ ሃማ ድርጊቱን ማመን ልክ "አሳማ መብረር ይችላል..."እንደ ማለት ይሆናል በማለት ለኒጀር መንግሥት መውደቅ በምዕራባውያኑ የተሰጠውን ምክንያት ያጣጥለዋል፡፡

ኒጀር የምታወጣውን የዩራኒም ማዕድን የምትሸጠው ለፈረንሣይ ነው፡፡ አገሪቱ ይኼንን ውድ የዓለማችን ማዕድን ሀብት ባለቤት ብትሆንም፣ በአፍሪካ እጅግ በድህነት ከሚታወቁ አገሮች አንዷ ከመሆን አልታደጋትም፡፡ የተትረፈረፈ ሀብት ቢኖራትም ኒጀር ዛሬም ከድሆች ተርታ ተሠልፋ እናገኛታለን፡፡

የጋምቢያ ፕሬዚዳንት የነበሩት ያያ ጃሜ፣ "ለእኔ አገሮች ሦስት በመቶ ወይም አምስት በመቶ ከማዕድን ሀብታቸው ለማግኘት መደራደር እንደ ስድብ እቆጥረዋለሁ፤ "በማለት የአፍሪካ አገሮች ከተፍጥሮ ሀብቶቻቸው ብዝበዛ እንዲቆም መጠየቃቸውን ይናገሩ ነበር፡፡ ‹‹ለኳታር ኦሚር ሁልጊዜ የምነግራቸው ነገር ቢኖር ከእሳቸው አገር ጋር አገሬ ጋምቢያ መፎካከር ትችላለች፡፡ ሁለቱም አገሮች ትንንሽ ናቸው፡፡ የኳታር ሕዝብ ኑሮ በእጅጉ የተሻሻለው ከጋምቢያ የበለጠ የተትረፈረፈ ጋዝ ክምችት በአገሪቱ መኖሩን አላውቅም..."በማለት ከአፍሪካ አገሮች ጋር ሁኔታውን አነፃፅረውት ነበር፡፡

"በተቃራኒው እኛ የአፍሪካ መሪዎች አምላክ የሰጠንን የተፈጥሮ ሀብቶች ተገቢውን ገቢ የማግኘት መብታችንን ተነፍገን፣ የተፈጥሮ ሀብቶቻችንን   ለሕዝቦቻችን ጥቅምና ኑሮ መሻሻል እንዳንጠቀም በሚያሳፍሩ ድርድሮች ተተብትበናል፡፡ ችግሩ ይኼ ነው፡፡ ምክንያቱም መጥተው አምስት በመቶ  እንደሚሰጡና ፕሬዚዳንቱ ምን ያህል ማግኘት እንደሚፈልግ ቢነግሩን ....እንስማማለን! የነዳጅ ሀብቶቹ ግን የፕሬዚዳንቱ ሳይሆን የጋምቢያ ሕዝብ ሀብቶች ናቸው፡፡ ስለዚህ በጋምቢያ ሕዝብ ስም አምስት በመቶ ወይም አሥር በመቶ አልቀበልም፡፡ ይኼንን የማይረባ መቶኛ ምጣኔ ብቀበል ለጋምቢያ ሕዝብ ምን እነግረዋለሁ?  እኛ አሥር በመቶ እናገኛለን፣ እነሱ ደግሞ 90 በመቶ ያገኛሉ ማለት ነው ብለው፣ በአፍሪካ የተፈጥሮ ሀብቶች ለአኅጉሪቱ ሕዝቦች ጥቅም እየዋሉ አለመሆናቸውን ሞግተው ነበር፡፡

ጃሜ የአምስት በመቶ ምጣኔው ፍትሐዊ አለመሆኑን ሲሞግቱ እ.ኤ.አ. በ2014 በነበረው መረጃ መሠረት፣ "....ዛሬ ነዳጅን ብንወስድ የአንድ በርሜል ነዳጅ ዋጋ 100 ዶላር ነው እንበል፡፡ ጋምቢያ አንድ ቢሊዮን በርሜል ነዳጅ ዘይት በዓመት ታመርታለች፡፡ አንድ ቢሊዮን በርሜልን በ100 ዶላር ብናባዛ የሚሰጠን ቁጥር 100 ቢሊዮን ዶላር ይሆናል፡፡ ድሮም ሆነ ዛሬ የነዳጅ ጉርጓድ ለመቆፈርና ሁሉም የካፒታል ወጪ ቢደመር ከሁለት ቢሊዮን ዶላር ያነሰ ወጪ ነው፡፡ በዘርፉ የተሰማራ ኩባንያ የወጣው  ሁለት ቢሊዮን ዶላር የካፒታል ወጪ  ለማካካስ አምስት ዓመት ወይም ስድስት ዓመት በቂ ቢሆንም፡፡ ታዲያ አሥር በመቶ ወይም አምስት በመቶ ምጣኔ ለበርካታ ዓመታት እንድንቀበል ይደረጋል?"ብለው ይጠይቃሉ፡፡ "ከሁለት ቢሊዮን ዶላር ወጪ በታች የሆነ የካፒታል ወጪ ለመሸፈን ሲባል አምስት በመቶ የሮያሊቲ ክፍያ በመቀበል  ለ35 ዓመታት አገሪቱ መዝለቅ የለባትም፤›› ይሉናል፡፡ ይህንን ያሉት ከሥልጣን ከመወገዳቸው በፊት መሆኑን ልብ ይሏል፡፡

እንዳለመታደል ሆኖ በየችኞቹ የአፍሪካ አገሮች ባልተጻፈ ሕግ፣ የተፈጥሮ ሀብቶቻቸው በውጭ ኩባንያዎች በተጠቀሰው መንገድ በልዩ ልዩ መነሻዎች በሚረቀቁ ብቃት የሌላቸው የማዕድን ሕጎች ሲበዘበዙ ይስተዋላል፡፡ በግዴለሽነት፣ በስንፍና፣ በአቅም ማነስ፣ በሙስና፣ በሕገወጥ ቡድኖች በመዘወር ወይም በተለያዩ ኩባንያዎች ተፅዕኖ በእነዚህ የማዕድን ሕጎች አማካይነት፣ የአፍሪካ አገሮች የማዕድን ሀብቶች ለውጭ ኩባንያዎች ማስረከብ የተለመደ አሠራር ሆኗል፡፡

ፓን አፍሪካዊነትን የሚያቀነቅነው ታዋቂው ኒው አፍሪካ መጽሔት እ.ኤ.አ. በፌቡሩዋሪ 2004 ዕትሙ፣ "Solving The Great Conundrum...How African Can Own Its Natural Resources"በሚል ርዕስ በሰጠው የሽፋን ዘገባው  የአፍሪካ ታላቁ እንቆቅልሽ፣ አፍሪካውያን እንዴት የተፈጥሮ ሀብቶቻቸው ባለቤት ይሆናሉ ብሎ ይሞግታል፡፡

እ.ኤ.አ. በ2003 የጋና ፓርላማ የማዕድን ሕግን ለማሻሽል ሲሞክር አስደንጋጭ ነገር ገጠመው፡፡ የማዕድን አምራች ኩባንያዎች ከዘርፉ የሚያገኙትን ገቢ በውጭ አገር በሚከፍቱት ባንክ እንዲቀመጥ መፍቀዱን ጨምሮ፣ የአገሪቱን የማዕድን ሀብቶች ባለሀብቶቹ እንደፈለጉ የሚያባክኑበት ክፍተቶች ያሉበትን ሕግ ማፅደቁ ከፍተኛ ክርክር አስነስቷል፡፡

የጋና  ፓርላማ የመንግሥት ፋይናንስ ኮሚቴ በድንገት አገሪቱ ባለፉት መንግሥታትም ሆነ እስከ እ.ኤ.አ. 2003 ድረስ ጋና የማዕድን ሀብቶቿን  በተመለከተ ያወጣቻቸውን ሕጎችና የተፈራረመቻቸውን ስምምነቶች ሲፈትሽ በደረሰበት ግኝት ተደናግጧል፡፡ በጋና የቀድሞ መንግሥታት የተፈረሙ የማዕድናት ሕጎችን በተመለከተ አገሪቱ የተፈራረመቻቸው አብዛኞቹ ስምምነቶች ለውጭ የማዕድን አውጭ ኩባንያዎች እጅግ ያጋደሉ መሆናቸው ተደረሰበት፡፡ በጋና ፕሬዚዳንት  የሕፈት ቤት  የፖሊሲ ግምገማና ክትትል ኃላፊ ዶ/ር ቶኒ አይዶ፣ እንዲህ ካለ ዘረፋ የጋና የተፈጥሮ ሀብቶች ከመሬት ሳይወጡ ቢቀሩ እንደሚሻል ተናግረው ነበር፡፡ ወደፊት አንድ ቀን አገር በቀል (ባህላዊ) ማዕድን አውጪዎች ምንም ያህል ኋላ ቀር ዘዴ ቢጠቀሙም፣ አቅማቸውን በማሳደግ ለአገር ጥቅም እንጂ ለውጭ ኩባንያዎች እንዳይውሉ ማድረግ እንደሚመርጡ  ተናግረው ነበር፡፡ በተነፃፃሪ ጋና ከአፍሪካ አገሮች የማዕድን ሀብቷን ለሕዝቧ ጥቅም በማዋል ረገድ የተሻለች እንደሆነች ይነገራል፡፡

የጋና የመሬትና ተፈጥሮ ሀብት ሚኒስቴር የጋናን የማዕድን ዘርፍ  የሚከታተልና በማዕድን ፍለጋና ማውጣት ለሚሰማሩ  ፈቃድ የመስጠት ሥልጣን አለው፡፡ በሚኒስቴሩ ሥር የማዕድን ኮሚሽን የተዋቀረ ሲሆን፣ የማዕድን ሕግን የሚከታተልና የማዕድን ፖሊሲ አፈጻጸም የሚከታተል ነው፡፡ ኮሚሽኑ የማዕድን ልማትን ለማስፋፋት መንግሥትን በዘርፉ የሚያማክር እንደሆነ ይነገራል፡፡ የጋና የከበሩ ማዕድናት ገበያ ኮርፖሬሽን መንግሥታዊ ድርጅት ሲሆን፣ አነስተኛና ጥቃቅን  እንዲሁም ባህላዊ የማዕድን አውጪዎችን በተለይ የወርቅና የአልማዝ ንግድ ልማት ላይ የሚሠራ ተቋም ነው፡፡ ኮርፖሬሽኑ የማዕድን ውጤቶችን በቀጥታ ወይም ፈቃድ ከተሰጣቸው አካላት የመግዛት ኃላፊነትም ተጥሎበታል፡፡ የማዕድን መምርያው የማዕድን የሥራ ደኅንነትና ጥንቃቄ ይከታተላል፡፡ የጋና ጂኦሎጂ ሰርቬይ መምርያ ጂኦሎጂካል ጥናቶችን በማከናወን ዘርፉን ያግዛል፡፡ የጋና ብሔራዊ ፔትሮሊየም ኮርፖሬሽን ደግሞ መንግሥታዊ ድርጅት ሲሆን፣ ለአገሪቱ የነዳጅ ፍለጋና ምርት ኃላፊነት የተሰጠው ተቋም ነው፡፡

የጋና የማዕድን ንግድ ምክር ቤት በማዕድን የተሰማሩ የግል ኩባንያዎች  ማኅበር ሲሆን፣ በዘርፉ ጤናማ ንግድ እንዲኖር የበኩሉን ሚና ይጫወታል፡፡ ምክር ቤቱ ለኅብረተሰቡ ስለጋና የማዕድን ዘርፍ መረጃ በመስጠትና ከዘርፉ የሠራተኞች ማኅበራት ጋር በመደራደር ይሠራል፡፡ በማዕድን ዙርያ የሚደርሱ አደጋዎች ሪፖርት የሚቀርቡት ለጋና ማዕድን ንግድ ምክር ቤት ሲሆን፣ ምክር ቤቱ ስለማዕድን ሕግ መረጃ መስጠትና ከዘርፉ ሠራተኛ ማኅበራት ጋር አባል ኩባንያዎቹን ወክሎ ይደራደራል፡፡ የጋና ማዕድን ተመጣጣኝ የሮያሊቲ ምጣኔና 45 በመቶ የቀረጥ ሥርዓት ደንግጓል (በአገራችን ሕግ ግን 35 በመቶ መሆኑን ልብ ይበሉ)፡፡ 

የኢትዮጵያን ማዕድን በጨረፍታ

ፖታሽ በማዕድን መልክ የሚመረት የሟሟ ፖታሽየም የተሰኘ ንጥረ ነገር የያዘ ጨው መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ ለማዳበሪያ በዓለም ዙሪያ   በዓመት 30 ሚሊዮን ቶን ይመረታል፡፡ ፖታሽ ጨርቃ ጨርቅ ለማንጣት፣ ለመስታወት ለሳሙና ማምረት፣ ማዳበሪያን ጨምሮ ብዙ ጥቅሞች እንዳሉት ይታወቃል፡፡ ኢትዮጵያ በዓለማችን  በፖታሽ  ክምችቷ  ቀዳሚዋ መሆኗና ከ14ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ  መመረት እንደ ጀመረ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡  በአፋር ክልል በዳሎል እ.ኤ.አ. ከ1900 ዓ.ም. የመጀመርያው የጣሊያን ኩባንያ  የፖታሽ  ማዕድን ያመርት ነበር፡፡ በኋላ በ1960ዎቹ የዩናይትድ ስቴትስ ፒርሰን  ኩባንያ በዳሎል ከተማ የፖታሽ ፋብሪካ በማቋቋም ያመርትበት የነበሩት ቁሳቁሶችና መኪናዎች የጨው ዓምድ ውጧቸው ተቀብረው ይታያሉ፡፡ በአንድ ወቅት ከዳሎል እስከ አስመራ በተዘረጋው ባቡር ሐዲድ የፖታሽ ምርትን ኢትዮጵያ እስከ ህንድና ሌሎች የዓለም ገበያ ታቀርብ ነበር፡፡

ዳሎል በምድራችን በጣም ሞቃታማ ከሚባሉ ቦታዎች አንዱ  ነው፡፡ መንገድ ባለመኖሩ የጨው ምርቱ በግመል ይጓጓዝ ነበር፡፡ በኤርትራ ከሚገኘው የመርሳ ወደብ እስከ ዳሎል ድረስ 28 ኪሎ ሜትር የሚዘልቅ የባቡር መስመር ተሠርቶ   እ.ኤ.አ. ኤፕሪል 1918 ተጠናቀቀ፡፡ የባቡር መንገዱ ከተሠራ በኋላ 50,000  ሜትሪክ ቶን ፖታሽ ይመረት የነበረ ሲሆን፣ ከአንደኛው የዓለም ጦርነት በኋላ ማቋረጡን መረጃዎች ያስረዳሉ፡፡ ለዚህም ምክንያቱ በጀርመን፣ በዩናይትድ ስቴትስና የቀድሞዋ ሶቪየት ኅብረት በብዛት መመረት መጀመሩ ይጠቀሳል፡፡ የፖታሽ ምርት  እ.ኤ.አ. ከ1920 እስከ 1929 በጣሊያን ኩባንያ ማምረቱን ጀምሮ 25,000 ቶን  በማምረት  ወደ ውጭ የተላከ ሲሆን፣ በዳሎል  አስመራ  ኩባንያ  እ.ኤ.አ. ከ1951 እስከ 1953 የተወሰኑ ፖታሽ ቶን ወደ ህንድ መላክ ችሎ ነበር፡፡ እ.ኤ.አ. በ1960ዎች  የዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ ፒርሰን ኩባንያ ጆሎጂካል ሰርቬይ አካሂዶ ወደ ማምረት ገብቶ ነበር፡፡ እ.ኤ.አ. በ1965 ብቻ 10,000 ጉድጓዶችን  በ65 ቦታዎች  በዳሎል አካባቢዎች ቆፍሮ ፖታሽን ሲያመርት ከቆየ በኃላ፣ ኩባንያው ባልታወቀ ምክንያት ሥራውን እርግፍ አድርጎ ትቶ ወጣ፡፡

ታዋቂው የማዳበሪያ አምራች ያራ ኢንተርናሽናል እ.ኤ.አ. በ2018 ፖታሽ ለማምረት ዕቅድ እንዳለውና የተለያዩ ኩባንያዎች የናይጄሪያዊው ቱጃር አሊኮ ዳንጎቴን ጨምሮ፣ በፖታሽ ምርት ዙሪያ ለሚመለከተው መንግሥት አካል ፕሮጀክት ማስገባታቸውን የእንግሊዝኛ ጋዜጦች  ዘግበዋል፡፡ (በነገራችን ላይ የማዕድን ዜናዎች  የሚበዙት በአገራችን በእንግሊዝኛ በሚታተሙ ጋዜጦች ነው፡፡ ምክንያቱም ኩባንያዎቹ መንግሥትንም ሆነ የፋይናንስ ተቋማትን በተዘዋዋሪ ተፅዕኖ ለማሳረፍ የሚፈልጉበት አዝማሚያ መረዳት ይቻላል)፡፡

ዳሎልን ጨምሮ የአገራችንን ልዩ ልዩ የማዕድንና የኢነርጂ መገኛ ሥፍራዎችን፣ ካርታዎችንና ጥናቶችን የሚያውቁ ዘርፉን የሚያሽከረክሩ ተፅዕኖ ፈጣሪ  ሰዎች  አሉ፡፡ በፖታሽ ዘርፍም መሰል ነገር እታየ ይመስላል፡፡ ወደ ኋላ ሄዳችሁ የማዕድን ዘርፉን ዘገባዎች ብትፈትሹ ልታገኙት ትችላላችሁ፡፡

የማዕድን ፈቃድ በማውጣት ከተወሰነ ጊዜ በኋላ በማዕድን ሕጉ በተቀመጠ አንቀጽ በመጠቀም ድርሻቸውን እያስተላለፉ ቀስ በቀስ እየወጡ፣ ኩባንያውን  በሕጋዊ መንገድ በውጭ ዜጎች እጅ በተዘዋዋሪ እንዲወድቅ ማድረግ የተለመደ አሠራር እየሆነ መጥቷል፡፡ ኢትዮጵያ በፖታሽ ምርት ቀዳሚ ብትሆንም፣ ኩባንያዎቹ  በፍጥነት ወደ ሥራ ገብተው አገራችን ከዘርፉ ተጠቃሚ  እየሆነች ነው ወይ? ብሎ መጠየቅ ያስፈልጋል፡፡ ጣሂር ሻህ “King Solomon’s Mines” መጽሐፉ (የኢትዮጵያ የወርቅ ሚስጥር ከንግሥት ሣባ እስከ 21ኛው ክፍለ ዘመን በሚል ርዕስ  የደራሲ ጣሂር ሻህ  ጋዜጠኛ ብሩክ መኰንን ተክለየስና  አቶ እንቆጳዚዮን ሀብታሙ ጃካሞ  ተርጉመውት ነበር)፡፡ ሃይተር በዚህ መጽሐፉ የኢትዮጵያን የወርቅ ማዕድን ሚስጥር፣ "….የማነበው መጽሐፍ የፊት ሽፋን ከላይኛው ከንፈሩ በላይ ያለውን ጺሙን ያሳደገው ኸይተር ሄልሜት ጭንቅላቱ ላይ አድርጎ የሳፋሪ ሸሚዝና ቁምጣ ለብሶ፣ እንዲሁም ረዥም የሲጋራ መሰኪያ ቀፎ ከንፈሩ መሀል ሰክቶ ይታያል፡፡ ከጀርባው ትልቅ የተዠጎረጎረ የነብር ቆዳ ተሰቅሏል፡፡ የመጽሐፉን የመጀመርያው ምዕራፍ ያለማቋረጥ አንብቤ ጨረስኩ፤"ይላል፡፡

ጣሂር ስለ ፍራንክ ኸይተር ሲናገር  እ.ኤ.አ. በ1902 በዌልስ የጠረፍ ከተማ ውስጥ ከአንድ በግብርና ከሚተዳደር ቤተሰብ ተወለደ መሆኑን፣  ከሕፃንነቱ ጀምሮ ታላቅ አዳኝ የመሆንና በጭለማው አኅጉር ጉዞ የማድረግ ህልም ነበረው፡፡ ህልሙን ዕውን ማደረግ የሚችልበት የመጀመርያው አጋጣሚ የተፈጠረው ለንደን ውስጥ በአንድ የዱር እንሰሳት ማሳያ ቦታ፣ የእንሰሳትን ሙሉ አካል የማድረቅ ሥራ ለመሥራት መቀጠሩን የጻፈው ጣሂር፣ በሚሠራው ሥራ ኩራት ይሰማው ነበር ይለናል፡፡ "...በአፍሪካ አንድ ያልተለመደ ጉዞውን የሚያደርገው ወደ አቢሲኒያ ሲሆን፣ የጉዞው  ዓላማ ለእንሰሳት ማሳያ ድርጅቱ መቶ ዝንጀሮዎችን ይዞ ለመምጣት ነበር፡፡ እ.ኤ.አ. በ1924 ኸይተር በባቡር ተሳፍሮ ወደ ማርሴይ ከተጓዘ በኃላ ከማርሴይ በሞተር ጀልባ ጅቡቲ ገባ፡፡ ከጂቡቲ በባቡር ወደ ድሬዳዋ ተጓዘ፡፡ በዚያን ጊዜ አሁን ጭር ያለው የባቡር መተላለፊያ ከተማ ግሪኮችና አርመኖች ማንኛውንም የንግድ ሥራ የሚያካሂዱበት፣ ከደንከል በረሃ የሚመጡ ጦረኞች ጋሻቸውን ከፍ አድርገው ይዘውና አንገታቸው ላይ የወንድ ብልት አንጠልጥለው የሚንጎራደዱበትና ወከባ የበዛበት ነበር፡፡ ኸይተር ከሐረር ከተማ ወጣ ባለ ቦታ ድንኳን ተክላ የተቀመጠች ብሩህ አዕምሮ ያላትና በአካባቢው ታዋቂ ከሆነችው ሮዚታ ፎርበት ከምትባል ተጓዥ ሴት ጋር ተዋውቆ ነበር፡፡

‹‹….ኸይተር በሚያስገርም ሁኔታ መቶ ዝንጀሮዎች ይዞ ወደ አገሩ በመመለስ ተልዕኮውን አጠናቀቀ፡፡ ሆኖም እንስሳቱን ይዞ ሲጓዝ ቅዱሶቹን እንስሳት ሰርቀሀል በማለት አንድ መንኩሴ ረግመውት ነበር፡፡ ኸይተር የመነኩሴውን እርግማን ከምንም ባለመቁጠር ዝንጀሮዎችን በመርከብ ጭኖ ወደ ለንደን ወሰዳቸው፡፡ ዝንጀሮዎቹን መርከብ ላይ የጫኑት ምንም ቦታ ክፍተት በሌለው ሳጥን ውስጥ ታሽጎባቸው ነበር፡፡ ነገር ግን ሌሊት ላይ የባህር ማዕበል ተነስቶ መርከቡ ላይ የተጫኑት ሳጥኖች ተሰባበሩ፡፡ ሳጥኖቹ ውስጥ የነበሩ ዝንጀሮዎች ረብሻ ሲፈጥሩ የመነኩሴው እርግማን ውጤት ታየ፡፡ በቀጣዮቹ ዓመታት ኸይተር ወደ ኢትዮጵያ በተደጋጋሚ መጥቷል፡፡ በዚች አገር ተለክፎ ነበር፡፡ በኑሮው የሚያስፈልገውን ገንዘብ ለማግኘት ወደ ሩቅ ቦታዎች ሲጓዝ ብዙ መከራ ድርሶበታል፡፡ አይጥና ቢራቢቢሮ አዳኝ ሆኖ ሲሠራ ቢቆይም ስሙ በስፋት የሚነሳው ግን በወርቅ አሳሽነት ሥራው ነው፤"ብሎ በመጽሐፉ ያትታል፡፡

እንደ ጣሂር መጽሐፍ እ.ኤ.አ. በ1920ዎቹ ኢትዮጵያ ውስጥ ውዥንብር ነግሦ ነበር፡፡ ምንም እንኳን  ዳግማዊ ምንሊክ ግዛታቸውን ለውጭው ዓለም ክፍት በማድረግ ሥልጣኔ ለማስፋፋት ሞክረው የነበረ ቢሆንም፣ አብዛኛው የአገሪቱ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ በገባር የአገዛዝ ሥርዓት ቁጥጥር ሥር ነበር፡፡ በጣት የሚቆጠሩ አውሮፓውያን የአገሪቱን ኋላ ቀርነት በመገንዘብ የቅንጦት ዕቃዎች የመግዛት አቅም ላላቸው ሰዎች በመሸጥ ሀብት ሲያካብቱ፣ ሌሎች አውሮፓውያን ደግሞ የከበሩ ማዕድናት ያሉበትን ቦታ ከመንግሥት በኪራይ እየወሰዱ ወርቅ በማውጣት ሥራ ተሰማርተው ነበር፡፡ ፍራንክ ኸይተር ወንዞችን በመገደብና ያልተነካ የወርቅ ክምችት የሚገኝባቸውን በምዕራብ ኢትዮጵያ አካባቢ ያሉ ቦታዎችን ብቻውን በመቆፈር ብዙ ዓመታት አሳልፏል፡፡ የአካባቢው ሰዎች "አባ ኩታ" (የእብደት አባት)  በሚል ቅጽል ስም ነበር የሚጠሩት፡፡ የአካባቢው ሰዎች ለኸይተር ይኼን ቅጽል ስም የሰጡበት ምክንያት እንደሱ ያለ የማይታክት ወርቅ አሳሽ አይተው ስለማያውቁ ነበር፡፡

ወርቅ በኢትዮጵያ ውስጥ ለብዙ ዓመታት ከመሬት እየተቆፈረ ስለመውጣቱና  በአካባቢው ወርቅ የማውጣት ሥራ ስለመካሄዱ ኸይተር እርግጠኛ ነበር፡፡ በኸይተር አመለካከት ኢትዮጵያ ጠቢቡን ንጉሥ በወርቅ ለማንቆጥቆጥ ወደ እየሩሳሌም ጉዞ ያደረገችው የንግሥት ሳባ ግዛት ነበረች፡፡ በሰሜን ተራሮች ውስጥ ዱካቸው የጠፋ በአንድ ወቅት በከፍተኛ ደረጃ ወርቅ ይወጣባቸው የነበሩ የዋሻ ሰንሰለቶች እንደነበሩ ኸይተር ያምናል፡፡ በዋሻዎች መግቢያ ላይ በተሠሩ ገዳማት ውስጥ የሚኖሩ መነኩሳት የውጭ ዜጎች በወርቅ ወደ ተሞሉት ዋሻዎች እንዳይገቡ እንደሚከላከሉና "የታላቋን …ንግሥት"መመለስ እንደሚጠብቁ ሰምቷል፡፡ በወርቅ ፍለጋ ብቻውን ሲባዝን ቆይቶ ቱሉ ወለል ከሚባል ተራራ ላይ መግቢያቸው በጥርብ ድንጋዮች የተዘጋ ወደ ወርቅ ማውጫ ጉድጓዶች የሚያስገቡ ዋሻዎችን አግኝቶ ነበር ፡፡

በዋሻው ውስጥ ያሉ አውሬዎችን እንዳይረብሽ በመፍራት ኸይተር በአንደኛው መግቢያ በቀስታ ወደ ውስጥ ገባ፡፡ ከዚያም "አንድ ጥልቅ ጉድጓድ ውስጥ የተደበቀ ሀብት አገኘሁ፤"ይላል፡፡ ሆኖም ወርቅና ሌሎች የከበሩ ማዕድናት ማውጣት ከመጀመሩ በፊት… በዋሻው ውስጥ በከፍተኛ ፍጥነት የሚፈስ ደራሽ ጎርፍ ስለመጣበት ከዋሻው ለመውጣት ተገደደ፡፡ አዳዲስ ቁሳቁሶች ይዞ ወደ ዋሻው ተመልሶ ሲመጣ የዋሻዎቹን መግቢያ ለማግኘት የተለያዩ ሙከራዎችን ቢያደርግም አልተሳካለትም፡፡

“Search of King Solomon’s Mine” በሚል ርዕስ በተጻፈው የጣሂር ሻህ መጽሐፍ፣ ‹‹ተጨማሪ መረጃ ሊሰጠው የሚችል አንድ ሰው ኢትዮጵያ ውስጥ እንዳለ አውቅ ነበር ... አዲስ አበባ ስንደርስ ስለ ፍረንክ ኸይተርና ስለ ቱሉ ወለል የበለጠ ማወቅ እንዳለብኝ ወሰንኩ፡፡ ዶ/ር ሪቻርድ ፓንክረስት አብዛኛውን ጊዜያቸውን ያሳለፉት ኢትዮጵያ ውስጥ ነው፡፡ ዶ/ር ፓንክረስት በኢትዮጵያ ኅብረተሰብና ታሪክ ዙሪያ ጥልቅ የምርምር በማካሄድ ይታወቃሉ፤›› በማለት፣ ስለቱሉ ወለል ወይም ፍረንክ ኸይተር ሰምተው ያውቁ እንደሆነ ፕሮፌሰር ሪቻርድ ፓንክረስትን ይጠይቃቸዋል፡፡

".....እንደ ማስታውሰው ከሆነ ቱሉ ወለል ከቤንሻንጉል ብዙም የማይርቅ ቦታ ነው፡፡ አካባቢው ጥራት ያለው ወርቅ የሚገኝበት መሆኑ በታሪክ ይታወቃል፡፡ ምኒልክ ቦታውን በ1886 ዓ.ም. የተቆጣጠሩት፣ በዚያ አካባቢ ያለውን የማዕድን ሀብት ለመጠቀም አስበው ነበር፡፡ የማዕድን ሀብቱን እንዲያወጣም ኢልግ ለሚባል ሰው ፈቃድ ሰጥተው ነበር፡፡ ሰውዬው ነጆ ውስጥ የጥንት ግብፃውያን ወርቅ ያወጡበት እንደነበር የገመተውን ቦታ አገኘ፤"ይላል፡፡ የዚያን ዕለት ፓንክረስት ስለጠቀሱለት ሰዎች የተጻፈ ነገር እንዳለ ለማረጋገጥ ያመጣቸውን መጽሐፎች አንድ ባንድ አሰሳቸው፡፡ ግሪካዊ የሥነ ምድር ባለሙያ አጋታኪደስ ከክርስቶስ ልደት በፊት በ140 ዓ.ም. የጻፈው መጽሐፍ የጦር እስረኞች ወርቅ በቁፋሮ በማውጣት አገልግሎት እንዲሰጡ ስለሚደረግበት ሁኔታ ይናገራል፡፡ "ብዛት ያላቸው የጦር እስረኞች በብረት ሰንሰለት ታስረው ቀንና ሌሊት እንዲሠሩ ይገደዳሉ፡፡ እስረኞቹ የማያውቁትን ቋንቋ በሚያወሩ ይጠበቁ ስለነበር የማምለጥ ተስፋ አልነበራቸውም፤"በማለት ጽፏል፡፡

አጋታኪድስ ከሞተ ከሰባት ምዕተ ዓመታት በኋላ ኮስሞስ የሚባል የግሪክ ቋንቋ የሚናገር ነጋዴ በጻፈው መጽሐፍ ውስጥ፣ በኢትዮጵያ ምዕራባዊ ጠረፍ አካባቢ ዕጣንና ወርቅ የሚገኝበት ቦታ እንዳለ ተጠቅሷል፡፡ ኮስሞስ በ524 ዓ.ም.  በወቅቱ የአክሱም ግዛት ከነበረችው የአዱሊስ ወደብ ሲደርስ በምዕራብ ኢትዮጵያ የሚኖሩ የአገው ጎሳዎች ወርቅ ማውጣት ሥራ እንደሚሠሩ፣ የሥነ ማኅበረሰብ ጥናት ባለሙያዎች አዝጋሚ የንግድ ሥርዓት በሚገልጹት ዕቃን በመለዋወጥ ላይ የተመሠረተ ንግድ ያካሂዱ እንደነበር መስማቱን ተናግሯል፡፡ በየዓመቱ የአክሱም ንጉሥ ከአገዎች ጋር የንግድ ልውውጥ እንዲያደርጉ ወኪሎችን ይልክ ነበር፡፡ ወኪሎች በብዙ ጠባቂዎች ታጅበው ከብት፣ ብረት፣ ጨውና ሌሎች ሸቀጦችን በማቅረብ በልዋጩ ወርቅ ይገዛሉ፡፡ የንግድ ልውውጥ በሚደረግበት ቦታ ድንኳን በመትከል ዙሪያውን በእሾሃማ እንጨት ያጥራሉ፡፡ የበሬ ሥጋና ሌሎች ሸቀጦች አጥሩ ላይ ይሰቅላሉ፡፡ ምሽት ላይ አገዎች የሚፈልጉትን ዕቃ በመውሰድ በምትኩ የወርቅ እንክብሎች ያስቀምጣሉ፡፡

ኮስሞስ አካባቢውን ከጎበኘ ከአንድ ሺሕ ዓመታት በኋላ ፖርቹጋላዊ ተጓዥና ፓትሪያሪክ ሁዋን ደ ቤርሙዴዝ የዓባይ ወንዝን ተከትሎ በምዕራብ ኢትዮጵያ ጉዞ አድርጓል፡፡ "የሀብት ጌታ"በሚል ቅጽል ስም የሚጠራው ቤርሙዴዝ በስሙ የተሰየመችው በካሪቢያን አካባቢ ያለችውን የቤርሙዳ ደሴት በማግኘቱ ዕውቅና ያገኘ ሰው ነው፡፡ ቤርሙዳ ደሴትን ያገኛት ከቨርጂኒያ ተነስቶ የባህር ጉዞ ሲያደርግ  መርከቡ ስለተሰበረችበት ማረፊያ መሬት ሲፈልግ ነው፡፡ ቤርሙዴዝ ኢትዮጵያን በተመለከተ የተራቆተ፣ ነገር ግን ሁለት እጁ ወርቅና ሲሶው ደግሞ ቀይ አፈር ያለበት ምድር መሆኑን መናገሩን ጣሂር በመጽሐፉ አስፍሯል፡፡ ይኼ የጣሂር ሻህ መጽሐፍ ስለአገራችን የወርቅና ማዕድን ሀብቶቻችን የሚነግረን ብዙ ነው፡፡ ከዚህ ሌላ የተለያዩ የኅትመት ወጤቶች የሚሰጡን መረጃዎች አሉ፡፡

እ.ኤ.አ. በጁላይ 1998 በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የታሪክ ትምህርት ክፍል ውስጥ አንድ በየአካባቢው ታሪክ መረጃዎችንና ምንጮችን ማሰባሰብና ጠብቆ ለማቆየት የሚያስችል ፕሮጀክት ተጀምሮ ነበር፡፡ ለዚህ ፕሮጀክት የሚያስፈልገውን ገንዘብ በዕርዳታ የሰጠው የኢጣሊያ የትብብር ፕሮግራም ነው፡፡ በዚህ ፕሮጀክት አማካይነት የተሠራ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲና በአፍሪካ የዓረብ አገሮች ጥናትና ምርምር ክፍል ኔፕልስ ኦሪያንታል ምርምር ክፍል ትብብር "የወለጋ የታሪክ ሰነዶች እ.ኤ.አ. ከ1880ዎቹ እስከ 1920ዎቹ "የሚል ርዕስ ያለው መጽሐፍ በአሌክሳንድሮ ትሪዮልዚና ተሰማ ታዓ አዘጋጅነት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬስ በ1997 ዓ.ም. ታትሞ ለንባብ በቅቷል፡፡ በዘመኑ የነበሩ ነገሥታት ከአካባቢው አስተዳዳሪዎች ጋር ያካሄዱትን የደብዳቤ ልውውጦች የያዘ ታሪካዊ ሰነድ ብቻ ሳይሆን፣ የወርቅ ማዕድን በውጭ ኃይሎች እንዴት ይመዘበር እንደነበር  ይጠቁማል፡፡ 

ጃንሆይ

....እነዚህ ነጆ ያሉት ፈረንጆች ዘንድሮ በሰኔ ጀመሩ፡፡ እኔ ካዲስ አበባ ሳለሁ እስከ ዛሬ ድረስ ከዚህ ከነጆ ያለውን አገር ዙሪያ ገባውን ሁሉ እየዞሩ በተራራ በተራራው በየጎብታው ሁሉ ባንዲራ ይተክላሉ፡፡ እኔ ደሞ ይኸ ባንዲራ መትከል የወርቅ ሥራ አይደለም ምንድን ነው ነገሩ ብዬ ብጠይቃቸው፣ ያገሩን እሩቅነትና ቅርብነቱን ለማወቅ ነው አሉኝ፡፡ ቅርብነቱና እርቀቱ በባንዲራ አይታወቅም ነበር፡፡ ሐምሌ 28 ቀን 1898 ዓ.ም. (የወለጋ የታሪክ ሰነዶች እ.ኤ.አ. ከ1880ዎቹ እስከ 1920ዎቹ)                                                                           ጃንሆይ

......ከነጆ ካሉት ከፈረንጆች ጋር ወርቁን ሥራ ተጠባበቁ ያሉኝን የዕለት የለቱን የአንዳንድ ቀኑን አሳዩኝ ብላቸው፣ ከመኪናው ባንድ ወር የተሠራውን አንድ ቀን ይወጣል እንጂ የዕለት የዕለቱን አይወጣም አሉኝ፡፡ ባንድ ወር ተሠራውን ከመኪናው አውጥተው ከነባዚቃው ብንመዝነው ሰባ ስድስት ወቄት ወርቅ ሆነ፡፡ ደግሞም ከነባዚቃው ማለቴ በጣም ተጠምቆ ዕቃ እንደሚቀባ ሆኖ ነው፡፡ ይኼንንም ከነባዚቃው ሰባ ስድስት ወቄት ሆነ፡፡ ዛሬ ዕለት የወጣውን ዕለቱን ይነጠርና ልየው  ብላቸው ዛሬ አናነጥረውም አይሆንም ይደር አሉኝ፡፡ ወርቁ ከነሱ እጅ አደረ፡፡ አድሮ ከኛ ፊት አነጠሩት፡፡ ቢነጠር 13 ወቄት ከአላድ ሆነ፡፡ ነገር ግን ዕለት የወጣውን የለቱን ብናነጥረው መልካም ነው፡፡ እነሱ እጅ አድሮ በማግስቱ ብናነጥረው ቢሰርቁስ በምን ይታወቃል?

