በአበበ ዓይነቴ
በዓረቡ ዓለም ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ የመጣው የእስልምና አክራሪነትና አሸባሪነት ከላይ ከተጠቀሰው አመለካከት በተቃራኒው በመቆም ሁሉንም በጠላትነት እየፈረጀም ቢሆን፣ አሁን ያለውን የዓለም ሥርዓት በመቃወም ከመላው ዓለም ደጋፊና አጋዥ እያስገኘለት መምጣቱ ችግሩን ውስብስብ ያደረገዋል፡፡
የጂኦፖለቲካዊ ፉክክር እንደ አዲስ ማቆጥቆጥ መጀመሩ ጉልቶ የታየው በዩክሬን ነው፡፡ ይህ በአሜሪካ፣ በአውሮፓ ኅብረትና በሩሲያ መካከል ያለው ፍጥጫ፣ እንዲሁም አሜሪካ በእስያ ፓስፊክ ባደረጋገቻቸው እንቅስቃሴዎች የተነሳ የወቅቱ የዓለም ፖለቲካ ሥርዓት ወደ ቀድሞው ጂኦፖለቲካዊ ፉክክር እየተመለሰ መሆኑን አመላካች ተደርጐ እየተወሰደ ይገኛል፡፡
የቻይና አዲሱ የሲልክ ሮድ ፕሮጀክት የአፍሪካን አንድ ጫፍ ከሌላው በመገናኛ አውታሮች በማስተሳሰርና የንግድ ትስስር በመፍጠር፣ የሰላምና የዕድገት ቀጣና ለማድረግ የተጀመረው ሒደት ለዘመናት በዕርዳታ በፖለቲካ ጣልቃ ገብነት ሥር ለነበሩ አገሮች እንደ አማራጭ መቅረቡ ፉክክሩን ጉልህ አድርጐታል፡፡
በአጠቃላይ የዓለም ሥርዓት በአዲስ መልክ በጂኦፖለቲካዊ ፉክክር ውስጥ እንዲገባ ካደረጉ ምክንያቶች አንዱና ትልቁ፣ በመካከለኛው ምሥራቅ የተፈጠረው የፖለቲካ ክፍተትና የቻይና በኢኮኖሚ፣ የሩሲያ በወታደራዊ ኃይል ጠንክረው መውጣት ነው፡፡ በሌላ በኩል መካከለኛ ደረጃ ላይ የሚገኙ አገሮች በኢኮኖማ ዕድገት ማስመዝገባቸውና አቅም መፍጠራቸው ተጠቃሽ ነው፡፡
ይህም የተለያዩ የበጐ አድራጎት ድርጅቶች እንዲመሠረቱና አክራሪነትን በፖለቲካና በገንዘብ እንዲደገፉ በር ከፍቶላቸዋል፡፡ የኒዩ ሊብራል ኢኮኖሚና የፖለቲካ ሥርዓት የበላይነት ማግኘቱ በጐ ያልሆነው አመለካከት በዓለም ላይ በቀላሉ እንዲስፋፋና መሠረት እንዲያገኝ አድርጓል፡፡ የኢኮኖሚ ቀውስ በአሜሪካና በአውሮፓ መከሰቱ ችግሩን አወሳስቦታል፡፡ በዚህ የተነሳ አክራሪነትና አሸባሪነት የዓለም ቁጥር አንድ አደጋ ወደ መሆን አድርሷል፡፡ መፍትሔውን ውስብስብ የሚያደርግ ነው፡፡
በመካከለኛው ምሥራቅ የሚገኙ አገሮች ያላቸው የእርስ በእርስ ፉክክርና አንዱ በሌላው ላይ የበላይ ለመሆን ያለው ፍላጐት፣ የዓረቡን የፖለቲካ የበላይነት ለብዙ ጊዜ ይዛ የቆየችው ግብፅ በሳዑዲ ዓረቢያ ቦታዋን መነጠቋ፣ ግብፅና ሳዑዲ ዓረቢያ ቅሬታ ውስጥ መግባታቸው፣ ግብፅ የሳዑዲ ዓረቢያ ባላንጣ ከሆነችው ኢራን ጋር ወዳጅነት ለማጠናከር መፈለጓ፣ ይህ በኢራን ዋነኛ ጠላት ተደርጋ በምትታየው እስራኤልና ተፎካካሪዋ ሳዑዲ በበጐ ዓይን ያለመታየቱ ፉክክሩን ያጐለዋል፡፡ አሁን በቀይ ባህር እየታየ ያለው ምልክት ተጠናክሮ እንዲወጣ ያደርጋል፡፡
ከአዘጋጁ፡- ጸሐፊው የኢትዮጵያየውጭግንኙነትስትራቴጂካዊጥናትኢንስቲትዩት ባልደረባ ሲሆኑ፣ ጽሑፉ የእሳቸውን አመለካከት ብቻ የሚያንፀባርቅ መሆኑን እየገለጽን በኢሜይል አድራሻቸው abe.eiipd@gmail.com ማግኘት ይቻላል፡፡
<span lang="NL" style="font-size:12.0pt;line-height:200%;font-family:"Ge" ez-1","sans-serif";="" mso-bidi-font-family:"ge\0027ez-1";color:black;mso-ansi-language:nl'="">