ነሐሴ 28 ቀን 1898 ተጻፈ (የወለጋ የታሪክ ሰነዶች እ.ኤ.አ. ከ1880ዎቹ እስከ 1920ዎቹ) 

የቺካጎ ታይምስ ጋዜጣ እ.ኤ.አ. በ1928  ዘገባው ጣሊያን ኢትዮጵያን ለሁለተኛ ጊዜ የወረረችው በዓድዋ ጦርነት የተከናነበችውን "ውርደት"ለመበቀል እንደሆነ፣ የሚቀርበውን የታሪክ ሀተታ ብቸኛ ምክንያት አለመሆኑን ይጠቅሳል፡፡ እ.ኤ.አ. በ1928 ቺካጎ ሰንደይ ታይምስ ጋዜጣ ይዞ በወጣው ዘገባ በኢትዮጵያ የማዕድን ሀብት መነሻ በጣሊያንና በእንግሊዝን ፉክክር የተነሳ ለሁለተኛ ጊዜ አገሪቱ እንደምትወረር ይጠቁም ነበር፡፡ ጀርመን፣ ፈረንሣይ፣ ጣሊያንና እንግሊዝ የአገሪቱን ሕዝቦች በጎሳ (Ethinic Group) በመከፋፈልና ቁርሾ በመፍጠር የአገሪቱን የተፈጥሮ ሀብቶች ለመጠቀም ያደረጉት ጥረት፣ ዛሬም ለእርስ በእርስ ግጭቶች መንስዔ እንደሆኑ የሚከራከሩ አሉ፡፡ ቺካጎ ሰንደይ ታይምስ እ.ኤ.አ. በ1928 ለንባብ ባበቃው ዘገባው ፍራንክ ኸይተር በጻፈው መጽሐፉ፣ የዓባይ ወንዝ መነሻ በሆነችው ኢትዮጵያ ያለውን ወርቅ ሞሶሎኒ አይቆጣጠረውም፣ ያንን ሀብት የሚያገኝ ቢኖር ታላቋ ብሪታኒያ መሆን አለባት ብሎ መናገሩን ጠቁሞ ነበር፡፡

በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 52 የፌዴራል   የኢኮኖሚ ነክ ዓላማዎች አንቀጽ 89  ንዑስ አንቀጽ 5 "መንግሥት መሬትንና የተፈጥሮ ሀብትን ለሕዝቡ የጋራ ጥቅምና ዕድገት እንዲውሉ የማድረግ ኃላፊነት አለበት፤"በማለት ደንግጓል፡፡ ‹‹ፌዴራል መንግሥት ሥልጣን የመሬት፣ ተፈጥሮ ሀብትና የታሪክ ቅርሶች አጠቃቀምና ጥበቃን በተመለከተ ሕግ ያወጣል፤›› ተብሎም ተቀምጧል፡፡ በአገራችንን በየትኛውም ጥግ የሚገኝ የተፈጥሮ ሀብት የአገሪቱ ሕዝቦች  በመሆኑ፣ ለአገሪቱ ሕዝቦች ኑሮ መሻሻልና ዘላቂ ልማት በሚያረጋግጥ ረገድ  የተፈጥሮ ሀብት አጠቃቀም እንዲኖር የማዕድን ሕጎቻችን በአግባቡ መፈተሽ ይኖርባቸዋል፡፡ አሁን አሁን በአፍሪካ ኅብረት  "African Mining Vision" (የአፍሪካ ማዕድን ራዕይ) የሚል እንቅስቃሴ ተጀምሯል፡፡ የአፍሪካን ማዕድን ሀብቶች ለዘላቂ ልማት ማዋል ስለሚቻልበት ሁኔታ ብርቱ ክርክር ይደረጋል፡፡ የማዕድን ዘርፍን መቆጣጠር የሚችል ጠንካራ ሕግና አሠራር መዘርጋት የሁሉም አገሮች ፈተና እየሆነ መጥቷል፡፡ አገራችንም ይኼንን ዘርፍ በአግባቡ አይኗን ከፍታ መመልከት ካልቻለች የምናጣው ብዙ ነው፡፡

ከአዘጋጁ፡- ጽሑፉ የጸሐፊውን አመለካከት ብቻ የሚያንፀባርቅ ሲሆን፣ ጸሐፊውን በኢሜይል አድራሻቸው eskinder.kebe1996@gmail.comማግኘት ይቻላል፡፡    

 

 

Standard (Image)

‹‹የበአሉ ግርማ ገጸ ባሕርያት››

$
0
0

 

በብሩክ አብዱ

በአሉ ግርማ (1931-1976 ዓ.ም.) ልጅነቱን ያሳለፈው በሱጴ (ኢሉባቦር)፣ ጉርምስናውን ደግሞ በአዲስ አበባ (“ልዕልት ዘነበወርቅ” እና “ጀነራል ዊንጌት” ትምህርት ቤቶች) ነበር። በመቀጠልም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅና በMichigan State University የጋዜጠኝነትና የፖለቲካል ሳይንስ ትምህርቱን ተከታትሏል። የሥራ ዘመኑንም በአብዛኛው ያሳለፈው በማስታወቂያ ሚኒስቴር በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ነበር።

በአሉ ስድስት ተወዳጅ ልቦለድ ሥራዎችን አሳትሟል። እኒህም “ከአድማስ ባሻገር” (1962 ዓ.ም.)፣ “የህሊና ደወል” (1966 ዓ.ም.)፣ “የቀይ ኮከብ ጥሪ” (1972 ዓ.ም.)፣ “ደራሲው” (1972 ዓ.ም.)፣ “ሐዲስ” (1975 ዓ.ም.) እና “ኦሮማይ” (1975 ዓ.ም.) ናቸው። ከኒህም በተጨማሪ በርካታ መጣጥፎችን፣ ቃለ መጠይቆችንና ርእሰ አንቀጾችን ጽፏል።

በዚች ጽሑፍ፣ በአሉ ግርማ “ከአድማስ ባሻገር” መጽሐፉ ላይ የተጠቀመባቸውን አንዳንድ የገጸ ባሕርያት አሳሳል ስልቶች በቅርበት ለማሳየት እሞክራለሁ።

ከአድማስባሻገር

ይህ መጽሐፍ ለመጀመሪያ ጊዜ ለንባብ የበቃው በ1962 ዓ.ም. ነበር። ምንም እንኳን ዳግመኛ እስኪታተም ሁለት ዓመት ቢፈጅበትም በወጣበት ዘመን በሰፊው ተነቧል (ከ1962 - 2004 ዓ.ም. ዘጠኝ ጊዜ ታትሟል)። ከ1980ዎቹ ጀምሮ ደግሞ በሬድዮ ትረካ ቀርቧል።

ከአድማስ ባሻገር” የበዓሉ ግርማ የመጀመሪያ የልብ ወለድ መጽሐፍ ቢሆንም በኩር የፈጠራ ሥራው አልነበረም። ከዚያ በፊት በዓሉ በተለያዩ የተማሪ መጽሔቶች (የጀነራል ዊንጌቱ “Chindit” እና የዩኒቨርስቲ ኮሌጁ “News and Views”) ግጥሞቹን ማቅረብ ለምዶ ነበር። ከፈጠራ ድርሰት ባሻገርም በጋዜጣና መጽሔት አዘጋጅነት (“News and Views”፣ “Addis Reporter”፣ “መነን” እና “አዲስ ዘመን”) የበርካታ ዓመታት ልምድ ነበረው። በኒህም ዓመታት በተቻለው መጠን የአዘጋጅነቱን ሚና በመጠቀም (በተለይ በ”መነን” እና “አዲስ ዘመን”) በርካታ ኪነ ጥበባዊ አምዶችን (ለምሳሌ “አጭር ልብ ወለድ”፣ “ከኪነ ጥበባት አካባቢ”) አስጀምሮ  ነበር።

ስለዚህ ከመጀመሪያው ልብ ወለዱ ኅትመት በፊት በአሉ ቢያንስ ለአሥር ዓመታት ያህል ኪነ ጥበባዊ ጽሑፎችን ሲያነብ፣ ሲጽፍና ሲያዘጋጅ የከረመ ደራሲ ነበር። እናም የበኩር መጽሐፉ እምብዛም የጀማሪ ድርሰት ባይሸጥ ብዙ ሊያስደንቀን አይገባም።

ከአድማስ ባሻገር

ታሪኩ በግርድፉ የሚከተለውን ይመስላል። ዕድሜውን በዘመናዊ ትምህርት ያሳለፈ አንድ ኢትዮጵያዊ ወጣት (አበራ) የምርጫ አጣብቂኝ ውስጥ ገብቷል። በአንድ ወገን፣ ብዙም ስሜት በማይሰጠው ሥራ በመትጋት ንብረትና ልጆች እንዲያፈራ ወንድሙ (‘ጋሽ’ አባተ) ቤተሰባዊ ግዴታውን ያስታውሱታል። በሌላ በኩል ደግሞ፣ “ጥሪውን” በመስማት ሥራውን ለቆ ሙሉ ሕይወቱን በሰዓሊነት እንዲያሳልፍ አብሮ አደጉ (ኃይለማርያም) እና አዲሲቷ ፍቅረኛው (ሉሊት) ይገፋፉታል። አበራ ግን የሚፈልገውን የሚያውቅ አይመስልምና መምረጥ ይቸግረዋል።

የአበራም  ወላዋይነት በራሱ፣ በቤተሰቡ፣ በጓደኛውና በፍቅረኛው ሕይወት ውስጥ የሚያስከትሉትን ለውጦችና መዘዞች ድርሰቱ በጥልቀት ይተርካል። እግረ መንገዱንም፣ ደራሲው የዛሬ 50 ዓመት ግድም በነበረው የአዲስ አበባ ማኅበረሰብ ውስጥ ይፋጩ የነበሩትን “ባህላዊነት” እና “ዘመናዊነት”፣ “ኃላፊነት” እና “ጥሪ”፣ “መተማመን” እና “ቅናት” በገጸ ባሕርያቱ በኩል ያሳየናል።

ይህ ልብ ወለድ ከ50 በላይ ገጸ ባሕርያትን አቅፎ ይዟል። ከእነዚህም አራቱ  ዋና ገጸ ባሕርያት (አበራ፣ ኃይለማርያም፣ ሉሊት፣ ‘ጋሽ’ አባተ) ሰባቱ ጭፍራ (‘እሜቴ ባፈና’፣ ሰናይት ‘ሱቅ በደረቴ’. . .)፣ ሃያዎቹ አዳማቂ (ሱዛን ሮስ፣ ትርንጎ፣ ሚኒስትሩ . . .)፣ እና ከሃያ በላይ ደግሞ ሥውር ገጸ ባሕርያት (ወፍራም ዝንብ፣ ባይከዳኝ. . .) ናቸው።

‘ዋና’ ገጸ ባሕርያትን  እንደ ድርሰቱ አጥንት፣ ‘ጭፍራ’ ገጸ ባሕርያትን ደግሞ እንደትረካው ሥጋ  ልናያቸው እንችላለን። ያለኒህ አሥር ግድም ገጸ ባሕርያት “ከአድማስ ባሻገር”ን አንብቦ ለመረዳት በጣም ያስቸግራል (አንድ ተማሪ “መጽሐፉን ወደ ተውኔት ለውጠህ ጻፍ” ወይም “ልብ ወለዱን ላናበቡ ጓደኞችህ በአጭሩ ተርክ” ቢባል እኝህኑ ዋናና ጭፍራ ገጸ ባሕርያት መጠቀሙ አይቀርም)። በተመሳሳይ መልኩ “አዳማቂ” ገጸ ባሕርያትን እንደ ክት አልባሳት ብናያቸው ያስኬዳል፤ እጅጉን ባያስፈልጉም ድርሰቱን በሚገባ ያስጌጡታልና።

ታዲያ የደራሲውን  ጥበብ ለመረዳት አንዱ መንገድ የፈጠራቸውን ገጸ ባሕርያት በምን መልኩ  ተንከባክቦ እንዳሳደጋቸው ለመረዳት መሞከር ነው።  በመቀጠልም፣ “ከአድማስ ባሻገር” ውስጥ ወሳኝ ባይሆንም ጠቃሚ ሚና ከሚጫወቱት ሃያ “አዳማቂ” ገጸ ባሕርያት አምስቱን መርጬ እንዴት አድርጎ  በአሉ ግርማ እንደሳላቸው ለማሳየት እሞክራለሁ።

እኒህንም አዳማቂ  ገጸ ባሕርያት የመረጥኩበት ምክንያት እንደሚከተለው ነው። አብዛኛውን ጊዜ ደራሲዎች የዋናና ጭፍራ ገጸ ባሕርያት አሳሳል ላይ ልዩ አትኩሮት (እንዲሁም በርካታ ገጾችን) ይሰጣሉ። በዚህም ምክንያት፣ የገጸ ባሕሪ  አሳሳል ችሎታቸውን በሚገባ ለመመዘን ያስቸግረናል. . .ብዙም ባልተካነ  ደራሲ እጅ እንኳን የዋና ገጸ ባሕርያት አሳሳል የስኬት ሚዛን ሊደፋ ይችላልና።

በአንፃሩ፣ በልብ ወለዱ ወሳኝ ሚና የማይጫወቱትን “አዳማቂ” ገጸ ባሕርያትን ለመሳል ደራሲው በአማካይ ከአንድ ገጽ በላይ ቀለም አያጠፋም። እኛም እንደ አንባቢነታችን  እኒህን መስመሮች በቅርበት በማስተዋል “ደራሲው ባለው ውስን ዕድል ገጸ ባሕሪውን በሚገባ አዳብሮታልን?”፣ “የገጸ ባሕሪው ልዩ የሆነ ምስል በምናባችን ሊሳል ተችሏልን?” የሚሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ መሞከር እንችላለን። በሌላ አነጋገር፣ ማንኛውም ደራሲ በበርካታ ገጾች ገለጻና ንግግር አንድን ገጸ ባሕሪ በጉልበት ምናባችን ውስጥ ቢያስገባውም፣ ጥበበኛ ደራሲ ግን በአንዲት አንቀጽ ብቻ አይረሴ ምስል በአዕምሯችን ሊቀርጽ ይችላል።

እናም የዚህ መጣጥፍ ጥያቄ፤ “በገጸ ባሕርያት አሳሳል ረገድ  በአሉ ግርማ ምን  ዓይነት ደራሲ ነው?” የሚል ይሆናል።

የአዳማቂ ገጸ ባሕርያት አሳሳል

የአንድ ልብ ወለድ ገጸ ባሕርያት ደራሲው በፈጠረላቸው ህዋና ባበጀላቸው ምሕዋር ይሽከረከራሉ። ይህም በሞላ ጎደል የሚቀየሰው በገጸ ባሕሪያቱ ንግግርና በተራኪው  ገለጻ ነው። የተራኪው ገለጻ የገጸ ባሕሪውን አጠቃላይ ገጽታ ሲወስንልን፣ የገጸ ባሕሪው ንግግር ደግሞ አስተሳሰቡንና ስሜቱን ቀንጭቦ ያሳየናል። በኒህም ሁለት ስልቶች  በመደጋገፍ ደራሲው በኛ ባንባቢዎች ላይ የገጸ ባሕርያትን ምስል ለመቅረጽ ይሞክራል።

በ“ከአድማስ ባሻገር” በአሉ በርካታ የፈጠራ ህዋዎችንና ምሕዋሮችን ቀይሷል፤ የተራኪው “ሁሉን አውቅ” ባይ መለኮታዊ ዕይታ፣ የአበራ ውጥንቅጥ ሐሳቦችና ምኞቶች፣ የገድሉ “ሉሊት ከበብ” ምሕዋር፣ የኃይለማርያም “አበራ ተኮር” እሽክርክሪት. . . ወዘተ። በሌላ አነጋገር፣ በልብ ወለዱ ውስጥ አበራ የድርሰቱ “ፀሐይ” ሲሆን፣ እነ ኃይለማርያምና ሉሊት ደግሞ ከአበራ ስበት  ማምለጥ አቅቷቸው እሱኑ የሚሽከረከሩት  ዓለማት ናቸው።  በልብ ወለድም  ውስጥ አብዛኛው ፍትጊያና ግጭት ያለው በነዚሁ በዋናና በጭፍራ ገጸ ባሕርያቱ መሀል ነው።

በተቃራኒ መልኩ፣ በድርሰቱ ወሳኝ ሚና የሌላቸው “አዳማቂ” ገጸ ባሕርያት ግን ብዙ  ጊዜ  የተረጋጋ ህልውና ያሳያሉ። አንድም፤ ምሕዋራቸው ከዋናው ገጸ ባሕሪ (አበራ ወርቁ) እጅግ የራቀ በመሆኑ፣ አንድም ደግሞ፤ እንደተወርዋሪ ኮከብ ብቅ ብለው ስለሚጠፉ የጭፍራ ገጸ ባሕርያትን ያህል  የድርሰቱ እሳትና ፍትጊያ ብዙም አያሳስባቸውም። በዚህም ምክንያት የደራሲውን ጥበብ ለመለካት ጥሩ መስፈርት ሆነው ሊያገለግሉ ይችላሉ።

በመቀጠል፣ በነዚህ ለታሪኩ ወሳኝ ሚና በማይጫወቱ አዳማቂ ገጸ ባሕርያት ላይ ደራሲው የተጠቀመውን የአሳሳል ስልት እዳስሳለሁ።

  1.  ሱዛንሮስ

“ከአድማስ ባሻገር” ትረካው የሚጀምረው ዋና ገጸ ባሕሪው አበራ ብቻውን በሐሳብ ባሕር እየዋኘ ማንነቱን ሲፈትሽ፣ ከዛም የድሮ ፍቅረኛውን (ሱዛን) ሲያስታውስ ነው። ተራኪው ስለዚች ገጸ ባሕሪ የሚከተለውን ዘርዘር  ያለ ገለጻ በጥቂት ገጾች ይሰጣል (በመጽሐፉ ገጽ 8-12)፤

‘የሰላም ጓድ ልኡካን ባልደረባ’፣ ‘ያለሙዚቃ ሰውነቷ አይፍታታም’፣ ‘ውርጭ ውስጥ እንዳደረ ብረት የሚቀዘቅዝ ጭን’፣ ‘ረጅም ጠጉሯ ስር ውሎ እንደ ዝሆን ጥርስ የነጣ ማጅራት’፣ ‘የታጠፈ ቀሚስ’፣ ‘ሲቃ የያዘው ድምጽ’፣‘ጉንጮቿ ላይ የነበረው ደም ቁልቁል የወረደ’፣ ‘ጸሀይ ያልነካው በሽተኛ ይመስል የገረጣች’፣ ‘ከሩቅ ሲመለከቱት ነጭ ከቅርብ ሲያዩት ሽሮ የሚመስል ጥርስ’፣ ‘በረጅሙ ተንፍሳ’፣‘ረጅም ጠጉሯን በሁለት እጆቿ ጭምድድ አድርጋ’፣ ‘እጆቿ ላይ ያሉት የደም ስሮች እንደሽምጥ አጥር ተገትረው’፣ ‘የቀሉት ትናንሽ ውብ ዓይኖቿ’፣ ‘እንባ እየፈለቀ የገረጡትን ጉንጮቿን ያርሰው’፣ ‘የየሙዚቃውን ስልት በግለት በስሜት. . . ትጠብቅ’፣ ‘ጸሀይ እንዳየች የጽጌረዳ እምቡጥ ወከክ ትርክክ’፡፡

ከላይ የምናየው ተራ ገለጻ አይደለም። ደራሲው የተራኪውን ድምፅ በሚገባ በመጠቀም የሱዛንን ሰውነት ብቻ ሳይሆን ስሜቶቿንም በሰፊው ስሎልናል። ቢሆንም በአሉ በዚህ አላበቃም። የራሷንም አንደበት በመጠቀም  የአስተሳሰቧን ህዋ ይስልልናል። ሱዛንም ስትናገር ከሌሎች አዳማቂ ገጸ ባሕርያት ተለይታ የምትሽከረከርባቸውን የቃላት ምሕዋር መለየት እንችላለን። እኒህም “መስጠት”፣ “ሙዚቃ”፣ “ትዝ”፣ “አብረን”፣ “ደስ/ደስታ”፣ “ደንታ”፣ “ጽጌረዳ” እና “ፍፁም” ናቸው። እስኪ ለምሳሌ ያህል ሦስቱን በቅርበት እንመልከት፤

ሙዚቃ

“ሙዚቃ ስጠኝና ፍቅር ልስጥህ።”

“ሙዚቃ ስጠኝ ነው የምልህ።

“ያለሙዚቃ አይሆንልኝም ፍፁም አይሆንልኝም።”

ትዝ

“አብረን የሰማናቸው ጥኡም ሙዚቃዎች ትዝ ይሉኛል።”

“እያንዳንዷ ደቂቃ ትዝ ትለኛለች።”

ደስ/ደስታ

“ብልጫ ያለውን ነገር የሚመርጡ ወንዶች ደስ ይሉኛል።”

“ወንዶችን ማሞላቀቅ ደስ ይለኛል።”

“እንዳንተ ያሉ … ሳገኝ ደግሞ የበለጠ ደስታ ይሰማኛል።”

ሱዛን ደምቃ የምትታይ “አዳማቂ” ገጸ ባሕሪ ናት። ከ“ሽሮ” ጥርሷ ጀምሮ እስከ “ደስ” የሚሏት ወንዶች በቀላሉ ለመገንዘብ ይቻላል። በአሉ በጥቂት መስመሮች ይህን ሁሉ በምናባችን መሳሉ የሚያስደንቅ ነው። እንዲያውም ተጨማሪ  ገጾችና ሚና ቢጨምርላት “ጭፍራ” ገጸ ባሕሪ ሆና መመደብ ትችል ነበር።

  1. ትርንጐ

ትርንጐ በድርሰቱ የአበራ የልጅነት የቤት ሠራተኛ የነበረች ናት። ተራኪው ስለዚች አዳማቂ ገጸ ባሕሪ የሚከተለውን ይገልጻል (በመጽሐፉ ገጽ 13)፤

‘ዕድሜዋ ከእሱ ዕድሜ ገፋ ያለ’፣ ‘ፊቷ እንደውድቅት ጨለማ ጠቁሮ በወዝ የተንጨፈጨፈ’፣ ‘ጠጉሯ አንድ ባንድ የሚቆጠር’፣ ‘ፍርጥምጥም ያለች ጉጭማ’፣ ‘መደብ ላይ ተጋድማ’፣ ‘ከባይከዳኝ ጋር ስትዳራ’፣ ‘ደንግጣ ከላይዋ ላይ ስትወረውረው’

ይህ ጥሩ ምስል-ሳይ አካላዊ ገለጻ ነው። ቢሆንም ስሜቷን በሚገባ አይገልጽልንም፤ የምናውቀው ድንጋጤዋን ብቻ ነው። ታዲያ ከአንድ ገጽ ባነሰች ስፍራ ደራሲው ስሜቶቿን ከዚህ ይበልጥ ሊገልጽ ቢያዳግተው ሊያስደንቀን አይገባም (ለ“ሱዛን” አራት ገጽ መመደቡን እያስታወስን)። በተጨማሪም፣ ከአንደበቷ የምንሰማው ንግግር ተለይቶ የሚሽከረከረው በሁለት ቃላት (“ና ” እና “እንጫወት“) ዙሪያ ነው፣

“ና እንጫወት።”

“ና ምን ቸገረህ እኔ አሳይሃለሁ።”

የኒህም ቃላት  ምናባዊ ኃይል በንግግሯና በተራኪው ገለጻ በመደጋገፉ (‘ታጫውተዋለች’፣ ‘ከባይከዳኝ ጋር ስትዳራ’) ሳይጠነክር አልቀረም። እናም ትርንጐን ስናይ፤ እንደ ሱዛን ያልደመቀች፣ ግን የራሷ የሆነ ልዩ ፍካት ያላት ገጸ ባሕሪ ሆና እናገኛታለን። ደራሲው ይህችን ገጸ ባሕሪ በሚገባ ለማድመቅ ያልመረጠበትን ምክንያት ግን (የቦታ ማጠር ይሁን ለታሪኩ ሒደት ከዚህ በላይ መግለጽ አለማስፈለጉ) በእርግጠኝነት ለማወቅ ያስቸግራል።

  1. ሴተኛአዳሪ

“ከአድማስ ባሻገር” ውስጥ አበራ ስሜቱን “ለማውጣት” (ለመወጣት) በተደጋጋሚ ሴተኛ አዳሪ ፍለጋ ይሰማራል። በድርሰቱ ላይ ተራኪው የሚከተለውን ገለጻ ይሰጠናል (በመጽሐፉ ገጽ 45 እስከ 46፣ 88)፤

‘ቀያይ መጋረጃዎቹን እየገለጡ ከየደጃፉ ብቅ ብቅ’፣ ‘ድምጿ ጨለማውንና ፀጥታውን ቀደደው’፣ ‘ከየሴቶቹ ቤት የሚመጣ የእጣንና የከርቤ ጢስ’፣ ‘በቀይ መብራት አንዷን ከሌላዋ መለየት አስቸጋሪ’፣‘ሁለቱ ያገር ልብስ የተቀሩት. . . ሰውነት ላይ ልክክ የሚሉ ቀሚሶች ለብሰው’፣ ‘ዳሌዋ ሰፋ ብሎ የታየችው’፣ ‘ሲገባ እንደሌሎቹ ወከክ ያላለችለት’፣  ‘በቅናት ዓይን ቆዳዋን ገፈፏት’፣  ‘የተቀባችው ሽቶ የተስማማው አይመስልም’፣‘የሸማኔ መወርወሪያ ይመስል ወዲህና ወዲህ ይሯሯጣሉ’፣  ‘አንገቷን እንደ እስክስታ ወራጅ እንክት’፡፡

በአሉ የሴተኛ አዳሪዎችን ገጸ ባሕሪያት በአንድ ክርታስ በጅምላ የሳላቸው ይመስላል። ከገለጻው ውስጥ በሚገባ ተነጥላ የምትታይ ሴተኛ አዳሪ የለችም፤ “መጋረጃ እየገለጡ”፣ “ወዲህና ወዲህ ሲሯሯጡ”፣ “በቀይ መብራት ሲዋሃዱ” ነው የምናስተውለው። በንግግራቸውም ቢሆን ሴተኛ አዳሪ ገጸ ባሕርያት በተወሰነላቸው የቃላት ምሕዋር (“አንቱ” እና “ኡኡቴ”) ነው የሚሽከረከሩት።

አንቱ

“አንቱ ዛሬ ደግሞ ውስኪ ይዘው መዞር ጀመሩ እንዴ?”

“ጋሼ አንቱ ምን እንጋበዝ ታዲያ?”

“ምን የሚያስቅ ነገር አገኙብኝ አንቱ?”

ደራሲው እዚህ ላይ  ግለሰባዊ ሳይሆን ማኅበረሰባዊ መልክ ያለው የሴተኛ አዳሪዎችን ምስል (በገለና ንግግር ታግዞ) ለመቅረፅ የመረጠ ይመስላል። በአሉም  ይህን ያደረገበት ምክንያት በልብ ወለድ ድርሰቱ ውስጥ የሴተኛ አዳሪ ገጸ ባሕርያት በታሪኩ ፍሰት ላይ ወሳኝ ሚና ስለማይጫወቱ ይሆናል። ዋናው ገጸ ባሕሪ አበራም ቢሆን “ስሜቱን ለማውጣት” ብቻ እንደፈለጋቸው ስናስታውስ ደራሲው በጅምላ ለምን እንደሳላቸው መረዳት እንችላለን።

  1. በቀለሽክታ

በቀለ “ከአድማስ ባሻገር” ውስጥ ከአበራ የመሥሪያ ቤት ባልደረቦች አንዱና አይረሴው ነው። ተራኪው ይህን ገጸ ባሕሪ በሚከተለው መልክ ይገልጸዋል (ገጽ 70 እስከ 73 እና 97)፤

‘ረጅም ቀጭን ቁመናውን እንደ ሽመል እያውዘገዘገ’፣ ‘የተቀባው ሽቶ ክፍሉን ሁሉ አውዶ’፣ ‘የሚናገረው በጥድፊያ’፣ ‘ሲናገር እንደ ሴት ይቅለሰለሳል’፣ ‘ሲሄድም ይውዘገዘጋል’፣ ‘ልብሱ ዳለቻ ሆኖ ከሀር ጨርቅ የተሠራ’፣‘ቀይ ክራቫት አስሮ’፣ ‘የፈነዳ ጽጌረዳ ቅርጽ ያለው. . . መሀረብ የደረት ኪሱ ላይ ሰክቶ’፣‘ረዥም ዞማ ጠጉሩ በቅባት ወደ ኋላ ተለጥጦ’፣ ‘ዘወትር ሙሽራ’፣ ‘ሴታ ሴት መልኩ ላይ የሚወራጭ ስሜት’፣ ‘ረጃጅም አርጩሜ መሳይ ጣቶች’፣  ‘ጀብዱ ለማውራት. . . ልብሱን ለማሳየት ከቢሮ ቢሮ መዞር ግዴታው’፣ ‘እዩኝ የሚል’፣  ‘በመስኮቱ መስተዋት የክራቫት አስተሳሰሩንና የጠጉሩን አበጣጠር እያየ ሲመጻደቅ’፤

በአንደበቱ ንግግርም በኩል የበቀለ “ሽክታነት” በአስተሳሰቡም መሆኑን በሚከተሉት ቃላት ይታየናል።

“አላማረብኝም?”

“ስላንዷ ሴት የሰባ ወሬ ነበረኝ።”

ታዲያ የበቀለ “ሽክታነት” እና ጀብዱ ለወግ ያህል እንደመሆኑ፣ ሌሎች ገጸ ባሕርያት ንግግሩንና ጀብዱዎቹን ከምር የወሰዱት አይመስልም። (እንዲያውም በሕይወቱ ሴት ነክቶ የማያውቅ ቢሆን አያስደንቅም!)

  1.  ሚኒስትሩ

በስማቸው የማይጠቀሱት “ሚኒስትሩ” በልብ ወለዱ ውስጥ የአበራ የበላይ በላይ  አለቃ እንዲሁም የታላቅ ወንድሙ የ’ጋሽ’ አባተ ወዳጅ ናቸው። ገጸ ባሕሪውን ተራኪው በሚከተለው መልክ ይገልጻቸዋል (ገጽ 79 - 80)፤

‘የቢሯቸው ስፋትና የጠረጴዛው ግዙፍነት. . . የማነስ ስሜት ያሳድራል’፥ ‘ግርማ ሞገሥ ሳይወዱ በግድ ያስደገድጋል’፥‘ወፍራም ድምፅ’፥ ‘ጥያቄያቸውን ከትዕዛዝ ለይቶ ለማወቅ ያዳግታል’፥ ‘ቀና ብለው ሰው አለማየት ልማድ’፣‘ሰው የሚያስበውን አስቀድመው የማወቅ ችሎታ ያላቸው የሚመስላቸው’፣‘ቁጭ በል ማለት አያውቁም’ ፥ ‘ዝም ካሉ ማሰናበታቸው’፡፡

ይህን ገለጻ ስናነብ አንዳንዶቻችን ሳንወድ በደመነፍስ የምንሽቆጠቆጥላቸውን ሰዎች ሊያስታውሰን ይችል ይሆናል – ጠንካራ ምስል-ሳይ ገለጻ ነውና። በዚህም ሳያበቃ ደራሲው በገጸ ባሕሪው አንደበት በርካታ የቃላት ምሕዋሮችን (“ለመሆኑ”፥ “ለማንኛውም”፥ “ልጅ/ልጅነት”፥ “ብቻ”፥ “ችሎታ”፥ “አልሰማህም?”) በምናባችን ያሽከረክራል። እስኪ ሦስቱን እንመልከት፤

ለመሆኑ

“ለመሆኑ ስንት ዓመትህ ነው?”

“ለመሆኑ ሚስት አግብተሃል?”

ብቻ

“ብቻ ያስጠራሁህ ለዚህ አልነበረም።”

“ብቻ አንድ ቦታ ረግተህ ለመሥራት አትችልም።”

“ብቻ እናንተ ወጣቶች ሁሉንም ባንዴ ለማድረግ ትጣደፋላችሁ።”

አልሰማህም?

“የረጋ ወተት ቅቤ ይወጣዋል ሲባል አልሰማህም?”

“ሲሮጡ የታጠቁት ሲሮጡ ይፈታል የሚለውን ምሳሌስ አልሰማህም?”

እኒህ ተደጋጋሚ ቃላት ከተራኪው ምናባዊ ገለጻ ጋር አንድ ከራሳቸው ጋር የሚነጋገሩ “ምክር አከፋፋይ” ባለሥልጣንን ምስል ይፈጥራሉ።

ማሳረጊያ

ደራሲው ከላይ በመጠኑ በተዳሰሱት አምስት ገጸ ባሕርያት አማካይነት፤ ነጥሮየወጣግለሰባዊነትን (“ሱዛን”)፣ ቡድናዊባህሪን (“ሴተኛ አዳሪዎች” እና “ሚኒስትሩ”)፣ አዝናኝነትን (“በቀለ ሽክታ”)፣ እንዲሁም የብዥታንምስል (“ትርንጐ”) በሚገርም መልኩ በምናባችን በቀላሉ ለመሳል ችሏል።

በአሉ ግርማ “ከአድማስ ባሻገር” ውስጥ እኒህንና የተቀሩትን 50 ገጸ ባሕርያት ሲስል እጅጉን ተጠቦበት እንደነበር ለማስተዋል አያዳግትም። ይህም ልብ ወለድ ዘመን ተሻጋሪ ተወዳጅነትን ለማግኘት ካስቻሉት ምክንያቶች አንዱ የገጸ ባሕርያት አሳሳል ስልቱ ሳይሆን አይቀርም። ለበአሉ የመጀመርያው ልብ ወለድ መጽሐፉ መሆኑን ስናስታውስ ደግሞ የድርሰት ጥበቡን ብስለት ያሳየናል።

ታዲያ ድርሰቱ ውስጥ የሚገኙትን  የገጸ ባሕርያት አሳሳል ስልቶች ሙሉ በሙሉ ገና አልተገነዘብንም። የበአሉ ግርማን ጥበብ በሚገባ ለመረዳት “ከአድማስ ባሻገር” ውስጥ ያሉትን ዋና፣ ጭፍራና ስውር ገጸ ባሕርያትንም በቅርበት ማጥናት ያስፈልጋል።  በዚሁ ድርሰትም  ያየነውን የገጸ ባሕሪ አሳሳል ስልት በሌሎቹ  አምስት ልብ ወለዶች (“የህሊና ደወል”፣ “የቀይ ኮከብ ጥሪ”፣ “ደራሲው”፣ “ሐዲስ” እና “ኦሮማይ”) ዳብሮ ወይ ቀንጭሮ እንደሄደ ማየት ይኖርብናል። ይህንንም ለመረዳት እያንዳንዱን ልብ ወለድ በተናጠል፣ ከዚያም  ስድስቱን የፈጠራ ድርሰቶች  በንፅፅር ማጥናት ሳይጠቅመን አይቀርም። ምናልባት ያኔ፣ የበአሉ ግርማን የገጸ ባሕርያት አሳሳል ጥበብ  በሚገባ  ተረድተናል ለማለት እንችል ይሆናል።

አባሪ

(ከአድማስባሻገር አዳማቂ ገጸ ባሕርያትንግግርናቃላት)

ሱዛን

“ብልጫ ያለውን ነገር የሚመርጡ ወንዶች ደስ ይሉኛል። ምክንያቱም ለውድና ለከፍተኛ ነገሮች የሚጣጣሩ ወንዶች ሲያጋጥሙኝ እኔ ስለራሴ ያለኝ አስተያየት ውኃ እንዳገኘ ጽጌረዳ ይለመልማል።” (ገጽ 8)

“ሙዚቃ ስጠኝና ፍቅር ልስጥህ።”

“ሙዚቃ ስጠኝ ነው የምልህ።”

“እውር ነህ ለማየት አትችልም።” (ገጽ 9)

“ያለሙዚቃ አይሆንልኝም ፍፁም አይሆንልኝም። ፍቅሬን ለወንድ አሳልፌ ከመስጠቴ በፊት ነፍሴ ወደ ሙዚቃ ዓለም መግባት አለባት። ከዚያ በኋላ ነፃነት ይሰማኛል። ውስጤ እንደ ጽጌረዳ እምቡጥ ይከፈታል። ለመስጠትም ሆነ ለመቀበል ዝግጁ እሆናለሁ።” (10)

“አበራ ለምን እንዲህ ትላለህ? ለቀለም ደንታ እንደሌለኝ እዚህ መምጣቴ ሊያረጋግጥልህ አይችልም?” (ገጽ 10)

“መልካም ፋሲካ ስኳር ወለላዬ። የትም ብሆን አብረን የሰማናቸው ጥኡም ሙዚቃዎች ትዝ ይሉኛል። የማዝነው አንተ ለጋብቻ ፍፁም ደንታ ስለሌለህና ብዙ ሙዚቃዎችን አብረን ሳናዳምጥ በጥቂት ጊዜ ውስጥ በመለያየታችን ነው። ሆኖም ቅሬታ የለኝም። እያንዳንዷ ደቂቃ ትዝ ትለኛለች።” (ገጽ 10)

“ወንዶችን ማሞላቀቅ ደስ ይለኛል። እንዳንተ ያሉ የእግር ጥፍራቸውን መቁረጥና የብብት ጠጉራቸውን መላጨት የማይችሉ ሳገኝ ደግሞ የበለጠ ደስታ ይሰማኛል።” (ገጽ 12)

ትርንጐ

“ና እንጫወት።”

“ና ምን ቸገረህ እኔ አሳይሃለሁ።” (ገጽ 13)

የጣልያንገረድ

“ብስብስ የወንድ አልጫ።” (ገጽ 16)

የበግነጋዴ

“ሃምሣ ብር።”

“ስድሳ ብር።” (ገጽ 25)

“ጮማነታቸው ላይ።”

“ከስድስት ባውንድ አይቀንስም።”

“ፋሲካ።”

“ታዲያ በግ ተራ ለምን መጡ?” (ገጽ 26)

ሴተኛአዳሪዎች

“አንቱ ዛሬ ደግሞ ውስኪ ይዘው መዞር ጀመሩ እንዴ?” (ገጽ 45)

“ጋሼ አንቱ ምን እንጋበዝ ታዲያ?” (ገጽ 46)

“ምን የሚያስቅ ነገር አገኙብኝ አንቱ። ሄደው መሳቂያዎን ይፈልጉ።”

“ታዲያ በማን ነው?”

“ኡኡቴ እርስዎ ከማን በለጡና!” (ገጽ 88)

እንጀራአባት

“አንተ ወስላታ ተነስተህ በሩን አትከፍትም?” (ገጽ 51)

ባልቻ

“ማን ነው የቀደመኝ? ስሮጥ የመጣሁት ለተሰማ ክብሪት ልሰጥ ነበር።” (ገጽ 69)

“አበራ ምን ነው ዛሬ የከፋህ ትመስላለህ? ሐዘኑንና ብስጭቱን ለኔ ተውና ይልቅ ቡና በለን። ተሰማ እንደሆን ዛሬ እማማ የኪስ ገንዘብ አልሰጡትም መሰለኝ። (ገጽ 70)

“አርፌ ሲጃራ እንዳልቃርምበት ነው ይህ ሁሉ። ደሞዝ ጭማሪ መጥታለች መሰለኝ።” (ገጽ 72)

“ለመሆኑ ሠርግሽን መቼ ነው የምንበላው?” (ገጽ 76)

“እንዲያው ስለእግዚአብሔር ብላችሁ ሰላሳ ብር አበድሩኝ።” (ገጽ 98)

በቀለሽክታ

“ይህንን ልብስ በስንት ገዛሁት? እስቲ ገምቱ። አላማረብኝም?” (ገጽ 70)

“ፋሲካን ያሳለፍኩት ከአንዲት አገር አሸነፈች ከየምትባል ኮረዳ ጋር ነበር። ታዲያ ምን ይሆናል እያለቀሰች ስቃይዋ ደስታ ላይሆነኝ። (ገጽ 71)

“አበሳ ነው እንጅ። ስለአንዷ ሴት የሰባ ወሬ ነበረኝ። ለሹመት ታጭተሃል እንዴ?” (ገጽ 73)

“ሉሊት ታደሰ ማን ናት?” (ገጽ 97)

“እንደኔ ያለው ወንድ ባያጋጥማት ነው። ግን ማን ነው ያልከው? አዎን ገድሉ የአበራ ጓደኛ ከሆነ አንተን ከመላክ እሱ ራሱ ለምን አይነግረውም?” (ገጽ 98)

ተላላኪ

“ሚኒስትሩ በአስቸኳይ ይፈልጉሃል።” (ገጽ 78)

ሚኒስትሩ

“ያንን ጥናት ምን አደረስከው?” (ገጽ 79)

“የእምቧይ ካብ ይሆናል ለማለት ነው? ችግሩ ሳይገባህ አይቀርም። ብቻ ያስጠራሁህ ለዚህ አልነበረም። የአባተ ወንድም አይደለህም? አዎን ትመሳሰላላችሁ። ጥሩ ችሎታ እንዳለህ ሰምቻለሁ። እኔም ራሴ ደርሼበታለሁ። ብቻ አንድ ቦታ ረግተህ ለመሥራት አትችልም። ስህተት ነው። የረጋ ወተት ቅቤ ይወጣዋል ሲባል አልሰማህም? ብቻ እናንተ ወጣቶች ሁሉንም ባንዴ ለማድረግ ትጣደፋላችሁ። ሲሮጡ የታጠቁት ሲሮጡ ይፈታል የሚለውን ምሳሌስ አልሰማህም? ብቻ ለማንኛውም ነገር ብዙ ታስቦልሃል። ልጅ እንደሆኑ ዘለዓለም አይኖርም። ረጋ ብለህ ሥራ። ለመሆኑ ስንት ዓመትህ ነው?” (ገጽ 79)

“በጣም ልጅ ትመስላለህ። ግን አርጅተሃል። ለመሆኑ ሚስት አግብተሃል?” (ገጽ 79)

“ታዲያ ምን ትጠብቃለህ? ሁሉም በልጅነት ሲሆን ያምራል። ለዕድገትም ሆነ ለማንኛውም ነገር የቤተሰብ ኃላፊነት ጥሩ ዋስትና አለው። አባትህ ስመ ጥር ጀግና ነበሩ። ታዲያ አስብበት እንጂ። ችሎታ ብቻውን መቼ ይበቃልና።” (ገጽ 80)

  • ፡- ጽሑፉ የጸሐፊውን አመለካከት ብቻ የሚያንፀባርቅ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

 

Standard (Image)

ሕገወጥ ዝውውርን አደብ ማስገዛት የሚቻለው ሕጉን ተግባራዊ በማድረግ ብቻ ነው

$
0
0

በበላይ ታምሩ

ሰሞኑን መንግሥት ከረጅሙ የተሃድሶ ግምገማ፣ በቅርቡም ከተከታታዩ የአመራር ሥልጠና በኋላ የዕርምጃ በትር ያነሳ መስሏል፡፡ ለዓመታት ሕዝቡ፣ የተወካዮች ምክር ቤት፣ ዋና ኦዲተርና መሰል አካላት ‹‹ኧረ ምንድነው ነገሩ?››  ሲሉባቸው የቆዩ መሥሪያ ቤቶችና የሥራ ኃላፊዎችን በሙስና ወንጀል መመርመር ጀምሯል፡፡ ጥልቀት ያለውና ቁርጠኝነት የታከለበት ከሆነ ደግሞ ይበል፣ ይጠናከር የሚባል ጅምር ይሆናል፡፡ ይህን ጉዳይ በደንብ ሲብላላና የክስ መዝገቡም ፍርድ ቤት መቅረብ ሲጀምር የምመለስበት ሆኖ፣ ለዛሬው ግን ተሃድሶውም ሆነ መገማገሙ ብዙም

የዳሰሰው ስላልመሰለኝ አንድ አንገብጋቢ ችግር ላወጋችሁ ወደድኩ፡፡

ሕገወጥ የሰዎች ዝውውር የታዳጊው ዓለም ዋነኛ ችግር ከሆነ ውሎ አድሯል፡፡ የስደቱ መነሻ የኢኮኖሚ ፍላጎት ማደግ፣ የዓለም ወደ አንድ መንደርነት መቀየርና የትም አገር ገብቶ የመሥራት ፍላጎት መጨመር፣ ወይም የፖለቲካ ነፃነት ማጣትም ይባል መገፋት ሊሆን ይችላል፡፡ ያም ሆኖ በአገራችን በሕጋዊ መንገድ ከአገር ወጥቶ ለመሥራት ጥረት ከማድረግ ይልቅ፣ በሕገወጥ መንገድ በተገኘው አጋጣሚ የሚፈረጥጠው ዜጋ ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ ተባብሷል፡፡ የተዳፈነ ቢመስልም ሲያገረሽ ታይቷል፡፡ ይህንኑ ፈተና ለመግታት በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚመራ ብሔራዊ የችግሩ ፈቺ ግብረ ኃይል ቢቋቋምም፣ እዚህ ግባ የሚባል ለውጥ ስለመምጣቱ ማረጋጋጫ አልተገኘም፡፡

እንዲያውም በአሁኑ ወቅት በተለይ በመካከለኛው ምሥራቅ እየሆነ ያለውን ለሚመረምር ሥር እየሰደዱ ዜጐችን ለአስከፊ የሰብዓዊ መብት ጥሰትና እንግልት እየዳረጉ ከሚገኙ ወንጀሎች አንዱና ዋናው፣ ሕገወጥ የሰዎች ዝውውር መሆኑን  በቀላሉ ለመገንዝብ አያዳግተውም፡፡ ሌላው ቀርቶ በደቡብ ሱዳን፣ በሱዳን፣ በኬንያና  ከእኛም በማይሻሉ አገሮች በርካታ ኢትዮጵዊያን በሕገወጥ መንገድ ስለመኖራቸው ብዙም ሲነገር አይሰማም፡፡ በእኛ አገር ያሉ የጎረቤት አገሮች ስደተኞችን ብዛትና ስብጥር ያህል ማለቴ ነው፡፡

በእርግጥ ሁሉም አገሮች ሕገወጥ የሰዎች ዝውውር ወንጀል ነው ብለው ከደመደሙ ከራርመዋል፡፡ ወንጀሉም በተለይ የሴቶችና የሕፃናት ዝውውርን እጅግ የከፋ የሚያደርግ ነው፡፡ ከዚሁ ጋር ያለውና ተያያዥ የሆነው ስደተኞችን በሕገወጥ መንገድ ድንበር የማሻገር ወንጀል እንደሆነም ታምኖበታል፡፡ ነገር ግን ስደተኞችን በየአገሩ ለማቆየት የሚያስችል ሁኔታ እንዲፈጠር የተደረገው በቂ ጥረት የለም፡፡ በእኛም አገር ቢሆን በየጊዜው እየሆነ ያለውን (የግብር መጫንና በአገር ውስጥ ሕዝቡ ከአነስተኛ ንግድ እንዲወጣ ማድረግ፣ የኑሮ ውድነት፣ የመልካም አስተዳዳር ዕጦት፣ የሙስና መባባስ፣ የፖለቲካው ሁሉን አሳታፊ አለመሆን፣ አለመተማማን …) ለታዘበ ስደትን የሚያስቀር ዕርምጃ ተወስዷል ለማለት አያስደፍርም፡፡

በአገር ደረጃ የሕገወጥ ስደት ከጥቅሙ ይልቅ አስከፊነቱን ደጋግመን ታዝበናል፡፡ ከዜጎች እንግልትና ሞት እስከ አሸባሪ ካራ ድረስ አርፎብናል፡፡ በሴቶችና በሕፃናት ዝውውርና ስደተኞችን በሕገወጥ መንገድ በማሻገር ወንጀልም፣ ቁጥራቸው በጣም ብዙ የሚባሉ ዜጐች ተጎድተዋል፡፡ ይህን ወንጀል ለመከላከል ከተለያዩ አገሮች ጋር ተባብሮ  ኃላፊነትን መወጣት የሚያስፈልገውም የችግሩ ዋነኛ ሰለባ ኢትዮጵያ በመሆኗ ነው፡፡ ለወንጀሉ ተጐጂዎች ጥበቃና እንክብካቤ ማድረግ፣ ለችግሩ ይበልጥ ተጋላጭ ለሆኑ የኅብረተሰብ ክፍሎች ዕድሜያቸውን፣ ፆታቸውንና ልዩ ፍላጐታቸውን ያገናዘበ የተለየ ጥበቃ እንክብካቤና ድጋፍ ማድረግም ወሳኙ የመንግሥት ኃላፊትነት ሊሆን ይገባል፡፡

ይሁንና በዚህ ረገድ ከተግባር በላይ ወሬው እየጮኸ ብዙ ትዝብት ላይ እየጣለን ነው፡፡ ባለፈው ጊዜ ከሳዑዲ ዓረቢያ ከ135 ሺሕ በላይ ዜጎች በግፍ ተፈናቅለው ወደ አገር ቤት ተመለሱ፡፡ ተቀባይ ኮሚቴ ተቋቋመ፣ የተለያዩ ተቋማት ባለሥልጣናት ተገኙ፣ በየአካባቢው ተደራጁ ተባለ፣… ነገር ግን ከአንድ ሰሞን ሆይ ሆይታ ያለፈ ሥራ ባለመሠራቱ፣ አብዛኛዎቹ ተመልሰው ከመሰደድ አልፈው በአገር ቤት የተውተረተሩ ቢኖሩም እምብዛም የተሳካላቸው አልነበሩም፡፡ ከዚሁ ሐሜት ሳይወጣም ይኼው በምንገኝበት ጊዜ ሌሎች በበርካታ ሺዎች የሚቆጠሩ ሕገወጥ ስደተኞች፣ ከዚያው አገር በግዳጅ እየተመለሱ ነው፡፡ ግን ለዘለቄታው ምን እየተሠራ ነው ብሎ መጠየቅ ያስፈልጋል፡፡  

 የዚህ ጽሑፍ ዓለማ ይበልጡኑ ሕገወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመግታት የወጣው የሕግ አተጋባበርና አስገዳጅነት ላይ ማተኮር ነው፡፡ በመሠረቱ ስደትን ለማስታገስም እንደ ሕዝብም ሆነ መንግሥት ከሚደረጉ ጥረቶች ባሻገር፣ ሕገወጥ አዘዋዋሪዎችን በቁርጠኝነት ለማስታገስም በወንጀል ሕጉም ሆነ በሌሎች ሕጎች የተቀመጡ ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች ወሳኝ ድርሻ አላቸው፡፡ በመሆኑም ከወቅቱና ከችግሩ ስፋት አንፃር በቂ ምላሽ የማይሰጡና ወንጀለኞችን ለጥፋታቸው ተገቢና ተመጣጣኝ የሆነ ቅጣት ለመጣል የማያስችሉ ሆነው ሲገኙም በየጊዜው እየታዩ መሻሻል አለባቸው፡፡

ከሁሉ በላይ ግን  ከገጠር ቀበሌዎች እስከ መካከለኛው ምሥራቅ ግዙፍ ከተሞች የተዘረጋው ሰንሰለትና አንዳንዴም የመንግሥት አካላት ጭምር የሚሳተፉበት አደገኛው መስመር የሚበጠስበት ሕጋዊ ዕርምጃ ሊጠናከር ግድ ይለዋል፡፡ ከቀበሌ መታወቂያ ሰጪው አንስቶ በየኤምባሲና ቆንስላ ጽሕፈት ቤቶች ለሕገወጥ ድለላ ወኪል እስከ ሆነው ጥቅመኛ ድረስ ሊጋለጥ የሚችለው፣ በዚሁ የሕግ ማስፈጸም ጥንካሬ መሆኑ መዘንጋት የለበትም፡፡ አሁን እንደሚታየው ‹ሲሞቅ በማንኪያ ሲበርድ በእጅ› ዓይነት አካሄድ ግን ከአረንቋው ሊያወጣን የሚችል አይደለም፡፡

‹‹ሕገወጥ የሰዎች ዝውውር አለ›› ሲባል ይህንኑ የማዘዋወር ተግባር የሚፈጽም ሕገወጥ አዘዋዋሪ፣ ወይም ስደተኞችን በሕገወጥ መንገድ ድንበር አሻጋሪ ወንጀለኛ አለ ለማለት  ነው፡፡ ‹‹ሕገወጥ አዘዋዋሪ›› ወይም ‹‹ድንበር አሻጋሪ›› የሚባለው ወንጀለኛ ደግሞ በማንኛውም መንገድ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ሕግን በመጣስ፣ ወይም በራሱ ፈቃድ ሕገወጥ የሰዎች ዝውውር ወይም ስደተኞችን በሕገወጥ መንገድ ድንበር የማሻገር ወንጀል የፈጸመ ወይም ለመፈጸም የሞከረ ሰው ነው፡፡ ይህ ዓይነቱ ወንጀል ደግሞ ያለጥርጥር የመንግሥት አካላት ወሳኝ ድጋፍ ሳይኖርበት ሊፈጸም አይችልም፡፡ እውነት ለመናገር በአንዳንድ አገሮች የሚገኙ ቀንደኛ ደላሎች እኮ እስከ ኤምባሲዎች የሚደርስ ኔትወርክ እንዳላቸውም ይታወቃል፡፡

በሌላ በኩል በዚሁ በሕገወጥ የሰዎች ዝውውር ወይም ስደተኞችን ድንበር የማሻገር የወንጀል ድርጊት ላይ በአባሪነት የተሳተፈ ሰው እኩል ወንጀለኛ ነው፡፡ ሌሎች ሰዎች በወንጀል ድርጊቱ እንዲሳተፉ ያደራጀ ወይም በተደራጀ የወንጀል ቡድን ውስጥ አመራር የሰጠ እሱም ወንጀለኛ ነው ከተባለ፣ በድርጊቱ ውስጥ ተሳትፈው የተገኙ አካላት በግምገማ ብቻ ሊታለፉ ባልተገባ ነበር፡፡ በተለይ አሁን መንግሥት በጥልቀት በመታደስ ላይ እገኛለሁ እያለ ባለፉት ጊዜያት እንደ ሥርዓት የፈተኑትን አጀንዳዎች እየመረመረ ባላበት ጊዜ፣ ነገሩ በቸልታ ሊታለፍ አይችልም፡፡ አይገባምም፡፡

ሰዎችን ከመኖሪያ አካባቢያቸው ጀምሮ የተስፋ ቃል በመስጠት ልክ ዶላር እንደ ቅጠል የሚሸመጠጥና እንደ አሸዋ የሚታፈስ እያስመሰለ በሐሰት ወሬ እያነሳሳ ለወንጀል ድርጊቱ ወይም ለስደተኝነት የዳረገ ሰው ወንጀለኛ ነው፡፡ በአጠቃላይ በማንኛውም መንገድ የወንጀል ድርጊቱ እንዲስፋፋ ያደረገ፣ ወይም የተደራጀ ቡድን ወንጀል ለመፈጸም ማሰቡን እያወቀ ለጋራ ዓላማ በቡድን ለተሰባሰቡ ሰዎች አስተዋጽኦ ያደረገ፣ ሕገወጥ አዘዋዋሪ ወይም ድንበር አሻጋሪ በሚለው ሥር ተፈርጆ በወንጀሉ ተጠያቂ ሊሆን ይገባዋል፡፡ በዚህ ረገድ ጥቂት ደላሎችን፣ አጓጓዦችንና ደባቂዎችን በመቅጣት ብቻ ሊቆም አይገባውም፡፡ ይልቁንም በመንግሥት መዋቅርም ውስጥ የፌደራልና የክልል ፖሊስ፣ የድንበር ጥበቃ ሥራ ላይ የተሰማሩ፣ እንደ ኢሚግሬሽንና መሰል ሥፍራዎች ላይ በመሆን ወንጀሉን የሚያሳልጡ ተባባሪዎች ሊመነጠሩ ግድና አስፈላጊ ነው፡፡

እዚህም አገር ያለው አቀባይ እዚያም አገር ያለው ተቀባይ ሰዎችን በሕገወጥ መንገድ እየተቀባበሉ ለብዝበዛ በመዳረጋቸው ከሕግ ተጠያቂነት አያመልጡም፡፡ ‹‹ሰዎችን ለብዝበዛ መዳረግ›› በሚለው ጽንሰ ሐሳብ ሥር የሚጠቃለሉ በርካታ መገለጫዎች አሉ፡፡ ለምሳሌ በሌሎች ሰዎች ዝሙት አዳሪነት መጠቀም ወይም ሌላ ማንኛውም ዓይነት ወሲባዊ ብዝበዛ፣ ወይም የጉልበት ብዝበዛ፣ ወይም የግዳጅ ሥራ ወይም የአገልጋይነት ብዝበዛ አለ፡፡ ባርነት ወይም ባርነት መሰል ተግባር፣ የወሲብ አገልጋይነቱን ጨምሮ ሰውን የማይገባ አገልጋይ ማድረግ፣ ሰውን በመያዣነት መያዝ ወይም አሳልፎ ለሌላ መስጠት፣ ወይም/እና የሰው ልጅን አካል ማውጣት ወይም መውሰድ (Body Parts)፣ ወይም አስገድዶ በልመና ማሰማራት… ሁሉም በሰብዓዊነት ላይ የሚሠሩ የሕገወጥ ዝውውርና የሕገወጥ ድንበር አሻጋሪነት ተግባር አስከፊ የብዝበዛ ውጤቶች ናቸው፡፡

ማንኛውም ሰው በኢትዮጵያም ውስጥ ሆነ ከኢትዮጵያ ውጪ ለብዝበዛ ዓላማ ሲባል በአገር ውስጥ ሥራና ሠራተኛን ለማገናኘት፣ ወይም ለሥራ ወይም ለልምምድ ወደ ውጭ አገር በመላክ ሽፋን፣ ወይም የጉዲፈቻ ስምምነት በማድረግና ይህም በዚሁ ሽፋን የተደረገ ከሆነ ወንጀል ነው፡፡ በሌላ በማንኛውም ዓይነት ዓላማ ዛቻን፣ ኃይልን፣ ወይም ሌላ የማስገደጃ ዘዴ በመጠቀም በማገት፣ በመጥለፍ፣ በተንኮል በማታለል ወይም የተስፋ ቃል በመስጠት ከተጠቀመ ወንጀል ነው፡፡

ሥልጣንን ያላግባብ በመጠቀም የሰዎችን ለጥቃት ተጋላጭነት በመጠቀም ወይም ስለሌላው ኃላፊነት ያለበትን ሰው ፈቃድ ለማግኘት መደለያ ወይም ጥቅም በመስጠት፣ ወይም በመቀበል ሰዎችን የመለመለ፣ ያጓጓዘ፣ ያዘዋወረ፣ ያስጠለለ ወይም የተቀበለ ሰው ወንጀለኛ ነው፡፡ ቅጣቱም ከ15 ዓመት እስከ 25 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራትና ከ250 ሺሕ እስከ 300 ሺሕ ብር በሚደርስ መቀጫ እንደሚቀጣ በሕጉ ተደንግጓል፡፡ ነገር ግን በዚህ ወንጀል ተጠርጥሮና በመረጃ ተረጋግጦ በሕግ የተጠየቀ ሰው ስለመኖሩ ፍንጭ የለም፡፡ ወይም ወሬ ነጋሪዎች እንኳን ትንፍሽ ብለው አልሰማንም፡፡ በሚሊዮን የሚቆጠር ሕገወጥ ስደተኛ በሚናኝበት አገር ማለት ነው፡፡ ስለዚህ እርስ በርሱ የሚጋጭ ሕግና ተግባር ታቅፈን የት ልንደርስ እንችል ይሆን?

በተለይ ደግሞ የወንጀል ድርጊቱ የተፈጸመው በሕፃናት፣ በሴቶች ወይም በአዕምሮ ወይም በአካል ጉዳተኞች ላይ ከሆነ፣ ተጐጂው ለአካላዊ ወይም አዕምሯዊ ጉዳት ከተዳረገ፣ አደንዣዥ ዕፅ ወይም የጦር መሣሪያ በመጠቀም ከሆነ፣ በመንግሥት ባለሥልጣን ወይም ሠራተኛ ከሆነና ወንጀሉን የፈጸመው የተሰጠውን ኃላፊነት መከታ በማድረግ ከሆነ ወይም በተጐጂው ወላጅ፣ ወንድም፣ እህት፣ አሳዳጊ ወይም በተጐጂው ላይ ሥልጣን ባለው ሰው ከሆነ ቅጣቱ ከባድ እንደሆነም የሚታወቅ  ነው፡፡ ከ250 ሺሕ እስከ 500 ሺሕ ብርና ከ25 ዓመት በማያንስ ፅኑ እስራት ወይም ዕድሜ ልክ እስራት መቀጮ እንደሚጣልበት ሕጉ በግልጽ አስቀምጧል፡፡ በተግባርስ የምንመለከታቸው ብዙ የዜጎች ጉዳቶች በእንዴት ያለ የሕግ ማከሚያ እንዲሽሩ ተደርጎ ነው ቀዳሚው ጥያቄ ፡፡

ይህ ብቻ አይደለም! ሕገወጥ የሰዎች ዝውውርን መደገፍና ማመቻቸት ራሱን የቻለ ከባድ ወንጀል ነው፡፡ ማንኛውም ሰው እያወቀ ወይም ማወቅ ሲገባው የራሱንም ሆነ በይዞታው ሥር ያለን ቤት ሕንፃ ወይም ግቢ ለሕገወጥ የሰዎች ዝውውር ዓላማ ያከራየ ወይም እንዲጠቀሙበት የፈቀደ ሰው ወንጀለኛ ነው፡፡ ሕገወጥ ዝውውርን ለማስፋፋት የተለያዩ የኅትመት ውጤቶችን ያባዛ፣ ያጠራቀመ፣ ያሰራጨ፣ ወደ አገር ውስጥ ያስገባ ወይም ወደ ውጭ ያስወጣ ሰው ጥፋተኛ ነው፡፡ ግን በመዲናችንም ሆነ በአንዳንድ የክልል ከተሞች በዚህ አሳፋሪ ተግባር ላይ የተሰማሩ ሕገወጦች እነማን እንደነበሩ የሚታወቅ ነው፡፡

ሕገወጥ የሰዎች ዝውውርን ለማበረታታት በማሰብ የሥራ ቅጥር ተቋም በማደራጀት ያስተዳደረ፣ የመራ ወይም በገንዘብ የደገፈ፣ እያወቀ የትራንስፖርት አገልግሎት ያመቻቸ ወይም ተጐጂዎችን በአየር፣ በምድር ወይም በባህር ያጓጓዘ ወይም አገልግሎቱን ያመቻቸ ሰው በሠራው ጥፋት በወንጀል ተጠያቂ ነው፡፡

ሕገወጥ የሰዎች ዝውውርን ለማመቻቸት ሌላውን ሰው የተጭበረበረ፣ ሐሰተኛ ወይም በሕገወጥ መንገድ መታወቂያ ወይም የጉዞ ሰነድ እንዲያገኝ የረዳ፣ እንዲዘጋጅ ያደረገ፣ ያቀረበ፣ ይዞ የተገኘ ወይም እነዚህን ሰነዶች ወደ ሐሰት የለወጠ ሰው ወንጀለኛ ነው፡፡ ይህንኑ ዝውውር ለማመቻቸት የሌላውን ሰው የመንቀሳቀስ ነፃነቱን እንዳይጠቀም፣ ወይም ሕዝባዊ አገልግሎቶች እንዳያገኝ ለማድረግ የተጐጂዎችን መታወቂያ ወይም የጉዞ ሰነድ መያዣ ያደረገ፣ በኃይል የነጠቀ፣ የሰወረ ያጠፋ ወይም እንዲጠፋ ያደረገ ከሆነ ከ15 እስከ 25 ዓመት በሚደርስ እስራትና ከ250 ሺሕ እስከ 300 ሺሕ ብር በሚደርስ ገንዘብ እንደሚቀጣ ተደንግጓል፡፡

ሕገወጥ ስደተኞችን የሚመለከት ሕግም አለ፡፡ ለምሳሌ የውጭ አገር ዜጋ በኢትዮጵያ ውስጥ እንዲቆይ ወይም እንዲኖር ለማድረግ የመኖሪያ ፈቃድ፣ መታወቂያ ካርድና ሌሎች የጉዞ ሰነዶች የሚያስፈልግ መሆኑን እያወቀ፣ ወይም ማወቅ ሲገባው ሕገወጥ ስደተኛ ወደ ኢትዮጵያ እንዲሻገር ድጋፍ የሰጠ፣ ወይም በሕገወጥ መንገድ ድንበር የተሻገረ ስደተኛ በኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ እንዲቆይ የረዳ ማንኛውም ሰው ከሦስት እስከ አምስት ዓመት የሚደርስ የእስራት ቅጣት ያገኘዋል፡፡

በተለይ በአሁኑ ጊዜ ማለትም ጽንፈኛ አሸባሪ ቡድኖች የአገሮችን ሰላም ለማናጋት እየተንቀሳቀሱ ባሉበት ሁኔታ፣ ሕገወጥ የውጭ አገር ሰዎችን መቀበልና መኖሪያ መስጠትና ማስጠለል፣ ያለሕጋዊ የመኖሪያ ፈቃድና መታወቂያ ወረቀት እንዲንቀሳቀሱ ሽፋን መስጠት አደጋው የከፋ መሆኑን ከወዲሁ አውቀን መጠንቀቅ አለብን፡፡ ለማይረባ ጥቅም አገርን አሳልፎ የመስጠት ያህል በመሆኑ በዚህ ጉዳይ ላይ ያለንን ግንዛቤ ማጠናከር አለብን፡፡ የማይታወቅ የውጭ አገር ሰው ሲያጋጥመን ወዲያውኑ ለፖሊስ ማሳወቅም ተቀዳሚ ኃላፊነታችን ነው፡፡

 የወንጀል ድርጊቶችን አለማሳወቅ በራሱ ጥፋት ነው፡፡ በወንጀል ድርጊት የተጠረጠረን ሰው ወይም ወንጀል ሊፈጽም የተዘጋጀን ሰው ለመያዝ፣ ለመክሰስ ወይም ለማስቀጣት የሚያስችል መረጃ ወይም ማስረጃ እያለው ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት ወይም አሳማኝ በሆነ ምክንያት መረጃውን/ማስረጃውን ለፖሊስ ወይም ለሌላ አግባብነት ያለው አካል ወዲያውኑ ያልገለጸ፣ ወይም ሐሰተኛ ማስረጃ የሰጠ ሰው ከአምስት ዓመት የማያንስና ከአሥር አመት የማይበልጥ እስራትና ከአሥር ሺሕ እስከ 50 ሺሕ ብር በሚደርስ መቀጮ ይቀጣል፡፡ ይህም ስለሕገወጥ ስደተኞች በወጣው የአዋጅ ድንጋጌዎች በግልጽ ሠፍሮ ይገኛል፡፡

ማንኛውም ሰው ሕገወጥ ዝውውርንና ሕገወጥ የድንበር ማሻገርን ወንጀል በተመለከተ መረጃ ወይም ማስረጃ የማቅረብ ግዴታውን ላለመወጣት ሲል ልዩ መብትን በምክንያትነት መጠቀም አይችልም፡፡ ግዴታውን ባለመወጣቱ ምክንያት ተጠያቂ ይሆናል፡፡ ይህ ኃላፊነት በእያንዳንዳችን ላይ አለ፡፡ ከሁሉ በላይ ግን የመንግሥትና የመንግሥት አካላት ዋነኛ ኃላፊነት ነው፡፡

በአጠቃላይ ከዚህ በላይ እንዳየነው ሕገወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመግታት በአሁኑ ጊዜ ከበፊቱ በጣም የተሻለ የሕግ ማዕቀፍ አለን፡፡ ፈተናው ግን ከመተግበሩ ላይ ነው፡፡ በመሠረቱ ጥሩ አዋጅ ማውጣቱ ብቻ ዘላቂ መፍትሔም አይደለም፡፡ የሕግ ማዕቀፍ ማበጀቱ በራሱ ታላቅ ሥራ መሆኑ ባይካድም፡፡ ዋናው ነገር ግን ይህን  የሕግ ማዕቀፍ ተግባራዊ ለማድረግ ወደ መሬት ሲወርድ የሚያስገኘው የአፈጻጸም ውጤት ነው፡፡      

ሕጉ ምን ውጤት አስገኘ? ብለን አዋጁን ለማስፈጸም ሥልጣን የተሰጣቸውን ተቋማት መጠየቅ መብታችን ነው፡፡ እነሱም ቢሆን በአዋጁ መሠረት ሕገወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመግታት ምን ያህል እንደተንቀሳቀሱ ራሳቸውን መገምገም አለባቸው፡፡ ሕገወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመግታት ሕጉ ምን ያህል ጉልበት ሆናቸው? ስንት የነበረው ሕገወጥ ዝውውር አሁን ስንት ደረሰ? አዋጁን በመፈጸም ረገድ ጥንካሬና ድክመታችን ምን ላይ ነበር? ወደፊት ያሉት መልካም ዕድሎችና ተግዳሮቶች ምንድን ናቸው? ከእስካሁኑ አሠራር ምን ትምህርት ተገኘ?… ለሚሉት ጥያቄዎች መልስ ማግኘት አለብን፡፡

በእርግጥ አዋጁ ገና አዲስ ቢሆንም ሕገወጥ ስደተኛው እየበዛ ሲገፈተር በምን እንመልሰው ብሎ ከመጨነቅ መታሰብ ያለበት ሕገወጥ መጓጓዙ በሕግ እንዴት ይገታ የሚለው ነውና በአጽንኦት መታየት አለበት፡፡ ሕዝብን ከመከራ አገርንም ከውርደት ማዳን የሚቻለው በዚሁ መንገድ ማሰብ ሲቻል ነውና፡፡

ከአዘጋጁ፡- ጽሑፉ የጸሐፊውን አመለካከት ብቻ የሚያንፀባርቅ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

 

Standard (Image)

ጣዕም መቀየሪያዎች የተጨመሩባቸው የሺሻ ትምባሆ ምርቶች መስፋፋትና ሕገወጥነት

$
0
0

በወንዱ በቀለ ወልደማርያም  

በኅብረተሰብ ጤና ዘርፍ ኢትዮጵያ ከፍተኛ የሚባል ለውጥ ካስመዘገቡ አገሮች ተርታ ትመደባለች፡፡ የጤና አገልግሎትን በቀበሌ ደረጃ ለማስፋፋት፣ በተለይም በዝቅተኛ የኢኮኖሚ ደረጃ ላይ የሚገኘውን የኅብረተሰብ ክፍል ማዕከል ያደረገና በዓለም አቀፍ ደረጃ ዕውቅና የተቸረውን የጤና ኤክስቴንሽን መርሐ ግብር ተግባራዊ በማድረግ፣ የዓለም መንግሥታት ድርጅትን የጤና የሚሊኒየም ግቦችን ለማሳካት ችላለች፡፡ እንደ አብዛኛው ታዳጊ አገሮች ሁሉ ባለፉት ዓመታት የመንግሥት የጤና ፕሮግራሞችና የአጋር ድርጅት ትኩረቶች ውስጥ ወባ፣ ኤችአይቪ/ኤድስና ሳንባ ነቀርሳ የመሳሰሉ ተላላፊ በሽታዎች የመከላከልና ቁጥጥር ሥራ፣ እንዲሁም የሕፃናትና እናቶች ጤናን ማሻሻል በዋናነት ይጠቀሳሉ፡፡ ሆኖም ግን ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ የአገሪቱ የበሽታዎች ሥርጭት ሁኔታ በለውጥ ሒደት ላይ ያለ ሲሆን፣ በተለይም በከተማዎችና በዙሪያቸው ባሉ ሥፍራዎች በመስፋፋት ላይ የሚገኙት የልብ፣ የመተንፈሻ አካላት፣ ስኳርና ካንሰርን የመሳሰሉ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ይጠቀሳሉ፡፡

ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች እየተስፋፉ በመምጣታቸው ምክንያት የጤና ጥበቃ ሚኒስቴርን የትኩረት አቅጣጫ የሚያሳይ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች መከላከያና መቆጣጠሪያ ብሔራዊ የድርጊት መርሐ ግብር ስትራቴጂ (National Strategic Action Plan (NSAP) for Prevention & Control of Non Communicable Diseases in Ethiopia) በ2007 ዓ.ም. ተዘጋጅቷል፡፡ ለእነዚህ በሽታዎች ወይም የጤና ሁኔታዎች ዋነኛ ምክንያቶች ተብለው ከተለዩት መካከልም ማንኛውንም ዓይነት የትምባሆ ምርት መጠቀም፣ ከመጠን በላይ የአልኮል መጠጦችን መውሰድ፣ በቂ የአካል እንቅስቃሴ አለማድረግና ለጤና ተስማሚ ያልሆኑ ምግቦችን ማዘውተር ይጠቀሳሉ፡፡

ከብሔራዊ የድርጊት መርሐ ግብር ስትራቴጂው በተጨማሪ በተመሳሳይ ዓመት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለተላላፊ ላልሆኑ በሽታዎች አጋላጭ ከሚባሉት ዋነኛ መንስዔዎች አንዱ የሆነውን የትምባሆ ምርትን በሚመለከት፣ በዓለም የጤና ድርጅት የወጣውን የትምባሆ ምርት ቁጥጥር ማዕቀፍ ኮንቬንሽን አፅድቋል፡፡ ተግባራዊነቱን የኢትዮጵያ የምግብ፣ መድኃኒትና ጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለሥልጣን እንዲከታተል ኃላፊነት በአዋጅ ቁጥር 822/2007 ሰጥቷል፡፡

በዚህ አዋጅ መሠረት የትምባሆ ምርት ቁጥጥር ማዕቀፍ ኮንቬንሽን ማፅደቂያ በከፊል ለማስፈጸም ባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ ከሁለት ዓመት በፊት የትምባሆ ቁጥጥር መመርያ አውጥቷል፡፡ የትምባሆ ቁጥጥር መመርያው ከአፈጻጸም ጋር በተያያዘ የተለያዩ ክፍተቶች ቢኖሩበትም፣ ሕፃናትንና ታዳጊ ወጣቶችን በእጅጉ ሱስ አስያዥ የሆነው ኒኮቲክ ለሚባለው ንጥረ ነገር ተጋላጭነት ለመቀነስና ብዛት ባላቸው አገሮች እያደገ በመጣው የትምባሆን ምርት ጣዕም መቀየሪያ እንዳይጨመርበት በመከልከል፣ ሊመሰገን የሚገባው የሕግ አቅጣጫ አስቀምጧል፡፡ ተመሳሳይ የሆኑ ድንጋጌዎች የያዘ የትምባሆ ምርት ቁጥጥርን መመርያ በተወሰኑ ክልሎችና በከተማ አስተዳደር ደረጃ ጭምርም የወጣ ሲሆን፣ ይህን ዓይነት ምርት በክልሎች ውስጥ ለሽያጭ ማቅረብ፣ መሸጥና ማከፋፈል የተከለከለ ነው፡፡ 

የኢትዮጵያ የምግብ፣ መድኃኒትና ጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለሥልጣን ባወጣው የትምባሆ ምርት ቁጥጥር መመርያ ቁጥር 28/2007 መሠረት፣ የትምባሆ ምርት የሺሻ ትምባሆን ጨምሮ ማንኛውንም በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ ከትምባሆ ቅጠል የተዘጋጀ በማጨስ፣ በመሳብ፣ በማኘክ፣ በማሽተት ወይም በሌላ መንገድ የሚወሰድ ንጥረ ነገርን እንዲያካትት ሆኖ ተተርጉሟል፡፡ ይህ ማለት ትምባሆ በስፋት በሚታወቀው የሲጋራ ምርት ብቻ ሳይወሰን የሚታኘክን፣ እንዲሁም የተለያዩ የማጨሻ መሣሪያዎችን በመጠቀም የሚጨስ እንደ ሺሻ ትምባሆ ያለን ምርት ያካትታል፡፡ ይህ የትምባሆ ምርት ትርጉም በተወካዮች ምክር ቤት በፀደቀው የትምባሆ ምርት ቁጥጥር ማዕቀፍ ኮንቬንሽን ጋር የተጣጣመ ሆኖ፣ የሺሻ ትምባሆን ወይም በባህላዊ መንገድ የሚዘጋጅ ጋያን በግልጽ እንዲያካትት ሆኖ ነው የተቀመጠው፡፡

የሺሻ ትምባሆን በትምባሆ ምርት ሥር በግልጽ መቀመጡ ሺሻ ከትምባሆ ምርት የተለየ እንደሆነ ለሚገነዘቡ ሰዎች የግልጽነት ችግር ወይም (የግንዛቤ ክፍተት) እንዳይፈጠር ይረዳል፡፡ ስለዚህ ሲጋራና የሺሻ ትምባሆን ጨምሮ ሌሎች በመመርያው የተካተቱ የትምባሆ ምርቶች ወይም ውጤቶች ሕጋዊ ቢሆኑም፣ ጥብቅ ቁጥጥር የሚደረግባቸው ለጤና እጅግ ጎጅ የሆኑ ምርቶች ሲሆኑ እነዚህ ምርቶች ሕገወጥ የሚሆኑበትም አግባብ መመርያው ያስቀምጣል፡፡

ምንም እንኳን የሺሻ ትምባሆ ቁጥጥር የሚደረግበት ለጤና እጅግ አደገኛ የሆነ ሕጋዊ ምርት ቢሆንም፣ ሕገወጥ የሚያደርገውም ሁኔታ በትምባሆ ምርት ቁጥጥር መመርያ ቁጥር 28/2007 አንቀጽ 10 ሥር ተቀምጧል፡፡ በዚህ አንቀጽ መሠረት የሺሻ ትምባሆ ሳይቀጣጠል ወይም በሚጨስበት ጊዜ ከትምባሆ ጣዕም ውጪ እንደ ፍራፍሬ፣ ቸኮሌት፣ ቫኒላ፣ ማር፣ ከረሜላ፣ ካካዎ፣ ሜንቶል፣ ሚንት፣ የአልኮል መጠጥ፣ ዕፅዋት (Herbs) ወይም ቅመም (Spice) የመሳሰሉ የተለየ (Distinguishable) ጣዕም ወይም ቃና የሚሰጥ ይዘት ያለው ከሆነ ሕገወጥ እንደሆነ መመርያው ይደነግጋል፡፡ ይህንን ክልከላ ተፈጻሚ ለማድረግም ማንኛውም ሰው እንደዚህ ዓይነት ተጨማሪ ጣዕም ያለው ምርት (Flavored Tobacco Product) ወደ አገር ውስጥ ማስገባት፣ በጅምላ መሸጥ፣ ማከፋፈል፣ መሸጥ ወይም ለመሸጥ ማቅረብ እንደማይችል አስቀምጧል፡፡

በተመሳሳይ ሁኔታ የትምባሆ ምርት ይዘቶች ለጤና የሚጠቅም ወይም ጤና ላይ የሚያስከትልን ጉዳት የሚቀንስ የማስመሰል ውጤት የሚፈጥሩ እንደ ቫይታሚን፣ ፍራፍሬና አትክልቶች፣ አሚኖ አሲድ፣ ጠቃሚ ፋቲ አሲዶችና ኃይልንና ጥንካሬን ከመስጠት ጋር የተያያዙ አነቃቂ ውህዶችን የያዘ የትምባሆ ምርት ወደ አገር ውስጥ ማስገባት፣ በጅምላ መሸጥ፣ ማከፋፈል፣ መሸጥ ወይም ለመሸጥ ማቅረብ እንደማይቻል በሌላ ንዑስ አንቀጽ ሥር ይደነግጋል፡፡ 

የሺሻ ትምባሆን በሚመለከት ሁለት ዋና ዋና የግንዛቤ ክፍተቶች በኅብረተሰቡ ውስጥ ይስተዋላሉ፡፡ እነዚህም ሁሉም የሺሻ ምርቶች በሕግ የተፈቀዱ እንደሆኑና ሺሻ ከትምባሆ የተለየ ምርት እንደሆነ ማሰብ ናቸው፡፡ እነዚህ እሳቤዎች ትክክል አይደሉም፡፡ በመጀመርያ ደረጃ በአሁኑ ጊዜ ኢትዮጵያ ውስጥ በተለያዩ መዝናኛ ቤቶች፣ እንዲሁም ሕጋዊ ባልሆኑ የሺሻ ማስጨሻ ቤቶች በስፋት ጥቅም ላይ እየዋለ ያለው ከትምባሆ ሞላሰስ የሚዘጋጅ የሺሻ ምርት ነው፡፡ ስለዚህ ሺሻ የትምባሆ ምርት አይደለም የሚለው እሳቤ ትክክለኛ ያልሆነ ድምዳሜ ነው፡፡ ይህ ማለት ግን ከትምባሆ ቅጠል ውጪ የሚዘጋጅ ሌላ ዓይነት ሺሻ የለም ማለት አይደለም፡፡ በሁለተኛ ደረጃ በአሁኑ ጊዜ በስፋት ጥቅም ላይ እየዋለ ያለው የሺሻ ትምባሆ እንደ ፍራፍሬ፣ ሜንቶልና ሚንት የመሳሰሉ ተጨማሪ ጣዕም የተጨመረበት ምርት በመሆኑ፣ የትምባሆ ቁጥጥር መመርያ ስለሚጥስ ሕገወጥ ነው፡፡

ስለዚህ በዚህ ዓይነት ምርት ላይና ሺሻውን በሚያቀርቡ የመዝናኛ ቤቶች ላይ የሕግ አስፈጻሚ አካላት አግባብ ያለውን ዕርምጃ ለመውሰድ የሕግ መሠረት አላቸው፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ የሚስተዋለው የግንዛቤ ችግር ፖሊስና ደንብ አስከባሪዎችን ጨምሮ ሌሎች የሕግ አስፈጻሚ አካላት በሺሻ ቤቶች ላይ ዕርምጃ ለመውሰድ የሕግ መሠረት የላቸውም የሚለው ድምዳሜ ትክክል አይደለም፡፡ ለምሳሌ ከትንሽ ወራት በፊት ‹በታዲያስ አዲስ› የሸገር ሬዲዮ ፕሮግራም ላይ አንድ የሕግ ባለሙያ ቀርበው የባለሥልጣኑን የትምባሆ መመርያን በመጥቀስ የሺሻ ምርቶች ሕጋዊ እንደሆኑ፣ እንዲሁም ፖሊስ በእነዚህ ምርቶች ላይ ዕርምጃ ለመውሰድ የሕግ መሠረት እንደሌለው የቀረበውና በማኅበራዊ ድረ ገጸች የተሠራጨው የሕግ ትንተና፣ የመመርያውን አንቀጽ 10 ካለማየትና በስፋት በጥቅም ላይ እየዋለ የሚገኘው የሺሻ ምርት ሕጋዊ ያልሆነ ጣዕም የተጨመረበት ምርት እንደሆነ ካለመረዳት የመነጨ ነው፡፡

ተጨማሪ ጣዕም ከሌለው ምርት ጋር ሲነፃፀር ተጨማሪ ጣዕም የሚጨመርበት የትምባሆ ምርት በተለይ ሕፃናትን በእጅጉ እንደሚስብ፣ የበለጠ ሱስ እንደሚያሲዝና ልጆችን በማማለል ለማጨስ እንደሚያነሳሳ በጥናት የታወቀ እውነታ ነው፡፡ በተለያዩ አገሮች ተጨማሪ ጣዕም የሚሰጡ ነገሮች በተጨመረበት የትምባሆ ምርት ምክንያት፣ ትምባሆ ማጨስ የጀመሩ ከአሥራ ስምንት ዓመታት በታች ያሉ ልጆችን የሚመለከት በተደረጉ የኅብረተሰብ ጤና ቅኝትና ኢፒዲሚዮሎጅ ጥናቶች መሠረት በትምባሆ ምርት ውስጥ እንደ ፍራፍሬ፣ ማር፣ ከረሜላ፣ ካካዎ፣ ሜንቶልና ሚንት የመሳሰሉ ተጨማሪ ጣዕምን መጨመር ምርቶቹ ሳቢ በመሆናቸው ለበለጠ ሱሰኛነት አጋላጭ እንደሚሆኑ ታውቋል፡፡

በእርግጥ የፍራፍሬ፣ ሜንቶል ወይም ሚንት ቃናን የመሳሰሉ ተጨማሪዎች ትምባሆ በሚጨስበት ጊዜ በጉሮሮ ላይ የሚፈጠረው የማይስማማ ስሜት ወይም እንደ ማሳል ያለን የሰውነት ተፈጥሯዊ ምላሽ ስለሚደብቅ ወይም ስለሚቀንስ፣ ለሚያጨሰው ሰው የትምባሆ ጭሱን በቀላሉ ወደ ሳንባ ማስገባት ያስችላል፡፡ ይህ ደግሞ ለሺሻ ትምባሆ አምራቾች የኒኮቲን ጥገኛ የሆነን ወጣት ለመመልመል ዓይነተኛ የሆነ መንገድ ነው፡፡ ልጆችም የትምባሆን ጎጂነት በአግባቡ ከመረዳታቸው በፊት የኒኮቲን ጥገኛ ይሆናሉ፡፡ ጣዕም መቀየሪያዎችን በሺሻ ትምባሆ ውስጥ መጨመር የተከለከለበት ዋነኛ የኅብረተሰብ ጤና ምክንያት ይኼው ነው፡፡ በተለያዩ አገሮች የትምባሆ አምራች ኢንዱስትሪ የወጡ የውስጥ ሰነዶችም እንደሚያሳዩት አምራቾች የትምባሆ ሱሰኛ የሚሆን የወደፊት አጫሽ ወይም ተጠቃሚ ለመፍጠር ታዳጊ ልጆችንና ወጣቶች ላይ ከማነጣጠር ባሻገር ብዙ ዓይነት መንገድ እንደሚከተሉ ይታወቃል፡፡

በአሁኑ ጊዜ ጣዕም መቀየሪያዎች የተጨመረበት ሕገወጥ የሺሻ ትምባሆ መጠቀም በአዲስ አበባ፣ በአንዳንድ የክልል ከተሞች ባሉ የምሽት መዝናኛ ቤቶች፣ እንዲሁም ሕጋዊ ባልሆኑ የሺሻ ማስጨሻ ቤቶች በስፋት እየታየ ነው፡፡ በእነዚህ ቦታዎች የሚቀርቡ የሺሻ ምርቶች ሁሉም በሚያስብል ሁኔታ በሕግ የተከለከሉ እንደ ፍራፍሬና ሜንት ይዘቶች ያላቸው ምርቶች ከመሆናቸው ባሻገር፣ ወደ አገር ውስጥ የገቡበትም መንገድም ሕጋዊ መንገድ የተከለ ነው ለማለት ያስቸግራል፡፡ እነዚህ ምርቶች ሕፃናትን፣ ወጣቶችንና ሴቶችን በተለየ ሁኔታ ሱሰኛ በማድረግ የኒኮቲን ጥገኛ የማድረግ አቅማቸው ጣዕም መቀየሪያዎች ካልተጨመረባቸው የትምባሆ ምርቶች አንፃር ከፍተኛ በመሆኑ፣ የፌዴራልና ክልል አስፈጻሚ አካላትን ትኩረት ይሻል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ጣዕም መቀየሪያዎች በተጨመረባቸው የሺሻ ትምባሆዎች ማጨስ ለጀመረ ወጣት ሲጋራ ለማጨስ በር ከፋች እንደሆኑ ጥናቶች ያመለክታሉ፡፡ ግማሽ ያህሉ የኢትዮጵያ የሕዝብ ቁጥር ከ15 ዓመታት በታች፣ እንዲሁም ወደ 70 በመቶ ደግሞ ከ30 ዓመታት በታች የሆነ ወጣት እንደመሆኑ መጠን፣ የኅብረተሰብ ጤናን ከማጎልበትና ወጣቶችን ከመጠበቅ አንፃር ከፍተኛ ሥራ መሠራት አለበት፡፡ በተለይ ፖሊስና የደንብ አስከባሪዎች እነዚህን ምርቶች ለመሰብሰብና በሺሻ ማስጨሻ ቤቶች ላይ ዕርምጃ ለመውሰድ በቂ የሕግ ሥልጣን ስላላቸው አስተዋጽኦ ማድረግ እንደሚችሉ ባለሙያዎች ይስማሙበታል፡፡

ከአዘጋጁ፡- ጸሐፊው የማቲዎስ ወንዱ የኢትዮጵያ ካንሰር ሶሳይቲ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ናቸው፡፡ ጽሑፉ የጸሐፊውን አመለካከት ብቻ የሚያንፀባርቅ ሲሆን፣ በኢሜይል አድራሻቸው wondu@mathycancersoc.orgማግኘት ይቻላል፡፡ 

Standard (Image)

ደንባራዎቹ መገናኛ ብዙኃን

$
0
0

 

(ክፍል አንድ)

በጀማል ሙሐመድ (ዶ/ር)

የህንዱገጠመኝ

እ.ኤ.አ. በ1998 በደልሂ ከተማ፣ በህንዳዊው የመገናኛ ብዙኃን ተቋም፣ ከ18 ታዳጊ አገሮች የተውጣጣን 19 ጋዜጠኞች ከትመናል ከደቡብ አሜሪካ፣ ከአፍሪካና ከእስያ፡፡ ለምን ተግባር? ስለ የልማት ጋዜጠኝነት ልንማር፡፡ እስካሁን የማልረሳውና በጣም የሚገርመኝ ጋዜጠኞቹ ደጋግመው ያቀርቡት የነበረ አንድ ስሞታ አለ፡፡ ‹‹የልማት ዘገባ መሥራት አስደሳች አይደለም›› የሚል ያቀርቡት የነበረው ዋና ምክንያታቸው ደግሞ ‹‹የልማት ፕሮግራሞች ወይም መጣጥፎች ታዳሚውን አያስቡም፣ የመነበብ፣ የመሰማት ወይም የመመልከት ፍላጎትን የሚዘጉ ናቸው፤›› የሚል ነው፡፡ የጋዜጠኝነትን ‹‹ሀሁ›› እየተማርኩ በነበርኩበት ወቅት ስለሆነ፣ ልማትን ከሚናፍቁ ታዳጊ አገሮች፣ ስለ የልማት ጋዜጠኝነት ሊማሩ መጥተው፣ የልማት ዘገባን ወይም የልማት ጋዜጠኝነትን የሚያስጠላ ቀለም ቀብተው ማቅረባቸው ግራ አጋባኝ፡፡ በዚህ ላይ በዲፕሎማ ደረጃ ልንማር የሄድነው፣ ራሱን የልማት ጋዜጠኝነትን ነው፡፡ ጥያቄው በአገራችን በመንግሥት መገናኛ ብዙኃን ውስጥ በሚሠሩ ጋዜጠኞች መካከል መኖሩን ለመረዳት ከህንድ ከተመለስኩ በኋላ ብዙም ጊዜ አልፈጀብኝም፡፡ እናም የልማት ጋዜጠኝነት ወይም ዘገባ ‹‹በደባሪነት›› የመከሰሱ ጉዳይ ለረጅም ጊዜ በአዕምሮዬ ሲብላላ መቆየቱ አልቀረም…    

የመገናኛብዙኃንባለቤትነት

መገናኛ ብዙኃንን በተመለከተ፣ በዓለም ዙሪያ ሦስት ዓይነት የባለቤትነት ዘርፎች አሉ፡፡ የመንግሥት፣ የንግድና የማኅበረሰብ፡፡ የእኔ ትኩረት በመንግሥት ሥር ስለሚገኙ መገናኛ ብዙኃን ስለሆነ፣ በእሱው ላይ ብቻ አተኩራለሁ፡፡ የልማት ጋዜጠኝነትም በዋናነት የሚቀነቀነው በመንግሥት መገናኛ ብዙኃን ወይም መገናኛ ብዙኃኑን በሚያስተዳድረው መንግሥት ነው፡፡ እንደሚታወቀው፣ የመንግሥት መገናኛ ብዙኃን በዋናነት አንድን አገር እየመራ ያለን መንግሥት ፍላጎትና አጀንዳ ለማራመድ የሚሠሩ ናቸው፡፡ ወይም አገላለጹን ለስለስ እናድርገው ካልን፣ አንድን አገር እየመራ ያለው መንግሥት ያወጣቸው ልዩ ልዩ የልማት መርሐ ግብሮች ከግብ እንዲደርሱ እየተካሄደ ያለውን ርብርብ ከሙሉ ልብ ማገዝ ነው ዓላማቸው፡፡

የኢትዮጵያ መንግሥት በሥሩ የሚቆጣጠራቸው መገናኛ ብዙኃን የሚከተሉትን ፍልስፍና በተመለከተ፣ የልማት ጋዜጠኝነት (Development Journalism) መሆኑን ውሎ አድሯል፡፡ በልማት ጋዜጠኝነት ጽንሰ ሐሳብ መሠረት መገናኛ ብዙኃን በሚሠሩበት አገር እየተካሄደ ያለው ፖለቲካዊ፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት ውስጥ ግንባር ቀደሙን ሚና መጫወት አለባቸው፡፡ ልማቱ እንዲፋጠን፣ እንዲስፋፋና የኅብረተሰቡን ኑሮ ትርጉም ባለው መንገድ እንዲቀይር ተገቢውን መረጃ በመስጠትና በማስተማር ተግተው መሥራት አለባቸው፡፡

የልማትጋዜጠኝነትመሠረታዊሐሳብናትግበራው

የልማት ጋዜጠኝነት መሠረታዊ ሐሳብ እንደሚያስረዳው፣ መገናኛ ብዙኃኑ የልማት ፕሮጀክቶች የመሠረት ድንጋይ ሲጣል ሳይሆን፣ ፕሮጀክቶቹን ለማቀድ የመንግሥት አካላትም ሆነ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ኅብረተሰቡን ሲያወያዩ መገናኛ ብዙኃኑ ከሥፍራው በመገኘት የውይይቱን ሒደት መዘገብ አለባቸው፡፡ ኅብረተሰቡ ስላሉበት የልማት ችግሮች በራሱ አነሳሽነት ውይይት ካደረገም እንዲሁ መዘገብ ይገባቸዋል፡፡ እንዲያውም የዚህ ዓይነቱን ተነሳሽነት ይበልጥ መደገፍ አለባቸው፡፡ በኅብረተሰቡ ቁርጠኝነት የሚጀመር የልማት ጥረት ከግብ የመድረስና ዘላቂ የመሆን ዕድሉ እጅግ ሰፊ ነውና፡፡

በዚህ መንገድ የልማት ችግሮችን ለመለየት በሚካሄዱ የውይይት መድረኮች የጀመሩትን የዘገባ ሥራ፣ በዕቅድ ውይይቱ፣ ከዚያም በተለያዩ ደረጃዎች የሚከወኑትን የልማት ፕሮጀክቱ ትግበራዎች በቅርብ በመከታተል ይዘግባሉ፡፡ በልማት ፕሮጀክቱ ምን ሊሠራ ነው የታሰበው? ያ የተለየ ፕሮጀክት እንዴትና ለምን ተመረጠ? በትግበራው ኅብረተሰቡን በምን መንገድ ያሳትፋል? የመንግሥትስ ሚና ምንድነው? የትግበራ ሒደቱ ምን ይመስላል? ያጋጠሙት ዋና ዋና ችግሮች ካሉ ምን ምን ናቸው? በልማት ፕሮጀክቱ ክወና ላይ የፈጠሩት ተፅዕኖስ ምንድነው? በምንስ መንገድ ተፈቱ? ለችግሮቹ መከሰት ተጠያቂው ማን ነው? በምን መንገድ ዕርምት ተወሰደ? ሲጠናቀቅ እነማንን ተጠቀሚ ያደርጋል? የትኛውን የኅብረተሰብ ችግር በዘላቂነት ይፈታል? ሌሎች የልማት ፕሮጀክቶች የሚቀስሙት ትምህርትና ተመክሮ ምንድነው?    

በአጭሩ በልማት ጋዜጠኝነት ፍልስፍና ላይ ተመሥርቶ የሚሠራ መገናኛ ብዙኃን ሚና ‹‹እዚህ ይኼ ሆነ፣ እዚያ ያ ተከሰተ›› እያሉ መሮጥ አይደለም፡፡ ማለቂያ የሌለውን የስብሰባዎች ዘገባ ማዥጎድጎድ አይደለም፣ ለስብሰባዎቹ የተለያዩ ስሞችን በመለጠፍ ‹‹ሰሚናር፣ ወርክሾፕ፣ ሥልጠና፣ የጋራ መግባቢያ መድረክ፣ ወዘተ›› እያሉ የዜና ድሪቶ ማግተልተል አይደለም፡፡ ወይም የልማት ፕሮጀክቱ እስከሚመረቅ ጠብቀው አብረው ሽር ጉድ ማለት፣ አብረው ‹‹ሪቫን›› ማስቆረጥ አይደለም ሚናቸው፡፡

መገናኛ ብዙኃኑ የልማት ሥራዎቹ የሒደት አካል መሆን አለባቸው፡፡ ስኬቱን ለማብሰር፣ አሜኬላውን አብረው መጥረግ አለባቸው፣ በዘገባ ሥራቸው፡፡ የአንድ የልማት ፕሮጀክት የመሠረት ድንጋይ ሲጣል ካጯጯሁ በኋላ፣ የትማቸውን ከርመው የፕሮጀክቱ ሥራ፣ በአግባቡም ይሁን አላግባብ የፈጀውን ጊዜ ፈጅቶ፣ የበላውን በጀት በልቶ ተጠናቆ ‹‹ሪቫን›› ሲቆረጥ (ሲመረቅ) በለመደ አፋቸው ማጯጯህ አይደለም፡፡ ይኼማ ለፕሮፓጋንዳ ተግባር የተሰለፈ (ያሰፈሰፈ) ብለው ይሻላል፡፡ መገናኛ ብዙኃን ተግባር ነው፡፡ ከዚህ ዓይነቱ የመገናኛ ብዙኃን ዘገባ ሕዝቡ የሚያገኘው ፋይዳ በጣም ውስን ነው ለምን ቢሉ የእሱ ተሳትፎም ይሁን የባለቤትነት ድርሻ ያልታየበት ነውና፡፡       

አብዛኛው ሕዝብ አርሶ አደር ብቻ ሳይሆን ድሃ በሆነባት አገር ኢትዮጵያ  መገናኛ ብዙኃን፣ በተለይም በመንግሥት (በፌዴራልም ሆነ በክልል) ቁጥጥር ሥር የሚገኙት፣ በአገሪቱ የሚካሄደውን የልማት ሥራ ከመደገፍ ውጭ አማራጭ ሊኖራቸው አይችልም፡፡ በድርቅ፣ እልፍ ሲልም በርሀብ በምትጠቃ አገር ኢትዮጵያ የመንግሥት መገናኛ ብዙኃን በአገሪቱ የሚካሄደውን የልማት ሥራ ከመደገፍ ውጭ አማራጭ ሊታያቸው አይገባም፡፡ አንድ የመንግሥት ኃላፊ በአንድ መድረክ ላይ ሲናገር እንደ ሰማሁት፣ ልብሱን በመርፌ እየጠቀመ የሚለብስ ሰው ያለው ኢትዮጵያ ውስጥ ነው፡፡ ድህነታችን ያን ያህል የከፋ የከረፋ ነው፡፡

እናም መገናኛ ብዙኃኑ በየአደባባዩ ያለውን (የህዳሴውን ግድብ፣ የባቡር መንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶችን፣ የታላላቅ መንገድ ግንባታዎችን፣ ወዘተ) ብቻ ሳይሆን በየጓዳውና በየጎድጓዳው እየተከናወኑ ያሉ የልማት ጥረቶችን በጥልቀት መዘገብ አለባቸው፡፡ በሌላ አነጋገር የልማት ሥራ ተብሎ የሚናቅ ነገር መኖር የለበትም፡፡ ዜጎች ራሳቸውን ከድህነት ለማውጣት የሚያደርጉትን መፍጨርጨር፣ እያገኙ ያሉትን ድጋፍ፣ እያጋጠማቸው ያለውን እንቅፋትና እንቅፋቱ የሚወገድበትን መንገድ፣ እያስመዘገቡ ያሉትን ውጤት፣ ወዘተ ጠንክሮ መዘገብን ይጠይቃል፡፡ የመንግሥት ተቋማት፣ ልዩ ልዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች፣ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፣ የግል ባለሀብቶች፣ ወዘተ የሚያደርጉትን ጥረት ብቻ ሳይሆን፣ እልህ አስጨራሽ ትግልና የትግሉን ዳገትና ቁልቁለት መንገር ብቻ ሳይሆን አሳምረው ማሳየት ይጠበቅባቸዋል፡፡ እንደ ተላጠ መንደሪን የሚያጓጓውን የትግሉን ፍሬ ብቻ ሳይሆን፣ ያን ፍሬ ገና ከችግኙ ሊያጨነግፉ ተጋርጠው የነበሩ መሰናክሎችን፣ የተከፈሉ እልህ አስጨረሽ ጥረቶችን፣ ወዘተ ልቅም አድርገው ማሳየት ይጠበቅባቸዋል፡፡

ይህንሲያደርጉአምስትዋናዋናፋይዳዎችይገኛሉ

አንድ፣ በተመሳሳይ የልማት ተግባር ላይ የሚሳተፉ የኅብረተሰብ ክፍሎችና የመንግሥት አካላት ተጨባጭ የሆነ ትምህርት ይቀስሙበታል፡፡ ሁለት፣ በልማት ትግሉ ውስጥ ያለፉት ይበልጥ ይበረታቱበታል፡፡ ለተጨማሪ ጥረትና ትግል ይነሳሱበታል፡፡ ሦስት፣ የመገናኛ ብዙኃኑ ዘገባም ማራኪና ተወዳጅ ይሆናል፡፡ ከማሰልቸትና እንጨት እንጨት ከማለት ይድናል፡፡ (እኒያ በህንድ አገር፣ በኒው ደልሂ ከተማ የልማት ጋዜጠኝነት ላይ አመድ በመንፋት፣የጋዜጠኝነት የወተት ጥርሴ ገና ሳይጠነክር ግራ ያጋቡኝ የሥልጠና ባልደረቦቼ ጥያቄም በተወሰነ ደረጃም ቢሆን መልስ ያገኛል፡፡) አራት፣ በልማት ሥራ ፕሮጀክቶች ላይ እንደ አልቀት ተጣብቀው የሕዝብን ሀብት የሚመጠምጡ ሙሰኞች እየተጋለጡ፣ ተገቢ ዋጋቸውን ያገኛሉ፡፡ ችግሩ ሥር ሳይሰድና ብዙ ኪሳራ ሳይከተል በቀላሉ መታረም ይችላል፡፡ ከዚህን መሰል የሙስና ተግባራቸው ይቆጠባሉ፡፡ (ነኝ ማለትና መሆን ለየቅል ናቸውና የልማት ጋዜጠኝነት ችግሩ እንዳይከሰት በማድረግ ወይም ችግሩ ብቅ ሲል በማድረቅ ተገቢውን ሚና መጫወት አልቻለም፡፡ ይኼው ከ50 በላይ ‹‹ከፍተኛ ኃላፊዎችንና ባለሀብቶችን በሙስና ወንጀል አስሬያለሁ›› በማለት መንግሥት እየተናረገ ነው፡፡ መንግሥት ‹‹እየተከተልኩት ነው›› የሚለው የልማት ጋዜጠኝነት በትክክል (በከፊል እንኳን) ሥራ ላይ ቢውል ኖሮ፣ ይህ ሁሉ ጥፋት ባልተከሰተ ነበር) አምስት፣ ከዚህ ትምህርት በመቅሰም ሌሎቹ በልማት ፕሮጀክት ላይ የሚለጠፉ አልቀቶች ከዚህን መሰል የሙስና ተግባራቸው ይቆጠባሉ፡፡ 

የልማትጋዜጠኝነትዘገባከሌላውየሚለይበት

የህንድ የሥልጠና ባልደረቦቼ (የአገሬም የመንግሥት ጋዜጠኞች) ጥያቄ ሙሉ በሙሉ መልስ ያገኝ ዘንድ፣ ተጨማሪ ነጥቦችን እናንሳ፡፡ የልማት ጋዜጠኝነት ዘገባ ይበልጥ ሳቢና ተወዳጅ እንዲሆን ለማድረግ፣ ከሌላው ዓይነት ጋዜጠኝነት የሚለይበትን ጠንቅቆ ማወቅ ያስፈልጋል፡፡

አንደኛ፣ የልማት ጋዜጠኝነት፣ የአራጋቢት ሚና አይጫወትም፡፡ ስሜት ቀስቃሽ የሆኑ መረጃዎችን እያነፈነፈ አያራግብም፡፡ ዓላማው ስሜት የሚያነሳሱ መረጃዎችን በማደን፣ ለመገናኛ ብዙኃኑ ተሰሚነትንና ገበያን መፍጠር አይደልም፡፡ ይህ የንግድ መገናኛ ብዙኃን ባህሪ ነው፡፡ ‹‹እከሌ የሚባለው የፊልም ተዋናይ ወይም የስፖርት ተጫዋች እከሌ ከምትባለው ተፋቶ፣ እከሌ ከምትባለው ጋር እየተቃበጠ ነው›› ወይም ‹‹እከሊትን አጨ›› ዓይነት ‹‹ዜና›› ተብዬ የአውሮፓ ልቅምቃሚ ወሬዎችን ማናፈስ አይደለም፡፡ ወይም ኳስ ሜዳ ገብተው ሊጫወቱ ይቅርና በአጋጠሚ እንኳን ኳስ በእግራቸው ነክተው የማያውቁትን ወጣቶች የአውሮፓ የኳስ ክለብ አፍቃሪ (አምላኪ?) ማድረግ አይደልም፡፡ ወይም የእንግሊዝ አገርን ካርታ በውል ሳያውቅ ‹‹ማንቼስተር››፣ ‹‹አርሴናል›› እያለ ልቡ ውልቅ የሚል ወጣት፣ ከዚያም አልፎ እነዚህን የኳስ ክለቦች ደግፎ፣ ከመደገፍል አልፎ አምልኮ አይነኩብኝ በማለት በፍለጥ የሚፋለጥ፣ በቦከስ የሚቧቀስ ትውልድ ማፍራት አይደለም፡፡   

ሁለተኛ፣ የልማት ጋዜጠኝነት፣ የፕሮፓጋንዳ መሣሪያ አይደለም፡፡ በፕሮፓጋንዳ ሥልት የተቃኘ መረጃ (ዜና፣ ፕሮግራም፣ መጣጥፍ፣ ወዘተ) ሁለት መሠረታዊ ባህርያት አሉት፡፡ አንደኛ፣ ስለአንድ ጉዳይ የሚነግረን መረጃ በአብዛኛው ሙሉ አይደለም፣ መረጃ ሰጪው አካል የሚነግረን እንድንሰማ የሚፈልገውን ብቻ መርጦ ስለሆነ ከልማት አንፃር ካየነው፣ እንዳንሰማ የተደረገው መረጃ፣ ይበልጥ ማወቅ የሚገባን ሊሆን ይችላል፡፡ ወይም የደበቀን ነገር ሳይኖር፣ ሁሉንም መረጃ ይነግረናል፡፡ ነገር ግን ቢያንስ የተወሰኑትና ሆኖም ቁልፍ የሆኑትን እውነታዎች ገለባብጦ ያቀርብልናል፡፡ እውነቱን ውሸት ወይም በተወሰነ መጠን ውሸት፣ ውሸቱን ደግሞ እውነት ወይም በተወሰነ መጠን እውነት አድርጎ ያቀርብልናል፣ ወይም ይግተናል፡፡

በዚህ ሒደት አንዳንድ ሰዎች ነገሩ ሊምታታባቸው ወይም ሊሳከርባቸው ይችላል፣ ችግር የለም፡፡ የፕሮፓጋንዳ አንዱ ዓላማ ይኼው ነው፡፡ ቢቻል፣ የፈነቀሉትን ድንጋይ ፈንቅሎ፣ ‹‹ድንጋዩን ዳቦ ነው›› ብሎ ጭምር የራስን አስተሳሰብ ሰዎች እንዲገዙት ማድረግ ነው፡፡ ያ ካልተሳካ፣ እንዲምታታባቸው ማድረግ፣ ለፕሮፓጋንዲስቱ በራሱ ውጤት ነው፡፡ ምንም ይሁን ምን የተምታታባቸው ሰዎች፣ አሁን በበፊቱ አቋማቸው ላይ አይደሉም፡፡ አሁን የበፊቱን ያህል የመደገፍ ወይም የመቃወም ጉልበት የላቸውም፡፡ ለፕሮፓጋንዳ ሰው ይህ በራሱ ውጤት ነው፡፡ ለልማት ዘገባ ጋዜጠኛ ግን ይኼ ክስረት ነው፡፡

ሁለተኛው የፕሮፓጋንዳ ባህሪ ድግግሞሹ ነው፡፡ እያቀረበ ያለው ጉዳይ ምንም ይሁን ምን፣ ድግድሞሹ ለከት የለውም፡፡ ‹‹ውኃ ቢወቅጡት እምቦጭ›› የሚለው ምሳሌያዊ አነጋገር፣ በነፕሮፓጋንዳ መንደር አይሠራም፣ ‹‹ውኃ ቢወቅጡት ውጤት›› የተባለ እስኪመስል፡፡ የምሳሌያዊ አነጋገር ጉዳይ ከተነሳ አይቀር፣ በፕሮፓጋንዲስቶች መንደር የሚሠራው ተረትና ምሳሌ፣ ‹‹ውሸት ሲደጋገም እውነት ይመስላል›› የሚለው እንደሆነ ይታወቃል፡፡        

ሦስተኛ፣ የመዝናኛ ድግስ ማቅረቢያ መድረኮች አይደለም፡፡ አዎ የማለዳው የመገናኛ ብዙኃን ዓላማ ‹‹ማሳወቅ፣ ማስተማርና ማዝናናት›› የሚል እንደ ነበር ለብዙዎቹ የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች የአደባባይ ሚስጥር ነው፡፡ ይህ ማለት ግን አንደኛ ነገር፣ ሦስቱ ዓላማዎች ተለያይተው መከወን አለባቸው ማለት አይደለም፡፡ ሦስቱ የዓላማ ዘሮች አንድ ላይ በመሰናሰን እንደ ዝግጅቱ ግብ አንዱ ወይ ሁለቱ መጉላታቸው እንደ ተጠበቀ ሆኖ መቅረብ አለባቸው፡፡ ‹‹ማዝናናት›› የሚለው ዓላማ ለብቻው ተገንጥሎ ማለትም ማስተማርና ማሳወቅን ወዲያ ጥሎ ወይም የሁለቱን ዓላማ እጅግ አድክሞ መቅረብ አለበት ማለት አይደለም፡፡

በአጭሩ የሬድዮና የቴሌቪዥን ፕሮግራሞች፣ በዘፈንና በድራማ ይጥለቅለቁ ማለት አይደለም፡፡ በተለይም በኅብረተሰቡ ውስጥ የማኅበራዊ ለውጥ ወይም የልማት አጋዥ ሆነው እንዲያገለግሉ በሚጠበቁ የመንግሥት ወይም የማኅበረሰብ መገናኛ ብዙኃን ከዚህን መሰሉ አሠራር መራቅ ግዳቸው ነው፡፡ ለምን ቢሉ፣ ከዚህ በላይ የሚጠበቅባቸው ዓላማ አላቸው፡፡ ሙዚቃ፣ ድራማ፣ ወዘተ ማሰራጨት ይህን ዓላማዬ ብለው የሚቋቋሙ የግል (የንግድ) ኤፍ ኤም ጣቢያዎች ተግባር ነው፡፡ ሲኒማና ቴያትር ቤቶችም ዋና ሥራቸው ይኼው ነው፡፡

ማዝናናት የሚለው ጽንሰ ሐሳብ እጅግ በተዛባ መንገድ በመተርጎሙና ሥራ ላይ በመዋሉ፣ ይህ ሁኔታም ከጋዜጠኞች አልፎ የታዳሚውን አመለካከት በመቅረፁ፣ ለምሳሌ አንድ ‹‹ትምህርታዊ›› የሬድዮ ፕሮግራም ከመቅረቡ በፊት ወይም እየቀረበ እያለ በመሀል ወይም ልክ ቀርቦ እንዳበቃ ዘፈን ካልተላለፈ፣ ወደ ጣቢያው ስልክ በመደወል ቅሬታቸውን የሚያሰሙ ቀላል የማይባሉ አድማጮች ተፈጥረዋል፡፡ ‹‹ፕሮግራማችሁ ዘፈን የለውም፣ ይደብራል፣ አትደብሩን፣ ዘፈን ልቀቁብን››… ወዘተ በማለት ቅሬታ የሚያሰሙ ታዳሚዎችን ቃል መስማት የተለመደ ነገር ከሆነ ሰነባብቷል፡፡ ለምን? ምክንያቱም ‹‹ማዝናናት›› የሚለው አንዱ የመገናኛ ብዙኃን ዓላማ፣ ለታዳሚዎች ዘፈን ወይም ሙዚቃ ማቅረብ ተደርጎ ስለተወሰደ፡፡

መጀመሪያ ነገር ‹‹ትምህርታዊ›› ፕሮግራሙ ሲዘጋጅ በአብዛኛው በአቀራረቡ በአድማጩ ላይ ጉጉት እንዲፈጥርና የአድማጩን ልቦና እንዲማርክ ተደርጎ አይዘጋጅም፡፡ ፕሮግራሞች ይህን ማድረግ ቢችሉ፣ የታዳሚውን ስሜት ጨምድደው መያዝ በቻሉ ነበር፡፡ ይህን ማድረግ ሲችሉ ደግሞ፣ አዝናኑ ማለት እሱ ነው፡፡ በመገናኛ ብዙኃን ሥራ ውስጥ ማዝናናት ማለት የመደመጥ/የመነበብ ፍላጎትንና ጉጉትን በታዳሚዎች ልብ ውስጥ መለኮስ መቻልና ያን የተለኮሰ ፍላጎት ማርካት ነው፡፡ አራት ነጥብ፡፡   

ግን ምን ይሆናል፣ ማዝናናት የሚለው ጽንሰ ሐሳብ እጅግ በተዛባ መንገድ በመተርጎሙና ሥራ ላይ በመዋሉ፣ ብዙዎቹ የአገራችን መገናኛ ብዙኃን የሥራ ክፍፍላቸውን ወይም መደባቸውን ሳይቀር በዚህ መንገድ ቃኝተውታል፡፡ አንዳንዶቹን ፕሮግራሞች ለምሳሌ የድራማ፣ የዘፈን ምርጫ፣ የሥነ ግጥም፣ ወዘተ ያሉበትን ‹‹የመዝናኛ ፕሮግራም›› በማለት ከፍለዋል፡፡ ይህ ክፍፍልም ወደ ጋዜጠኞቹ የሥራ መደብ በመግባት ‹‹የመዝናኛ ፕሮግራም አዘጋጅ›› የሚል ፈጥሯል፡፡ ወደ ቀናት ድረስ በመዝለቅ ‹‹የዚህ ቀን›› ለምሳሌ የእሁድ መዝናኛ የሚል ፈሊጥ ወልዷል፡፡

ጉዳቱ ምንድነው? ከራሳቸው ከጋዜጠኞች አንፃር ብዙዎቹ ጋዜጠኞች ‹‹መዝናኛ›› የሚል ‹‹ታርጋ›› ከተሰጣቸው ፕሮግራሞች ውጭ ባይመደቡ ይመርጣሉ፡፡ ለምን?

አንደኛ፣ ሌሎቹ ፕሮግራሞች ለታዳሚው ‹‹አሰልቺ፣ ምንችኬና ደባሪ ናቸው›› የሚል እምነት አብዛኛዎቹ ጋዜጠኞች ስላላቸው፣ ታዳሚ የማይፈልገው ፕሮግራም መሥራት ጥቅሙ ምንድነው? ተደብሮ፣ መደበር ካልሆነ በስተቀር? ይህ የሥነ ልቦና ዝግጅት በራሱ በሌሎቹ ወይም ‹‹ትምህርታዊ›› በሚባሉት ፕሮግራሞች አዘገጃጀት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ማሳደሩ አይቀሬ ነው፡፡ ‹‹እኔ ወጤ መቼ ይጣፍጥልኛል›› እያለች ወጥ የምትሠራ ሴት ወጧ የመጣፈጡ ነገር አጠያያቂ ነው፣ ‹‹ጣት ሊያስቆረጥም›› ይቅርና፡፡ 

ሁለተኛ፣ ‹‹የመዝናኛ ፕሮግራሞች›› ሥራቸው ቀላል ነው ተብሎም ይታመናል፡፡ ከማንም ጋር የማያነካኩ ከመሆናቸውም በላይ፣ ያለ ውጣ ውረድ በቀላሉ የሚገኙ ናቸው፡፡ አንድን የሙዚቃ ወይም የድራማ ባለሙያ ማነጋገር ወይም ከስቱዲዮ ቁጭ ብሎ ዘፈን እያከታተሉ መጋበዝ ጠና ሲል የስልክ መልዕክት መቀበልና ማስተላለፍ ቢኖር ነው፡፡ ከሌላው የዘገባ ተግባር አንፃር ሲታይ በጣም ቀላል ሥራ ነው፡፡ በአጭሩ ለስንፍና ይመቻል፡፡

ሦስተኛ፣ የታዳሚው ቁጥር በሽ (በብዙ ሺዎች) ነው፡፡ ጋዜጠኛው ከሚጠብቀው በላይ አድማጭ ወይም ተመልካች ያለው ፕሮግራም የመሆን ዕድሉ ከፍተኛ ነው፡፡ ዞሮ ዞሮ ለዚህም ተጠያቂዎቹ እኛ ባለሙያዎቹ ከመሆን አንዘልም፡፡ ማዝናናት የሚለውን ፅንሰ ሐሳብ የመደመጥ ወይም የመነበብ ፍላጎትንና ጉጉትን በታዳሚዎች ልብ ውስጥ በመለኮስ እሱን ለማርካት መሥራት (መዘገብ) መሆኑ ቀርቶ፣ ቁንፅል ትርጓሜ ሰጥተን በመተግበራችን የተከሰተ ነው፡፡

የማስታወቂያ ድርጅቶችም መረባረባቸው የማይቀር ነው፡፡ እነሱ አንደዚያ ናቸው፡፡ እነሱ እንደ አቧራ ናቸው፡፡ ነፋሱን ተከትለው ነው የሚከንፉት፡፡ መዝናኛ የሚባሉ ፕሮግራሞች ነፋስ ሆነው ታዳሚውን ሲነዱት፣ ማስታወቂያ ድርጅቶች አቧራ ሆነው ይከተላሉ፡፡ ይኼ ሁኔታ ሁለት መልክ ያለው ነው፡፡ ጥቅምም፣ ጉዳትም፡፡ ጥቅሙ፣ ፕሮግራሙ የማስታወቂያ ድርጅቶችን መጎተት ስለቻለ የመገናኛ ብዙኃኑ ደጎስ ያለ ጥቅም ያገኛል፡፡ ጉዳቱ በመገናኛ ብዙኃን መልዕክት አማካይነት የአመለካከትና የአስተሳሰብ ለውጥ ያመጣል ተብሎ የሚጠበቀው አብዛኛው ሕዝብ ከመዝናኛ ፕሮግራሞች ጋር እንደ ሙጫ ይጣበቃል፡፡ የመዝናኛ ፕሮግራሞች እያዝናኑ አያሳውቁም ወይም አያስተምሩም ባይባልም፣ የሚሰጡት ትምህርት አንደኛ መጠኑ የሌሎቹን ‹‹ትምህርታዊ›› ተብለው የተያዙትን ያህል አይሆንም፡፡ ሁለተኛ፣ በአቀራረቡ ትምህርታዊ እንደሚባሉት ቀጥተኛና እሱኑ ዓላማ አድርጎ የሚቀርብ አይደለም፡፡ ካስተማረም፣ በተዘዘዋሪ ማስተማር ነው የሚቀናው፡፡ ይህ ደግሞ አብዛኛው ኀብረተሰብ በዝቅተኛ የትምህርት ደረጃ ላይ በሚገኝበት አገር ውጤታማነቱ ያን ያህል አይደለም፡፡     

በሌላ በኩል ከመዝናኛ ውጭ ያሉ ፕሮግራሞች በደፈናው የማያስደስቱ፣ የማይስቡና ደባሪ ተደርገው ስለተወሰዱ፣ ታዳሚው ወይም በጥቅሉ ሕዝቡ ርቋቸዋል፡፡ ወይም እነሱን ለማዳመጥና ለመከታተል ከፊትና ከኋላቸው በሙዚቃና በዘፈን መታጀብ አለባቸው፡፡ ልደመጥ ካሉ፣ በዘፈን መሀል የሚገባ ሳንዱዊች መሆን ይኖርባቸዋል፡፡ ትምህርታዊ የሆኑ ፕሮግራሞች አዘጋጆች በዚህ በኩል የተዋጣላቸው ሳንዱዊች አዘጋጆች ናቸው፡፡ 

ይህ ግን በራሱ ተደማጭነትን ወይም ተፈላጊነትን የማረጋገጫ መንገድ ላይሆን ይችላል፡፡ ምክንያቱ አጭር ነው፡፡ ሰው በተፈጥሮው መራጭ ነው፡፡ መርጦ እንደሚወድ፣ መርጦ እንደሚበላ፣ መርጦ እንደሚለብስ ሁሉ፣ የመገናኛ ብዙኃንን መረጃዎችንም ሆነ ይዘቶችን መርጦ ነው የሚወስደው፣ መርጦ ያዳምጣል፣ ይሰማልም፣ መርጦ ያያል፣ ያነባልም፡፡ እናም ምንም እንኳን የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ወይም ጋዜጠኞች ለፕሮግራማቸው ‹‹ጣዕም›› ለመስጠት በማሰብ ዘፈን ከታች፣ ዘፈን ከላይ በማድረግ የፕሮግራማቸውን ይዘት መሀል ላይ በማስቀመጥ ሳንዱዊች ቢጤ ቢሠሩም፣ ታዳሚዎች ተፈጥሯዊ የመምረጥ ክሂላቸውን በመጠቀም፣ የሳንዱዊቹን ላይና ታች ብቻ ‹‹በመመገብ›› መሀሉን እንዳልበሰለ እንቁላል የመጣላቸው ዕድል የሰፋ ነው፡፡

ዞሮ ዞሮ ግን የሳንዱዊች ሥልት በተለይም በሬድዮ ጋዜጠኞች ፕሮግራምን የማስወደድ እንኳን ባይሆንም የማስደመጥ ብቸኛው ‹‹አማራጭ›› ተደርጎ ከተወሰደ ዘመን ተቆጠረ፡፡ ለዚህም ነው፣ ‹‹ወደሚቀጥለው ፕሮግራም ከማለፋችን በፊት፣ ዘና እንድትሉ አንድ ሙዚቃ እንጋብዛችሁ›› የሚል ፈሊጥ የተለመደ መሆኑ፡፡ ፕሮግራሞችን በዘፈን ማጀብ የተለመደ የሥርጭት ሥልት ተደርጎ ከመወሰዱና አድማጩም በዚህ የአሠራር ልማድ ከመቃኘቱ (ከመቅረፁ) የተነሳ፣ ከፍ ሲል እንደ ተገለጸው በርካታ አድማጮች ወደ ሬድዮ ጣቢያዎች ስልክ በመደወል ‹‹ዛሬ ሙዚቃ አሳንሳችኋል… ቆየት ካሉ ሙዚቃዎች ጋብዙን… ዛሬ ዘመናዊ ሙዚቃ አንሷል…›› ሲሉ የሚደመጠውም ለዚህ ነው፡፡ እነዚህን መሰል አድማጮች ወይም ታዳሚዎች በተላለፈው ትምህርታዊ ፕሮግራም ላይ አስተያየት ለመስጠት ቢረባረቡ ምንኛ ጥሩ ነበር፡፡ ምንኛ የጣቢያውን ውጤት ማመላከቻ በሆነም ነበር፡፡ ሆኖም የእነሱ ዋና ጭንቀታቸው ከላይና ከታች ስለቀረበው ወይም መቅረብ ስላለበት ዳቦ እንጂ፣ ስለእንቁላሉ አይደለም፡፡ የጣቢያው ዓላማ ደግሞ ከመሀል የቀረበው እንቁላል እንዲበላለት፣ እንዲሰለቀጥለት ነው፡፡

በዚያም አለ በዚህ ‹‹ማዝናናት›› የሚለው ዓላማ በተንሻፈፈና ቁንፅል በሆነ መንገድ መተርጎሙና መተግበሩ፣ መገናኛ ብዙኃን በኅብረተሰቡ አመለካከትና አስተሳሰብ ላይ አዎንታዊ ተፅዕኖ በመፍጠር፣ ሕዝቡ በተለያዩ መስኮች (ግብርና፣ ጤና፣ ትምህርት፣ ወዘተ) እየተደረገ ያለው የልማት ጥረት አካል በማድረግ፣ ቀጥተኛ ተሳታፊና ከፍተኛ የድጋፍ ኃይል እንዲሆን ለማስቻል የሚጠበቅባቸውን ሚና ለመጫወት ታላቅ እንቅፋት ፈጥሮባቸዋል፡፡ ‹‹በምን መንገድ?›› ከተባለ ተደማጭነትን በማሳጣት፡፡ (እዚህ ላይ፣ ‹‹ታዕማኒነት በማሳጣት›› አላልኩም፡፡ እሱም የራሱ የሆነ ድርሻ አለው፣ ሆኖም የራሱ የሆነ ወሰብሰብ ያለ ችግር ያለበት ስለሆነ፣ በሌላ ጊዜ ለብቻው ማየቱ ይመረጣል፣ ኢንሻ አሏህ!)

ሌላው ለአገራችን በተለይም ‹‹በልማት ጋዜጠኝነት ፍልስፍና እንመራለን›› ለሚሉት ማለትም ለመንግሥት መገናኛ ብዙኃን ፕሮግራሞች ተደማጭነት ወይም በአጭሩ ተፈላጊነት መቀነስ ትልቅ ሚና ያለው ተግዳሮት የሚቀርቡት ፕሮግራሞች ሊተነበዩ የሚችሉ (Predictable) የመሆናቸው ጉዳይ ነው፡፡ እዚህም ላይ ዘፈን እንዱ ‹‹ባለድርሻ አካል›› ነው፡፡ ስለትምህርት የሚወያይ ፕሮግራም የሚቀርብ ከሆነ፣ የፕሮግራሙ አዘጋጅ አስቀድሞ ‹‹ተማር ልጄ›› የሚል ዘፈን ይጋብዛል፡፡  

የዚህ ዓይነቶቹ ድርጊቶች ፕሮግራሞቹን ተተንባይ በማድረግ፣ አጓጊ እንዳይሆኑ ያደርጓቸዋል፡፡ ምን እንደሚከተል ያወቀ ታዳሚ ልብና ጆሮውን አይሰጥም ወይም በግማሽ ልብ ነው የሚያዳምጥና የሚከታተል፡፡ ሁለተኛው ችግር አቀራረቡን አሰልቺ ያደርገዋል፡፡ አላስፈላጊ ድግግሜ በማምጣት ይህ አጠቃቀም ልክ ከማሳጣቱ የተነሳ፣ አንዳንድ ጋዜጠኞች ከሚቀርበው ይዘት ጋር የሚገጥም ዘፈን ሲያጡ፣ ከፕሮግራሙ ውስጥ ያለ አንድ ቃል ወይም ሐረግ የያዘን ዘፈን ይጠቀማሉ፡፡ ለምሳሌ እነሱ ያዘጋጁት ፕሮግራም ስለጤና አጠባበቅ የሚዳስስ ፕሮግራም ቢሆን፣ ስለጤና የሚያወሳ ዘፈን ካጡ፣ ‹‹ያላንተ ጤናም የለኝ›› እያለች አንዲት ዘፋኝ ያንጎራጎረችውን የፍቅር ዘፈን ሊያስደምጡን ይችላሉ፡፡ ለምን? ከዘፈኑ ውስጥ ‹‹ጤና›› የምትል ቃል ስላለች ብቻ! ይኼውላችሁ የሚዲያዎቻችን የዘፈን አጠቃቀም እንዲህ ቅጥ አጥቷል፡፡ እና እነዚህን ዓይነት መገናኛ ብዙኃን ‹‹ደንባራ›› ቢባሉ ‹‹በዛባቸው›› ይባል ይሆን?

ቅጥያጣውየአየርጊዜሽያጭ

ልክ ያጣው የአየር ጊዜ ሽያጭም፣ ሌላው የልማት ጋዜጠኝነት ሥጋት ወይም እንቅፋት ነው፡፡ የመንግሥት ሬድዮና ቴሌቪዥን ጣቢያዎች (ኢቢሲም ሆነ የየክልሎቹ) የአየር ጊዜ ሽያጫቸው ገደቡ እስከምን ድረስ ነው? ለጤና ጥበቃ፣ ለግብርና፣ ለገቢዎች፣ ለፖሊስ፣ ለትራንስፖርት… ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች ወይም ቢሮዎች ዛሬ የአየር ጊዜ ሸጠዋል፡፡ የመንግሥት ተቋም ናቸውና ሰጥተል ቢባልም ችግር የለም፡፡ የመንግሥት ተቋማቱ ለአየር ጊዜው ደጎስ ያለም ሆነ አነስ ያለ ገንዘብ ቢከፍሉ ስለእሱ የሚያጨቃጭቀን ነገር የለም፣ የገንዘብ ዝውውሩ ከቀኝ ኪስ ወደ ግራ ዓይነት ነውና  ከመንግሥት፣ ወደ መንግሥት፡፡

ዋናውና አሳሳቢው ጥያቄ እነዚህ ተቋማት ያንን የወሰዱትን የአየር ጊዜ ‹‹ለምን ተግባር ያውሉታል?›› የሚለው ነው፡፡ ለምሳሌ የፌዴራሉ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ወይም አንድ የክልል ጤና ቢሮ፣ የሬድዮ ወይም የቴሌቪዥ የአየር ጊዜን በመጠቀም ኅብረተሰቡን ስለተለያዩ ጤናን የሚመለከቱ ጉዳዮች ትምህርት ቢሰጥ ‹‹ሥራው ባለቤቱን አገኘ›› ማለት ይኼ ነው፡፡ የዚህ ዓይነቱን ሥራ ጋዜጠኛው ከሚሠራው፣ የሕክምና ባለሙያው ቢሠራው ይመረጣል፡፡ ጉዳዩን ከሥር ከመሠረቱ ያውቀዋልና፡፡ አንዳንድ ከጋዜጠኝነት ጋር የሚገናኙ የቴክኒክ ጉዳዮችን በሬድዮ/ቴለቴቪዥን ትምህርት ለሚሰጡት የሕክምና ባለሙያዎች አጫጫር ሥልጠና በመስጠት አቅማቸውን መገንባትና ክፍቱተን መሙላት ይቻላል፡፡ መንግሥታዊ ተቋማቱ (ግብርና፣ ገቢዎች፣ ፖሊስ…) የአየር ጊዜውን በዚህ መንገድ የሚጠቀሙበት ከሆነ፣ ማንኛውም ተቋም መውሰዱ መገናኛ ብዙኃንን በመጠቀም ልማትን የማገዙን ተግባር ስለሚያቀላጥፈው እሰዬ የሚያስብል ነው፡፡

ሆኖም ነገር የሚመጣው፣ ማለትም ከልማት የጋዜጠኝንት መርሕ ጋር መላተም የሚመጣው መንግሥታዊ ተቋማቱ የወሰዱትን ወይም የገዙትን (በተባባሪነት የሚያሩትን) የአየር ጊዜ የሥራ ዕቅዳቸውና አፈጻጸማቸው ሪፖርት ማቅረቢያ መድረክ ማድረግ ሲጀምሩ ነው፡፡ ይኼን ይኼን ሠራን፣ እንዲህ እንዲህ ፈጸምን›› በማለት ስለሠሩት የልማት ተግባር ማሳወቂያ መሣሪያ አድርገው መጠቀም የለባቸውም፡፡ ለምን?

አንደኛ፣ አንድ ተቋም ስለራሱ የሥራ ክንውን ሚዛናዊ ሆኖ ይዘግባል ተብሎ አይጠበቅም፡፡ ‹‹ለራስ ሲቆርሱ አያሳንሱ›› ነውና የሠሩትን አጋነው ማቅረባቸው አይቀርም፡፡ ሳያጋንኑ ቢነግሩን እንኳን፣ ያጎደሉትንና ያበላሹትን ደፍረው አይናገሩም፡፡ ‹‹እንናገራለን›› ቢሉም እንኳን፣ ሁሉንም ፍርጥርጥ አድርገው አይናገሩም፡፡ ሕዝብ ደግሞ ሁሉንም የማወቅ መብት አለው፡፡

ሁለት፣ ጣቢያውን በከፍተኛ ደረጃ ለገፅታ ግንባታ ያውሉታል፡፡ እሳት የላሱ የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያዎች የተቋማቸውን ስምና ዝና ለመትከል ይጠቀሙበታል፡፡ የልማት ጋዜጠኝነት ዓላማ ግን እሱ አይደለም፡፡ ሕዝቦች ከድህነትና ኋላ ቀርነት እንዲላቀቁ ያለባቸውን የመረጃና የእውቀት ድህነት ማስገድ ነው፡፡ (የገፅታ ግንባታቸውን በሌሎች የኮሙዩኒኬሽን መንገዶች፣ በማስታወቂያ፣ የተለያዩ መድረኮችን በማዘጋጀት፣ ወዘተ ነው ማከናወን ያለባቸው)

ሦስት፣ ተጠያቂነት ይጠፋል፡፡ የመልካም አስተዳደር ችግር የገነገነው ተጠያቂነት በመጥፋቱ ነው፡፡ ተጠያቂነት ሕይወት ከማንሰራራት አልፎ፣ ወደ ባህልነት ሊቀየር የሚችለው የጣቢያዎቹን ማይኮች ጋዜጠኞች ሲይዟቸው ነው፡፡ በየተቋሙ ሥር ያሉ የኮሙዩኒኬሽን ባለሙያዎች ሲቆጣጠሯቸው አይደለም፣ አይገባቸውምም፡፡ (ወይም ለተባባሪ መሥሪያ ቤት የተሰጠ በማለት፣ የዚያ መሥሪያ ቤት የኮሙዩኒኬሽን ክፍል በቀደደው ቦይና ባሰመረው መስመር ላይ የጋዜጠኛው ዘገባ እንዲፈስ ማድረግ አይደለም፡፡) አንዳንድ የአየር ጊዜ የገዙ የመንግሥት ተቋማት፣ የአየር ጊዜ በገዙት ሬድዮ ወይም ቴሌቪዥን ጣቢያ የዜና እወጃ ወቅት የተነገረባቸውን የሕዝብ ቅሬታ በአየር ጊዜያቸው የማስተባበያ ፕሮግራም እሰከመሥራት መድረሳቸው ይነገራል፡፡

አራት፣ ታዳሚው መገናኛ ብዙኃኑን ይርቃል፡፡ ስኬታቸውን በመሰቃቀል፣ የአንድ ወገን ዘገባ በማቅረብና ከዚያም አልፈው ደግመው ደጋግመው በማስጮህ ታዳሚውን ያሰለቹታል፣ ያደነቁሩታል፡፡ አደንቋሪ ይጮሀል እንጂ ሰሚ የለውም፡፡ እስካሁንም ይኼ አልሆነም ለማለት አይቻልም፡፡

አምስት፣ ጋዜጠኞቹ ምን ይሥሩ? ሁሉም ወይም ብዙዎቹ የመንግሥት ተቋማት የአየር ጊዜ ከወሰዱ ወይም ከገዙና ስለራሳቸው፣ ራሳቸው እየዘገቡ የሚያሰራጩ ከሆነ፣ ጋዜጠኞች ለምን ያስፈልጋሉ?

ሙያንለባለሙያአለመተው

የዜናዘገባከጋዜጠኞችእጅወጣ?

ከላይ የተጠቀሰው ዓይነት ተግባር ወደ ዜና ዘገባም አልገባም ለማለት ያስቸግራል፡፡ ኢቢሲ፣ በዜና እወጃው ወቅት ‹‹የዚህ ክልል የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ›› ወይም ‹‹የዚህ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት የኮሙዩኒኬሽን… ዜናውን አድርሶናል›› በማለት ዜና ማሰራጨት ከጀመረ እጅግ ሰነባብቷል፡፡ ‹‹ዜናውን አድርሶናል›› ማለት ምን ማለት ነው? ለአንድ መገናኛ ብዙኃን ዜና መሥራት ያለበት ማን ነው? መልሱ አጭር ነው፡፡ አንድ ራሱ፣ ሁለት የዜና አገልግሎት ድርጅት፡፡ (ከሌላ የመገናኛ ብዙኃን ሊወስድ ቢችልም፣ ያ ዋና ምንጭ ተድርጎ አይወሰድም፡፡ ቢወስድም ዞሮ ዞሮ የዜናው ሥራ ባለቤትነት ከጋዜጠኞች እጅ አይወጣም፡፡)

ዜና፣ በተለይም በብዙኃን መገናኛ የሚተላለፍ ዜና ተፈጥሯዊ ባለቤቶች ጋዜጠኞች ናቸው፡፡ ከእነሱ ውጭ ባለባለሙያ አይሠራም፣ ቢሠራም የሙያውን ሥነ ምግባር የተከተለ አይደለም፡፡ በተጨማሪም ታዕማኒነት አይኖረውም፡፡ ኢቢሲ ሰማይ እስከሚነካ፣ ለሕዝብ ሳይሆን ለመንግሥት ወግኖ ቢሠራ፣ ዜና በሚዘግበው ጋዜጠኛ ኅሊና ውስጥ ግን ሕዝብን የማገልገል ሙያዊ ግዴታውና ሥነ ምግባሩ ይጮህበታል፡፡ የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ፣ የመረጃ ምንጭ ከመሆን አልፎ፣ ያለሙያው ገብቶ ዜና ሲዘግብ በኅሊናው ውስጥ የሚጮህበት የሙያ ግዴታውና ሥነ ምግባሩ መሥሪያ ቤቱን በሚገባ ስለማስተዋወቁ (ስለማንቆላጰሱ) ነው፡፡ ስለሆነም ልማታዊ ዘገባውን ቀርቶ፣ ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ ተብሎ የሚሠራውን ዜና እንኳን ሳይቀር ጋዜጠኛው ቢሠራው ይመረጣል፡፡ ለማኅበራዊና ልማታዊ ዘገባውማ የግድ ነው፡፡

የሕዝብ ግንኙነት (የኮሙዩኒኬሽን) ባለሙያዎች ዋና ተግባራቸው የማይነጥፍ የመረጃ ምንጭ መሆን ነው፡፡ ለብዙኃን መገናኛ ዜና መሥራት አይደለም፡፡ ጋዜጠኛው የት ሄዶ? ጋዜጠኛው መረጃ ሲጠይቃቸው መልካም አፈጻጸም ካልሆነች ውጣ ውረድ የሚያበዙ፣ ስብሰባ የሚበዛባቸው ጥቂቶች እንዳልሆኑ ይታወቃል፡፡ መልካም አፈጻጸም ስትኖር ደግሞ የዘግቡልን ኡኡታ የሚያሰሙ እንዳሉ በብዙኃን መገናኛው ሠፈር የአደባባይ ሚስጥር ነው፡፡ መልካም አስተዳደር ቁልፍ ችግር ለመሆን በበቃበት ሒደት ውስጥ፣ የዚህ ዓይነቱ የተዛነፈ የሚዲያ አጠቃቀም አንዱ ባለድርሻ አካል እንደሆነ ይሰማኛል፡፡ ‹‹አልነበረም›› የሚል ካለ፣ እንዲህ ትልቅ ችግር ነው ብሎ መንግሥት ዕውቅና ሰጥቶት እያለ፣ ምነው በውል ሳይዘገብ መቅረቱ?

የመንግሥት መገናኛ ብዙኃን ተጠሪነት ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ሳይሆን፣ ለተወካዮች ምክር ቤት መሆኑም አንድ ትልቅ ማሳያ ነው፡፡ የተወካዮች ምክር ቤት፣ የመንግሥት ተቋማትና ኃላፊዎቻቸው በገቡት ቃል መሠረት የሕዝብን አደራ እየተወጡ ለመሆናቸው አንዱ የሚያረጋግጥበት መንገድ ነው፣ የመገናኛ ብዙኃኑ ዘገባ፡፡ እናም እዚህ ጋር መደናበሩ አለ፡፡ አውቀውም ይሁን ሳያውቁ መገናኛ ብዙኃኖቻችን እየተደናበሩ ነው፣ በዚያውም የልማት ጋዜጠኝነትን እያጠለሹት፡፡ ( ሳምንት ይቀጥላል)

ከአዘጋጁ፡-ጸሐፊው የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነትና ኮሙዩኒኬሽን ትምህርት ክፍል መምህር ሲሆኑ፣ ጽሑፉ የእሳቸውን አመለካከት የሚያንፀባርቅ መሆኑን እየገለጽን በኢሜይል አድራሻቸው jemalmohammed99@gmail.comማግኘት ይቻላል፡፡ 

 

Standard (Image)

ነጠብጣቡን ማገናኘት . . . ዓባይ የዘመኑ እንቆቅልሽ በግጭት ወይስ በትብብር?

$
0
0

 

 በእስክንድር ከበደ

በአንድ ወቅት አንድ ዕውቅ ኢትዮጵያዊ ምሁር ለኢትዮጵያውያን ዲፕሎማቶች በተዘጋጀ ዓውደ ጥናት ላይ የኢትዮጵያን የውጭ ግንኙነት አስመልክተው በሰጡት ማብራሪያ፣ ‹ንክኪ ካለ (Intensity of Contact) ግንኙነት አለ። ያለንክኪ ፍቅርም ሆነ ጥላቻ ሊኖር አይችልም› ብለው ነበር፡፡

ይህን የንክኪ ጽንሰ ሐሳብ ጸሐፊው ለዚህ ጽሑፍ እንደ መንደርደሪያነት የተጠቀመበት ያለምክንያት አይደለም፡፡ ኢትዮጵያ ጎረቤተ ብዙ እንደ መሆኗ የንክኪዋ መጠንም ሆነ ፈርጅ እንደዚሁ የተበራከተ ነው። በእርግጥም ኢትዮጵያ የጎረቤትም ሆነ የጉርብትና ችግር የለባትም፡፡ ዋናው ቁም ነገር ግን አጎራባቾቿ በሙሉ በተለያዩ የፖለቲካ ርዕዮትና የፍልስፍና መንገድ የተቃኙ መሆናቸው ነው፡፡

ዓባይም አንድ የንክኪ ዘርፍ በመሆኑ ኢትዮጵያ ከሱዳንና ከግብፅ ጋር በሚኖራት ግንኙነት ላይ የራሷ አንድምታ ይኖረዋል፡፡ የወንዝ ንክኪ ከአየር ንክኪ ይልቅ በአንድ አገር ግንኙነት ላይ በበጎም ሆነ በክፉ ገጽታው የተሻለ ፋይዳ አለው፡፡ ንክኪው ከየብስ ንክኪ አንፃር ሲታይ ጠቀሜታውም ሆነ ጉዳቱ ብዙም አይደለም፡፡

ኢትዮጵያ ከሱዳን፣ ከሶማሊያ፣ ከጅቡቲ፣ ከኬንያና ከኤርትራ ጋር በየብስ ትዋሰናለች፡፡ ከእነዚህ አገሮች ጋር ያላት የንክኪ መጠን በጋራ ጥቅም ላይ የተመሠረተ ቢሆን ጥቅሙ የሚያመረቃና ልማቱ ቋት የሚሞላ ሲሆን፣ ለጥፋት ከዋለም ጉዳቱ የከፋና የመጎርበጥ እንዲሁም የእያንዳንዱን አገር ህልውና የሚፈታተን እንደሚሆን ይታመናል፡፡

በሌላም በኩል ኢትዮጵያ ከግብፅ ጋር ካላት ንክኪ አንፃር ሲሰላ ፋይዳው ከአማካይ በታች ቢሆንም ጉዳቱና ውስብስብነቱ ከሁሉም የላቀ ሆኖ ይታያል፡፡ በተለይም ወታደራዊ ኃይላቸው የፈረጠመ፣ ፖለቲካዊ ክንዳቸው የረዘመ፣ ኢኮኖሚያዊ አቅማቸው የደለበ አገሮች በሌሎች አገሮች ውስጥ ያላቸውን ጥቅም ለማስከበር አልፎ ተርፎም ተፅዕኖአቸውን ለማሳረፍና አመለካከታቸውን ለማስረፅ ከታላሚ (Target) አገሮች ጋር የየብስ ንክኪ ባላቸው አገሮች ሲጠቀሙ ይስተዋላሉ፡፡ እንዲሁም በተለያየ መንገድና ደረጃ በዲፕሎማሲያዊ ትግል ተግዳሮት የሚፈጥሩበት ሁኔታም ይስተዋላል፡፡

የግብፅን ሁኔታ የተመለከትን እንደሆነ፣ ከዚህ አመለካከት የፀዳች አይደለችም፡፡ ከኢትዮጵያ ጋር በተለያየ መንገድ ንክኪ ባላቸው አገሮች በመጠቀም በኢትዮጵያ ውስጥ ያላትን ጥቅም ለማስከበር ደፋ ቀና ስትል ይታያል፡፡

በአንፃሩ ኢትዮጵያ ለመልካም ጉርብትና ከምንም በላይ ቅድሚያ በመስጠት የአጎራባች አገሮች ሰላምና ደኅንነት የተጠበቀ እንዲሆን፣ አልፎ ተርፎም ለአፍሪካ አንድነት ነፃነትና ብልፅግና ወሳኝ ሚና ለመጫወቷ ታሪክ ህያው ምስክር ነው፡፡ ለአብነት ያህልም የቀድሞው  የአፍሪካ አንድነት ድርጅት የአሁኑ የአፍሪካ ኅብረት እንዲመሠረት ያደረገችው ግንባር ቀደም ተሳትፎ፣ ከአጎራባች አገሮች የሱዳንና የሶማሊያን የውስጥ ችግር ለመፍታት የተጫወተችው ሚና፣ በአኅጉር ደረጃ የኮንጎ፣ የላይቤሪያ፣ የሩዋንዳንና የቡሩንዲን የውስጥ ግጭት ለማስወገድ ያደረገችውን ጥረት ከእነዚህም በተጨማሪ ለዚምባቡዌና ለደቡብ አፍሪካ ነፃነት ያደረገችውን አስተዋጽኦ ማመልከት ይቻላል፡፡

 

ይሁን እንጂ ለዚህ በጎ የመልካም ጉርብትና እንቅስቃሴ በአጎራባቾቻችን በኩል አዎንታዊ ምላሽ መስጠት ሲገባው፣ አንዳንድ ጎረቤቶቻችን ከግብፅ ጋር ድርና ማግ በመሆን የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ሲፈታተኑ ቆይተዋል፡፡ ጎረቤት አገሮች ይህን አሉታዊ እንቅስቃሴ የሚያደርጉት ከብሔራዊ ጥቅማቸው አንፃር ብቻ ጠቃሚ ሆኖ ስላገኙት ሳይሆን፣ አንዳንዴም በስተጀርባው የውኃ ፖለቲካን ያዘለ የግብፅን ድብቅ አጀንዳ የማራመድ ዓላማን ለማሳካት የተደረገ እንቅስቃሴ ሊሆን እንደሚችል ይገመታል፡፡

ኢትዮጵያና ግብፅ ከአንድ ወንዝ ውኃ የሚጠጡ፣ ረዥም ታሪክና የታሪክ ትስስር ያላቸው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት መሥራች አባሎች ቢሆኑም፣ እንዳላቸው ትስስር ግንኙነታቻው በሚፈለገው መልክ ጠንካራ ነበር ማለት አያስደፍርም፡፡ ግብፅ ናይልን በተመለከተ ስታራምድ የቆየቻቸው ፖሊሲዎች በዓይነት የተለያዩ ቢመስሉም በይዘት አንድና አንድ ስትራቴጂ፣ ግባቸውም አንድና አንድ ነው፣ “ዓባይን ከምንጩ”የሚል ነው፡፡ 

 ታሪክ እንደሚያመለክተው የዓባይ ውኃ ጥያቄ የትናንትና ሳይሆን ዘመን ያስቆጠረ፣ እስከ ዛሬም ድረስ ዘለቄታዊ ዕልባት ያላገኘና ሥር የሰደደ ጥያቄ ነው፡፡ በተለይም በኢትዮጵያ ላይ ቀና አመላካከት የሌላቸው አንዳንድ የግብፅ ባለሥልጣናትና ምሁራን ኢትዮጵያ እስካለች ድረስ መሪዎቹ የመንፈስ እርጋታ፣ ሕዝቡም ሰላምና ዕፎይታ እንደማያገኝ ይዘክራሉ፡፡ ስለሆነም የግብፅ መንግሥት ፖለቲካዊ መረጋጋት፣ የአገሪቱ ኢኮኖሚያዊ ብልፅግናና የሕዝቡ ውሎ ማደር ዋስትና የሚኖረው ዓባይን ከምንጩ መቆጣጠር ሲቻል ነው የሚል ህልም አላቸው፡፡ ለዚሁ ግብ ስኬታማነት በኢትዮጵያ ላይ አፍራሽ አመለካከት ሲያራምዱ ይታያሉ፡፡

 

ዓባይን ከምንጩ የሚለው መርህ ግብፆች በራሳቸው የፈጠሩት ሳይሆን፣ ከእንግሊዝ ቅኝ ገዥዎች የተማሩት ነው፡፡ በተለይም በ18ኛው ክፍለ ዘመን እ.ኤ.አ. ከ1861 እስከ 1949 የኖረው ዕውቅ እንግሊዛዊ የፖለቲካ ጂኦግራፊ ምሁር ጆን ማኪንደር “The Heart Land” (The Land Foyer of Eurasia)” የሚባለውን አካባቢ መቆጣጠር ዓለምን መቆጣጠር ያስችላል የሚለው መርህ በግብፅ መሪዎች ዘንድ ሰርፆ በመግባቱ፣ የመምህራቸውን የማኪንደርን ፈለግ በመከተል “የራስጌ አገሮችን መቆጣጠር ዓለምን መቆጣጠር ያስችላል” በሚል እሳቤ የዓባይን ሸለቆ በተለይም ኢትዮጵያን ለመቆጣጠር ያላደረጉት ጥረት የለም፡፡

በቱርክ ሥልጣን የግብፅ አስተዳዳሪ ሆኖ የተሰየመው መሐመድ ዓሊ ፓሻ በግብፅ ያለውን የማምሉክ አስተዳደር ካስወገደ በኋላ ጠንካራ ማዕከላዊ መንግሥት በማቋቋም በርካታ ግድቦች፣ እርከኖችና ሰፋፊ የመስኖ ሥራዎች ከመጀመሩም ባሻገር ዘመናዊ የጦር ሠራዊት በማደራጀት ወደ ሱዳን፣ ኡጋንዳና ኢትዮጵያ ወሰን ያደረገው የመቆጣጠር እንቅስቃሴ፣ ከዲቪ እስማኤል ፓሻ የተባለው የመሐመድ ዓሊ ፓሻ የልጅ ልጅ ደግሞ የአያቱን ህልም ዕውን ለማድረግ በመጀመርያ ሶማሊያንና ሐረርን ለመቆጣጠር፣ በመቀጠል ደግሞ በ1875 ዓ.ም. በጉራዕ፣ በ1876 ዓ.ም. በጉንደት ያደረገው የጦርነት እንቅስቃሴ ለአብነት የሚጠቀሱ አንኳር የጠብ አጫሪነት ዕርምጃዎች ናችው፡፡

በአጠቃላይ በግብፅ ፖለቲካዊ ሕይወት ውስጥ ከመሐመድ ዓሊ ፓሻ እስከ ንጉሥ ፋሩቅ ድረስ በትረ መንግሥቱን የጨበጡ የግብፅ መሪዎች በሙሉ ታላቁ ህልማቸው ዓባይን ከምንጩ የመቆጣጠር ዕቅድ ስለነበር፣ በመጀመርያው የግብፅ ፖሊሲ ጎራ የሚካተቱ ናቸው፡፡

 

የጉራዕና የጉንደት የፀረ ወረራ አሻራ፣ የዓደዋው ፀረ ቅኝ አገዛዝ ድል ‘’ዓባይን ከምንጩ’’ የሚለውን የግብፅ ህልም ወደ እውንነት ሊለወጥ የማይችል መሆኑን ጠቋሚዎች ከመሆናቸውም በላይ ኢትዮጵያውያ፣ ለሉዓላዊነታቸውና ለነፃነታቸው ያላቸውን ፅኑ ዓላማ የሚያመላክቱ ናቸው። በመሆኑም የግብፅ ኢትዮጵያን የማጠቃለል ፖሊሲ ፋይዳ ትርጉም የለሽ እንቅስቃሴ እንደሆነ በማያሻማ ሁኔታ አሳይተዋል።

ስለሆነም የግብፅ መራሔ መንግሥታት ኢትዮጵያን የማጠቃለል ፖሊሲ ገቢራዊ ሊሆን እንደማይችል በመገንዘብ ስትራቴጂያዊ ዓላማው ያው ቢሆንም፣ በታክቲክ ደረጃ ለየት ያለ ፖሊሲ መከተል ግድ ሆነባቸው። በዚህም መሠረት ፀረ ኢትዮጵያ ኃይሎችን በማደራጀት፣ በመርዳትና በመንከባከብ አልፎ ተርፎም በቀጥታ በማስፈራራትና ወታደራዊ ኃይል በመገንባት ኢትዮጵያን የማዳከም እንቅስቃሴ ሲያራምዱ ቆይተዋል። ዛሬም ቢሆን ዓባይን ለጋራ ብልፅግና በጋራ ማልማት ሳይሆን ‹‹ዓባይ የለም ማለት ግብፅ የለችም›› (Out  Nilus Out Nihil) የሚለው ብቻ ሳይሆን፣ ኢትዮጵያ አለች ማለት የግብፅ ሕዝብ በልቶ አያድርም የሚል ሥር የሰደደ ውስጣዊ አመለካከት ስላላቸው፣ ኢትዮጵያን ለማሽመድመድ ወይም ለእነርሱ ጠቀሜታ እንድትንበረከክ ለማድረግ አዕምሮአቸው የሚላቸውን ሁሉ እየሠሩ ይገኛሉ።

እ.ኤ.አ. ከ1992 የግብፅ አብዮት ወዲህ ፕሬዚዳንት ጋማል አብዱልናስር ከአፄ ኃይለ ሥላሴ ጋር የቅርብ ግንኙነት ስለነበራቸው ግብፅ በኢትዮጵያ ላይ ዓይኑን ያፈጠጠ የከፋ እንቅስቃሴ ባታደርግም፣ ከ1956 ዓ.ም. የስዊዝ ካናል ጦርነት ወዲህ ‹‹የውኃ ደኅንነትን ማስጠበቅ››በሚል ኢትዮጵያን በማግለል ያደረገችው የአስዋንን ግድብ የመገንባት እንቅስቃሴና የዓባይን ውኃ ከሱዳን ጋር ብቸኛ ተጠቃሚ ለመሆን ያደረጉት የ1956 ዓ.ም. የተናጠል ስምምነት ሲታይ፣ አገሮቹ በኢትዮጵያ ላይ ቀና አመለካከት ነበራቸው ለማለት አያስደፍርም።

ፕሬዚዳንት አንዋር ሳዳት በትረ መንግሥቱን ከጨበጡ ወዲህ ደግሞ በህቡዕ የነበረውን ፀረ ኢትዮጵያ እንቅስቃሴ በገሐድ በማውጣት የለየለት የጠብ አጫሪነት ፖሊሲ ማራመድ ጀመሩ። ከእነዚህም የጠብ አጫሪነት እንቅስቃሴዎች መካከል ዋና ዋናዎቹ የሚከተሉት ናቸው፡፡

የግብፅ የመከላከያ ሚኒስትር የነበሩት ሌተና ጄኔራል ከማል ሐሰን ዓሊ ዲሴምበር 6 ቀን 1997 በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፣ ‹‹ግብፅ ሥልታዊ ጠቀሜታን    ለማስከበር ወደ ጦርነት ታመራለች››፣ እንዲሁም የግብፅ የመስኖ ሚኒስትር አብዱል አዚም አብዱል አታበሜይ እ.ኤ.አ. ሜይ 13 ቀን 1978 በሰጡት መግለጫ፣  ‹‹ኢትዮጵያ የዓባይን ውኃ እንድትጠቀም ግብፅ በፍፁም አትፈቅድም፤›› ሲሉ ፕሬዚዳንት አንዋር ሳዳት ደግሞ በሌላ ጊዜ ራሳቸው እ.ኤ.አ. ሜይ 30 ቀን 1978 ዓ.ም. በሰጡት መግለጫ፣ ‹‹ኢትዮጵያ በጣና ሐይቅ ላይ ግድብ ለመሥራት ብትሞክር ግብፅ ጦርነት ታውጃለች፤››በማለት የተናገሩት ይገኙበታል።

ከዚህም ባሻገር የተለያዩ ፀረ ኢትዮጵያ ኃይሎችን ከማደራጀትና ከማስታጠቅ በተጨማሪ፣ የጣና በለስ ፕሮጀክት ስኬታማ እንዳይሆን የዓለም ባንክና የዓለም የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) ለኢትዮጵያ የውኃ ልማት ብድር እንዳይሰጡ ግብፅ ያደረገችው ህቡዕ እንቅስቃሴ ቀላል ግምት የሚሰጠው አይደለም።

ለዚህም የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምር ሙሳ እ.ኤ.አ. በየካቲት 1990 ከአንድ የአገር ውስጥ ጋዜጠኛ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፣ ‹‹ኢትዮጵያ መብታችንን እስካልነካች ድረስ ዕቅዶቿን ለማሰናከል ፍላጎት የለንም፤›› ማለታቸው ማስፈራሪያ አዘል መልዕክት ያለው መሆኑ ጥርጣሬ ያስነሳል፡፡ ‹‹መብታችንን እስካልነካች ድረስ›› የሚለው ሐረግ ግብፅ ከኢትዮጵያ በየዓመቱ የምታገኘው 84 ኪዩቢክ ሜትር ውኃና ከ100,000 ቶን በላይ ለም አፈር ቅንጣት ብትጎድል ወዮላት የሚል መልዕክት ያለው ይመስላል።

ግብፅ ኢትዮጵያንና ዓባይን ለመለያየት ወይም ከኢትዮጵያ ውጪ የሚገኙ የራስጌ አገሮችን ፍቅር ለማትረፍ ያላደረገችው ጥረት የለም። ከእነዚህም ከፍተኛ ጥረቶች አንዱ ‹ኡንዱጉ› የተባለውን ማኀበር መመሥረት ነበር። ‹ኡንዱጉ› የስዋህሊ ቃል ሲሆን፣ ትርጉሙም ወንድማማችነት፣ ጓደኝነት እንደ ማለት ነው። ግብፅ ይህንን ስትመሠርት መጠሪያው በስዋህሊ እንዲሆን ያደረገችው አስባበት እንደሆነ መገንዘብ አያዳግትም። ይኼ ማኀበር የተመሠረተው እ.ኤ.አ. በ1983 ሲሆን፣ የመጀመርያውን ጉባዔ በካርቱም ከጥቅምት 2 እስከ 4 ቀን 1983 ዓ.ም.፣ የሁለተኛውን በዛየር ኪንሻሳ ከመስከረም 3 እስከ 4 ቀን 1984 ዓ.ም.፣ ሦስተኛውን በካይሮ ከነሐሴ 7 እስከ 8 ቀን 1985 ዓ.ም.፣ አራተኛውና ሌሎች ቀጣይ ስብሰባዎችም ከዚያ በኋላ ተካሂደዋል፡፡  

እጅግ በጣም የሚያሳዝነውና የሚያስገርመው ነገር ቢኖር 86 በመቶ የዓባይ ምንጭ የሆነችው ኢትዮጵያ በማኀበሩ ውስጥ ያለመታቀፏ ነው። ግብፆች አንዳንዴ ሲያሰኛቸው ኢትዮጵያ በታዛቢነት እንድትገኝ አልያም የእነርሱ አርቲፊሻል ማኀበር ሰለባ እንድትሆን ሲወተውቱ መቆየታቸው አዲስ ነገር አይደለም። የዚህም ማኀበር ዋና ዓላማ  በቀጥታ ሲታይ ወንድማማችነትን ማጠናከር መስሎ ቢታይም፣ ድብቅ አጀንዳው ግን በዓባይ ላይ የሚደረጉ ማናቸውም የልማት እንቅስቃሴዎች ከግብፅ ዕይታ እንዳይወጡ መቆጣጠሪያ ዘዴ እንደሆነ ብዙም ጥናት የሚያስፈልገው ጉዳይ አይደለም።

በኢትዮጵያ በኩል በማወቅም ሆነ ባለማወቅ እስከ አምስተኛ ጉባዔ ድረስ አልፎ አልፎ ድምጿን ለማሰማት ከሞመከር ያለፈ እምብዛም የረባ እንቅስቃሴ ሲደረግ አልታየም። ከዚያ ወዲህ ግን ናይል 2002 ዓ.ም. በተባለውና በኢትዮጵያ አቆጣጠር በ1993 ዓ.ም. በተመሠረተው ጉባዔ ኢትዮጵያ መሳተፍ ከመጀመሯም በላይ፣ አምስተኛውንና ስምንተኛውን የናይል ጉባዔ በማስተናገድ ወደ መጫወቻ መድረኩ በቀጥታ የገባች ይመስላል።

የዓባይ ውኃን አጠቃቀም በተመለከተ ኢትዮጵያም ትሁን ሌሎች አዋሳኝ አገሮች ሁሉን የሚያካትት ወጥ ሕግ የላቸውም። ሆኖም በጋራ ለመጠቀም የሚያስችሉ ስምምነቶች አሏቸው። ከዚህ ውጪ የትኛው አገር ምን ያህል ውኃ መጠቀም እንደሚችል የሚያመለክት ነገር የለም።

በግብፅና በሱዳን የተደረገው እ.ኤ.አ የ1959 ስምምነት ሌሎችን የሚያካትት ሳይሆን ሙሉ በሙሉ የግብፅን ጥቅም የሚያስጠብቅ ነው። ይህ ውል በሁለቱ አገሮች መካከል ያለውን መብትና ግዴታ ከማመላከት ባሻገር የሚያመጣው ፋይዳ አይኖርም። ከዚህ ይልቅ የጋራ ሀብትን ግብፅ በማናለብኝነትና በብቸኝነት ለመጠቀም የምታደርገውን እንቅስቃሴ በጉልህ ያሳያሉ። በተለይም ግብፅ በዓባይ ዙሪያ (በኢትዮጵያ) ላይ የምታደርገው ፖለቲካዊና ዲፕሎማሲያዊ እንቅስቃሴ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅምና ደኅንነት አኳያ መታየት ስላለበት፣ ጉዳዩ በኢትዮጵያ በኩል ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ነው፡፡

አንዳንድ የፖለቲካ ተንታኞች እንደሚሉት በግብፅ ዓይን ሱዳን ቁልፍ ስትራቴጂ ከመሆኗም ባሻገር፣ ሱዳንን በክፉ የሚመለከት ኃይል ግብፅን አያስደስታትም፡፡ ስለሆነም ሱዳን በተቻለ መጠን ከግብፅ መዳፍ እንዳታፈተልክ የማያደርጉት እንቅስቃሴ የለም። ምንም እንኳን ግብፅ ሱዳን የሸሪዓ ሕግ በማወጇና ከሊቢያና ከኢራን ጋር የምታደርገው ድብቅ እንቅስቃሴ ባያስደስታቸውም፣ የሱዳንን መልካም ወዳጅነት ማጣት ግን አይፈልጉም።

ጠቅለል ባለ መልኩ የግብፅና የሱዳን ጥብቅ የፖለቲካ ግንኙነት ሲታይ እውነትም በሁለቱ አገሮች መካከል ያለውን መግባባት የሚያመላክት ሳይሆን፣ ግብፅ ከሱዳን በስተጀርባ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚደረገውን ጠቅላላ ሁኔታ ለመከታተል እንዲያመቻት የምታደርገው እንቅስቃሴ ሊሆን እንደሚችል ይገመታል። ለዚህም ስኬታማነት የተለያዩ የግብፅ መሪዎች ከሱዳን ጋር በርካታ ስምምነቶች ያደረጉ ሲሆን ከእነዚህም መካከል፣ እ.ኤ.አ. የ1959 የዓባይ ውኃ ክፍፍል ስምምነት፣ እ.ኤ.አ. የ1976 የመከላከያ ስምምነት፣ እ.ኤ.አ. የ1982 የውህደት ስምምነት፣ ግብፃውያንን ለመጥቀም የተደረገው የጆንግሊ ካናል ቁፋሮ ስምምነት ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡

ዛሬ አል ኢትሃድ አልወጠኒ የተባለው ፖለቲካዊና ሃይማኖታዊ አንጃ በሱዳን ውስጥ የግብፅን ጥቅም የሚያስጠብቅ ግብፅ ዘመም ድርጅት ሲሆን፣ የሁለቱ አገሮች ስምምነት ሲጤን አብሮ ግምት የሚሰጠው ጉዳይ ነው።

ሶማሊያ የዓረባዊነት ስሜት ከሚታይባቸው የምሥራቅ አፍሪካ አገሮች አንዷ ስትሆን፣ ግብፅም ይህንኑ መሠረት አድርጋ በሶማሊያ የምታደርገው እንቅስቃሴ ቀላል ግምት የሚሰጠው አይደለም። በተለይም የሶማሊያ ችግር በኢትዮጵያ ሽምግልና እልባት እንዲያገኝ ግብፅ የሚጠበቅባትን ያህል ሚና አለመጫወቷ ሊጤን የሚገባው ጉዳይ መኖሩን ያመለክታል፡፡

ዓባይ 6,825 ኪ.ሜ ርዝመት ያለው በዓለም ውስጥ በርዝመቱ የመጀመርያውን ደረጃ ይዞ የሚገኝ፣ አሥር አገሮችን የሚያዋስን፣ የወንዙ አመንጪና ባለቤት አገሮች የማይጠቀሙበት፣ በአንፃሩ ለወንዙ ምንም ዓይነት አስተዋጽኦ የሌላቸው አገሮች ሙሉ በሙሉ በባለቤትነት የሚጠቀሙበት ትልቅ እንቆቅልሽ ያዘለ ወንዝ ነው።

እስከ ዛሬ ድረስ የተፋሰሱን አገሮች የሚያስተሳስርም ሆነ ወንዙን በጋራ ለመጠቀም የሚያስችል ስምምነት የለም። በአንዳንድ የተፋሰሱ አገሮች መካከል የተደረጉ ስምምነቶች ቢኖሩም፣ እነርሱም ሙሉ በሙሉ በግብፅ የፖለቲካ ጠበብት ለግብፅ ጥቅም ሲባል የተቃኙ በመሆናቸው በሌሎች የተፋሰሱ አገሮች ተቀባይነት የላቸውም።

በተለይ በ19ኛውና በ20ኛው ክፍለ ዘመን ግብፅና ሱዳን የእንግሊዝ ቅኝ ግዛቶች  ስለነበሩ የእንግሊዝን ወቅታዊ ጥቅም ለማስከበር ሲባል ብቻ፣ በወቅቱ በዓባይ ላይ የተደረጉ ስምምነቶች ግብፆችን ከመጥቀሙ በተጨማሪ በወንዙ ላይ ለሚነሱ ውዝግቦች ሁሉ መነሻ ሆኗል።

ከዚህ በተጨማሪም እንግሊዞች በኢትዮጵያ የቅኝ ግዛት ስላልነበራቸው ኢትዮጵያን ለማዳከም ሲሉ በኢትዮጵያ ላይ የረዥም ጊዜ የቅኝ ግዛት ፍላጎትና ዕቅድ ያላትን ጣሊያንን የቅኝ ገዥ አጋር በማድረግ፣ በዓባይ ውኃ አጠቃቀም በተዋናይነት እንድትሠለፍ አድርገዋል።

ዛሬም ግብፅ የቅኝ ገዥዎችን ፈለግ በመከተል የዓባይን ወንዝ በብቸኝነት ለመጠቀም የማታደርገው ዲፕሎማሲያዊና ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ የለም። ከእነዚህ ፈርጀ ብዙ እንቅስቃሴዎች አንዱ የቅኝ ግዛት ዘመን ስምምነቶች እንዳሉ እንዲተገበሩ ያላት ፍላጎት ነው።

  1. የ1902 የኢትዮጵያና የእንግሊዝ ስምምነት

ይህ በዳግማዊ ምኒልክና በታላቋ ብሪታኒያ መካከል በአዲስ አበባ እ.ኤ.አ. ሜይ 15 ቀን 1902 የተፈረመው የመጀመርያው ዓባይ (ጥቁር) ነክ ስምምነት ነው። የዚህ ስምምነት አንቀጽ 3 በእንግሊዝኛው እንደሚከተለው ሰፍሯል፡፡

“The Emperor Menlik  engages not to construct or allow to be constructed any work across Blue Nile, Lake Tana or the Sobat which would arrest the flow of the water into the Nile except in agreement with the Government of Great Britain and the Sudan.”

የዚህ ስምምነት ፍሬ ነገር በጥልቀት ሲጤን አራት ጠቃሚ ነገሮችን የሚያመለክት ሆኖ ይታያል። አፄ ምኒልክ ከእንግሊዝ ጋር ያደረጉት ስምምነት ወንዙን በከፊልም ሆነ በተሟላ መልኩ እንዳይጠቀሙ የሚያግድ አይደለም። ምክንያቱም (Which Would Arrest) የሚለው ሐረግ ውኃውን ሙሉ በሙሉ እንዳይፈስ ከመገደብ ውጪ፣  ኢትዮጵያ ዓባይን ከመጠቀም የሚከለክላት ነገር የለም። “Except in Agreement with Great Britain” የሚለው ሐረግ ጊዜያዊነትን የሚያመለክት እንጂ ዘለቄታዊ አይደለም። ሌላው የስምምነቱ መንፈስ ከእንግሊዝና ከሱዳን መንግሥት ምክክር ውጪ ይላል እንጂ ስምምነቱ ግብፅን አይመለከትም። የከለከሉት ምኒልክን ስለሆነ ምኒልክ ሲያልፉ አብሮ የሚሞት ጉዳይ እንጂ ነባራዊነት የለውም።

  1. የ1906 ስምምነት

እ.ኤ.አ. ከ1906 ዓ.ም. ወዲህ ኢትዮጵያን የማያካትት ወይም ከኢትዮጵያ ዕውቀት ውጪ የተደረገው የናይል ውኃ ስምምነት የ1906 የሦስትዮሽ ስምምነት በመባል የሚታወቀው እንግሊዝ፣ ጣሊያንና ፈረንሣይ ለንደን ላይ እ.ኤ.አ. ታኅሳስ 13 ቀን 1906 ያደረጉት ስምምነት ነው። ይሁን እንጂ ይህ ስምምነት አውሮፓውያን ኢትዮጵያን ለመቀራመት ያደረጉት በመሆኑ፣ አፄ ምኒልክ ‹‹ስምምነቱ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት የሚፃረር ነው፤››በማለት ውድቅ አድርገውታል።

3 . የ1925 የእንግሊዝና የጣሊያን ስምምነት (Exchange of Notes)

ዓባይን ከምንጩ ለመቆጣጠር ፍላጎት ያላት እንግሊዝ አሁንም በኢትዮጰያ በኩል ተቀባይነት እንደማታገኝ ስለገባት፣ ጥቅሟን ለማስከበር ስትል በጣሊያን በኩል የእጅ አዙር እንቅስቃሴ ቀጠለች። በዚህም መሠረት እ.ኤ.አ. በ1925 ከጣሊያን ጋር ግብፅና ሱዳን በዓባይ ውኃ ጠቀሜታ ላይ ቅድሚያ እንዲኖራቸው ስምምነት ላይ ደረሱ። ከዚህ በተጨማሪም ጣሊያን በጥቁር ዓባይና በሶባት ላይ ምንም ዓይነት ሥራ ላለማከናወን ስምምነት አደረገች።

ይህ ስምምነት ሲደረግ በወቅቱ ኢትዮጵያ የሊግ ኦፍ ኔሽንስ አባል ስለነበረች፣ በዚያ በኩል በመልክዕተኛዋ አማካይነት በሉዓላዊነቷ ላይ የተቃጣ ስምምነት መሆኑን በማመልከት ከፍተኛ ተቃውሞዋን አሰማች። በዚህም ምክንያት ስምምነቱ ተግባራዊ ሳይሆን ቀርቷል።

4. የ1929 ስምምነት

ሌላው ስምምነት እ.ኤ.አ. ግንቦት 7 ቀን 1929 በግብፅና እንግሊዝ (ሱዳንን በመወከል) መካከል የተደረገው ስምምነት ሲሆን በዚህ ስምምነት መሠረት ግብፅ የውኃውን 48 ቢሊዮን ኪዩብክ ሜትር፣ ሱዳን ደግሞ አራት ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ታገኛለች የሚለው ነው።

ይህ ስምምነት የፈጠረው አጋጣሚና አስደናቂ ነገር ቢኖር፣ ግብፅ በአንድ በኩል ሱዳን በውኃው የመጠቀም መበት እንዳላት ማወቋ ሲሆን፣ በሌላ በኩል ደግሞ በውኃው የመጠቀም ቅድሚያ እንዳላት የሚያረጋግጥ የስምምነት ሐረግ ለመጨመር ያደረገችው ጥረት ነው።

ኢትዮጵያ የዚህን ስምምነት ዋጋም ሆነ የግብፅን ታሪካዊ መብት አልተቀበለችውም፣ ልትቀበለው የምትችለው ጉዳይም አይደለም። የመቀበል ግዴታም  (Binding Effect) የለባትም። ምክንያቱም ሁለቱ አገሮች የሚያደርጉት ስምምነት ሦስተኛውን ወገን/ካለእርሱ ስምምነት ማካተት አይገባውምና።

በሌላ በኩል ሱዳንም ብትሆን ነፃ ከወጣች ወዲህ ስምምነቱ በሱዳን ኪሳራ ግብፅን ለማበልፀግ ወይም የሁለቱን አገሮች ወዳጀነት ለማጠናከር የተደረገ እንቅስቃሴ ስትል ትተቸዋለች።

5. የ1959 ስምምነት

ይህ ስምምነት ሌሎች የዓባይ ተፋሰፍ አገሮችን በማግለል ግብፅና ሱዳን ብቸኛ ተጠቃሚ ለመሆን ያደረጉት ፍትሐዊ ያልሆነ ስምምነት ነው። በዚህ ስምምነት የታየው አዲስ ነገር ቢኖር ግብፅ የመጠቀም ቅድሚያ (Acquired Rights) የሚለውን አቋሟን በመለወጥ፣ የሱዳን ፍፁም የግዛት አንድነት (Absolute Territorial Integrity) በሚለው መርህ እስከ 18.5 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውኃ እንድትጠቀም መፍቀዷ ነው።

ኢትዮጵያ በድርድሩም ሆነ በስምምነቱ ተቃውሞዋን ከማሰማቷ ባሻገር ስምምነቱን የማትቀበል መሆኗን አሳውቃለች። በሌላ በኩል የስምምነቱ መንፈስ ሲታይ በሁለቱ መካከል ያለውን መብትና ግዴታ ከማመላከት ባለፈ፣ ሌሎች አገሮችን ከግብፅና ከሱዳን ፈቃድ ውጪ የሚያካትት አይሆንም።

ከአዘጋጁ፡- ጽሑፉ የጸሐፊውን አመለካከት ብቻ የሚያንፀባርቅ ሲሆን፣ ጸሐፊውን በኢሜይል አድራሻቸው eskinder.kebe1996@gmail.com. ማግኘት ይቻላል፡፡

 

 

Standard (Image)

መንግሥት እንኳን የግሉን የራሱንም ሚዲያዎች አልታደገም!

$
0
0

 

በዳግም አሳምነው ገብረወልድ

የዚህ ጽሑፍ መነሻ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትሩ ነገሪ ሌንጮ (ዶ/ር) ‹‹የተናገሩት›› በሚል ‹‹አዲስ ልሳን›› የተባለ መንግሥታዊ ጋዜጣ ያወጣው ዜና ነው፡፡ ርዕሱ ‹‹መንግሥት የግሉን ሚዲያ ተሳትፎ ለማሳደግ ይሠራል›› የሚል ሲሆን፣ አገሪቱ ያላትን የግል ሚዲያዎች ተደራሽነትና ተሳትፎ በማስፋት ጥረቱን በማሳደግና ተወዳዳሪነቱን በማጠናከር ረገድ ያለውን የአቅም ክፍተት በመድፈን ለዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ያላቸውን ሚና ያሳድጋል ይላል፡፡ በነሐሴ 23 ቀን 2009 ዓ.ም. የጋዜጣው እትም፡፡

ዜናው የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን ባዘጋጀው አንድ ዓውደ ጥናት ላይ ተመሥርቶ የተሠራ ሲሆን፣ በመድረኩ ሁለት ጥናታዊ ጽሑፎች መቅረባቸውንም አውስቷል፡፡ ይሁንና ‹‹ከአንድ ሺሕ በላይ ከተመዘገቡ የኅትመት ሚዲያዎች በሥርጭት ላይ ያሉት 18 ጋዜጦችና 43 መጽሔቶች ብቻ ናቸው›› ከሚል ፀፀት በስተቀር ባለፉት 12 ዓመታት ተደጋግመው የተባሉ ሐሳቦች በመድረኩ መሰንዘራቸውን የሚያመለክት ነው፡፡

በዚህ ጽሑፍ እንደመከራከሪያ ነጥብ ለማንሳት የምሻው የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤትም ሆነ የክልል ቢሮዎች ከተቋቋሙ ወዲህ እንኳንስ የግሉ ሚዲያ ሊስፋፋ የመንግሥት መገናኛ ብዙኃንም መዳከማቸውን ነው፡፡ በአንድ በኩል ‹‹ልማታዊ ጋዜጠኝነትና ኮሙዩኒኬሽን›› ሚናቸው ተቀላቅሎ የተበራከቱበት ወቅት ላይ እንገኛለን፡፡ በሌላ በኩል የአገሪቱ አንጋፋ የመገናኛ ብዙኃን በአዋቂ ከመመራት ይልቅ በካድሬ፤ በልምድ ከመሥራት ይልቅ በጥራዝ ነጠቆች እየኮሰመኑ ያሉበት ወቅት ላይ በመሆናቸው ነው፡፡

መንግሥት ‹‹የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች›› የተባለውን ተቋም ከፌዴራል እስከ ወረዳ በአዲስ መልክ ሲያደራጅ የተጣሉ ተስፋዎች ነበሩ፡፡ አንደኛው የመንግሥት ሕዝብ ግንኙነት (ማስታወቂያ) ሥራ ከቃል አቀባይነት አልፎ በሕዝብና በመንግሥት መካከል ድልድይ መሆን እንዲችል ነበር፡፡ ይህ ፍፁም ላለመሳካቱ አሁን የተያዘው የሕዝቡ ጥያቄ ሕዝብ ግንኙነቱ ከሚያነበንበው ፕሮፖጋንዳ ጋር ያለው ተቃርኖ ‹‹ፍየል ወዲህ ቅዝምዝም ወዲያ›› መሆኑ አመላካች ነው፡፡

ሌላኛውና የዚህ ጽሑፍ ማጠንጠኛ የመሥሪያ ቤቱ መቋቋም የመገናኛ ብዙኃንና የመረጃ ነፃነት ሕጉ በተሟላ መንገድ እንዲተገበር ነበር፡፡ ይህም የዜጎችን የሐሳብ ነፃነት ይበልጥ በማረጋገጥ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት እንዲያብብ መሠረታዊ ጉዳይ መሆኑ ይታመናል፡፡ በተጨባጭ መሬት ላይ ያለው እውነት ግን ሚኒስቴሩ አራት የሥራ ኃላፊዎችም ተቀያይረውበት ስንዝር የለውጥ ምልክት አለመታየቱን ነው፡፡ ይህን መሠረታዊ ክፍተት ደግሞ መንግሥት ራሱ ከሚመራቸውና ከሚያስተዳድራቸው ‹‹የሕዝብ›› ሚዲያዎች መዳከም ጋር አስተሳስሮ መመልከት ያስፈልጋል፡፡

የሕትመት ሚዲያው መንገታገት

በክልል መንግሥታት ከሚታተሙት የፓርቲና የመንግሥት ልሳኖች ባሻገር በፌደራል ደረጃ የኅትመት መገናኛ ብዙኃን ሥራ የሚሠራ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የተባለ ተቋም አለ፡፡ ይህ አንጋፋ መሥሪያ ቤት አዲስ ዘመን፣ ኢትዮጵያን ሔራልድ፣ ዘመን መጽሔት፣ በሬሳና አልዓለም የተባሉ ኅትመቶችን በተለያዩ ቋንቋዎች እያዘጋጀ ያሠራጫል፡፡ በክልል የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን እየታተሙ የሚሠራጩ ጋዜጦች (ትግራይ - መቓልህ ትግራይ፤ ኦሮሚያ፣ አማራ በኩር፣ ደቡብ - ንጋት፣ አዲስ አበባ - አዲስ ልሳን) የተባሉ የኅትመት ውጤቶች አሉ፡፡

እነዚህና ሌሎች ያልተጠቀሱ በመንግሥት ቁጥጥር ሥር ያሉ ከ25 በላይ የኅትመት ውጤቶች የየራሳቸው ኤዲቶሪያል ፖሊሲ ቢኖራቸውም፣ ሕገ መንግሥቱና አዋጅ 590/2000 ‹‹የፕሬስ ነፃነትን›› ቢያስተጋቡም፣ በጥብቅ ‹‹የኤዲቶሪያል ኮሚቴ አሠራር›› የተከረቸሙ ናቸው፡፡ ለዚህ ደግሞ ምክንያቱ ራሳቸው የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን መሥሪያ ቤቶች በሳምንታዊ አቅጣጫ፣ በቦርድ ሰብሳቢነትና ‹‹በአቅም ግንባታ ሥልጠና›› ስም እንዳይላወሱ ስላደረጓቸው ነው፡፡ የእጅ አዙር ቅድመ ምርመራ ይሉሃል ይህንኑ ነው፡፡

ለረዥም ጊዜ በሙያው ውስጥና በአንጋፋ የኅትመት ተቋማት የሠሩ ጋዜጠኞች እንደሚናገሩት፣ መንግሥት በአገራዊና ዓለም አቀፋዊ ጉዳይ የሚዲያ ትኩረት አቅጣጫ መስጠቱ ተገቢ ነው፡፡ ነገር ግን ‹‹ይህን ጻፍ፣ ያንን አትጻፍ፣ እገሌ አባባሉ በሚዲያው እንዳይስተናገድ ወይም ሕዝቡ የሚነጋገርበትን ጉዳይ አትንካው…›› እያለ የሚገድብ መንግሥታዊ አካል ካለ ሞቶ የተቀበረው ቅድመ ምርመራ ተመልሶ ስለመምጣቱ ዋስትና የለም ባዮች ናቸው፡፡ ከዚህ አንፃር የኅትመት መገናኛ ብዙኃን አንዳንድ ሙያተኞች በግል ጥረት የሚያሳዩትን የሐሳብ ነፃነትና መንግሥታዊ ሒስ ጭምር ሊገፉበት እንደማይችሉ ዕሙን ነው፡፡ (እዚህ ላይ ዶ/ር ጀማል መሐመድ ‹‹ደንባራዎቹ መገናኛ ብዙኃን›› ሲሉ በጥልቀት የታዘቡትን ጽሑፍ በነሐሴ 21 ቀን 2009 ዓ.ም. ሪፖርተር ጋዜጣ መመልከት ይገባል፡፡

ክቡር ሚኒስትርና የቀድሞው የዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነትና ኮሙዩኒኬሽን መምህሩ እንደሚያውቁት ጋዜጠኝነት የህሊና ነፃነትና ሚዛናዊነትን ግድ የሚል ሙያ ነው፡፡ በዚህ ረገድ እውን አሁን ባሉት መንግሥታዊ የመገናኛ ብዙኃን ከፓርቲ አባልነት ውጪ የሆኑ ኤዲተሮችና አዘጋጆችን ማግኘት ይቻላል?! ታዲያ በየትኛው መርህ (በፓርቲ አባልነቱ ወይስ በጋዜጠኝነቱ) እየተመሩ ነው ለሐሳብ ብዝኃነት ልዕልና በመሥራት ዴሞክራሲውን የሚያሳድጉት!? መፈተሽ ያለበት ጥያቄ ነው፡፡

በአገሪቱ ያሉት ዋና ዋናዎቹ የመንግሥት የኅትመት መገናኛ ብዙኃን አይደለም በደርግ ዘመን በንጉሡም ጊዜ የነበሩ ናቸው፡፡ ልዩነቱ ያኔ መነግሥት በጀት መድቦ እንዲታተሙ ያደርግ ነበር፡፡ አሁን ግን በራሳቸው የማስታወቂያ ገቢ እየተንገዳገዱ (ያለምንም የመንግሥት በጀት ድጎማ) መታተማቸው ነው፡፡ በይዘት ረገድ የታዩ እንደሆነም ትናንትም ሆነ ዛሬ ‹‹የየሥርዓቶቹ አገልጋዮች ናቸው›› በሚል አንባቢው ደምድሞ ቁጭ ካለ ከራርሟል፡፡ የልማት ጋዜጠኝነትን ሸርፎ መጓዝ ያመጣው ጣጣ ይኼ ነው፡፡

ሌላው አሳዛኝ እውነታ ከ75 ዓመታት በላይ ዕድሜ ያላቸው ጋዜጦች ስርጭት አሁንም ከአሥር ሺሕ ያለመዝለሉ ነው፡፡ (እንዲያውም ደርግ በግዳጅ ስርጭትም እስከ 35 ሺሕ በማድረሱ ቢያንስ ለንባብ ባህልና ለሥነ ጽሑፍ ዕድገት የተጫወቱት ሚና የሚናቅ አልነበረም፡፡) በባለሙያ ረገድም ብዙዎቹ የተባ ብዕር ያላቸውና እያረገፉ በድዳቸው ቀርተዋል፡፡ ጥቂት ስሜትና ሙያ ያላቸው ታታሪ ጋዜጠኞች የሉም ባይባልም ኢንዱስትሪው ከሚፈልገው ነፃነት፣ ብርቱ የአመራር ድጋፍ፣ በቂ ክፍያና ጥቅማ ጥቅም አንፃር እርካታ በማጣት ቀለማቸው እየደረቀ ሄዷል፡፡ ሥር ነቀሉን ለውጥ ለማምጣትም የሚቻላቸው አይደሉም፡፡

የብሮድካስቱ ሚዲያ ፈር እየለቀቀ መሄድ

አንድ ለእናቱ የነበረው የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የአሁኑ ‹‹ኢቢሲ›› ከመሪ ቃሉ አንስቶ ለብዝኃነት የቆመ መሆኑን ይገልጻል፡፡ ይሁንና ለቋንቋ፣ ብሔርና ለጾታ ብዝኃነት የሚጨነቀውን ያህል (ያውም ከተጨነቀ) ለአመለካከት ብዝኃነት ደንታም የለውም፡፡ በዚህች አገር ውስጥ በርካታ አስተሳሰቦች እንደሚራመዱ ብቻ ሳይሆን ጫፍና ጫፍ ላይ ቆመው እንደሚካረሩ ቢታወቅም የምርጫ ሰሞን የሚያደርገውን ሙከራ ያህል እንኳን ፎረም አይፈጥርም፤ አጀንዳ አይቀርፅም፤ ከመንግሥት (የገዢው ፓርቲ) አቋም የተለየ ሐሳብ ማስተላለፉን (የሐሳብ ሙግት ማድረግን) ‹‹እንደ ወንጀል›› ቆጥሮ ዓይኑን ከጨፈነም ውሎ አድሯል፡፡ ይኼ ለዴሞክራሲ ተግባር ደግሞ በሕግ ባይደገፍም በኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት አቅጣጫ እንደተቆለፈ አለመጠርጠር የዋህነት ነው፡፡

በመንግሥት ቁጥጥር ሥር ያሉ የሬዲዮ ጣቢያዎች አካሄድ ከቴሌቪዥን የመሻል ነገር ቢኖረውም ተመሳሳይ ነው፡፡ ሌላው ቀርቶ በሕዝቡ ውስጥ ለዓመታት ሲቦካ፣ ሲጋገር የነበረውን የሙስናና የመልካም አስተዳደር እጦት አጀንዳ በቆሪጥ ሲመለከቱ ከርመው አሁን ላይ በመንግሥት (ፓርቲ) ውሳኔ ‹‹ሙሰኛ መጠየቅ ሲጀምር›› ያዙኝ ልቀቁኝ ማለት አሳፋሪ ነው፡፡

የብሮድካስት ሚዲያ የሚባሉት የቴሌቪዥንና የሬዲዮ ጣቢያዎች አንድ ጊዜ መሠረተ ልማቱ ከተዘረጋላቸው እንደ ኅትመት ሚዲያ ያለ የኅትመት ወጪ አያስጨንቃቸውም፡፡ ይሁንና ሕዝቡ ውስጥ በጥልቀት ደርሰው ተፅዕኖ ለመፍጠር የብዙኃኑን ሐሳብ የሚያካትት፣ በአንፃሩም ቢሆን ሚዛናዊና ገለልተኛ አካሄድ መከተል አለባቸው፡፡ አሁን ከተጣባቸው የአንድ ወገን መረጃና የስኬት ዘገባ (Success Story) ማማ ላይ ወርደው ወደ አዝመራው ውስጥ ገብተው ማረምና መድከም ካልቻሉም ለዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታው ጠብታ አስተዋጽኦ ሊኖራቸው አይችልም (እዚህም ላይ የዶ/ር ጀማልን ጽሑፍ ያጤኑዋል!)፡፡

የብሮድካስት ሚዲያው ፈሩን እየለቀቀ ነው የሚባለው ግን ሕገ መንግሥታዊውን የሐሳብ ነፃነት በመገደቡ ብቻ አይደለም፡፡ ይልቁንም የማንነት፣ የባህል፣ የቋንቋ፣ የአመለካከት… ብዝኃነት በታጨቀበት አገር ውስጥ፤ ድህነቱ እንደ መርግ የከበደው ዜጋ ቁጥር በሚያኩራራ ደረጃ ገና ሳይራገፍ ለውጭው ዓለም ስፖርትና መዝናኛ እንዲሁም ለቧልትና እንቶ ፈንቶ ወግ የመደቡት የአየር ሰዓት በመብዛቱ ነው፡፡ (በኢቢሲ፣ ሬዲዮ ፋናና አዲስ አበባ መገናኛ ብዙኃን ለመዝናኛ የተሸጡ የአየር ሰዓቶችን ያስታውሷል፡፡)

በመሠረቱ በኢትዮጵያ የሚዲያ ምህዳር ውስጥ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ጎልቶ እየታየ ያለው ብቃት ያለው ሙያተኛ ረሃብ ቀላል ችግር አይደለም፡፡ ከጊዜ ወደ ጊዜ እጃቸውን የፈቱና ‹‹ዕውቅና›› የሸመቱት ሁሉ ለምን የብሮድካስቱን ሚዲያ እየተዉ ወጡ? በእንዴት ያለ ፍጥነት የግል አየር ሰዓት ለመክፈትስ ቻሉ፣ ብሔራዊውን ሚዲያ ተመሳሳይ አመለካከትና እምነት በያዙ ሙያተኞች መሙላቱስ ጉዳቱና ጥቅሙ ምንድን ነው? ብሎ የሚመረምር ያለ አይመስልም፡፡ እውነታው ግን ኢትዮጵያን መምሰል ያለባቸውና በሙያ ብቃትና ግልፅ አሠራር ሊመሩ የሚገባቸው የሚዲያ ተቋማት ሳይቀሩ ያልሆነ መልክ እየያዙ መምጣታቸውን ቁልጭ አድርጎ ያሳያል፡፡

የሚዲያው አመራር ምን ያህል ተራማጅ ነው?

በአገራችን የመገናኛ ብዙኃን ታሪክ ውስጥ በስም ተጠቃሽ የሥራ ኃላፊዎች፣ ኤዲተሮችና ጋዜጠኞች እንደነበሩ ይታወቃል፡፡ ብዙም በማያፈናፍኑት የፖለቲካ ሥርዓቶች ሐሳባቸውን በግልጽም፣ በገደምዳሜም የሚያወጡ፣ የሕዝቡን ጥያቄ ለመንግሥት ለማድረስ የሚጥሩም ነበሩ፡፡ (ከዚህም በላይ በአገሪቱ ሥነ ጽሑፍ ዕድገት ውስጥ ጉምቱ አሻራ ያሳረፉ ጋዜጠኞችና አርታዕያን ዛሬም ድረስ ስማቸው ይጠራል፡፡ (እነ በዓሉ ግርማ፣ ጳውሎስ ኞኞ፣ ስብሐት ገብረእግዚአብሔር፣ ሙሉጌታ ሉሌ፣ ብርሃኑ ዘሪሁን… ከኅትመት ዘርፍ እንዲሁም ከብሮድካስት እነ አሳምነው ገብረወልድ፣ ታምራት አሰፋ፣ ሻምበል ግዛው ዳኜ፣… አፈሩ ይቅለላቸውና ይጠቀሳሉ፡፡) በሕይወት ያሉም ብዙዎችን ማውሳት ይቻል ይሆናል፡፡ እስኪ ከዚህኛው ትውልድ ማንን እንጥቀስ፡፡ በተለይ በመንግሥት ሚዲያው ውስጥ ‹‹ማንን አንቱ እንበል!?›› ብሎ መፈተሽ ያስፈልጋል፡፡

አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ የጋዜጠኝነት ሙያን ጠንቅቆ አውቆ፣ ሠርቶ ከሚያሠራው ኃላፊና አርታዒ ይልቅ በበረኝነት ታዛዥነት ‹‹ጉብዝናው›› የተመረጠው በርክቷል፡፡ ዓለም የደረሰበትን ሁኔታ ተገንዝቦ፣ የአገሪቱን የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ፍላጎት ተረድቶ የሐሳብ ብዝኃነትን ከሚያስተናግደው ይልቅ በቀድሞዎቹ ሥርዓቶች አንጎበር እየተንገዳገደ የሚመራው ብዙ ነው፡፡ ይህን ደግሞ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ጠንቅቆ ከማወቅም በላይ ይገነዘበዋል፡፡ ሊለውጠውም ፍላጎት የለውም፡፡

በመሠረቱ ተራማጅነት (Progressiveness) የሚመዘነው የተለያዩ አዳዲስ አስተሳሰቦችን፣ ጊዜው የሚጠይቀውን ብቃት በመያዝና በመተግበር ነው፡፡ ሌላው ቀርቶ አገራችንም ሆነች ሕዝቦቿ ከአሥር ዓመታት በፊት በነበሩባት ቁመና ላይ አይደሉም፡፡ የሚዲያ ኢንዱስትሪው ራሱ በማኅበራዊ ድረ ገጾችና እንደ አሸን በሚፈሉ የሳተላይት የቴሌቪዥን ጣቢያዎች በግልጽ እየተፈተነ ነው፡፡ የአገራችን የመንግሥት ሚዲያ አብዛኛው አመራሩ ግን ይህን ‹‹ቻሌንጅ›› ስለመኖሩ ማሰብ አይፈልግም፡፡ ከሙያው ተወዳዳሪነት ይልቅ በስመ ‹‹ካድሬነት›› የተሰጠውን ወንበር እየጠበቀ ካለለውጥ ሕዝቡንም፣ መንግሥትንም እንዳስቀየመና እንዳራራቀ መቀጠል ይሻል፡፡

በፌዴራሉ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት እየተመደበ ‹‹ድጋፍ›› የሚደረግለት ይኼ ኃይል በየሩብ ዓመቱ እየተገናኘ ሥራውን ይገመግማል፡፡ ኃላፊዎች፣ ዋና አዘጋጆችና መምሪያ ኃላፊዎች ሁሉ በተገኙበት በሚደረገው የጋራ ፎረም ግን ተሞጋግሶ፣ አለባብሶ ከመሄድ ያለፈ ውጤት አላሳየም፡፡ ወይ በጅምላ ይወቀሳል፡፡ አልያም ‹‹የሕዝብ ሚዲያው›› ተብሎ በአንድነት ይመሰገናል፡፡ እንጂ ደካማ፣ ከጠንካራ አይለይም፡፡ ዕውቅና አይሰጥም፤ ምርጥ ተሞክሮ ተለይቶ እንዲሰፋ አይሞከርም፡፡ ታዲያ ይኼ እውነታ እየታወቀ በየትኛው ብርታት ነው ከመንግሥት ሚዲያ አልፎ የግሎቹን ለማጠናከር የሚቻለው!? ያው የተለመደ ቧልት ካልሆነ በስተቀር፡፡

በየትኛውም የሥራ መስክ ቢሆን ሙያተኛውም ሆነ ራሱ ተቋሙ (መሥሪያ ቤቱ) አመራሩን መምሰሉ አይቀርም፡፡ በሚዲያው ዘርፍም ይህ ሐቅ ሲንፀባረቅ እንደሚታይ ሙያተኞች ይናገራሉ፡፡ አንዳንድ በሙያ ብቃት የሚታወቁ የሥራ መሪዎች ሥልጠናና ድጋፍ ከመስጠት አልፈው፣ ጠንካራ ፎረምና ‹‹ዲስኮርስ›› እንዲጀመር አድርገዋል፡፡ አብዛኛው ‹‹የዘልማድ›› የሚዲያ መሪ ግን የመንግሥትና የፓርቲ ሥራን እየደበላለቀ፣ በጎሳና በመንደር ልጅነት እያደራጀ፣ ተላላኪና ካለመርህ የሚታዘዝን እየኮለኮለ ካለውጤት የሚውል ነው፡፡ መጠላለፍ የበዛባቸው የሚዲያ ክፍሎችም ሙያተኛውን አሽቀንጥረው እየገፉት ይገኛሉ፡፡

በመንግሥት የመገናኛ ብዙኃኖች ውስጥ ጎልቶ የሚታየው የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ችግር፣ የአደረጃጀት ጉድለት የሥልጠናና ግንባታ ማነስ ሁሉ የአመራሩ ውድቀት ተደርጎ መወሰድ አለበት፡፡ በሚያሳዝን ደረጃ አንጋፋዎቹ ጋዜጦች የአንድ ግለሰብ ጦማሪ (ብሎገር) ያህል ድረ ገጽና ጎብኝ የላቸውም፡፡ በአንድ የሚዲያ ተቋም ውስጥ አንድ የድረ ገጽ ባለሙያ መረጃ ጭኖ፣ ለአስተያየት መልስ ሰጥቶ፣ ግብረ መልስ ሰብስቦ እንዴት ይቻላል? በአንድ እጅ ከማጨብጨብ አይለይም፡፡ (ዓለም በቴክኖሎጂ ሲገሰግስ ሚዲያው ወደኋላ ይመለስ የተባለ ይመስል ተደጋግሞ የሚታይ ክፍተት አሁንም አለ፡፡ የሬዲዮ ጣቢያ ወይም የቴሌቪዥን መስኮት ይዞ ፖርታል (ድረ ገጽ) አለመኖር ከዚህ ውጭ ምን ሊባል ይችላል!?

‹‹የልማት ጋዜጠኝነት›› በተሸራረፈ መንገድ ተገንዝቦ ዴሞክራሲን ለመገንባት በሚታትር ሕዝብ ውስጥ መተግበር አዳጋችነቱ ግልጽ ሆኗል፡፡ ያውም ኮሙንኬተሩና ጋዜጠኛው ሚናቸው ተቀላቅሎ ሁሉም ዜና ሠሪዎች በሆኑበት፣ ፕሮፓጋንዳውና መሬት ላይ ያለው እውነት በሚጋጭበት፣ የምርመራ ዘገባን አጥብቆ ለመያዝ ባልተቻለበት ሁኔታ የልማት ጋዜጠኝነትና ኮሙዩኒኬሽን ብቸኛ አማራጭ ‹‹ይሁን!›› መባሉም በጥልቀት ሊፈተሽ የሚገባው ነው፡፡ ካልሆነ ግን የሐሳብ ነፃነትና የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ አደጋ ላይ መውደቃቸው አይቀሬ ነው፡፡ በተጨባጭም እየወደቁ እንደሆነ መታየቱን ተገንዝቦ ዘላቂ መፍትሔ ለማመላከት የሚደፍር አንድም የሚዲያ አመራር፣ የዘርፉ ምሁራን ሙያተኛ አልታየም፡፡ ‹‹ቄሱም ዝም መጽሐፉም ዝም››፡፡

እንግዲህ ይህ ዓይነቱ አካሄድ ነው እንኳንስ ለሰፊዋ ኢትዮጵያ ይቅርና ለራሱ ለኢሕአዴግ (ለመንግሥትም) የሚበጅ አይደለም የሚባለው፡፡ ለተጀመረው የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታና የሕዳሴ ጉዞም ቢሆን አረም ይሆን እንደሁ እንጂ ‹‹ኮምፖስት›› ለመሆን አይቻለውም፡፡

በጥቅሉ ‹‹ማን ላይ ሆነሽ ማንን ታሚያለሽ?›› እንዲሉ፣ ክቡር የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሚኒስትሩ በመንግሥት ሚዲያው ላይ የተንሰራፋውን ችግር ተሸክመው፣ ሌላውን እናድናለን ማለታቸው ነው ፀሐፊውን ኮርኩሮ ብዕር ለመጨበጥ ያነሳሳው፡፡ እናም ይህን ለዘመናት ያልታየ ዘርፍ መንግሥት ፈትሾ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታውን እንዲያጠናክር የግል ምክር ከመሰንዘር ሌላ ምን ይባላል፡፡

ከአዘጋጁ፡- ጽሑፉ የጸሐፊውን አመለካከት ብቻ የሚያንፀባርቅ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

 

Standard (Image)

የነገውን ሰው ማነፅ - ይድረስ ለወላጆች !!

$
0
0

በመምህር ሣህሉ ባዬ

የዛሬዋ መጣጥፌ መልዕክቷን የምትጀምረው ባሳለፍነው ዓመት ሕፃናት ጤናማ የሆነ አካል፣ አዕምሮ፣ ስሜትና ማኅበረ ሥነ ልቦና ተላብሰው እንዲያድጉ በማስቻል ረገድ አስፈላጊውን ጥረት ላደረጋችሁ የኅብረተሰብ አባላት እንኳን ለ2010 ዓ.ም. አዲስ ዓመትና አዲሱ የትምህርት ዘመን በሰላም አደረሳችሁ በማለት ነው፡፡

ትምህርት ለአንድ አገር ዕድገት ወሳኝ መሣሪያ መሆኑ ተደጋግሞ ሲገለፅ የቆየ ዕውነታ ነው፡፡ ከዚህ መሠረታዊ ሐሳብ በመነሳት ዘመናዊ ትምህርት በአገራችን ከተጀመረበት ጊዜ ጀምሮ የዕውቀት ገበታን ለማዘመን በርካታ ጥረቶች ተከናውነዋል፡፡ ይሁን እንጂ ዘመናዊ ትምህርትን በጥራት ደረጃ ለማዘመን ብዙ የሚቀሩን የቤት ሥራዎች ቢኖሩም ጥረታችን በበጎ መልኩ እየቀጠሉ መምጣታቸው ተስፋ ሰጪ ነው፡፡ ለምሳሌ ትምህርትን ለማስፋፋት የተደረገው ጥረት በመደበኛ ትምህርት ሥርዓተ  ማዕቀፍ ውስጥ የአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርትንና የኢኮኖሚ ዕድገት ፍላጎት የሚጠይቀውን የሠለጠነ የሰው ኃይል ማፍራት በሚያስችሉ የሦስተኛ ደረጃ ሥልጠናዎች ላይ ያተኮረ መሆኑ መልካም ቢሆንም፣ በሌላ በኩል ግን ሕፃናት ገና ከመጀመሪያዎቹ የዕድገት ዓመታት ጀምሮ በአካል፣ በአዕምሮ፣ በሕይወት ክህሎትና መልካም ማኅበረ ሥነ ልቦና ታንፀው እንዲያድጉ የወላጆችና መምህራን ትብብርን የማሳደጉ ጥረት ግን ብዙ ትኩረት ያገኘ አይመስልም፡፡ ስለሆነም በመግባባትና በዕቅድ ላይ የተመሠረተ የወላጆችና የመምህራን ትብብር ለነገው ሰው ሁለንተናዊ ዕድገት ምትክ የሌለው አስተዋፅኦ እንደሚያበረክት የበርካታ አገሮች ተሞክሮ ያሳያል፡፡

በማኅበረሰባቸውና ዜጎቻቸው ሁለንተናዊ ዕድገት ላይ (ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ መደላድል) መፍጠር የቻሉ አገሮች ሕፃናትን ከመነሻው ኮትኩቶ ማሳደግ የነገውን አገር ዛሬ እንደመሥራት የሚቆጠር መሆኑን ስላመኑበት የላቀ ትኩረት በመስጠት ብሔራዊ አጀንዳ አድርገውታል፡፡ በዚህ ሒደት ውስጥ የወላጆችና መምህራን ጥምረት ትልቁን ድርሻ እንደያዘ በዘርፉ የተከናወኑ ጥናቶች ያመለክታሉ፡፡ ስለሆነም ወላጆች ለትምህርት ቤቶች ግዙፍ ሀብት መሆናችንን በመገንዘብ ልጆቻችን ስለሚማሩባቸው ትምህርት ቤቶች መረዳት፣ በእንቅስቃሴዎች ውስጥ መሳተፍ፣ ስለ ትምህርት ቤቶቹ መርሐ ግብሮችና ስለሚኖሩን ተሳትፎዎች መጠየቅ ይገባናል፡፡ በዕቅድ ላይ የተመሠረተ የወላጆች ተግባራዊ ተሳትፎና የውይይት መርሐ ግብር በእጅጉ አስፈላጊ ጉዳዮች ናቸው፡፡ ከተቻለም ሌሎች የቤተሰብ አባላት በውይይቱ ሒደት ቢካፈሉ ጠቀሜታው የተሻለ ይሆናል፡፡ ወላጆች ከልምዳችንና ማኅበራዊ መሠረታችን በመነሳት በተወሰኑ ርዕሶች ላይ ተጋባዥ መምህራን በመሆን ልምዳችንንና ተሞክሯችን ለተማሪዎች ብናካፍል ተጨማሪ ግብዓት ይሆናል፡፡

አንድ ሕፃን መደበኛ ትምህርት ከመጀመሩ በፊት የነበረው የቤት ውስጥ ተሞክሮ ለቀጣዩ የትምህርት ስኬት ወይም ውድቀት ወሳኝ ምክንያት መሆኑን የትምህርት ሥነ ልቦና ባለሙያዎች ይስማማሉ፡፡ የሕፃኑ የትምህርት ዝግጁነት ማለትም ትምህርት ቤት ገብቶ ለመማር የሚያስችለውን ፍላጎት፣ ክህሎት፣ ጥበብና ዘዴ የመላበሱ ሁኔታ፤ ወይም የችሎታ ውስንነት፣ ምኞት፣ ፍርሃት፣ ድንጋጤ፣ ሐዘንና የስሜት ጉዳት…ወዘተ መጠን በቤት ውስጥ ከነበረው ማኅበራዊ መሠረቶች ወይም ልምዶች ጋር የተቆራኘ ስለመሆኑ የመስኩ ተመራማሪዎች ሮሆቦት ሄስና ቨርጅንያ ሽፕማን በጥናታቸው አረጋግጠዋል፡፡ በመሆኑም ወላጆች የልጆቻቸውን ሁኔታ በትዕግስት ማስተዋል ይጠበቅባቸዋል፡፡

የእያንዳንዱ ሕፃን ዕድገት በእያንዳንዱ የዕድገት ሒደት ላይ የተመሠረተ ነው፡፡ ሕፃናት በተለያዩ የዕድገት አቅጣጫዎች በአካል፣ በአዕምሮ፣ በማኅበራዊ ሥነ ልቦናና በስሜት ያድጋሉ፡፡ ይሁን እንጂ አንድ ሕፃን በአንዱ የዕድገት አቅጣጫ ቀድሞ ሲገኝ በሌላው አቅጣጫ አዝጋሚ ሊሆን ይችላል፡፡ ይኼ የሚያሳየን ፈጣን የዕድገት ሒደት ማለት በጣም የተሻለ ነው ማለት አለመሆኑን ነው፡፡ ስለሆነም የሕፃናትን ተፈጥሮ ለመረዳት ማሰተዋልን ይጠይቃል፡፡ በሕፃናት አስተዳደግ ላይ ጥናት ያደረጉት ሚስ አሊኖር ኮሎምበስ፣ አንድ ያልታወቀ ፈላስፋ ስለ ሕፃናት አፈጣጠርና የባሕርይ ልዩነቶች ያሰፈረውን አስተውሎት በሚከተሉት ሥነ ቃሎች አቅርበውልናል፡፡

  • አንዳንድ ሕፃናት እንደ ጋሪ ግፊት ይፈልጋሉ፡፡
  • አንዳንድ ሕፃናት እንደ ታንኳ መቀዘፍ ይፈልጋሉ፡፡
  • አንዳንድ ሕፃናት ፈጣን ስለሆኑ ትኩረት ይሻሉ፡፡
  • አንዳንድ ሕፃናት በአንድ ነገር ላይ ለማተኮር ትዕግስት የላቸውም፡፡
  • አንዳንድ ሕፃናት እንደ ተሳቢ መኪና መጎተትና መሳብን ይሻሉ፡፡
  • አንዳንድ ሕፃናት በነፋስ እንደተሞሉና ለመፈንዳት እንደተዘጋጁ ነገሮች አያያዝ ጥንቃቄ ይሻሉ፡፡
  • አንዳንድ ሕፃናት ዘወትር እምነት የሚጣልባቸው ተባባሪና ተግባቢ ናቸው፡፡

ምንም እንኳን የእያንዳንዱ ሕፃን ባሕርይ የተለየ ቢሆንም ሁሉም ሕፃናት የሚጋሯቸው ተመሳሳይ መሠረታዊ ባሕርያትም አሏቸው፡፡ ለምሳሌ ፍቅር፣ ደኅንነት፣ ጥበቃ፣ ዋስትና፣ መረጋጋት፣ መልካም አመጋገብ፣ ሥርዓት፣ አካላዊ እንቅስቃሴ፣ ከለላ፣ ቁጥጥር፣ ተቀባይነት ወይም ተሰሚነት፣ መወደድ…ወዘተ. ከሚያመሳስሏቸው ባሕርያት ውስጥ ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ ማንኛውም ሕፃን በራስ የመተማመን ባሕርይ እያዳበረ ሲመጣና ራሱን ለመቻል አንድ ዕርምጃ ወደፊት በሚራመድበት ወቅት የምክር አገልግሎት ሊያገኝና የቁጥጥር ሥርዓት ሊበጅለት ይገባል፡፡ ይኼንንም ሥራ ወላጆችና መምህራን በመተባበር የምናከናውነው ተግባር መሆኑን መረዳት ይኖርብናል፡፡

በሕፃናት የዕድገት ሒደት ውስጥ እንደ አካላዊና አዕምሯዊ ዕድገቶች ሁሉ የሕፃኑ ማኅበራዊና ስሜታዊ ዕድገቶችም በጣም አስፈላጊዎች ናቸው፡፡ አንድ ሕፃን ነፃና ብቁ ሆኖ  በመማር ማስተማሩ ሒደት ውስጥ ለመሳተፍ ፍላጎት የሚያሳየው በአካባቢው ተስማሚ ስፍራ ያለው መሆኑ ሲሰማው ነው፡፡ የሕፃኑ የዕድገት አካባቢዎች አንዱ ከሌላው የተያያዙ መሆናቸው በእጅጉ ጠቃሚ ነው፡፡ በለውጥ ሒደት ውስጥ የመረጋጊያ ወቅቶችን ተከትለው የሚመጡ አካላዊ ለውጦች የሚስተዋሉባቸውና አዳዲስ ትምህርቶች የሚቀሰሙባቸው ጊዜ አሉ፡፡ እነዚህ ክስተቶች በሌሎች የማስተካከያ ሒደቶች ውስጥ ያልፋሉ፡፡ እያንዳንዱ የዕድገት ሒደት ሕፃኑን ለቀጣይ የዕድገት ሒደት ያዘጋጀዋል፡፡ በአጠቃላይ ጤናማ የሕፃናት ዕድገት የወላጆችን፣ የመምህራንና የማኅበረሰቡን ትብብር የሚሻ አንኳር ጉዳይ መሆኑን እየጠቆምኩ በቀጣይ መምህራን ሚና ላይ በምታተኩረው መጣጥፌ እስከምንገኛኝ ድረስ ለአዲሱ ዓመት በጎውን ሁሉ እየተመኘሁ እሰናበታለሁ፡፡  መልካም መልካሙን ለሕፃናት!!!

 

  ከአዘጋጁ፡-መምህር ሣህሉ ባዬ የትምህርትና የአስተዳደር ባለሙያ (MBA, MA, BA & IDPM) ናቸው፡፡ ጽሑፉ የጸሐፊውን አመለካከት ብቻ የሚያንፀባርቅ ሲሆን፣ ጸሐፊውን በኢሜይል አድራሻቸው Eecd@ethionet.et and/or sahilubaye@gmail.comማግኘት ይቻላል፡፡

Standard (Image)

ነገውን ሰው ማነፅ ይድረስ ለአፀደ ሕፃናት መምህራን!

$
0
0

በመምህር ሣህሉ ባዬ
ባሳለፍነው ዓመት ሕፃናት ጤናማ የሆነ አካል፣ አዕምሮ፣ ስሜትና ማኅበረ ሥነ ልቦና ተላብሰው እንዲያድጉ በማስቻል አስፈላጊውን ጥረት ላደረጋችሁ የአፀደ ሕፃናት መምህራን፣ እንኳን ለ2010 አዲስ ዓመትና አዲሱ የትምህርት ዘመን በሰላም አደረሳችሁ እያልኩ በሕፃናት አስተዳደግ ሒደት ውሰጥ የመምህራን ሚናን በተመለከተ አንድ፤ ሁለት… ነጥቦችን ለማንሳት ወደ ዛሬዋ መልዕክቴ እሸጋገራለሁ፡፡

የመጀመሪያው መሠረታዊ ነጥብ የመምህር፤ ወላጅና ልጅ ግንኙነት ረብ የለሽ ከሆነ የሕፃኑ አዕምሮአዊ፣ አካላዊ፣ ስሜታዊና ማኅበረ ሥነ ልቦናዊ ዕድገቶች በእጅጉ የሚደናቅፉ መሆናቸውን መረዳት ነው፡፡ በልክ የተቀናጀና ትርጉም ያለው የመማር ማስተማር ከባቢ ለመፍጠር መምህራን የወላጆችን ፍላጎትና በወላጆችና ልጆች መካከል ያለውን ግንኙነት ማወቅ ይኖርብናል፡፡ የሰውን ችግር እንደራስ ችግር የማዳመጥና ግልጽነት የሰፈነበት የቡድን ውይይት ዘዴ መጠቀም አስፈላጊ ነው፡፡ በዚህ ውይይት መምህራን የማይቃወሙ መሪዎች (Passive Leaders) በመሆን ወላጆች ደግሞ ስለ ልጆች አስተዳደግ ያሏቸውን ልምዶች በውይይቱ ላይ ንቁ ተሳታፊ (Active Participants) በመሆን ተሞክሯቸውን እንዲያካፍሉ ሁኔታዎችን ማመቻቸት ነው፡፡ ለምሳሌ ውይይቱ የሚያጠነጥንባቸው ጉዳዮች ወላጆች ስለ ‹‹ጥሩ ልጅ›› ምንነት ባላቸው አስተያየት ወይም አንድ ሕፃን ‹‹ጥሩ ልጅ›› እንዲሆን የወላጆች ሚና ምን መሆን እንዳለበትና ወላጆች ራሳቸው በወላጆቻቸው እንዴት ‹‹ጥሩ ልጆች››ሆነው እንዲያድጉ እንደተደረገ ባላቸው ተሞክሮ ላይ ሊሆን ይችላል፡፡ ተመራማሪ ዶ/ር ኔኻማ ‹‹መምህራን ከወላጆች የሚማሩ ከሆነ ልጆችን በተሻለ ሁኔታ ሊያስተምሩ ይችላሉ›› ብለው ያምናሉ፡፡

በሦስት፣ አራት ወይም አምስት ዓመት ዕድሜያቸው ወደ አፀደ ሕፃናት የመጡ ሕፃናት በቤት ውስጥ ባገኟቸው ልምዶች ሳቢያ የተሻለ አዕምሮአዊ ቅርፅ ሊኖራቸው ይችላል፡፡

ሁለተኛው ነጥብ ወላጆች ለሚያነሷቸው ጥያቄዎች አስፈላጊውን መልስ በወቅቱ መስጠት ወይም ማስረዳት የእኛ የመምህራን ተግባር መሆኑን ነው፡፡ ወላጆች ከአፀደ ሕፃናት ግቢ ውጪ እንዲሆኑ አናስገድዳቸው፡፡ የሕፃናትን የትምህርት ቤት ውሎ ለወላጆች ማካፈል የተግባራችን አንዱ አካል ነው፡፡ ከሁሉም በላይ የምናስተምራቸው ሕፃናት የእነርሱ ልጆች ስለሆኑ በሕይወታቸው ከልጆቻቸው በላይ የሚወዱት ነገር ያለመኖሩን መገንዘብ ተገቢ ነው፡፡ ልጆችም ከወላጆቻቸው በላይ ማንንም አይወዱም፡፡ ወላጆች ልጆቻቸው በሚማሩባቸው ትምህርት ቤቶች እንቅስቃሴዎች ውስጥ የመሳተፍ መብት አላቸው፡፡ አፀደ ሕፃናቱንም እንዲጎበኙልንና ፈቃደኛ ከሆኑም ደግሞ ድጋፍ እንዲያደርጉልን ለማበረታታት ወላጆችን በ‹‹እንኳን ደህና መጡ›› አቀባበል ምቾት መስጠት ቀዳሚ ተግባራችን መሆኑን መገንዘብ ጠቃሚ ነው፡፡ የወላጆች ስሜት በበጎ መልኩ መቀየር የልጆቻቸውን ስሜት ይቀይራል፡፡ ሕፃናት ወደ አፀደ ሕፃናት በመሄዳቸው ወላጆቻቸው የሚደሰቱ መሆናቸውን ካስተዋሉ ሁሌም በአፀደ ሕፃናቱ ውስጥ ለመገኘት ፈቃደኞች ይሆናሉ፡፡ በአጠቃላይ ከመምህራንና ወላጆች ጤናማ ግንኙነት ይበልጥ ተጠቃሚዎቹ ሕፃናት መሆናቸውን መገንዘብ ያሻል፡፡ ወላጅ መሆን ቀላል ነገር ስላልሆነ ለወላጆች ስሜት ተገቢውን ክብርና ድጋፍ እንስጥ፡፡ ወላጆች የግል ጉዳያቸውን ለእኛ ለማካፈል ፍላጎት ካሳዩና ግልፅ ከሆኑ በአክብሮትና በጥሞና እናዳምጣቸው፡፡ ከተቻለም አረጋጊና አዝናኝ እንሁንላቸው፡፡ ያገኘነው መረጃ በየትኛውም ሁኔታ እንዳይባክን ምስጢር ጠባቂ መሆን ይኖርብናል፡፡ እኛ መምህራን ክቡር ባለሙያዎች ስለሆንን የያዝነውን መረጃ የሙያ አጋር ካልሆነ ሰው ጋር መወያየት አይኖርብንም፡፡

ሦስተኛው ነጥብ ልጆች በአፀደ ሕፃናት ውሏቸው የተማሯቸውንና ያከናወኗቸውን ወላጆች እንዲመለከቷቸው ከተቻለም እንዲተገብሯቸው ማድረግ ጠቃሚ መሆኑን ማወቅ ነው፡፡ እነዚህ መድረኮች ወላጆች የልጆቻቸውን ሙከራ እንዲሁም ምን ተምረው ምን እንዳወቁ በመፈተሽ ግንዛቤ እንዲያገኙ ይረዷቸዋል፡፡ ዘወትር ለሕፃናት የምናደርገው የሞቀ አቀባበልና አሸኛኘት፣ ለሥራችን የምናደርገው ጥንቃቄና የምንሰጠው ትኩረት መገለጫ መሆኑን ተረድተን ወላጆች እንዲረዱን እንጣር፡፡

አራተኛው ነጥብ ወላጆች ለአፀደ ሕፃናት ጠቃሚ ሀብት መሆናቸውን መረዳት ነው፡፡ አንዳንድ ወላጆች በክፍል ውስጥ ለሕፃናት ታሪክ በመተረክ፣ ተረት በማውጋት፣ ዘፈኖችን በመዝፈን፤ ዜማዎችን በማዜም ወይም በመዘመር ነፃ አገልግሎት መስጠት ያስደስታቸው ይሆናል፡፡ አንዳንድ ወላጆች የሙዚቃ መሣሪያዎችን በመጫወትና ያልተለመዱ፣ ብርቅዬና ተወዳጅ እንስሳትን በማስተዋወቅ የትምህርት መርሐ ግብሩን ማጎልበት ይፈልጉ ይሆናል፡፡ አንዳንድ ወላጆች ምግብ ማዘጋጀት ወይም ማብሰል ይፈልጉ ይሆናል፡፡ አንዳንድ ወላጆች የስብሰባ ዕቅድ ማዘጋጀት ይመርጡ ይሆናል፡፡ አንዳንድ ግልፅና ወዳጃዊ የሆኑ ወላጆች ደግሞ ስለ ልምዳቸውና ግላዊ ሕይወታቸው ሊያካፍሉን ይፈልጉ ይሆናል፡፡ ለወላጆች የተዘጋጀው ፕሮግራም ምንም ይሁን ምን ለባህል፣ ለዘር፣ ለጎሳ፣ ለብሔር፣ ለብሔረሰብና ለሃይማኖታዊ ልዩነቶች አክብሮት መስጠት ጠቃሚና አስፈላጊ ስለሆነ ትኩረት እንስጥ፡፡ የወላጆች ምርጫ ምንም ይሁን ምን ምርጫቸው ይከበር፡፡ ይህንንም ዕድል ስንጠቀም ባለን ዕውቀት ላይ ተጨማሪ ዕውቀት አገኘን ማለት ነው፡፡

አምስተኛውና አንኳር ነጥብ የቀዳማይ ልጅነት የዕደገት ሒደት መገለጫዎችን ተረድቶ እነሱን ማጎልበት ነው፡፡ ይህ የዕድገት ሒደት የሕፃናት አዕምሮ የሚለወጥበትና የሚለጠጥበት፤ ሕፃናት ከአካባቢያቸው ጋር በሚያደርጉት መስተጋብርና በሚያገኟቸው ማነቃቂያዎች የአዕምሮ ሕዋሶቻቸው (ሴሎቻቸው) እርስ በርሳቸው የሚገናኙበትና የሚናበቡበት፤ የመማር ፍላጎታቸው መሠረት የሚጣልበት፣ ክህሎት፣ ጥበብ፣ ዘዴ፣ ችሎታቸውና የማኅበራዊ ግንኙነታቸው አድማስ የሚሰፋበት…… ወቅት መሆኑን ተረድተን የሕፃናትን አዕምሮ ለማበልፀግ መጣር ይጠበቅብናል፡፡ ስለሆነም ወደ ግባችን ለማምራት ሥራችንን በአትኩሮት ማከናወን (Focusing)፣ ጤናማ የባሕርይ ለውጥ የሚያስከትል የዕውቀት ሽግግር ማድረግ (Mediation of Meaning)፣ ዕውቀትን ማሻሻልና ማስፋፋት (Transcendence)፣ ሕፃናት የብቃት ስሜት እንዲያዳብሩ ማስቻል (Mediation of Competence)፣ ባሕርይን የመከታተልና የመቆጣጠር ልምድን በማዳበር (Regulation of Behavior) የሕፃናትን ሰብዕና መቅረፅ ይቻላል፡፡ በተጨማሪም የመሠረታዊ ዕውቀት ማሸጋገሪያ ዘዴዎችን ማለትም መዝሙሮችን፣ ዘፈኖችን፣ የሚያስደስቱና የሚያዝናኑ ቀልዶችን፣ የተለያዩ ጨዋታዎችን፣ ሥዕሎችን፣ ትምህርታዊ ንግግሮችን፣ የፈጠራ ሥራዎችን፣ አስተውሎት ወይም ምልከታዎችን፣ ትርጉሞችና ማብራሪያዎችን፣ ጥያቄና መልሶችን፣ ዘገባዎችን፣ የሰውነት እንቅስቃሴዎችን፣ ማበረታቻዎችን፣ ጭፈራና ዳንሶችን፣ አዳዲስ ግኝቶችን፣ የእንግዳ ግብዣን፣ ተደጋጋሚ ሙከራዎች ወይም ልምምዶችን፣ ትዕግስትን፣ ምክንያታዊነትን…… ወዘተ በቅድመ መደበኛ የመማር ማስተማር ሒደት ውስጥ የማይተካ አስተዋጽኦ ያላቸው መሆኑን ተረድተን መተግበር ይጠበቅብናል፡፡ እያንዳንዱ የሕፃኑ የዕድገት ስኬት ሕፃኑን ለቀጣይ የዕድገት ሒደት ያዘጋጀዋል፡፡ ምንም እንኳን በሕፃናት መካከል ግላዊ የሆኑ ልዩነቶች ቢስተዋሉም አጠቃላዩ የዕድገት ሒደት ጉዞ ግን ለሁሉም ተመሳሳይነት አለው፡፡ የሕፃናት ጤናማና የተስተካከለ ዕድገት ወደ ላይ የማደግ አቅጣጫን ያመለክታል፡፡ በመማር ማስተማር ሒደት ውስጥ ለሕፃናት ጤናማ ዕድገት አስተዋጽኦ ከሚያበረክቱ ሥነ ልቦናዊና ፔዳጎጅካዊ አቀራረቦች ውስጥ የሚከተሉትን የዕድገት ሒደቶች ማስተዋል ጠቃሚ ነው፡፡

 

  1. በመማሪያ ክፍላችን ውስጥ ያሉ ሕፃናት ሁሉ አሁን በደረሱበት የዕድገት ደረጃ ላይ የነበሩ አለመሆናቸውን መረዳት፡-

እነዚህ ሕፃናት በለጋነታቸው ሙሉ በሙሉ የሌሎች ጥገኞች ነበሩ፡፡ አሁን ደግሞ ራሳቸውን መርዳት ፈልገዋል፡፡ በራሳቸው ዙሪያ ስለምትሽከረከረው ትንሿ ዓለም ጥቂት ነገሮችን ማወቅ ጀምረዋል፡፡ አሁን ያች ትንሽ ዓለም እየሰፋችና እየተለጠጠች መጥታለች፡፡ ይሁን እንጂ በአፀደ ሕፃናት የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ሕፃናት ስለራሳቸው ብቻ ስለሚያስቡና ማንኛውንም ነገር ከራሳቸው ዕይታ አንፃር ብቻ ስለሚመለከቱ የራስ ወዳድነት (Ego-Centeric) ጠባይ ያጠቃቸዋል፡፡ አንድ ሕፃን አዘውትሮ የሚያንፀባርቃቸው ቃላት ራሱን ብቻ የሚወክሉ ለምሳሌ እንደ ‹‹እኔ››‹‹የእኔ››የመሳሰሉ ናቸው፡፡ ሕፃኑ በለጋ ዕድሜው በራሱ ዙሪያ የሚገኝ ማንኛውም ነገር የእርሱ የግል ንብረት እንደሆነ ወይም የእርሱ መሆን እንደሚገባው አድርጎ ያምናል፡፡ ለምሳሌ ‹‹ይህ የእኔ ነው፣››‹‹ይህ የእኔ ኳስ ነው››‹‹እሷ የእኔ እናት ነች›› ፣‹‹ያን እፈልጋለሁ››የሚሉ አባባሎችን ደጋግሞ ይጠቀማል፡፡ የአፀደ ሕፃናት ከባቢ እነዚህን ባሕርያት ማስተናገድ ይኖርበታል፡፡

በአንድ ወቅት እናት፣ አባትና የቅርብ ቤተሰብ አባላትን ብቻ ያካትት የነበረው ጠባብና ውስን አካባቢ አሁን ሰፋ ወዳለ አካባቢነት ተለውጧል፡፡ የአካባቢው መለወጥ በርካታ ሌሎች ሰዎች በአካባቢው መኖራቸውን እንዲያውቅ ወይም እንዲረዳ ማረጋገጫ ሆኖለታል፡፡ ለምሳሌ መምህራን፣ ነርሶች፣ የጥበቃ ሠራተኞች፣ የፅዳት ሠራተኞች፣ አትክልተኞች… በዙሪያው መኖራቸውን እየተረዳ ነው፡፡ ሕፃኑ አሁን ለተጨማሪ አዳዲስ ሁኔታዎች ተጋላጭ ሆኗል፡፡ ከወላጆቹ ሌላ በትምህርት ቤቱ ውስጥ ትልቅና ጎልማሳ የሆኑ መምህራንና እጅግ በርካታ አዳዲስ ፊቶች ያሏቸውን ሕፃናት ማየት ጀምሯል፡፡ የሕፃኑ ዓለም እየተቀያየረ መጓዙን ቀጥሏል፡፡ ባሕርይውም እንዲሁ፡፡ እሱም ከአዳዲስ ሁኔታዎች ጋር ራሱን የማስማማትና የማለማመድ ፈተናን እየተጋፈጠ በመጓዝ ላይ ነው፡፡ በአዳዲስ አካባቢያዊ ሁኔታዎች በመዋጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ከሚያስተውላቸው ነገሮችና ክስተቶች ጋር ራሱን እያለማመደ ዕድገቱን ቀጥሏል፡፡ ታዲያ ይህ ሁሉ የሚከናወነው በተከታታይ በሚተገበር ሙከራና ልምምድ ነው፡፡ ካለተጨባጭ ተሞክሮ፣ ልምድና ዕውቀት እንዴት ሊገኝ ይችላል? ሕፃኑ ይጥራል፤ በአካባቢው የሚያገኘውን ማንኛውንም ነገር ይሞክራል፡፡ ሁሉንም ነገሮች ለመመርመር ይጣደፋል፡፡ አዳዲስ ስኬቶችና ትንንሽ ዕውቀቶችን ወደ ራሱ ስብስብ ለማካተት ይጓጓል፡፡ ያገኛቸውን ነገሮች ይነካካል፣ ይዳስሳል፣ ያስተውላል፡፡ የሕፃኑ ሙከራና በሒደት የመማሩ እውነታ ይኼው ነው፡፡ ሙከራውና ልምምዱ በሕፃኑ ዕድሜ፣ የዕድገት ደረጃ፣ ጤና፣ ባህልና ሰብዕና ላይ የተመሠረተ ነው፡፡ መምህራንና ወላጆች ይህን የሕፃኑን አዳዲስ ነገሮችን የመሞከርና የመለማመድ ውስጣዊ ፍላጎት፣ ጥረትና ባሕርይ በጥንቃቄ ተከታትለን ማገዝ ይጠበቅብናል፡፡

በተወሰነ የዕድሜ ክልል የሚገኝ ለምሳሌ የሁለት ዓመት ሕፃን ማሳየት የሚኖርበት የተወሰነ ባሕርይ ያለውና በሦስተኛ ዓመት የልደት ቀኑ ደግሞ ተዓምራዊ በሆነ ለውጥ ወደ ብስለት ይሸጋገራል ብሎ ማሰብ የማይቻል ነው፡፡ እያንዳንዱ ሕፃን ልዩ በመሆኑ መወዳደር ካለበት መወዳደር ያለበት ከራሱ ጋር ብቻ ነው፡፡ ይሁን እንጂ በአጠቃላይ አፈራረጅ እያንዳንዱን የዕድሜ ክልል የሚወክሉ መሠረታዊ መመሳሰያ ባሕርያት አሉ፡፡ የታዳጊ ሕፃናትን ባሕርያት፣ ፍላጐትና የዕድገት ሒደት ሥርዓት መረዳት ለእያንዳንዱ ክፍልና ለእያንዳንዱ ሕፃን ተዛማጅ የሆኑ ዓላማዎችን በቅደም ተከተል ነድፈን የምንተገብረው መርሐ ግብር እንድናዘጋጅ ይረዳናል፡፡ ሕፃናት ወደ አፀደ ሕፃናት የሚሄዱበት የዕድሜ ክልል እንደሚኖሩበት አካባቢ ይለያያል፡፡ በአንዳንድ አገሮች በሦስት፣ በአራት፣ በአምስትና በስድስት ዓመታቸው የሚጀምሩ ሲሆን በሌሎች አገሮች ደግሞ በሁለት ወይም በሦስት ዓመታቸው ይጀምራሉ፡፡ እንደ ባለሙያዎቹ አገላለፅ ሕፃናት በሁለት ዓመታቸው አዳዲስ ነገሮችን መማር ይችላሉ፡፡ በአካባቢያቸው የሚገኙ ነገሮችን ያስተውላሉ፡፡ ለአካላዊ እንቅስቃሴያቸው የሚረዷቸውን መራመድንና መሮጥን ይለማመዳሉ፡፡ ከፍ ያሉ ነገሮችን በመያዝ መንጠላጠል ይጀምራሉ፡፡ እንዲህ፣ እንዲህ እያሉም ወደ ሦስተኛ ዓመታቸው ይሸጋገራሉ፡፡

በሦስት ዓመታቸው አብዛኞቹ ሕፃናት ቢያንስ መሠረታዊ የመናገር ክህሎት ስለሚኖራቸው የቃላት ክምችታቸው በየዕለቱ ይጨምራል፡፡ በዙሪያቸው ካሉ ሌሎች ሰዎች ጋር ቀስ በቀስ እየተግባቡ መስማማትን መፍጠር ይጀምራሉ፡፡ ማንኛውንም ነገር መመርመር፣ መፈተሸ፣ መሞከር፣ መጠንቆል፣ መቅመስ…ወዘተ ይጀምራሉ፡፡ አንዳንድ ሰዎች የሕፃኑን የማያቋርጥ ቀጣይ እንቅስቃሴ በመገንዘብ ይህን ዕድሜ ‹‹የመገስገስ›› ዕድሜ ይሉታል፡፡ በእርግጥ ይህ ዕድሜ ሕፃናት የመስማት፣ የመናገር፣ የማስተዋል፣ የመተባበር፣ የመረዳዳት ችሎታዎችንና የእኔነት ስሜቶችን ማዳበር የሚጀምሩበት ዕድሜ ነው፡፡ ሆኖም በዚህ ዕድሜ ክልል ውስጥ ሕፃናት የራስ ወዳድነት ባሕርይ ስለሚያጠቃቸው ከሌሎች ሕፃናት ጋር ለመጫወት ያላቸውን ዝግጁነት እምብዛም አያሳዩም፡፡ በዚህም ምክንያት ለብቻቸው የጎንዮሽ ጨዋታ መጫወትን ይመርጣሉ፡፡ በነፃነት መንቀሳቀስ ስለሚፈልጉ አንዳንዴ የአዋቂዎችን ዕርዳታ ተስፋ በሚያስቆርጥ ሁኔታ ይቃወማሉ፡፡ ወደ አራተኛ ዓመታቸው መሸጋገሪያ ላይ እንደ ግል ባሕሪያቸው ከገደባቸው የመውጣት አዝማሚያ ያሳያሉ፡፡ በመቀጠል ዓመት በማይበልጥ ጊዜ ውስጥ ሕፃናት ተለዋዋጭ ለሆኑት የዕድገት ሒደቶች ተገዢ በመሆን እርስዎን ለማስደሰት የሚችሉትን ሁሉ ለማድረግ ይሞክራሉ ፡፡ ‹‹አይሆንም/አይደለም››የሚባሉ የእምቢተኝነት ቃላት አሁን ‹‹አዎ/አቤት/እሺ›› ወደሚባሉ ጠቃሚ ቃላት የሚለወጡበት አራተኛ ዓመት የዕድሜ ክልል ተሸጋግረዋል፡፡

ሕፃናት አራተኛ ዓመታቸው ላይ ሲደርሱ ከየትኛውም ጊዜ በተሻለ ራሳቸውን የመቆጣጠር፣ የመስጠትና የመቀበል ብቃት ማሳየት ይጀምራሉ፡፡ ድርሻ የመውሰድ፣ የመጋራት ወይም የሌላውን ስሜት የመካፈል ጠባያትን መማር የሚያዳብሩበት ዕድሜ  ነው፡፡ አሁን ከሌሎች ሕፃናት ጋር የመጫወት ፍላጐታቸውና ችሎታቸው እያደገና እየጨመረ መጥቷል፡፡ ስለሆነም የሕፃናት ሰብዕና እንዲያብብና ፈክቶ ፍሬ እንዲያፈራ ለሚሞክሯቸው ሙከራዎች ልናመሰግናቸው፣ ልናደንቃቸውና ልናበረታታቸው ይገባል፡፡  ይሁን እንጂ በዚህ የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ሕፃናት ግልፅ የሆነ የማሰብ ችሎታቸውን ተጠቅመው ከገደብ የመውጣት አዝማሚያቸውንም በቃላትና በተግባር ይገልፁታል፡፡ እነዚህ ሕፃናት የመማር ወሰኖች ወይም ድንበሮች አሏቸው፡፡ ይህ የዕድሜ ክልል ታላላቅ መሠረታዊ ጥያቄዎች የሚፈልቁበት የዕድሜ ክልል ነው፡፡ ‹‹እንዴት?›› እ‹‹ለምን?›› የሚሉ ጥያቄዎችን የሚያቀርቡበት፣ ለነገሮች መግለጫ፣ ማብራሪያ ወይም መረጃ የሚጠይቁበት የዕድሜ ክልል ነው፡፡ የአራት ዓመት ሕፃናት በርካታ ተግባራትን ማከናወን ይማራሉ ወይም ለማከናወን ይጥራሉ፡፡ አንዳንዴ ሕፃናት በሥራ ስለሚደክሙ ውጤታቸውንና ደስታ ፈጣሪ ዜናዎቻቸውን ለሚያዳምጣቸው ሰው ሁሉ ማካፈል ይፈልጋሉ፡፡ ከአንደበታቸው የሚወጡ ቃላት ‹‹ጉራ በኪሴ›› ዓይነት ሰዎች ያስመስሏቸዋል፡፡ ለምሳሌ አንድ ሕፃን ስለ ሁኔታው እንዲህ በማለት ለአድማጩ ይገልፃል፡፡ ‹‹ተመልከቱኝ! ከዚህ ቅርንጫፍ ላይ መወዛወዝ እችላለሁ!››፣ ‹‹ማፏጨት እችላለሁ!››፣ ‹‹መስማት ትፈልጋላችሁ? ዛሬ ልብሴን የለበስኩት እኔ እራሴ ነኝ! ማንም የረዳኝ የለም!›› በማለት የአድማጩን ትኩረት ለመሳብ ይጥራል፡፡ ሆኖም ሕፃኑ በሀቅ እየፎከረ አይደለም፡፡ ይልቁንም እነዚህን ተግባራት ማከናወኑን ወይም ለማከናወን መብቃቱን በእጅጉ ማመን ስላቃተው ነው፡፡ ለሕፃናት ‹‹ትልቅ›› የመሆን ስሜት በጣም አስፈላጊ ጉዳይ ነው፡፡ በዙሪያቸው የተዘጋጁት ነገሮች ሁሉ ለትላልቅ ወይም ለአዋቂ ሰዎች የሚያገለግሉ ናቸው፡፡ ለምሳሌ የበርና የመዝጊያ እጀታዎችን፣ ጠረጴዛዎችን ወይም ወንበሮችን ያጤኗል፡፡ አንዳንድ ጊዜ በመስኮት ወደ ውጪ ለመመልከት ሲፈልጉ ወንበር ላይ ለመንጠላጠል ይገደዳሉ፡፡ ጉዳት እንዳይደርስ ጥንቃቄ የማድረጉ ጠቀሜታ እንደተጠበቀ ሆኖ የሕፃኑ ሙከራና ጥረት ይበረታታለት፡፡ ይሁን እንጂ የምናደርገው ማበረታቻ ለሁሉም ሙከራዎች አንዴ ብቻ እንዳይሆን ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ የሚደረገው ማበረታቻ እያንዳንዱ አዲስ የተናጠል ጥረት ወይም ሙከራ ከሚያስከትለው ደስታና ከሚደረገው ጥንቃቄ ጋር የተዛመደ መሆን ይኖርበታል፡፡

ዓመታት እየተቆጠሩና የሕፃናት ዕድሜ እየጨመረ ሲሄድ ፍላጎታቸው በሚገርም ሁኔታና እየጨመረና እየሰፉ ይመጣል፡፡ የማሰብ ችሎታቸው ከወትሮው በተለየ መልኩ ይበልጥ በተጨባጭ ወይም በምክንያታዊ ጥያቄዎች የተሞላ ይሆናል፡፡ አሁን ሕፃናት ራሳቸውን ለመቆጣጠር ዝግጁ ስለሆኑ ከዚህ በኋላ ገደባቸውን አይዘሉም፡፡ አሁን የሕፃናት አካላዊ እንቅስቃሴ በሒደት እየተቀናጀ መጥቷል፡፡ በማኅበራዊ ባሕርያቸው ተግባራዊ ዕቅዶችን አብረዋቸው በማውጣት የሚተገብሩ የቡድን አባላት አሏቸው፡፡ ሕፃናት ካለፈው ጊዜ በተሻለ ከሁኔታዎች ጋር ራሳቸውን የመለዋወጥና የማጣጣም ባሕርይ አላቸው፡፡ እንዲህም እያለ የሕፃናት ዕድገት ይቀጥላል፡፡ በሰባት ዓመታቸው አካባቢ ወደ መደበኛ ትምህርት ይሸጋገራሉ፡፡

2. የሕፃናት ዕድገት መሰላልን መገንዘብ፡-

ስለ ሕፃናት ዕድገት ሒደት ግንዛቤ ሲኖረን በሥርዓተ ትምህርቱ ውስጥ የሕፃናት ተሳትፎ ምን መሆን እንዳለበት ፍንትው ብሎ ሊታየን ይችላል፡፡ ለምሳሌ ሕፃኑ ለጨዋታ የሚጠቀምበትን የሸክላ አፈር ወይም ጭቃ በምሳሌነት እንውሰድ፡፡ ቀደም ሲል በሸክላ አፈር ወይም በጭቃ የመጫወት ዕድል አግኝቶ የማያውቅ ሕፃን ከጭቃው ወይም ከሸክላው አፈር ጋር የሚገናኝበትን መንገድ ይፈልጋል፡፡ የሸክላ አፈሩን ወይም ጭቃውን ይነካል፣ ይወቅጣል፣ ይወጋል፣ ይበሳል፣ ይደነቁላል፣ ያሸታል…ወዘተ፡፡ ጭቃው ምን እንደሆነና አገልግሎቱም ምን ሊሆን እንደሚችል ለማወቅ ይፈትጋል፣ ይፈቀፍቃል፣ ይጨብጣል ወይም ይጠፈጥፋል፡፡ ቀጥሎም ጭቃ ጠቅልሎ በመቆራረጥ፣ ወይም በማድቦልቦል ወይም በመጠፍጠፍ ኳስ ወይም እባብ መሳይ ቅርፆች መሥራት ይጀምራል፡፡ እያንዳንዱን ቁስአካል ባወቀና በተረዳ መጠን ከልምድ ያገኛቸውን ዘዴዎች በማቀናጀት ተጨማሪ ቅርፆች ይፈጥራል፡፡ የፈጠራውን ሥራ እንዳጠናቀቀ ውጤቱን ያስተውላል፡፡ ውጤቱ ሌላ ነገር የሚያስታውሰው ከሆነ ወዲያውኑ ለውጤቱ ስም ያወጣለታል፡፡ ‹‹ተመልከት! ኳስ ሠራሁ›› በማለት ውጤቱን ያበስራል፡፡

በፈጠራው ሒደት ወቅት የሚያገኘው ውጤት ሌላ ነገር ባስታወሰው ቁጥር ስያሜውን ለበርካታ ጊዜ ሊለዋውጠው ይችላል፡፡ ይሁን እንጂ ሕፃኑ ከፍ እያለና ትንሽ እየበሰለ ሲመጣ ሊሠራ ያሰበውን በቅድሚያ ይወስናል፡፡ ማኅበራዊ ዕድገቱ ይበልጥ እየዳበረ ሲመጣ በቡድን ተደራጅቶ የተለያዩ የሥራ ዕቅዶችን ይወጥናል፡፡ ሕፃኑና ጓደኞቹ ዕቅድን በቡድን በመተግበር ውጤት ለማምጣት ይጥራሉ፡፡ ለምሳሌ በጣም ትንሽ የእርሻ ቦታን በመፍጠር ከሸክላ አፈርና ከጭቃ የተለያዩ የእንስሳት ቅርፆችን ይሠራሉ፡፡ በተመሳሳይ መንገድ አንድ ሕፃን ላልተለመደ ወይም እንግዳ ነገር ያለውን አስተያየት ወይም ምላሽ በማስተዋል ስለ ዕድገቱ ሁኔታ ልንረዳ እንችላለን፡፡ ለምሳሌ አንድ ሕፃን መጀመሪያ አንድን ቁስ በመፈተሽ ምንነቱን ለማጥናት ወይም ለምን እንደሚጠቅም ለማወቅ ይፈልግ ይሆናል፡፡ ይህን ለማረጋገጥ ሕፃኑ ቁሱን ወደ አፉ ይወስዳል፡፡ በዕድሜ ትንሽ ከፍ ያለው ሕፃን ደግሞ በዕቃው ውስጥ ያለውን ነገር ለማወቅ በተለየ ሁኔታ ያወዘውዛል፣ ያንከባልላል፣ ይገፋል፣ ከፍ ዝቅ ያደርጋል ወይም ያንቀሳቅሳል፡፡ የአምስትና የስድስት ዓመት ሕፃን ይህን ቁስ አካል ለይቶ ለመመደብ የተሻለ ግንዛቤ አለው፡፡ በዚህ ዕድሜ ክልል የሚገኝ ሕፃን በስሜት ህዋሳቱ አማካይነት ነገሩ የት እንደሚመደብና ለምን ዓላማ እንደታቀደ ይረዳል ወይም ይገነዘባል፡፡ ቁስ አካሉ አደገኛና ችግር ፈጣሪ ከሆነም፣ ይህንን የማወቅ ችሎታ ስላለው ለመምህሩ ወይም በዙሪያው ላለ አዋቂ ሰው ያስረክባል፡፡ ይሁን እንጂ ምንም እንኳን አጠቃላዩ የሕፃናት የዕድገት ሒደት መሠረታዊ ተመሳሳይነት ቢታይበትም እያንዳንዱ ሕፃን ከሌላው የተለየ ሰብዕና ያለው መሆኑን እንርሳ፡፡

እያንዳንዱ ሕፃን ከሌላው የሚለይበት ልዩ ሰብዕና ያለው በመሆኑ ባሕርይውን የሚያንፀባርቅበት የራሱ የሆነ መንገድ አለው፡፡ ለምሳሌ ከሌሎች ሕፃናት ጓደኞቹ ጋር እንዴት እንደሚቀላቀልና ትብብር እንደሚፈጥር ልብ ይበሉ፡፡ በአቋሙ የሚፀና ጥብቅ ወይም ግትር ነው? ወይስ ይደራደራል? ስምምነት ላይ ለመድረስ ይጥራል? የሌሎችን አስተያየት ይቀበላል? ያከብራል? ይስማማል? ወይስ የራሱን ሐሳብ ብቻ በሌሎች ላይ ለመጫን ሁልጊዜ ይወተውታል? ወይስ በራሱ መንገድ ብቻ መሄድን ይመርጣል? ወይስ ለሌላ ሐሳብ በቀላሉ እጁን በመስጠት ለመብቱ አይቆምም? እኛ መምህራን ሕፃናትን ይበልጥ ባወቅናቸው መጠን ስለ ሁኔታቸው የመረዳት ዕድል ስለምናገኝ እያንዳንዱ ሕፃን በየትኛው የዕድገት እርከን ላይ እንደሚገኝ ለመገንዘብ ምቹ ሁኔታን ይፈጥርናል፡፡ ለወላጆችም እንደዚሁ፡፡

ሕፃናት ለወላጆቻቸው የደስታ፣ ፍሥሐና ስኬት ምንጭ ሲሆኑ ለአገራቸው ደግሞ ተስፋና ቃልኪዳን ናቸው፡፡ ወላጆች ለልጆቻቸው መልካም ምኞትና ተስፋ የሰነቁ በመሆናቸው በአፀደ ሕፃናት ቆይታቸው ወቅት የመምህራንን ጥበቃና ክብካቤ እያገኙ እንዲማሩላቸው በመፈለግ የሚሳሱላቸውን ልጆች በአደራ መንፈስ ለእኛ ያስረክባሉ፡፡ እምነትም ይጥሉብናል፡፡ እንደ ወላጆቻቸው ሁሉ ሕፃናትም የራሳቸውን ተስፋና ምኞት የሰነቁ ስለሆነ ካልተገደቡ በቀር መማር፣ ማወቅና ውጤታማ መሆን ይሻሉ፡፡ ይሁን እንጂ ሕፃናት ወደፊት ስለሚሆኑት ጉዳይ ማንኛውም ሰው በእርግጠኝነት ሊናገር ወይም ዋስትና ሊሰጥ ወይም ቃል ሊገባ አይችልም፡፡ ሆኖም ለጊዜውም ቢሆን እነኚህ ሕፃናት በእኛ ቁጥጥርና ክብካቤ ሥር ስለሆኑ በምቹ ሁኔታ ላይ በተገነባ የሞቀ ወዳጃዊ ስሜት አስፈላጊውን ዕውቀት ሰጥተንና ኮትኩተን ማሳደግ የእኛ የመምህራን የሥራ ድርሻ ስለሆነ፤ አንዳንዴ የቡድን አስተምህሮት ዘዴን፣ አንዳንዴ ደግሞ የአንድ ለአንድ ያስተምህሮት ዘዴን እንጠቀም፡፡ ይህን ከመተግበራችን በፊት ግን ከምንም በላይ ስለ ሕፃናት ጠንቅቀን ማወቅ የሚገቡንን እውነታዎች መረዳት ወይም ማወቅ ይኖርብናል፡፡ ለዚህ መሠረታዊ ሐሳብ ድጋፍ የሚሆኑን ትምህርታዊ ዕውነታዎች ታዋቂዋ የቶለራንስ ካሊፎርኒያ ሄራልድ ጋዜጣ አምደኛ ዶርቲ ሎውናታል እ.ኤ.አ በ1954  “Creative Family Living” በሚል ርዕስ ሥር ያሰፈረቻቸውን ምክሮች ማጤኑ በጣም ጠቃሚ ነው እላለሁ፡፡

  • አንድ ሕፃን ከወቀሳና ትችት ጋር ካደገ፤ ማውገዝንና መንቀፍን ይማራል፡፡
  • አንድ ሕፃን በፍርሃትና ስጋት ውስጥ ካደገ፤ ጭንቀትን ይማራል፡፡
  • አንድ ሕፃን ከጥላቻ ጋር ካደገ፤ ጠብን ይማራል፡፡
  • አንድ ሕፃን ከሐዘንና ፀፀት ጋር ካደገ፤ በራሱ ላይ እያዘነ መኖርን ይማራል፡፡
  • አንድ ሕፃን እየተፌዘበት ካደገ፤ ዓይን አፋርነትን፣ ድንጉጥነትንና ደንጋራነትን ይማራል፡፡
  • አንድ ሕፃን ከቅናት ጋር ካደገ፤ ምቀኝነትን ይማራል፡፡
  • አንድ ሕፃን ከሀፍረትና ውርደት ጋር ካደገ፤ ጥፋተኛነትንና ኃጢያተኛነትን ይማራል፡፡
  • አንድ ሕፃን እየተበረታታ፣ እየተደፋፈረና እየተነቃቃ ካደገ፤ በራስ መተማመንን ይማራል፡፡
  • አንድ ሕፃን ከትዕግስትና መቻቻል ጋር ካደገ፤ ቻይነትንና ጥንቁቅነትን ይማራል፡፡
  • አንድ ሕፃን ከምስጋና ጋር ካደገ፤ ማድነቅን  ይማራል፡፡
  • አንድ ሕፃን ከተደማጭነት ጋር ካደገ፤ አፍቃሪነትን ይማራል፡፡
  • አንድ ሕፃን ከመፍቀድና ማፅደቅ ጋር ካደገ፤  ራስን መውደድና መቀበልን  ይማራል፡፡
  • አንድ ሕፃን ዕውቅና ከማግኘት ጋር ካደገ፤ የዓላማ ጠቃሚነትን ይማራል፡፡
  • አንድ ሕፃን ያለውን ከማካፈልና ከመረዳዳት ጋር ካደገ፤ ደግነትን፣ ቸርነትን ወይም ለጋስነትን ይማራል፡፡
  • አንድ ሕፃን ከቅንነት፣ ታማኝነትና ሚዛናዊነት ጋር ካደገ፤ እውነተኛነትና ፍትሐዊነትን ይማራል፡፡
  • አንድ ሕፃን ከመልካም አያያዝና ደኅንነት ጋር  ካደገ፤ በራሱና እርሱን በተመለከቱ ጉዳዮች እምነት ይኖረዋል፡፡
  • አንድ ሕፃን ከወዳጃዊ አቀራረብና ጨዋታ ጋር ካደገ፤ ዓለም ምቹ የመኖሪያ ስፍራ መሆኗን ይማራል፡፡
  • እርስዎ ከመንፈስ እርካታ ጋር የሚኖሩ ከሆነ፤ ልጅዎ በሰላማዊ አዕምሮ ውስጥ ይኖራል፡፡

ለመሆኑ የልጆቻችን ሕይወት በየትኛው ሁኔታ ወይም እውነታ ውስጥ ይገኛል? ሕፃናት የሚያንፀባርቋቸው ባሕርያት በአብዛኛው በወላጆቻቸው ቤት ውስጥ ባለው ሕይወት ተፅዕኖ ሥር የወደቁ ናቸው፡፡ የተመጣጠነ ምግብ፣ ልብስ፣ ጥበቃና እንክብካቤ ያገኛሉ? በቂ እንቅልፍስ ይተኛሉ? እነዚህንና እነዚህን የመሳሰሉ አካባቢያዊ ሁኔታዎች በሕፃናት ባሕርያት ይንፀባረቃሉ፡፡ የማንኛውም ሕፃን ባሕርይ ከደረሰበት የዕድገት ደረጃ ጋር የተገናኘና የተዛመደ ነው፡፡ ይህም ማለት ሕፃኑ የዕድሜውን ይተውናል፣ ያከናውናል ወይም ይተገብራል ማለት ነው፡፡ ስለሆነም ለሕፃናት ርኅሩኅ፣ ደግና ቸር እንሁንላቸው፡፡ በአክብሮትና ጨዋነት እንከባከባቸው፡፡ እያንዳንዱ ሕፃን የመከበርና የተፈላጊነት ስሜት እንዲሰማው ማድረግ ለጤናማ ዕድገቱ በጣም አስፈላጊና መሠረታዊ ጉዳይ ነው፡፡ በምንም ምክንያት በየአጋጣሚው ሁሉ ማፌዝ፣ ማላገጥ ወይም ሕፃኑን ማሳነስ፣ ማንኳሰስና በሕፃኑ ላይ አላስፈላጊ ድርጊቶችን መፈፀም እኩይና ክፋት የተሞላበት ተግባር ነው፡፡ በሕፃናት መካከል አድሏዊ ከመሆን እንቆጠብ፡፡ ሁልጊዜም ግልፅና ሚዛናዊ መሆናችንን እናሳያቸው፡፡ ሕፃናት ለሚያቀርቧቸው ጥያቄዎች ሁሉ ግልፅ፤ ቅን፣ ታማኝ፣ ለዕድሜያቸውና ለደረሱበት የዕድገት ደረጃ ተስማሚ የሆኑ መልሶች መመለስ ከእኛ ከመምህራንና ወላጆች የሚጠበቅ ተግባር ነው፡፡ የገባንላቸውን ቃል ማክበር ወይም በወቅቱ መፈፀም የማንችል ከሆነ ከመጀመሪያውኑ ባንሞክረው ይመረጣል፡፡ ሕፃናት በቀላሉ የሚያምኑና የሚታለሉ ናቸው፡፡ ሕፃናት በሥርዓት ሲያዙ፣ ሞቅ ያለ አቀባበልና እንክብካቤ ሲደረግላቸው መልካም ባሕሪያትን በመማር ተመሳሳይ ጠባያትን ያንፀባርቃሉ፡፡ ለሕፃናት እንክብካቤና ድጋፍ የምናደርግ ሰዎች ሁሉ በሕፃናት ሰብዕና ላይ የበኩላችንን ሚና የምንጫወት ሰዎች ስለሆን የሕፃናትን የወደፊት ዕጣ ፈንታ በመቅረፅ ረገድ ጉልህ ተፅዕኖ የምናሳድር መሆናችን መረዳት ይኖርብናል፡፡ መምህራን በአፀደ ሕፃናት ውስጥ ስንሠራ ከፍተኛ የሙያና የሞራል ኃላፊነት የተሸከምን ስለመሆናችን ለአፍታም አንዘንጋ፡፡

የአፀደ ሕፃናት መምህራንና የሕፃናት ተንከባካቢዎች መሆናችን ወይም ለመሆን ማሰባችንና ሕፃናትን መውደዳችን ሕፃናት ከእኛ ጋር በሚሆኑ ወቅት ተደስተውና አዕምሮአዊ መነቃቃት አግኝተው በግቢያችን ውስጥ እንዲቆዩ ይረዳቸዋል፡፡ የሕፃናትን ባሕርያት ይበልጥ እየተረዳን በሄድን ቁጥር እነርሱን ለመምራት ወይም አቅጣጫ ለማስያዝ ብቁ እንሆናለን፡፡ ስለ እያንዳንዱ ሕፃን ቤተሰባዊ መሠረት፣ ያለፈ ታሪክና ልምድ የምንችለውን ያህል ለማወቅ ጥረት በማድረግ የሕፃኑን ሁኔታ ይበልጥ ለመረዳት እንጣር፡፡ ከሁሉም በላይ ጠቃሚው ነገር በእኛ ክብካቤ ሥር የሚገኙ ሕፃናት ከእኛ ጋር በሚሆኑበት ወቅት የደኅንነትና ምቾት ስሜት የሚሰማቸው መሆኑን ማረጋገጥ ነው፡፡ ከአሳዳጊዎቻቸውና ከመኖሪያ ቤታቸው ሲነጠሉ ለአብዛኞቹ ሕፃናት የመጀመሪያ ተሞክሯቸው ነው፡፡ አንዳንድ ሕፃናት በአዲሱ ሁኔታና አካባቢ እርግጠኛ ስለማይሆኑ ይፈራሉ፡፡ በአፀደ ሕፃናት ቆይታቸው ከሚያገኟቸውና ከሚነካኳቸው ነገሮች ይልቅ በቅድሚያ ከለላና እንክብካቤ ይፈልጋሉ፡፡

ሕፃናት የመጡበት ቤተሰብ የቅርብ ግንኙነት የተጠናከረበትና ፍቅር የሰፈነበት ከሆነ አዲሱን አካባቢ ተቀብሎ ከሌሎች ለመቀላቀልና ለመዋሃድ የተሻለ ዝግጁነት ሊኖራቸውና ሊያሳዩ ይችላሉ፡፡ በቤታቸው ውስጥ ያሳለፉት ምቹ የሕይወት ቆይታና ያገኙት ልምድ ዓለም አመቺ የመኖሪያ ቦታ መሆኗን፤ ሌሎችንም ማመን የማይጎዳና ጠቃሚ ጉዳይ መሆኑን እንዲያምኑ ይረዳቸዋል፡፡ በሌላ በኩል ዘወትር ገደብየለሽ ቅጣትን፣ መከፋትንና ቅሬታን ማስተናገድ ባህሉ ከሆነ ቤተሰብ ውሰጥ የመጡ ሕፃናት መጀመሪያ እርስዎንና አዲሱን አካባቢ ሊጠራጠሩ ይችላሉ፡፡

በዚህ ወቅት ለእነዚህ ዓይነት ሕፃናት ከፍተኛ ትዕግስት ሊኖረንና የምንችለውን ያህል የጋለ ፍቅርና መረጋጋት ልንለግሳቸው ይገባል፡፡ ሦስት እጅ የሆነውን የሕፃናት ደኅንነትና ክብካቤ ተግባራችንን በአፀደ ሕፃናታችን ውስጥ ለሚገኙ ሕፃናት በበርካታ መንገዶች ማስፈን ይቻላል፡፡ እነዚህንና መስል ጉዳዮችን ይዤ በሌላ ዝግጅት እስከምንገናኝ ድረስ አዲሱ ዓመት መልካም መምህራንና መልካም ወላጆች በመሆን የልጆቻችንን ጤናማ ሰብዕና የምንቀርፅበት፣ የሞራል ብቃታችንን የምናድስበትና የምንደሰትበት ዓመት ይሁንልን እያልኩ እሰናበታለሁ፡፡

መልካም መልካሙን ለሕፃናት!

ከአዘጋጁ፡-መምህር ሣህሉ ባዬ የትምህርትና የአስተዳደር ባለሙያ (MA in Chid Development, BA in Psychology, MBA & IDPM in Project Management) ናቸው፡፡ ጽሑፉ የጸሐፊውን አመለካከት ብቻ የሚያንፀባርቅ ሲሆን፣ ጸሐፊውን በኢሜይል አድራሻቸው www.enrichmentcenters.org and/or sahilubaye@gmail.comማግኘት ይቻላል፡፡

Standard (Image)
Viewing all 88 articles
Browse latest View live